Get Mystery Box with random crypto!

Muktar Hussen የሱና ወዳጆች ቻናል ቡታጅራ ከተማ ከስልጤ አጠገብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ httpmuktarhussen — Muktar Hussen የሱና ወዳጆች ቻናል ቡታጅራ ከተማ ከስልጤ አጠገብ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ httpmuktarhussen — Muktar Hussen የሱና ወዳጆች ቻናል ቡታጅራ ከተማ ከስልጤ አጠገብ
የሰርጥ አድራሻ: @httpmuktarhussen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.73K
የሰርጥ መግለጫ

➾ቅድሚያ ለተዉሒድ ለአላህ መብት ለሆነው/ወደዚህ ምድር ለምን እንደመጣን እንወቅ/ከሺርክ እናስጠንቅቅ ከአደንዛዥና ከሀራም ነገሮች እንረቅ ለእውቀት ቦታ እንስጥ እናንብብ እንወቅ እውቀት ከፍ ያደርጋል ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት 09253 44831 ሙክታር ሁሴን✅

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-10-19 20:23:09
إنك لا تهدي من أحببت ولكن الله يهدي من يشاء ، فهذه من الله . #العلامةرسلان


https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
13.4K viewsedited  17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 14:22:18 አዲስ ግጥም ሼር ሼር አድርጉት
======================
ወንጀልተላመድን-ሓላልእየመሰለን
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አዎ ወንጀል ተለመደ ሓላልም መስለዋል
የነብያቶች መልእክት የሚፃረር በዝተዋል
ከትእዛዛቸው እንዳንወጣ አላህም አዞናል
እኛሰዎች ግን ሰምቶ መተግበር አቅቶናል
እኛሰዎች ግን ሰምቶ መተግበር አቅቶናል
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ወንጀል መስራት  እንደ ቀላል አየነው
ቀልባችን ደረቀ አላህን መፍራት ተሳነው
የመፈጠራችን አላማ ሁላችን ዘነጋነው
ማስተንተን አቃተን ግዜያችን አቃጠልነው
ማስተንተን አቃተን ግዜያችን አቃጠልነው
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በማይጠቅመን ቀልድ ለሰዎች የሚያስቅ
ትልቅመንስኤ የሆነ ቀልባችን እንዲደርቅ
አሲቂኝ ነገሮች ሼር  ከማድረግ  ይልቅ
ይሻለናል የ ኢስቲግፋር ጥቅም ማወቅ
ይሻለናል የ ኢስቲግፋር ጥቅም ማወቅ ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በማህበራዊ ሚዲያ ወንጀላቶች በዛ
የሚጠቅመን ከመስራት ሆነናል ደንዛዛ
ለሰዎች መጥቀም ትተን ተኝተናል ለዛ
ሩሀችን ወደ አኺራ ትሂድ ኸይር ነገር ይዛ
ሩሃችን ወደ አኺራ ትሂድ ኸይር ነገር ይዛ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
   ካለዛ እማ ወንድም እህቶቼ  
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ወንጀል በወንጀል ላይ ተጠምደን ከቀረን
የዘልአለም ሂወት  የእኛ እጣ ፈንታችን
በረሳችን ስንፈት ከከሳሪዎች መሆናችን
ጥርጥር የለውም ወይኔ ወይኔ ማለታችን
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ያአላህ ያረሒም እድለኞች አድርገን
በራሕመትህ ከራሕመትህ አታስወጣን
በዱንያ ስንኖር  ዛሂዶች  አድርገን
መሳቅ መደሰት ይሻላል በአኺራ ቤታችን
መሳቅ መደሰት ይሻላል በአኺራ ቤታችን
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ተፃፈ በወንድማቹ ሙክታር ሁሴን
የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ

https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
╚══════════════════╝
14.4K viewsedited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 14:22:15
9.6K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 18:56:56 በጣም ጠቃሚ ትምህርት ስለሆነ ሁሉም ሙስሊም ሼር ሼር ሼር ያድርገው አደራ
===================================

አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ሙሥሊም እህትና ወንድሞቼ!

