Get Mystery Box with random crypto!

#hafi_ነኝ ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ እስኪ እናስብ በጣ | 🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤

#hafi_ነኝ
ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ
እስኪ እናስብ

በጣም የሚፋቀሩ ጥንዶች ነበሩ፡፡ ነገር ግን በትንሽ አለመግባባት ምክንያት ግንኙነታቸውን አቋረጡ፡፡ ከተለያዩ በኀላ ሁለቱም በእየፊናቸው የሚያስቡት ይሄን ነበር፡፡

ወንዱ፡- በስተመጨረሻ ተለየዋት።
ሴቷ፡- በስተመጨረሻ ተለየኝ፡፡
ወንዱ፡- ለምን እንደዛ እንዳረኩ አላቅም፡፡
ሴቷ፡- ምናልባት ጠንካራ ምክንያት ቢኖረው ነው የተለየኝ፡፡
ወንዱ፡- ከእሷ ጋር ፍፁም ደስተኛ ነበርኩ፤ ፍፁም የሆነች ሴት ነበረች፡፡
ሴቷ፡- ሁሌ የማደርገው ነገር ቢኖር እሱን ማናደድ ነው፤ አስቀድሜ ላስብበት ይገባ ነበር፡፡
ወንዱ፡- አዲስ ሴት አግኝቻለው፤ ነገር ግን ደስ እንኳን አትለኝም፡፡
ሴቷ፡- የሚያፈቅራት ሴት አግኝቷል፡፡
ወንዱ፡- ከአዲስ ሴት ጋር የሆንኩት እሷን መርሳት ስለከበደኝ ነው፡፡
ሴቷ፡- ትዝ እንኳን አልለውም፡፡
ወንዱ፡- በህይወቴ እሷን የሚተካ የለም፡፡
ሴቷ፡- በቀላሉ በዛች ሴት ተካኝ፡፡
ወንዱ፡- ከአዲሷ ጓደኛዬ በብዙ ነገር የተሻለች ናት፡፡
ሴቷ፡- እኔ የሌለኝ ሁሉም ነገር አላት፡፡
ወንዱ፡- እሷን መልሼ ማግኘት በጣም እፈልጋለው፡፡
ሴቷ፡- ስሜን እንኳን መስማት አይፈልግም፡፡
ወንዱ፡- ሁሉ ነገሬ ናት፡፡
ሴቷ፡- ለእሱ ምኑም አይደለውም፡፡
ወንዱ፡- ግን አሁን ጠልታኝ ይሆናል፡፡
ሴቷ፡- ግን መቼም ልረሳው አልችልም፡፡
ወንዱ፡- በጣም ናፍቃኛለች፡፡
ሴቷ፡- ናፍቆኛል፡፡
ወንዱ፡- እስካሁን አፈቅራታለው፡፡
ሴቷ፡- እስካሁን አፈቅረዋለው፡፡

ወዳጄ ይሄ ሁሉ በዕራስ ዋሻ መሽጎ መብሰልሰል፣ በሀሳብ ባህር እየዘቀጡ መሰቃየት ከምን የመነጨ ይመስልሀል? ውስጥ ያለን ስሜት አውጥቶ ባለመነጋገር ነው፡፡ ይህ አለመነጋገር ደሞ ከፍራት፣ ከኩራት፣ ወይም ደሞ ከሰዎች ጫና ሊመነጭ ይችላል፡፡ ነገር ግን ወዳጄ "ዝምታ ወርቅ ነው" ፍቅር ላይ አይሰራም፡፡ የሚሰማህን ነገር በሙሉ ተንፍሰው፡፡ ሌላው ቢቀር ውስጥህ ቀለል ይለዋል፡፡ የሰላም እንቅልፍም ትተኛለህ፡

@hafila25
@hafila25 join and shr