Get Mystery Box with random crypto!

👳‍♂ አል ወዱድ ጀመአ 👳‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ al_wedud_jema — 👳‍♂ አል ወዱድ ጀመአ 👳‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ al_wedud_jema — 👳‍♂ አል ወዱድ ጀመአ 👳‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @al_wedud_jema
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.63K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ❤የ አል ወዱድ የሀድራ ጀመአ❤የቻናል ገጽ ነዉ ። የሀድራ መንዙማዎች ኢስላማዊ ትምህርቶች ዲን ተኮር ትምህርቶች እና ቂሳዎች ።
እናም የተለያዩ አዳዲስ የመንዙማ ስራዎች የኛንም ጨምሮ እናም አዳዲስ ነሺዳዎች ያገኛሉ ።
ለአስታየት👉 @yehabibelahI
አርሂቡ ብለናል ....... 🙏🙏🙏
🙏🙏🙏🙌🙌🙌🙌🙏🙏🙏

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 19:53:58 አምስት ነገራቶችን አትከልክለን፦
ሲትርህን፣ምህረትህን፣ ውዴታህን፣ ያማረ ኻቲማንና ጀነትህን...  ያአሏህ  
73 views{^Sala^}, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:53:37 هَٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ይህ (ቁርኣን) ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ (ሊመከሩበት)፣ በእርሱም ሊስፈራሩበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት (የተወረደ) ነው፡፡                                                    ሱረቱል ኢብራሂም
74 views{^Sala^}, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:53:57 1497ኛው የነብዩ ሙሐመድ ﷺ መውሊድ አቀባበል || በታላቁ ኑር መስጂድ አዲስ አበባ


62 views{^Sala^}, 20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:52:55
የነብዩንﷺ ውልደት አሏህ ከፍ አድርጎ አክብሮታል:: አሏህ ለውልደታቸው የጀሃነም በሮች እንዲዘጉ የጀሃነሙን መላኢካ ማሊክን አዘዘው ፣ ለውልደታቸው ጀነት እንዲዘይን የጀነቱ መላይካ ሪድዋንን አዘዘው ፣ ለሺ አመታት ሲቀጣጠል የነበረው እሳት ለክብራቸው አጥፋው ፣ እብሊስ ተወገረ.... በነብዩﷺ ውልደት እጅግ ብዙ ብዙ ጉዳ ጉዶች ሆኑ

ነቢ ﷺ ቢወለዱ

አብሮ የመጣው ኑር አለሙን አበራ
በየኮረምታው ላይ ሀቲፉ ተጣራ
ተወለዱ እያለ የከውኑ ሙሽራ
መላይካውም ቆሞ እየተሰለፈ
በየኮረምታው ላይ ሀቲፉን አጠፈ
ተወለዱ ማለት ባገር ተረፈፈ
የምስራች ማለት እጀነት አለፈ
ማሊክ ታዘዘና አዛብ ተቆለፈ
ጅብሪል ታቀፈና በጀነቱ ሀር
ያዘውና ሄደ በሀዋ ሲበር
አግብቶ አስጠወፈው በጀነት ሀገር
ስንት አጃኢብ ታየ ለቁጥር የጠፋ
ሺ አመት የበራው እሳትም ጠፋ
እብሊስ ይሄድ ነበር ሰማይ እየወጣ
ወሬ እየሰረቀ ለሰዉ ሊያመጣ
ያንን እያወራ ተመንገድ ሊያወጣ
ነቢﷺ ቢገኙ ይሄን ሹመት አጣ
64 views{^Sala^}, 20:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:47:02

93 views{^Sala^}, 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:36:23 በሚጠቅምህ ነገር ላይ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿احْرِصْ على ما يَنْفَعُكَ، واسْتَعِنْ باللَّهِ وَلا تَعْجِزْ، وإنْ أَصابَكَ شَيءٌ، فلا تَقُلْ: لو أَنِّي فَعَلْتُ كانَ كَذا وَكَذا، وَلَكِنْ قُلْ: قَدَرُ اللهِ وَما شاءَ فَعَلَ؛ فإنَّ (لو) تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطانِ.﴾