ለዛሬ ያዘጋጀሁት ርዕስ የአዋቂዎች ዝምታና ዉሸት የወጣቱ ፈታና የሚል ርዕስ ነው ።ዝም ብዬ ይሄንን ርዕስ የመረጥኩ አይምሰላችሁ ዉስጤ ስለተነካና ከዝምታ መነገር ይሻላል ሀቁን መነገር ወይም መምረጥ ግዴታ ስለሆነብኝ ነው ሙስሊም እህት ወንድሞቼ።

እዉነት ብርሃን ነው ዉሸት ጨለማ ነው :
ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ሃቁን አሳዉቀዉ:
የነብዩን አደራ የአላህን ትዕዛዝ ወዴት አደረስከዉ::

እንደሚታወቀው ወጣቱ ማህበረሰብ በብዙ ነገሮች ተወጥሮ ይገኛል፦
በሶሻል ሚዲያ
በጫት (በሱስ )
በኳስ ፍቅር
በፊልም ወይም በሙዚቃ
በነሺዳ ወይም በመንዙማ(በሙዚቃ ወንድም)

ከላይ በጠቀስኳቸውና ከእነዚህም ዉጭ በብዙ ነገሮች ወጣቶች ምርኮኛ ሆነው ይገኛሉ። እነዚህን ወጣቶች እንዴት ከዚህ አደገኛ ተግባር እናስጠነቅቅ ማለት ሲገባ ትናንት ትልልቅ ሰዎች ናቸው የተበሉ ሰዎች ዛሬ ግን ትልቅ ደረጃ ሲደርሱ ሃቅን ከመናገር ዉሸትን መርጠዋል። ሀቅን ደብቀዋል ተዉ አላህን ፍሩ ማለት ሲገባ የፈለገ ጫት ይቀም ፣የፈለገው ይተው ፣የፈለገው ይደንስ ፣የፈለገው ይተው ፣የፈለገው ይስካር፣ የፈለገው ደግሞ አይስካር፡ የሚል ፌዝ የተሞላበት ንግግር እየሰማን ነው ።

ትልልቅ ሰዎች ናቸው ከሚበሉት ሰዎች ይህንን ሰማን እሺ ወጣቱን ትልልቅ ሰዎች አላህን ፍሩ ተዉ ይህ መጥፎ ነገር ነው የማይሉ ከሆነ የወጣቱ መጨረሻ ምን ይሆን?

ተዉ አባቶቼና ኡስታዞቼ ሃቅን ተናገሩ
የእስልምና ዉበት ሰይገበዉ ምስጥሩ
በአጉል ስልጣኔ ተማርከው በአጭር እንዳይቀሩ
ለወጣቶች ምክር ስጡ እያላችሁ አብሽሩ
በእስልምና አላም የእዉነት በፍቅር ይኑሩ
ማንነታቸውን ትተው በአጉል ስልጠኔ አይኑሩ::
እናንተ ትልልቅ ሰዎች ወጣቱን አደራ ምከሩ

ያ እሩቅ የሚመስለው ሞት ነገር እንደሚመጣ እየታወቀ እንዴት አላህን ፍሩ መጥፎ ተግባር ይቅርባችሁ ብሎ መነገር ያቅተዋል እስልምና የስንቱ መጫወቻ ሆኖ ይችለዋል ።

ወንዱን ተዉ የሚል ጠፋና  ነሺዳ እያለ ሙዚቃ አወጣ ጭራሽ አሁን ደግሞ ሴቱም ነሺዳ እያለ በሶሻል ሚዲያ በVIDO ብቅ እያለ ነው::

ለምን ትልልቅ አባቶች ሀቅን ትደብቃላችሁ?? ዉሸት ትናገራላችሁ አላህን አትፋሩም ወጣቱ ማህበረሰብ ስንት ነገር ማድረግ እየቻለ የማይሆን ቦታ ሲገኝ ለምን ዝም ትላላችሁ

