Get Mystery Box with random crypto!

Hijra Tube [Official]

የቴሌግራም ቻናል አርማ hijranews — Hijra Tube [Official] H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hijranews — Hijra Tube [Official]
የሰርጥ አድራሻ: @hijranews
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.45K
የሰርጥ መግለጫ

ሒጅራ ቲዩብ ኢስላማዊ ድረገፅ ትኩስ ትኩስ የሙስሊሙን አለም የተመለከቱ መረጃዎች ጠቃሚ ፅሁፎችና ዳእዋዎች ይቀርቡበታል

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-26 13:27:42 https://fb.watch/lp8qAXJViv/
1.3K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 10:19:39
ቀሪዎቹን ቀናት እንወጥር ፤እንበራታ ፤ እንጠንክር ኢንሻአላህ
==============
የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ማክሰኞ ሰኔ 20 ነው።
================
ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦
﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾
“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”
ሙስሊም ዘግበውታል: 1162
=============
1.6K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 23:20:19 በዓረፋ ቀን ልንተገብራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት የትኞቹ ናቸው?

ኢብኑ ረጀብ ለጣኢፉ አል-መዓሪፍ በተባለው ኪታባቸው ላይ የጠቀሱትን እና ሌሎችም ዑለማዎች ከጠቆሟቸው ነጥቦች ከዋና ዋናዎቹ የተወሰኑትን በአጭሩ እንመልከት:‐
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ:- “በዓረፋ እለት ከእሳት ነፃ መውጣቱን እና ለወንጀሎቹ ምህረትን የሚፈልግ ሰው ለዚያ ሰበብ የሚሆኑ ነገሮችን መፈፀም ይኖርበታል:: ከነዚያ ሰበቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:-
የዓረፋን ቀን መፆም:-
አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)

መላ አካላትን አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ማራቅ በተለይ ፈፅሞ አላህ ምህረት ከማያድርግለት ወንጀል በእሱ ላይ ማጋራት (ሺርክ) እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል::

የተውሂድ መገለጫ የሆነውን እና የአላህን አጋር የሌለው ብቸኛ አምላክነት እንዲሁም በሁሉ ነገር ላይ ቻይነት የሚያረጋግጠውን “ላ ኢላሃ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢ ቀዲር ” የሚለውን ዚክር ማብዛት:: ይህ ዚክር በእለቱ አላህን ከምናወድስባቸው ቃላት የተሻለውና ምርጡ እንደሆነ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ በተናገሩበት ወቅት እንዲህ ሲሉ አሳውቀዋል:– "እኔና ከኔ በፊት የመጡት ነብያት ከተናገርነው ንግግር ሁሉ በላጩ ይህ ነው።"

አላህን ምህረት እንዲያደርግለት እና ከእሳት ነፃ ከሚወጡት ባሮቹ እንዲያደርገው አብዝቶ መለመን:: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- “ከዓረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም::” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በተጨማሪም ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:- “ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::” ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን፣ ለልጆቻችን፣ ለባለቤቶቻችን፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።

በአጠቃላይ በተሰማራንበት ቦታ ሁሉ በቻልነው አቅም መልካም ነገሮችን ከማድረግ እንዲሁም አላህን ከማውሳት ልንሳነፍ አይገባም:: በተለይ ከሰላት በኋላ ተክቢራ ማድረግ ከዛሬው እለት ፈጅር ሰላት የሚጀምር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም:: ይህም ማለት ተክቢራ ማድረጉ ዛሬ የተጀመረው ከአምስቱ ግዴታ ሰላቶች በኋላ የተገደበ (ሙቀየድ) በመባል የሚታወቀው ነው እንጂ ከዚያ ውጪ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) በመባል የሚታወቀው የተክቢራ አይነት እስከ አያመ-አተሽሪቅ ማብቂያ ማለትም የአስራ ሶስተኛው ቀን ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ይቀጥላል::

አላህ በመልካም ስራ ላይ ያበረታን እንዲሁም ይቀበለን!