“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ። አንዳች ነገር ባጋጠመህ ጊዜ ይህን ይህን ነገር ባደርግ ኖሮ ይሄ ነገር አይከሰትም አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ። እሱም የፈለገውን ነገር ያደርጋል’ በል። ለው ‘እንዲህ ባደርግ ኖሮ’ የሸይጧንን ስራ ትከፍታለች።”
ሙስሊም ዘግበውታል: 2664
82 views{^Sala^}, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:34:30 አስደናቂው #ለማኝ እና የባለታሪኩ ገጠመኝ

በመንገድ ላይ በመጓዝ ላይ ሳለ፣ አንድ ምስኪን ለማኝ የሚሰራው ድርጊት ላይ አይኑ አረፈ። ትኩረቱን ሰጥቶ መከታተሉን ቀጠለ። ለማኙ እንዲህ ነበር የሚያደርገው.... መጥቶ ሰደቃ የሚሰጠው ሰው ጋር ረዘም ያለ ንግግር ያደርጋል። ሁሉም ሰው ሰደቃ ሊሰጠው በመጣ ቁጥር፣ እንደ ሌሎቹ ሳይሆን ረዘም ያለ ጊዜን ያናግራል። እሩቅ ላይ ስለነበሩ የሚሉትን ነገር ለመስማት አልቻለም። በመሆኑም ጠጋ ብሎ ሰደቃ በመስጠት የሚናገረውን ነገር ለማዳመጥ ወሰነ።

ኪሱ ውስጥ የነበረው 50ብር ብቻ ነበር። ታድያ 10ብር ሰጥቼ በዛውም 40ብቅ እስኪመልስልኝ ሰፊ ግዜን ወስጄ አዳምጣለሁ በማለት፤ ሄዶ ያሰበውን አደረገ። 50ብር ሰጠውና 40ብር መልስልኝ አለው። ለማኙም እንዲህ አለው........ "ያንተ ብር የሚሆነው ይህ ወደ ኪስህ የመለስከው 40ብር ሳይሆን ለእኔ የሰጠኀኝ 10ብር ነው። ምክንያቱም ይህንን 40ብር የምታውለው ምናልባት ለዱንያዊ ጥቅም ይሆናል። ጥቅሙም እዚሁ ዱንያ ላይ ይቀራል። ነገር ግን ለእኔ የሰጠኀኝ ብር ወደ አኼራ ካዝናህ ተዘዋውሯል "....

ንግግሩ ውስጤን ስለነካው በቃ እሺ መልስ አልፈልግም አልኩት። "አይይይ እኔ አንተ ብር እንድትሰጠኝ ብዬ አይደለም ይህንን የነገርኩህ። ቀሪውን 40ብር ለኔ ሳይሆን ሌላ እኔን ለመሰለ አልያም ከእኔ ለባሰ ምስኪን ለግሰው" ሲል በድጋሚ ልቤን የሚነካ ንግግር ተናገረ። ያለኝን ለመፈፀም ልጓዝ ዞር ስል እንደገና ወደ ኋላ ጠራኝ። እኔም አቤት ብዬ በደስታ ተመለስኩ። እንዲህ አለኝ "ሌላ ንግግር ጀምረን ዋናውን ጉዳይ ረሳሁት። የብርህ ምንጭ ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ። እኔም ሃላል እንደሆነ በደንብ አስረዳሁት። እሱም"እንደዛ ከሆነ ማሻ አላህ!! ብርህ ምንጩ ሃራም ቢሆን ኖሮ አልቀበልህም ነበር። ወላሂ የሚመለከተኝ አላህ ምስክሬ ነው። ከማንም ሰው የብሩን ሃላል መሆን ሳላረጋግጥ ተቀብዬ አላውቅም። ሃራም ከሆነ የሰጠኝ የብር መጠን የፈለገ ቢበዛ መልስልምታለሁ" እንዲህ እያወራን የዝሁር አዛን ወጣ። እሱም አንስቼው ዊልቸሩ ላይ እንዳስቀምጠው ነገረኝ። የዙሁር ሰዓት ብዙ ሰው ከስራ ስለሚወጣ ለልመና አመቺ ሰዓት ነው። ነገር ግን እሱ ሰላቱን በማስቀደም ለአላህ እጁን ሰጠ። ወደ መስጅድ እየገፋሁኝ ወሰድኩት። እናንተ እግር፣ እጅ፣አይን እያላችሁ ሰላተል ጀመዓ የሚያመልጣችሁ ወንዶች ከዚህ ሰውዬ የት አላችሁ!!? አንቺም ሙሰልሰል እየተመለከትሽ ሰላት የሚያልፍሽ፣ቻት ላይ ተጥደሽ ወቅቱን የምታሳልፊ እህቴ ወንድሜ ከዚህ ለማኝ አንፃር አላህ ምን ይለን ይሆን!!?

