Get Mystery Box with random crypto!

#hafi_ነኝ እስኪ እናስብ ታማኝነት..! ባለቤቴ ከአጠገቤ ተኝታለች... በድንገት | 🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤

#hafi_ነኝ
እስኪ እናስብ
ታማኝነት..!

ባለቤቴ ከአጠገቤ ተኝታለች... በድንገት የፌስቡክ ማሳወቂያ (notification) ደረሰኝ ... ከአንዲት ሴት ከእኔ ጋር ጓደኛ እንድትሆነኝ የሚጠይቅ ነበር እኔ ተቀበልኳት። ቀጥዬም እንዲህ የሚል መልዕክት ላኩላት <እንተዋወቃለን> እሷም <እንደአገባ ሰምቼ ነበር ግን እኔ አሁንም አፈቅርሃለሁ> አለችኝ።

ልጅቷ የድሮ ጓደኛዬ ነች። በfacebook ላይ ያለው ምስል በጣም ቆንጆ እንደሆነች ያሳያል። ንግግራችንን አቆምኩና ሚስቴን አስተዋልኳት... ባለቤቴ በከፍተኛ ድካም ጥልቅ የሆነ እንቅልፍ ውስጥ ላይ ነች። እሷን እያየው የማስበው እሷ ከእኔ ጋር መተኛቷ ምን ደህንነት እንደተሰማትና በአዲሱ ቤቷ ከእኔ ጋር በምቾት ያለጭንቀት እንደተኛች ነው።

ከቤተሰቦቿ በጣም እርቃ ነው ያለችው..24ሰዓት ከቤተሰቦቿ ጋር ከነበረችበት። በማንኛውም ጊዜ ብትናደድ እናቷ አጠገቧ የነበሩበት ማልቀስም ብትፈልግ የሚያፅኗኗት... ወንድሞችና እህቶቿ ቀልድ እየነገሩ ፈገግ እንድትል የሚያደርጉበት፣ አባቷ የምትፈልገውን ቤቷ ይዞ ከተፍ የሚልበት ነበር፣ ግን እሷ በእኔ በጣም ተማምና እዚህ ነው ያለችው ሁሉም አሳቦች ወደ ጭንቅላቴ መጡ... ከዛም ስልኬን አንስቼ ብሎክ(block) የሚለውን ተጫንኩኝ። ወደ ሚስቴ ዞርኩና እንቅልፌን ተኛሁኝ።

እኔ ኃላፊነቴን የማውቅ ወንድ ነኝ ደግሞም ቃል ገብቻለሁ ለባለቤቴ ታማኝ ልሆን። ይሄን ደግሞ ዕድሜ ልኬን እጠብቀዋለሁ... በሚስቴ ላይ ማግጩ በቤተሰቤ መበተን ምክንያት የምሆን ሰው አይደለውም።

@hafila25 @hafila25