Get Mystery Box with random crypto!

Hagerie Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ hageriemedia — Hagerie Media H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hageriemedia — Hagerie Media
የሰርጥ አድራሻ: @hageriemedia
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.59K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 35

2022-09-27 21:56:31
በላጎ ተራራ በምስራቅ አማራ ፋኖ ጀግኖች እና በጥምር ጦሩ ዛሬ የተሰበረ ምሽግ ነው።የበላጎ ደጋውን ክፍል ጥምር ጦሩ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረዋል።በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የምስራቅ አማራ ፋኖ በዚህ ግንባር ትልቅ ታሪክ ሰርቷል።
1.3K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 21:02:25
ከጦር ግምባር የተሰማ ሰበር መረጃ
በጥምር ጦሩ የተነጠቁትን ቦታ መልሶ ለመያዝ እና የደረሰባቸውን ከባድ ምት ለማካካስ የህውሃት ታጣቂዎች እራሳቸውን በማደራጀት እና ሃይል በመጨመር የመልሶ ማጥቃት ሙከራ እያደረጉ ሲሆን ከትላንት ጀምሮ ውጊያው አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።ህውሃት በሸወይ በኩል ተኩለሽን መልሶ ለመያዝ እና ከቆቦ እስከ ጎብየ ያለው ሃይላቸው እንዳይቆረጥ በማሰብ ያለ የሌለ ሃይሉን እየተጠቀመ ይገኛል።በሰንደይ በር አካባቢ ሻሪያ ገነት በሚባል ቦታ በዚህ ሰዓት ጦርነቱ እንደቀጠለ ይገኛል።በራያ ግንባር ዛሬ በአራዱምና አርበት ተራሮች ላይ አየር ሀይል ጥቃት ሲፈፅም ውሏል።ህውሀት በዚህ ግንባር አሁንም በሰው ማዕበል ሃይል ለማስገባት እየሞከረ ይገኛል።ህውሀት ወደ አርበትና ድኖ ለማቅናት ከአራዱም በስተምዕራብ በኩል በአራፋ ጊወርጊስ ግራና ቀኝ የማጥቃት ሙከራ እያደረገ ሲሆን በበላጎ ቆላማው አከባቢ እና በጎብዬ ዙሪያ ባሉ ተራሮች ላይ የነበሩ ምሽጎች በአብዛኛው ተሰብረዋል።ጥምር ጦሩ ጎብዬን በቅርብ እርቀት እየተመለከተ ይገኛል ሲሉ የመረጃ ምንጮቻችን ከስፍራው አድርሰውናል። ኢበንዲህ እንዳለ ጄግናው ፋኖ አሸናፊ አለሙ የበላጎ ምሽግን ሰብሮ ተሰውቷል::ፋኖ አሸናፊ የምስራቅ አማራ የስልጠና ሃላፊ ነበር።ፋኖ አሸናፊ አሟሟቱ የጀግና፣አኗኗሩም የጀግና ነበር።የምስራቅ አማራ ፋኖ አባሉ ጀግናው ፋኖ አሸናፊ አለሙ በበላጎ በነበረው ከባድ የጨበጣ ውጊያ የበላጎ ምሽግን ሰብሮ መሰዋቱ ተገልጿል: መስከረም 16 ቀን 2015 አ.ም የምስራቅ አማራ ፋኖ በላጎ የነበረውን የአሸባሪው ህውሀት ምሽግ ሰብሮ መቆጣጠሩ ይታወሳል።ከአሸባሪው ወገን አያሌ ተዋጊዎች የሞቱ ሲሆን ምርኮና ቁስለኛውም ጥቂት አይባልም።
1.3K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 15:31:13
ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ።
ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ለኢፕድ ገልጸዋል። ድምፆዊ ማዲጎ አፈወርቅ እንደማንኛውም ድምፆዊ ዘመን የሚሻገር ስራ ባለቤት ነው።ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሔድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት ነበር።
1.4K viewsedited  12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 19:52:27
#የኢትዮጲያ_ጥምር_ጦር_አስደሳች_ድል_ተቀናጀ_ጉዞ_ወደ_መቀሌ_
