Get Mystery Box with random crypto!

꧁# እስኪ እናስብ _[1]꧂ ባሏ በህመም ምክንያት ከስራ የተሰናበተባት እና 7 ልጆች ያሏት አ | 🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤

꧁# እስኪ እናስብ _[1]꧂

ባሏ በህመም ምክንያት ከስራ የተሰናበተባት እና 7 ልጆች ያሏት አንዲት እናት ቤት ውስጥ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ነገር ባለመኖሩ ከሰፈሯ ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ሱቅ በመሄድ በብድር አስቤዛ እንዲሰጣት ባለሱቁን ትጠይቀዋለች።

ባለሱቁም ሂጂ ከዚህ አልሰጥሽም ይላታል። ነገር ግን ባዶ የሆነባት እናት አጥብቃ ትለምነው ጀመር። ገንዘብ እንዳገኘሁ ወዲያውኑ ነው የምከፍለው ብትለውም እኔ ለማላውቀው ሰው ብድር አልሰጥም በማለት ይመልስላታል። ነገር ግን ሴትየዋ አጥብቃ በምትለምንበት ጊዜ ከሱቁ እቃ ሊገዛ የመጣ አንድ ደንበኛ ንግግራቸውን ሲያደምጥ ቆይቶ ነበርና ለባለሱቁ እኔ ዋስ እሆናለው የምትፈልገውን ስጣት ቢለውም በእምቢታው ቀጠለ።

ባለሱቁ እንደገና በማፌዝ የምትፈልጊውን አስቤዛ በሙሉ በወረቀትሽ ላይ ፅፈሽ ወረቀቱን ሚዛኑ ላይ አስቀምጪ በሱ ክብደት ልክ የምትፈልጊውን እሰጥሻለው ሲላት ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ስታስብ ቆየችና ወረቀት ተቀብላ የሆነ ነገር ፅፋ ሚዛኑ ላይ ጣል ስታደርገው ሚዛኑ ድንጋይ የተጣለበት ያክል ወደ ታች ወደቀ።

ባለሱቁና የሴየዋን ሁኔታዋን ይከታተል የነበረው ደንበኛ ሚዛኑን በማየት ይገረሙ ነበር። ባለሱቁ ባንደኛው ሚዛን ላይ የሚያስቀምጠው የሴትየዋን አስቤዛ በሌላኛው ጎን ያለውን ወረቀት ከፍ አድርጎ ሁለቱ የሚዛኑ አካሎች መመጣጠን አልቻሉም። እናም መጨመር መጨመር ሆነ ስራው። በስተመጨረሻም ምን አይነት ስልት ነው የተጠቀምሽው ብሎ ወረቀቱን አንስቶ ማንበብ ጀመረ።

ከዛም እጅግ በጣም ተገረመ ውስጡ ያለውም ፅሁፍ የምትገዛቸው ነገሮች ዝርዝር ሳይሆን "ፈጣሪዬ ሆይ የሚያስፈልገኝን አንተ ታውቃለህና ያለህበትን ሁኔታዬን ላንተ ሰጥቻለው" የሚል ነበር። ባለሱቁም ሚዛኑ ላይ የተቆለለውን ሁሉን አስቤዛ ከሰጣት በዋላ ወደ ቤቷ ስትመለስ በዝምታና በግርምት ያያት ነበር።

አዎ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ፈጣሪ ከኛ ቀድሞ ያውቃል እኛ ልምድ ሆኖብን ብንናገርም እሱ ሁሉን ያውቀዋል። እንዲሁም ደሞ ምንም ነገር ከፈጣሪ አይበልጥምና ከልባችን ቅን ምኞትን በፈጣሪ ወይም በቅዱስ እግዚአብሔር ላይ ጥልቅ እምነት ታክሎበት ምኞታችን በእግዚአብሔር ላይ ከሆነ ሚዛን ይደፋል ድልም እናደርጋለን።
የቅዱስ እግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት አይለየን።
አሜን

ምንጭ፦@hafizy_25
ሃሳቦን በ @hafizy_25 ያጋሩን
::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::

@hafila25
@hafila25