*ጣሀ አህመድ (ዙል–ሒጃ 1441 የተፃፈ)*
1.6K views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 20:29:49 ወቅታዊ ማስታወሻ ለሙስሊሞች
   
ውድ ሙስሊም ወንድም ና እህቶች
ይህን ወቅታዊ ማስታወሻዬን ጥቂት ጊዜያችሁን ሰውታቹ እንድታነቡት አደራ አደራ እላለሁ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ አና በጣም አዛኝ በሆነው
ያለንበት ወቅት በ ዱንያ ካሉት ቀናቶች በጣም በላጭ የሆኑ እና አላህ ዘንድ በእነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ ስራዎች ከሌሎች በተለየ ና በበለጠ  ተወዳጅ የሚሆንበት 10ቱ ቀናት ላይ ነው ያለው

ማስታወሻዬም የሚያተኩረው በእነዚህ ውስጥ በሚገኘው በጣም ታላቅ ና ትሩፋቱ የበዛ ስለሆነው ስለ  ዓረፋ
(የዙልሂጃ 9ኛው ቀን) ነው
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የዚህን ቀን ትሩፋቶች በሚገባ አብራርተዋል

ነብያችን እንዲህ ይላሉ : አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ ከዐረፋ ቀን የበለጠ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት የሆነ አንድም ቀን የለም
ከዛም በመቀጠል ያሉት :እኔም ከኔም በፊት ከነበሩት ነብያት ካሉት ንግግር በላጩ
لا ﺇﻟﻪَ ﺇﻻَّ ﺍﻟﻠَّﻪ ﻭﺣْﺪﻩُ ﻻَ ﺷَﺮِﻳﻚَ ﻟﻪُ، ﻟَﻪُ ﺍﻟﻤُﻠْﻚُ، ﻭﻟَﻪُ ﺍﻟﺤﻤْﺪُ، ﻭَﻫُﻮ ﻋَﻠَﻰ ﻛُﻞِّ
ﺷَﻲﺀٍ ﻗَﺪِﻳﺮ
ላ ኢላሃ ኢሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር የሚለው ነው::
ይህን ዚክር በብዛት በማለት እንበርታ
ሌላው ነብያችን እንዲህ ብለዋል
በላጬ ዱዓ ማለት የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓ ነው

በዚህ በላጭ በሆነው የዓረፋ(ዙልሂጃ 9) ቀን አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ
-ከእሳት ነፃ ከሚያደርጋቸው
-ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ባሮቹ መሆን የፈለገ ሰው
የዓረፋን ቀን ይፁም
ነብያችን እንዲህ ይላሉ :
{የዐረፋ ቀን በመፆም አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል እንደ ሚምር እተሳሰባለሁ}
{የዐረፋ ቀን የፆመ የሆነ ሰው ተከታታይ የሆኑ የሁለት አመት ወንጀሎቹን ይማርለታል}
የተውሂድ ቃል ዚክር ማለትን ያብዛ
ላ ኢላሃ ኢሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር
አላህ እንዲምረው እና ከእሳት ነፃ ከሚሆነው እንዲያደርገው መለመንን ያብዛ
አሏሁመ  አእቲቅ ሪቃበና ሚነን ናር የምትለዋን ዱዓ በማለት አላህን እንለምን
በዚህ ቀን ዱኣ ተቀባይ መሆኑ በጣም የሚከጀልበት ነው

ለዚህም ቀን ኸይር ፈላጊ የሆነ
ሙስሊም ራሱን ባለቤቱን እህት ወንድሞቹንና ልጆቹን  ይህንን የተከበረ ቀን እንዲፆሙ ይቀሰቅሳል

አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ የዚህን ቀን ትሩፋቶች ከሚያገኙ እና ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ሰዎች እንዲያደርገን እለምነዋለሁ በመልካም ዱዓቹ አትርሱኝ

ይህን አንገብጋቢ ማስታወሻ ለምታውቁትም ለማታውቁትም ሙስሊም ለሆነ አካል እንድታሰራጬ እና የመልካም ስራ ተቋዳሽ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
طلحة أحمد
1.6K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 18:16:16 ሑጃጆች ልብ ይበሉ!

