Get Mystery Box with random crypto!

🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ hafila25 — 🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤
የቴሌግራም ቻናል አርማ hafila25 — 🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤
የሰርጥ አድራሻ: @hafila25
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 231
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ላይ ከተለያዩ ፈላስፋዎች የተገኙ የፍልስፍና ሀሳቦች እና ታሪኮች እንዲሁም አንዳንድ አስገራሚ ፣ አሲቅኝ፣ እና አስተማሪ ፁሁፎች ይቀርቡበታል።
ለአስተያየት ወይም ለቻናሉ ይሆናሉ ምትሉት ፅሁፍ ካለ በዚ @hafizy_25 ያናግሩን።
👇👇👇👇👇👇
#Cross @hafizy_25

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-13 00:46:34 #hafi_ነኝ
ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ
እስኪ እናስብ

በጣም የሚፋቀሩ ጥንዶች ነበሩ፡፡ ነገር ግን በትንሽ አለመግባባት ምክንያት ግንኙነታቸውን አቋረጡ፡፡ ከተለያዩ በኀላ ሁለቱም በእየፊናቸው የሚያስቡት ይሄን ነበር፡፡

ወንዱ፡- በስተመጨረሻ ተለየዋት።
ሴቷ፡- በስተመጨረሻ ተለየኝ፡፡
ወንዱ፡- ለምን እንደዛ እንዳረኩ አላቅም፡፡
ሴቷ፡- ምናልባት ጠንካራ ምክንያት ቢኖረው ነው የተለየኝ፡፡
ወንዱ፡- ከእሷ ጋር ፍፁም ደስተኛ ነበርኩ፤ ፍፁም የሆነች ሴት ነበረች፡፡
ሴቷ፡- ሁሌ የማደርገው ነገር ቢኖር እሱን ማናደድ ነው፤ አስቀድሜ ላስብበት ይገባ ነበር፡፡
ወንዱ፡- አዲስ ሴት አግኝቻለው፤ ነገር ግን ደስ እንኳን አትለኝም፡፡
ሴቷ፡- የሚያፈቅራት ሴት አግኝቷል፡፡
ወንዱ፡- ከአዲስ ሴት ጋር የሆንኩት እሷን መርሳት ስለከበደኝ ነው፡፡
ሴቷ፡- ትዝ እንኳን አልለውም፡፡
ወንዱ፡- በህይወቴ እሷን የሚተካ የለም፡፡
ሴቷ፡- በቀላሉ በዛች ሴት ተካኝ፡፡
ወንዱ፡- ከአዲሷ ጓደኛዬ በብዙ ነገር የተሻለች ናት፡፡
ሴቷ፡- እኔ የሌለኝ ሁሉም ነገር አላት፡፡
ወንዱ፡- እሷን መልሼ ማግኘት በጣም እፈልጋለው፡፡
ሴቷ፡- ስሜን እንኳን መስማት አይፈልግም፡፡
ወንዱ፡- ሁሉ ነገሬ ናት፡፡
ሴቷ፡- ለእሱ ምኑም አይደለውም፡፡
ወንዱ፡- ግን አሁን ጠልታኝ ይሆናል፡፡
ሴቷ፡- ግን መቼም ልረሳው አልችልም፡፡
ወንዱ፡- በጣም ናፍቃኛለች፡፡
ሴቷ፡- ናፍቆኛል፡፡
ወንዱ፡- እስካሁን አፈቅራታለው፡፡
ሴቷ፡- እስካሁን አፈቅረዋለው፡፡

ወዳጄ ይሄ ሁሉ በዕራስ ዋሻ መሽጎ መብሰልሰል፣ በሀሳብ ባህር እየዘቀጡ መሰቃየት ከምን የመነጨ ይመስልሀል? ውስጥ ያለን ስሜት አውጥቶ ባለመነጋገር ነው፡፡ ይህ አለመነጋገር ደሞ ከፍራት፣ ከኩራት፣ ወይም ደሞ ከሰዎች ጫና ሊመነጭ ይችላል፡፡ ነገር ግን ወዳጄ "ዝምታ ወርቅ ነው" ፍቅር ላይ አይሰራም፡፡ የሚሰማህን ነገር በሙሉ ተንፍሰው፡፡ ሌላው ቢቀር ውስጥህ ቀለል ይለዋል፡፡ የሰላም እንቅልፍም ትተኛለህ፡

@hafila25
@hafila25 join and shr
693 views21:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 00:44:41
656 views21:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 10:46:42 #hafi_ነኝ
እስኪ እናስብ
ራስን መሆን!

ራስህን ስትሆን ሰዎች ላይወዱህ ይችላሉ፤ አስቂኙ ነገር....አይነግሩህም እንጂ በውስጣቸው እነሱም እንዳንተ መሆን ይፈልጋሉ። ወዳጄ በምንም አይነት ከባድ ሁኔታ ውስጥ ያመንክበትን ከማድረግና ራስህን ከመሆን ማቆም የለብህም!