ኡስታዝ ሆናችሁ ብዙ የሶሻል ሚዲያ ተከታይ ያላችሁ ሰዎች ለምን ሀቅ አትናገሩም ቢያንስ በስራችሁ ያሉ ሰዎች እናንተ አላህን ፍሩ ብትሏቸው ሁሉም ባይሆን የተወሰነው ወጣት ብዙ ለዉጥ ያሳይ ነበር በእርግጠኝነት።

ለዚህች አጭር እድሜ ለዚህች አጭር አላም
የእውነት ሞት እያለ  እየኖርን በዉሸት አላም
የአላህ ትዕዛዝ ጥሶ በእርጋታ መኖር የለም
የነብዩን ትዕዛዝ ጥሶ መኖር የለም በሰላም

ወጣት ሆይ ለራስህ ስትል ነቃ በል

አደራ እስልምና ብዙ ዋጋ ተከፍሎበት እዚህ ደረጃ ደርሶአል በአንተና በእኔ ግዜ መቀለጃ አናድርገው:: እስልምና የአለም ብርሀን ነዉና ለሰዎች አብርተን እናሳይ ትልልቆቹ ዝም ቢሉም አንተና እኔ ጠንክረን ከሰራን ብዙ ወጣትን ከመጥፎ ቦታ ከአጉል ቦታዎች መዉጣት እንችላለን በአላህ ፍቃድ።

ተፃፈ በወንድማቹ ሙክታር ሁሴን ፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ

https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
╚══════════════════╝
15.2K viewsedited  15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 18:56:49
9.3K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 14:26:43
11.2K views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 14:26:38 አዲስ ግጥም ሼር ሼር አድርጉት
======================

ተዘናጋን ብዙ --- ሞት እንደሌለብን
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አዎ ተዘናጋን ብዙ -- ሞት እንደሌለብን
የተፈጠርንበት አላማ ማወቅ ተሳነብን
ምንድነው ችግሩ ? ማስተንተን ያቃተን
ወደ አላህ እንመለስ በፍጥነት ሁላችን
ወደ አላህ እንመለስ በፍጥነት ሁላችን
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አባት እናቶቼ ሃሳቤ በረታ ከምላቹ በላይ
ቁርአን እና ሓዲስ  አጥተዋል  ተከታይ
የሚቀራው  የለ  በዝተዋል  አስመሳይ
እኔስ አቅቶኛል አስፈርቶኛል ለቀጣይ
እኔስ አቅቶኛል አስፈርቶኛል ለቀጣይ ፡፡
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ለቀጣይትውልድ የማናስብ ሰዎች
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ምን አይነት ትውልድ ነው የምንተካው ??
አላህልጅ ሰጥቶን ሲያበቃ ሳናስተምረው
ወደዚምድር ለምን እንደመጣ ሳንነግረው
ከንቱ ፍጥረት እንዲሆን እኛ አደረግነው
ከንቱ ፍጥረት እንዲሆን እኛ አደረግነው ፡፡
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ህሊናችን እናሰራው ወንድም እህቶቼ
እንደ እንስሳ አንሁን ይብቃን ወገኖቼ
ከከሳሪዎች  እንዳንሆን  ወሏሂ  ሰግቼ
ወደ አላህ ሳንመለስ እንዳንሞት ፈርቼ
ወደ አላህ ሳንመለስ እንዳንሞት ፈርቼ ፡፡
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እባካቹ እንመለስ ቀልባችን እናስራው
ሞ--ት የሚባል ስም ትልቁ እንግዳው
ከመጣ የማይምር የለም የሚያስቀረው
አጀላችን እስኪደርስ  የሚጠባበቀው
አጀላችን እስኪደርስ  የሚጠባበቀው ፡፡
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጠፊ በሆነች ዱንያ  ብዙ አንታለል
ጥለናት ለምንሄድ አለም ብዙ ለፍተናል
ለአኺራ ቤታችን ግን መስራት ተሳንፈናል
ተዉ እንመካከር የዘላለም ቤት ይሻለናል
ተዉ እንመካከር የዘላለም ቤት ይሻለናል፡፡
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተዘናጋን ብዙ -- ሞት እንደሌለብን
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
እኔማ አለኝ አደራ የምላቹ በቁም ነገር
ብዙ አንልፉ ባልታዘዝነው መስራት ይቅር
እንስራ ለአኺራ ቤት የሚጠቅመን ነገር
አላማችን ይሁን መደሰቱ በማይጠፋ ሀገር
አላማችን ይሁን መደሰቱ በጀነቱ ሀገር ፡፡
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ተፃፈ በወንድማቹ ሙክታር ሁሴን ፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ

https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
╚══════════════════╝
11.7K viewsedited  11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 14:26:07
#ትክክለኛዉ እስልምና ፈጠራ ከሆነዉ መውሊድ የራቀ ነዉ

በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን በቅበት ከተማ አስተዳዳር በሰነና ገሬራ ቀበሌ መንደር 2 ሂዳያ መስጂድ የተደረገ ሙሐደራ።

በኡስታዝ ሻኪር ሱልጠን

https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
8.8K viewsedited  11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 20:30:21 አዲስ ግጥም ሼር ሼር አድርጉት
======================

መዉሊድ --- አላከብርም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
አልሐምዱሊላሂ የመሐመድኡማ ያደረገኝ
ቢድዓ  እና  ሱና  ለይቶ  ላሳወቀኝ
የሳቸው መንገድ ተከታይም ያስደረገኝ
ምስጋና ይድረሰው ተውሒድን ለሰጠኝ
ምስጋና ይድረሰው ተውሒድን ለሰጠኝ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
ቁርአን  እና  ሱና  ያለንን  ብንከተል
ከጉድለት የጠራ ጌታችን ይቀበለናል
ውድ ሐቢቡና ረሱላችንም ብለውናል
እኔን  የተከተለ  ሁሉ  ጀነትን  ያገኛል
እኔን የተከተለ  ሁሉ  ጀነትን  ያገኛል ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
ሶላት እንስገድ አምስት ወቅታችን
የጀነት በር ቁልፍ ናት  እኮ ሶላታችን
አደራ  በሶላት  እንዳሉ  ነብያችን
ሩሀቸው እስክትወጣ ነገሩን ረሱላችን
ሩሀቸው እስክትወጣ ነገሩን ረሱለችን
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
ያዘዙትን ትተን ያላዘዙት መስራት
መዘዙ ከባድ ነው ለአኺራ ቅጣት
አወይ መከራችን ከማለታችን በፊት
ከሺርክ እና ቢድዓ ይሻለናል መውጣት
ከሺርክ እና ቢድዓ ይሻለናል መውጣት ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿
ኩሉ ሙሕደሲን ቢድዓህ ወኩሉቢድዐቱን
ደላላ ወኩሉ ደላለቲ ፊንናር መባባላችን
ጠቃሚ ነው  እና  ለኡማው  ህዝባችን
ሁላችን  እንገዛ  ለ አንዱ  አላህ  ጌታችን
ሁላችን  እንገዛ ለ አንዱ  አላህ  ጌታችን ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡     መዉሊድ-አላከብርም አሁንም ልበላቹ
ነብየን  ወዳጅ  ነኝ  ብየም  ልንገራቹ
እሳቸው መውደድ እንዴት ለሳያቹ ????
ባዘዙኝ መገኘት ነው በቃኝ ልበላቹ
ባዘዙኝ መስራት ነው የቀረ የለም የምላቹ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿✿

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ተፃፈ በወድንማቹ ሙክታር ሁሴን

የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ

https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
╚══════════════════╝
13.8K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 20:30:19
9.7K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