በግዳን ግንባር ቀይ አፈር ላይ የነበረው የወገን ጦር ተኩለሽን፣ሸዊ ማርያምን ተቆጣጥሮ ገደባ ላይ ደርሷል።ትናንት በበቅሎ ማነቂያ በኩል ያለው ግንባር ከአራዶም በ5 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ አረፋ ጊዮርጊስ ደርሶ ወደ ፊት እያጠቃ ይገኛል።በቃሊም በላጎ ግንባር በአስሜላ በኩል ቆርጦ የገባው የወገን ጦር እጅግ ገዥ የሆነውን ጤፍ ውኃን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ቆላ በላጎ ላይ እየተፋለመ ይገኛል። የአላውሃ ግንባር በግራ በኩል የገባው የወገን ጦር ፊት ለፊት አሰፍስፎ የነበረውን ጠላት እየጠረገ ዱር ለበስ አድርሶታል። በራያ ግንባር ከሌሊቱ 11 አዓት ጀምሮ ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን በጀግኖቹ የአማራ ልዩ ሀይል ጣና ብርጌድ አና በኩሩው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አንድ ዙ 23 ከነተሽከርካሪው የማረኩ ሲሆን እንዲሁም በርካታ የህውሀት ታጣቂዎችን ደምስሰዋል።ቀይ አፈር በሚባለው ቦታ ላይ የህውሀት ታጣቂዎች 2 ኦራል ጥለው ሸሽተዋል: የህውሀት ቡድን ወረራ ከፈፀመባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው የራያ ግምባር ሳኒቃት መድሐኒያለም ቤቴክርስቲያን በመግባት አምስት ቄሶችን አግቶ ወስዶ ከምሽጋቸው አስሯቸዉ የነበረ ሲሆን የመከላከያ ሰራዊት ሲደርስበት ሁሉንም ቄሶች ገሏቸው ሄዷዋል:በአጠቃላይ አሁናዊ የወገን ጦር እንቅስቃሴ እጅግ የተናበበ መከላከያም በአካባቢውን ኅብረተሰብ እና በሚመለከታቸው አመራሮች የሚሰጠውን መረጃና ጥቆማ በተገቢው እየተጠቀመበት ይገኛል። የህዝቡ ደጀንነት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
1.6K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 22:04:08
#ቪዲዮ መንግስት በእርቅ ስም የአሰረውን ዘመነ ካሴን በአስቸኳይ ከእስር ይፍታልን ሲል አርበኛ መሳፍንት ተናገረ
1.7K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 17:12:01
አሁን ከጦር ግምባር የደረሰን ሰበር መረጃ ተሰማ
በአዲአርቃይ ዛሬ ጠዋት ጀምሮ በግራ እና በቀኝ ዙሪያውን ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን ከሰቆጣ አከባቢም ተጨማሪ ሀይል እንደወሰደ ለማወቅ ተችሏል።ወደ አዲአርቃይ ከተማ ግን እስካሁን አልገቡም።አፋር አብአላ ዉጊያዉ እንደቀጠለ ሲሆን በተጨማሪ ህውሀት ግራካሱ ተራራ ላይ ከፍተኛ ጦር አስቀምጧዋል አሁንም ሀይልም እየጨመረ ይገኛል።ከቆቦ ከወጣሁ በሚል እሳቤ ትልቅ ወታደራዊ ጠቀሜታ ወዳለው የግራ ካሱ ተራራ ሀይሉን እየሰበሰበ ሲሆን ቃሊም ግንባር ትላንት በነበረው ውጊያ ጥምር ጦሩ አስሜላ ሚካኤልንና አካባቢውን ተቆጣጥሮ የነበረ ቢሆንም ሌሊት ላይ በተደረገ ውጊያ እነዚህ አካባቢዎች ተመልሰው በህውህት እጅ ሆነዋል አሁንም ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል።
1.8K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 20:24:06
ጦርነቱ በአየርና በምድር ህውሀት እያዳፋ መቀሌ ተቃረበ
ዛሬ አብአላ፣ዉቅሮ፣አዲግራት እና ኮረም ላይ ማምሻውን የወያኔ ሰራዊት በጀግናው አየር ሃይል እምሽክ ተደርጓል።ሮቢትና አራዶም 3 የህውሀት መድፎች በአየር ሀይል መመታታቸው ታውቋል:ህውሀት ለወራት እዋጋባቸዋለሁ ብሎ በሰው ቁመት ልክ ያዘጋጃቸው ሹሉበር እና ምንደና ተራራ ስር የሚገኙ ምሽጎች በወገን ጦር ቁጥጥር ስር ውለዋል።በዚህ ግንባር አብዛኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ምሽግ ውስጥ እንዳለ አልቋል።ቃሊም ግንባር ሰንደይ በር አካባቢ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል።እጅግ በጣም ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለውን አዋስ አምዜ የሚባል ቦታን የኢትዮጲያ ጥምር ጦር ተቆጣጥሯል::
