Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው ተባለ የአገሪቱ የሲል ባለስልጣናትን እና የአ | ሁለገብ መረጃ

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው ተባለ

የአገሪቱ የሲል ባለስልጣናትን እና የአገሪቱን ጦር ስምምነት በመቃወም ከሰሞኑ ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የሱዳን አካባቢዎች ሰልፎች ሲደረጉ እንደነበር የቅርብ ቀናት ውስጥ ትውስታዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር #አብደላ_ሃምዶክ ከሲቪል ባለስልጣናት ሹመት ጋር በተያያዘ አለ ባሉት ጣልቃገብነት ምክንያት ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውንና የጠቅላይ ሚኒስርነታቸውን ስልጣን ሊለቁ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰዓታት ውስጥ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ያስገባሉ ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።