የቂራን ወይም የተመቱዕ እርድ ግዴታ የሆነበት ሰው የማረድ አቅም እያለው ማረዱን ትቶ መጾም አይፈቀድለትም::
ምክንያቱም የቁርኣን አንቀጹ "የሚያርደውን እንሰሳ ያላገኘ... ይጹም" ነውና የሚለው። -(አልበቀረህ 196-)
ማረድ እየቻሉ ወደ ጾም መሸጋገር የሚቻለው እንደ- ጸጉርን መላጨት፣ ሽቶ መቀባትና ወዘተ. መሰል በኢሕራም ምክንያት የተከለከሉ ነገሮችን ላደረገ ሰው ነው።
ገንዘብ እያለ በመሰሰት ወይም ገዝቶ እራስ ማረድን እንኳ ባይችሉ ፈቃድና እውቅና ላላቸው ተወክለው ለሚያርዱ ተቋማት አለመስጠት ሐጅ/ዑምራን ያጎድላል (ወንጀለኛ ያደርጋል)።
ልክ እንደዚሁ የሐጅ ቀናት ሳይጠናቀቁ በፊት መጾም አለበት የተባለን ጾም በግዴለሽነት ሳይጾም የሐጅ ቀናት ያለቁበት ሰው ወንጀለኛ ይሆናል።
ፈጥኖ መቶበትና ጊዜው ቢያልፍም ያለበትን ጾም መክፈል ይኖርበታል።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
@ዛዱል መዓድ
           


https://telegram.me/ahmedadem

"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!
አል-ኢማሙ ማሊክ
1.6K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 12:23:47
የዓረፋን ኹጥባህ በአማርኛ ለመጀመሪያ ጊዜ።

Arafat Khutbah to be translated in 20 languages!

1. English
2. French
3. Malay
4. Urdu
5. Persian/ Farsi
6. Chinese
7. Turkish
8. Russian
9. Hausa
10. Bengali
11. Swedish
12. Spanish
13. Swahili
14. Amharic
15. Italian
16. Portuguese
17. Bosnian
18. Malayalam
19. Filipino
20. German
1.3K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 01:55:21
1.5K views22:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 01:55:17 #የታረዘው_ልጅ

(እጅግ አሳዛኝ እውነተኛ ታሪክ)

አንድ የሞላለት ባለጠጋና ልጁ ቅንጡና ውድ እቃዎች ወደሚሸጡበት ሞል ሄዱ። የሚሸምቱትን ሸማምተው ወደ መኪናቸው ሲመለሱ አንድ የተቀዳደደ ልብስ የለበሰ ልጅ ወደነሱ ቀረብ ብሎ.....

"አባባዬ እርዳኝ፣ የምለብሰው ልብስ ሰውነቴ ላይ አለቀ
....ሃሩርና ቁር ተፈራረቁብኝ" አለው።

ሀብታሙ ሰው ልጁን መልከት ሲለው ደነገጠ። እውነትም በጣም የታረዘ መሆኑን አለባበሱ ይናገራል።

"ስንት አመትህ ነው የኔ ልጅ?" ሲል በርህራሄ ጠየቀው።

"አስር ዓመቴ ነው።"

"እንደዛ ከሆነ ጥሩ ነው፤ የኔም ልጅ አስር አመቱ ነው። አሁን የተገዙለት አዳዲስ ልብሶች ልክህ ይሆናሉ ማለት ነው።" አለና...........