ውብ ቅዳሜ ተመኘንላችሁ
@hafila25
957 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 21:29:32 #hafi_ነኝ
እስኪ እናስብ
ታማኝነት..!

ባለቤቴ ከአጠገቤ ተኝታለች... በድንገት የፌስቡክ ማሳወቂያ (notification) ደረሰኝ ... ከአንዲት ሴት ከእኔ ጋር ጓደኛ እንድትሆነኝ የሚጠይቅ ነበር እኔ ተቀበልኳት። ቀጥዬም እንዲህ የሚል መልዕክት ላኩላት <እንተዋወቃለን> እሷም <እንደአገባ ሰምቼ ነበር ግን እኔ አሁንም አፈቅርሃለሁ> አለችኝ።

ልጅቷ የድሮ ጓደኛዬ ነች። በfacebook ላይ ያለው ምስል በጣም ቆንጆ እንደሆነች ያሳያል። ንግግራችንን አቆምኩና ሚስቴን አስተዋልኳት... ባለቤቴ በከፍተኛ ድካም ጥልቅ የሆነ እንቅልፍ ውስጥ ላይ ነች። እሷን እያየው የማስበው እሷ ከእኔ ጋር መተኛቷ ምን ደህንነት እንደተሰማትና በአዲሱ ቤቷ ከእኔ ጋር በምቾት ያለጭንቀት እንደተኛች ነው።

ከቤተሰቦቿ በጣም እርቃ ነው ያለችው..24ሰዓት ከቤተሰቦቿ ጋር ከነበረችበት። በማንኛውም ጊዜ ብትናደድ እናቷ አጠገቧ የነበሩበት ማልቀስም ብትፈልግ የሚያፅኗኗት... ወንድሞችና እህቶቿ ቀልድ እየነገሩ ፈገግ እንድትል የሚያደርጉበት፣ አባቷ የምትፈልገውን ቤቷ ይዞ ከተፍ የሚልበት ነበር፣ ግን እሷ በእኔ በጣም ተማምና እዚህ ነው ያለችው ሁሉም አሳቦች ወደ ጭንቅላቴ መጡ... ከዛም ስልኬን አንስቼ ብሎክ(block) የሚለውን ተጫንኩኝ። ወደ ሚስቴ ዞርኩና እንቅልፌን ተኛሁኝ።

እኔ ኃላፊነቴን የማውቅ ወንድ ነኝ ደግሞም ቃል ገብቻለሁ ለባለቤቴ ታማኝ ልሆን። ይሄን ደግሞ ዕድሜ ልኬን እጠብቀዋለሁ... በሚስቴ ላይ ማግጩ በቤተሰቤ መበተን ምክንያት የምሆን ሰው አይደለውም።

@hafila25 @hafila25
389 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 21:05:11 #hafi ነኝ
እስኪ እናስብ
....
ብዙ የማውቃቸው ሰዎች ሀይማኖት ያላቸው ሲኦል እና ገነት አለ ስለተባሉ ነው። ከክፋት የሚቆጠቡት ሲኦልን ፍራቻ እንጂ መልካም መሆን ምንም ሽልማት የለውም ክፉ መሆንም ምንም ቅጣት የለውም ቢባሉ ለክፋት የሚግደረደሩ ናቸው። በሰውነት ሰው ስለመሆን ሳይሆን እግዚአብሔር ወይም አላህ ወይም ሌላኛው አምላክ በክፋታቸው ይቀጣናል ፤ በመልካም ስራቸው ይሸልመናል ብለው ስለሚያምኑ ነው ሚዛን የሚሰሩት። እስኪ እውነት እናውራ ከተባለ የብዙ ሀይማኖቶች መደምደሚያ ከሞት በኋላ ያለ ሽልማት ወይ ቅጣት ባይሆን ምን ያህል ሰው ሀይማኖት ይኖረው ነበር? ምን ያህል ሰው ቅዱስ የሚለውን ስራ ለመስራት ይጋጋጣል? ምን ያህሉስ ሰው ወደሀይማኖት ተቋማቱ እየሄደ አቴንዳንስ ያስመዘግብ ነበር?

ሜሪ ፈለቀ

እስኪ የናንተን ሃሳብ አጋሩን

@hafila25 @hafila25
936 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 21:45:01 #hafi_ነኝ
እስኪ እናስብ
ዕውቀት የሌለው ሰው ዕውቀት ማጣቱን ቢናዘዝ አዋቂ ሆነ ማለት ነው!


የአዋቂ ሰው ታላቅነት የሚገለጽው በተግባሩ እንጂ በንግግሩ አደለምና!

ታላቅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ታላቅነቱ ባለመታወቁ የማይናደድ ሰው አሱ በእርግጥ ታላቅ ነው።

ክቡራን ቤተሰቦቻችን!