659 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 19:22:44
#መስከረም_11_ቀን_2015_ዓ_ም_ሰበር_ወታደራዊ_መረጃዎች
ጥምር ጦሩ ጠዋት በጀመረው ውጊያ እስካሁን በወርቄ በኩል 5 የጁንታው ምሽጎች ተሰብረዋል።ራማ ላይ ዉጊያ የከፈተዉ የህውሀት ቡድን በሚገባ እየተመታ ሲሆን በዚህ አካባቢ በርካታ ምሽጎች ላይ የተሳካ የድሮን ድብደባ ተፈፅሟል።በተንቤን ግንባር እርምጃ ከተወሰደባቸዉ የህውሀት አመራሮች መካከል ኮለኔል በሀታ ሀለፎም እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን ይህም ሰው የጀነራል ድንኩል ምክትል መሆኑ ተገልጿል።በመተማ የህውሀት አስተኳሽ ተይዞ ገቢ ተደርጓል:የሀገር መከላከያ ሰራዊት የራያን ግንባር በሚገባ ሰርቶታል።በግራ በቀኝ ሰብስቦ ወደ ራያ ሜዳ ቁልቁል እየነዳቸው ሲሆን የህውሀት ታጣቂ የጥምር ጦሩን ምት መቋቋም አልቻለም::ከቆቦ በስተምዕራብ በኩል በቀይ አፈር፣በወትወትና አረግዛ፣በጎሳምባ፣በአርበትና ድኖ ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል።ከሮቢት በስተምዕብ በኩል በአዋስ ስላሴ፤በማደሬ በር፣በላጭ ሚካኤል ከአምዜ ማርያም እስከ ጭራሮ አምባ ያለው የመንግስት ጥምር ሃይል ከፍተኛ ውጊያ እያደረገ ይገኛል።ከዚህ በተጨማሪ እንዶድ በሚባ አካባቢ ውጊያው እንደቀጠለ ሲሆን አቡዬ ተራራ ላይ ሰፍሮ የነበረው የህውሀት ታጣቂ በከባድ መሳሪያ እየተመታ ግማሹ ወደ ጤፍውሃ ወርዷል።ዛሬ በነበረው ውጊያ በጠቅላላው ከ580 በላይ የህውሃት ታጣቂዎች መማረካቸው ታውቋል።አራዶም በኦራል ተጭኖ በነበረ ተተኳሽ ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሙን ለማወቅ ተችሏል:ህውሀት ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በሌላ አዲስ ግንባር ማለትም ትግራይ ክልል በከፊል ከሚያዋስነው የአፋር ሰሚናዊ ዞን በራህሌ ወረዳ በተለምዶ አሳዳ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በኩል የሃይል ሚዛን ለማዛባትና ለመከፋፈል አዲስ ጥቃት የከፈተ ሲሆን እስካሁኗ ሰአት ድረስ ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል።
1.3K viewsedited  16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 12:22:22
#ዘመነ #ካሴ #ተያዘ
በአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን የታክቲክ ምርመራ ምክትል ዘርፍ ኀላፊ ኮማንደር ክንዱ ወንዴ በሰጡት መግለጫ፤ ዘመነ ካሴ በኅብረተሰቡ ጥቆማ በሕግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሔደበት ነው ብለዋል።
በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከግለሰብ ቤት መያዙን ገልጸዋል።የወንጀል ተጠርጣሪው በሕግ ቁጥጥር ሲውል 541 ሺህ ብር እና ከሌሎች ኤግዚቢቶች ጋር መያዙን ተናግረዋል። ምርመራው የሚካሔደው በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑን አረጋግጠዋል። ኮማንደር ክንዱ ተጠርጣሪው በሕግ ሲፈለግ እንደቆየ ገልጸው እንዲያዝ ለተባበረው ማኅበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል። ማንም ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል የተጠርጣሪው መያዝ ማሳያ ነው ብለዋል።
1.5K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 07:29:57 ቆቦ በህውሃት ታጣቂ አስከሬን ተሞላች
ጎንደር መተማ ልዩ ሀይልና ፋኖ ታሪክ ሰሩ


1.7K views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