ወደራሱ ልጅ ዘወር ብሎ
"የኔ ልጅ ለዚህ ብላቴና ዛሬ የተገዙልህን ልብሶችህን በመስጠት ደግነትህን ታሳየኛለህ አይደል? ነገ መጥተን ላንተ ሌላ እንገዛለን" አለው።

"ደስ ይለኛል!" ሲል ልጁም ተስማማ።

አባትም የገዟቸውን ልብሶች እያወጣ ለዛ ደሃ ልጅ ሲሰጠው በልጁ ፊት ላይ የደስታ ብርሃን ፍንትው ብሎ ሲበራ አየና
......
"የት ነው የምትኖረው ግን?" ሲል ጠየቀው።

ደሃው ህፃንም "ከፊት ለፊት ካለው ድልድይ ስር በስተቀኝ በኩል ባለው ፕላስቲክ ቤት ውስጥ" ሲል መለሰ።

ቃለ-ምልልሳቸው በዚሁ አብቅቶ ሃብታሙ ለጋስና ልጁ ወደ መኪናቸው ገብተው እስኪሄዱ ያምስኪን የተሰጠውን ልብስ በደረቱ አጣብቆ አቅፎ በደስታ እያያቸው ነበር.......

ከሶስት ወር በኋላ ያ ሃብታም ያንን የጎዳና ህፃን ፈልጎት መጣና ወደ መኪናው በመውሰድ በትልቅ ሻንጣ የታጨቁ ልዩ ልዩ አልባሳትና ጫማዎችን ሲሰጠው እንዲህ አለው......

"እነዚህ ልብሶችና ጫማዎች የልጄ ነበሩ አሁን ግን ያንተ ናቸው" ሲል ሃዘን ባደበዘዘው ፈገግታ ታጅቦ ነገረው።

ደሃው ህፃን የደስታ እንባ እያነባ

"አባባ ያንተ ልጅስ? ምን ይለብሳል?" ጠየቀ።

"አንተ ትንሽ ልጅ አትጨነቅ። የኔ ልጅ እነዚህን አልባሳት አሁን አይፈልጋቸውም....ምክንያቱም አሁን እሱ በገነት ውስጥ ነውና፤ የኔ ጣፋጭ ትንሹ ልጅ ከሳምንታት በፊት በካንሰር ህመም ህይወቱ አልፋለች። ከካንሰር ጋር እየታገለ ሶስት አመት ኑሯል....እናም ከኛ ጋር እንደሚለያይና ትቶን እንደሚሄድ እናውቅ ነበር። የኔ ጣፋጭ ልጅ በመጨረሻው የመለያያ ጊዜያችን እንዲህ አለኝ 'አባ አንተንና እማዬን የምለይበት ጊዜ በጣም ቀርቧል....ከንግዲህ ዳግም የምንገናኘው በገነት ብቻ ነው። አባ የኔ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ለዛ በድልድዩ ስር ለሚኖረው የጎዳናው ልጅ ስጥልኝ' ብሎኝ ተለየኝ።

አባት ለተወሰነ ጊዜ እንባውን እያፈሰሰ ንግግሩን ገታ።

" የኔ ልጅ ምናልባት ደሃ ስለሆንክ ታዝን ይሆናል። ግን አስታውስ ጤናን እና ህይወትን የታደልክ ሃብታም መሆንህን እንዳትረሳ። እኔ ያለኝ ገንዘብና ቁሳዊ ሃብት ልጄ ከገጠመው የጤና ድህነትና በመጨረሻም ከሞት አልታደገውም...እናም እልሃለሁ እያንዳንዳችን ያጣናቸው ነገሮች ቢኖሩም በጃችን ያሉና ምንም ያልመሰሉን ግን ሌላው ያጣቸው፣ የተቸገረባቸው፣ የተሰቃየባቸው ብዙ ድልብ ሃብቶች አሉ...እነሱን በደንብ ተንከባክበን እና እያመሰገንን በመጠበቅ የጎደሉንን ደግሞ መፈለግ ነው ያለብን...." ሲል በተሰበረ ልብ መከረው።
.
.
ልጀ ደስ ካለህ ከኔ ጋር ብትሆንና የልጀ ማስታወሻ ብትሆነኝ ደስ ይለኛል አለ አባት እንባ እየተናነቀው

ልጅም በአውንታ ግንባሩን ነቀነቀው

ሁለቱም ደስታና ሃዘን ተደራርበው ያመነጬባቸውን የንባ ዘለላዎች እየጠረጉ ወደ ቤት አመሩ ......