ከዓመታት በኋላ ይህንን ሰው ከቦታው ላይ አጣሁት። በአካባቢው የሚገኙ ሰዎችን ስለ እሱ እንዲነግሩኝ ጠየኳቸሁ። እነሱም እርሱ ልመናውን ትቶ። ከውጭ ሀገር በመጡ #በጎ_ፍቃደኞች እግሩን ታክሞ ድኖ፣ልመና ከመተዉም አልፎ ውጭ ሀገር ሄዶ ባካበተው ሃብት አማካኝነት ትልቅ ደካሞችንና ህፃናትን የሚረዳ ተቋም ማቋቋሙን ነገሩኝ። እኔም በአላህ ስራ ተደንቄ ከዚያን ቀን ጀምሮ በቀን ሰደቃ ሳልሰጥ ውዬ አላውቅም።


ሁላችንም ዛሬ፣አልያም ይህን ሳምንተ በየቀኑ ከ5ብር በማንሳት እስከ 1ብር ሰደቃ በመስጠት ለሰባት ተከታታይ ቀናት ታላቅ አጅርን እናግኝ!!

"#ውሃ እሳትን እንደምታበርደው ሁሉ #ሰደቃ የአላህን ቁጣ ታበርዳለች" ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አላህ በብዙ ነገር ሊቆጣብን ይችላል። ይህን ሃያል የጌቴችን ቁጣ ሰደቃ በመስጠት እናብርደው።

ይህንን ፅሁፍ #ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!!

ሼር ሼር ሼር ሼር
https://t.me/al_wedud_jema
75 views{^Sala^}, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 12:17:47 ➢ከልብሳቹሁ ይልቅ ልባችሁ እንዳይቆሽሽ ጥንቃቄ አርጉ!
ልብሳቹሁን ከአኮራ እና ከቆሻሻ እንደምትጠብቁ ሁሉ ልባችሁን ከተንኮል፣ ከክፋት፣ከትእቢት፣ ከሀሜት፣ከቅናትና ከምቀኝነት ጠብቆት።
ልክ እንደ ልብስ ልብም ሲቆሽሽ ጠረን ያመጣል።
166 views{^Sala^}, edited  09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:47:32 ለሁሉም ነገር ማፅጃ አለው። የቀልብ ማፅጃው አላህን ማውሳት ነው።
https://t.me/al_wedud_jema
138 views{^Sala^}, edited  05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:24:01 ለፈገግታ

በአንድ ወቅት ሼክና ደረሳ ነበሩ።አንድ ቀን የሆነ ቤት ሰደቃ ተጠሩና ሄዱ።

ከዛም ምግብ ቀርቦላቸው ሲያዩት በደረሳው በኩል አንድ አጥንት አለ
ከዛም ,.....


ሼኩ :- ልጄ አለማችን እንዲህ ትሽከረከራለች በማለት ያዩትን ስጋ ወደራሳቸው ያዞሩትና መመገባቸውን ይቀጥላሉ።በዚህ ሰዓት የስጋውን ቦታ መቀየር ያየ ደረሳ ምን ቢል ጥሩ ነው ፡፡
















እንዴ ያ ሼክ ዞራ እኮ አታበቃም ድጋሜ እንዲህ ትዞራለች ብሎ እሱም.........ወደ ራሱ መለሳት..... ክክክክ

ደፋር ደረሳ ነው የሚባለው ብልጡ ደረሳ ? ክክክክ

https://t.me/al_wedud_jema
https://t.me/al_wedud_jema
143 views{^Sala^}, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