:- ጥያቄ !

:-አስተያየት!

:- ማከል የምትፈለጉትሀሳብ ካለ!



@hafizy_25
@hafizy_25


ለናንተ መልስን እናደርሳለን
1.9K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 21:27:19
አርቲስት ዘነቡ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች!

"ሁለገቧ አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ ከደቂቃዎች በፊት አርፋለች ። አርቲስቷ ባደረባት የጡት ካንሰር ህመም በህክምናም በፀበልም ስትረዳ መቆየቷ ይታወቃል። የቀብር ስርዓቱ ነገ ከ8:00 - 9:00 ሰዓት በቡልቡላ መድሀኒዓለም ቤተክርስትያን ይፈጸማል።"

ለወዳጅ ዘመዶቿ እና አድናቂዎቿ መጽናናትን እንመኛለን።
1.1K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 05:18:15 ꧁# እስኪ እናስብ _[1]꧂

ባሏ በህመም ምክንያት ከስራ የተሰናበተባት እና 7 ልጆች ያሏት አንዲት እናት ቤት ውስጥ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ነገር ባለመኖሩ ከሰፈሯ ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ሱቅ በመሄድ በብድር አስቤዛ እንዲሰጣት ባለሱቁን ትጠይቀዋለች።

ባለሱቁም ሂጂ ከዚህ አልሰጥሽም ይላታል። ነገር ግን ባዶ የሆነባት እናት አጥብቃ ትለምነው ጀመር። ገንዘብ እንዳገኘሁ ወዲያውኑ ነው የምከፍለው ብትለውም እኔ ለማላውቀው ሰው ብድር አልሰጥም በማለት ይመልስላታል። ነገር ግን ሴትየዋ አጥብቃ በምትለምንበት ጊዜ ከሱቁ እቃ ሊገዛ የመጣ አንድ ደንበኛ ንግግራቸውን ሲያደምጥ ቆይቶ ነበርና ለባለሱቁ እኔ ዋስ እሆናለው የምትፈልገውን ስጣት ቢለውም በእምቢታው ቀጠለ።

ባለሱቁ እንደገና በማፌዝ የምትፈልጊውን አስቤዛ በሙሉ በወረቀትሽ ላይ ፅፈሽ ወረቀቱን ሚዛኑ ላይ አስቀምጪ በሱ ክብደት ልክ የምትፈልጊውን እሰጥሻለው ሲላት ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ስታስብ ቆየችና ወረቀት ተቀብላ የሆነ ነገር ፅፋ ሚዛኑ ላይ ጣል ስታደርገው ሚዛኑ ድንጋይ የተጣለበት ያክል ወደ ታች ወደቀ።

ባለሱቁና የሴየዋን ሁኔታዋን ይከታተል የነበረው ደንበኛ ሚዛኑን በማየት ይገረሙ ነበር። ባለሱቁ ባንደኛው ሚዛን ላይ የሚያስቀምጠው የሴትየዋን አስቤዛ በሌላኛው ጎን ያለውን ወረቀት ከፍ አድርጎ ሁለቱ የሚዛኑ አካሎች መመጣጠን አልቻሉም። እናም መጨመር መጨመር ሆነ ስራው። በስተመጨረሻም ምን አይነት ስልት ነው የተጠቀምሽው ብሎ ወረቀቱን አንስቶ ማንበብ ጀመረ።

ከዛም እጅግ በጣም ተገረመ ውስጡ ያለውም ፅሁፍ የምትገዛቸው ነገሮች ዝርዝር ሳይሆን "ፈጣሪዬ ሆይ የሚያስፈልገኝን አንተ ታውቃለህና ያለህበትን ሁኔታዬን ላንተ ሰጥቻለው" የሚል ነበር። ባለሱቁም ሚዛኑ ላይ የተቆለለውን ሁሉን አስቤዛ ከሰጣት በዋላ ወደ ቤቷ ስትመለስ በዝምታና በግርምት ያያት ነበር።

አዎ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ፈጣሪ ከኛ ቀድሞ ያውቃል እኛ ልምድ ሆኖብን ብንናገርም እሱ ሁሉን ያውቀዋል። እንዲሁም ደሞ ምንም ነገር ከፈጣሪ አይበልጥምና ከልባችን ቅን ምኞትን በፈጣሪ ወይም በቅዱስ እግዚአብሔር ላይ ጥልቅ እምነት ታክሎበት ምኞታችን በእግዚአብሔር ላይ ከሆነ ሚዛን ይደፋል ድልም እናደርጋለን።
የቅዱስ እግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት አይለየን።
አሜን

ምንጭ፦@hafizy_25
ሃሳቦን በ @hafizy_25 ያጋሩን
::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::

@hafila25
@hafila25
943 views02:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