Get Mystery Box with random crypto!

በጣም ጠቃሚ ትምህርት ስለሆነ ሁሉም ሙስሊም ሼር ሼር ሼር ያድርገው አደራ ============== | Muktar Hussen የሱና ወዳጆች ቻናል ቡታጅራ ከተማ ከስልጤ አጠገብ

በጣም ጠቃሚ ትምህርት ስለሆነ ሁሉም ሙስሊም ሼር ሼር ሼር ያድርገው አደራ
===================================

አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ሙሥሊም እህትና ወንድሞቼ!

ለዛሬ ያዘጋጀሁት ርዕስ የአዋቂዎች ዝምታና ዉሸት የወጣቱ ፈታና የሚል ርዕስ ነው ።ዝም ብዬ ይሄንን ርዕስ የመረጥኩ አይምሰላችሁ ዉስጤ ስለተነካና ከዝምታ መነገር ይሻላል ሀቁን መነገር ወይም መምረጥ ግዴታ ስለሆነብኝ ነው ሙስሊም እህት ወንድሞቼ።

እዉነት ብርሃን ነው ዉሸት ጨለማ ነው :
ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ሃቁን አሳዉቀዉ:
የነብዩን አደራ የአላህን ትዕዛዝ ወዴት አደረስከዉ::

እንደሚታወቀው ወጣቱ ማህበረሰብ በብዙ ነገሮች ተወጥሮ ይገኛል፦
በሶሻል ሚዲያ
በጫት (በሱስ )
በኳስ ፍቅር
በፊልም ወይም በሙዚቃ
በነሺዳ ወይም በመንዙማ(በሙዚቃ ወንድም)

ከላይ በጠቀስኳቸውና ከእነዚህም ዉጭ በብዙ ነገሮች ወጣቶች ምርኮኛ ሆነው ይገኛሉ። እነዚህን ወጣቶች እንዴት ከዚህ አደገኛ ተግባር እናስጠነቅቅ ማለት ሲገባ ትናንት ትልልቅ ሰዎች ናቸው የተበሉ ሰዎች ዛሬ ግን ትልቅ ደረጃ ሲደርሱ ሃቅን ከመናገር ዉሸትን መርጠዋል። ሀቅን ደብቀዋል ተዉ አላህን ፍሩ ማለት ሲገባ የፈለገ ጫት ይቀም ፣የፈለገው ይተው ፣የፈለገው ይደንስ ፣የፈለገው ይተው ፣የፈለገው ይስካር፣ የፈለገው ደግሞ አይስካር፡ የሚል ፌዝ የተሞላበት ንግግር እየሰማን ነው ።

ትልልቅ ሰዎች ናቸው ከሚበሉት ሰዎች ይህንን ሰማን እሺ ወጣቱን ትልልቅ ሰዎች አላህን ፍሩ ተዉ ይህ መጥፎ ነገር ነው የማይሉ ከሆነ የወጣቱ መጨረሻ ምን ይሆን?

ተዉ አባቶቼና ኡስታዞቼ ሃቅን ተናገሩ
የእስልምና ዉበት ሰይገበዉ ምስጥሩ
በአጉል ስልጣኔ ተማርከው በአጭር እንዳይቀሩ
ለወጣቶች ምክር ስጡ እያላችሁ አብሽሩ
በእስልምና አላም የእዉነት በፍቅር ይኑሩ
ማንነታቸውን ትተው በአጉል ስልጠኔ አይኑሩ::
እናንተ ትልልቅ ሰዎች ወጣቱን አደራ ምከሩ

ያ እሩቅ የሚመስለው ሞት ነገር እንደሚመጣ እየታወቀ እንዴት አላህን ፍሩ መጥፎ ተግባር ይቅርባችሁ ብሎ መነገር ያቅተዋል እስልምና የስንቱ መጫወቻ ሆኖ ይችለዋል ።

ወንዱን ተዉ የሚል ጠፋና  ነሺዳ እያለ ሙዚቃ አወጣ ጭራሽ አሁን ደግሞ ሴቱም ነሺዳ እያለ በሶሻል ሚዲያ በVIDO ብቅ እያለ ነው::

ለምን ትልልቅ አባቶች ሀቅን ትደብቃላችሁ?? ዉሸት ትናገራላችሁ አላህን አትፋሩም ወጣቱ ማህበረሰብ ስንት ነገር ማድረግ እየቻለ የማይሆን ቦታ ሲገኝ ለምን ዝም ትላላችሁ

ኡስታዝ ሆናችሁ ብዙ የሶሻል ሚዲያ ተከታይ ያላችሁ ሰዎች ለምን ሀቅ አትናገሩም ቢያንስ በስራችሁ ያሉ ሰዎች እናንተ አላህን ፍሩ ብትሏቸው ሁሉም ባይሆን የተወሰነው ወጣት ብዙ ለዉጥ ያሳይ ነበር በእርግጠኝነት።

ለዚህች አጭር እድሜ ለዚህች አጭር አላም
የእውነት ሞት እያለ  እየኖርን በዉሸት አላም
የአላህ ትዕዛዝ ጥሶ በእርጋታ መኖር የለም
የነብዩን ትዕዛዝ ጥሶ መኖር የለም በሰላም

ወጣት ሆይ ለራስህ ስትል ነቃ በል

አደራ እስልምና ብዙ ዋጋ ተከፍሎበት እዚህ ደረጃ ደርሶአል በአንተና በእኔ ግዜ መቀለጃ አናድርገው:: እስልምና የአለም ብርሀን ነዉና ለሰዎች አብርተን እናሳይ ትልልቆቹ ዝም ቢሉም አንተና እኔ ጠንክረን ከሰራን ብዙ ወጣትን ከመጥፎ ቦታ ከአጉል ቦታዎች መዉጣት እንችላለን በአላህ ፍቃድ።

ተፃፈ በወንድማቹ ሙክታር ሁሴን ፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ

https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
╚══════════════════╝