በ: Chima_Dickson ተፅፎ
በ: አለበል ንጋቱ ተተረጎመ
__________
1.6K views22:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 12:14:54
Bio9
ባዮ ናይን የፀጉር ቅባት ወደ ራስ ቅላችን ዘልቆ በመግባት ፀጉራችን እንዲያድግ እና እንዲፋፋ የሚረዳውን ፎሊክልስ የተባለ የቆዳችንን ክፍል በማነቃቃት ፀጉራችን እንዲፋፋ እንዲያድግ ያደርጋል።
ባዮናይን ለፀጉራችን እድገት አስፈላጊ የሆኑ ዘጠኝ አይነት የተፈጥሮ ዘይቶችን የያዘ ሲሆን ለምሳሌ ሮዝመሪ እና ሬት የመሳሰሉ essential 9 አይነት የተፈጥሮ ዘይቶችን ይዟል።
ባዮናይን የፀጉር ቅባት ሙሉ ለሙሉ ከተፈጥሮአዊ የቅባት ተክሎች የተመረተ ሲሆን ምንም አይነት ኬሚካል የሌለው የኸርባል ምርት ነው።
አጠቃቀሙም በፀጉር ቆዳችን ላይ ለሁለት ደቂቃ ማሸት ሼባ ሳሙና (Sheba soap)

ሼባ ሳሙና ከተለያዩ የ10 እጽዋት አይነቶች ከቤንቶናይት፣ ከቀርከሃ ከሰል ፣ከሺያ በተር፣አኩሪ አተር ዘይት ና ሌሎችም የተዘጋጀ ሙሉ በሙሉ ተፈጥሮአዊ ሳሙና ነው።

ጥቅሞች
የውጫዊ ቆዳ ችግሮችን ይፈታል

ለቆዳችን ልስላሴን ይሰጣል

መርዛማ ነገሮችን እና አላስፈላጊ የሰውነት ሽታን ከሰውነታችን ያስወግዳል።

Albent Healing Clay:- አልቤንት ክሌይ ከእሬት ተክል እና ከእሳተገሞራ ፍንዳታ የሚገኘው በውስጡ ከ50 በላይ ማእድናትን ከያዘው ቤንቶናይን ክሌይ የሚመረት ሲሆን የፊታችንን ሆነ የመላ ሰውነታችን የሞተ ቆዳ በማንሳት ጤናማ እና ብሩህ ገፅታ እንዲኖረን ያደርጋል።

ሁሉንም መርዛማ ቆሻሻዎች የሞቱ የቆዳ ሴሎች ቅባቶች ባክቴሪያ ዘይቶችን ከቆዳችን ያስወግዳል

አስፈላጊ የሆኑ ንጠረ ነገሮችን ለቆዳችን
ይመግባል

ለፊታችን ለብጉር ቦታዎች ሰውነታችንን ለመታጠብ እና እግርን ለመንከር ይጠቅማል በ 0912127383 ይደውሉ
2.8K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 19:13:13
አፋልጉን...
አባታችን አቶ ሳሚ ሀቢብ አህመድ ከቦሌ አካባቢ ባለፈው ቅዳሜ የወንድም አንዋርን ቀብር ለመገኘት እንደሄዱ አልተመለሱም።

ያሉበትን ያወቀ ለልጃቸው ይደውል

Tewfik habib
+251911913715
3.0K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