Get Mystery Box with random crypto!

GOFERE BUSINESS TIPS 💰

የቴሌግራም ቻናል አርማ goferebusiness — GOFERE BUSINESS TIPS 💰 G
የቴሌግራም ቻናል አርማ goferebusiness — GOFERE BUSINESS TIPS 💰
የሰርጥ አድራሻ: @goferebusiness
ምድቦች: ንግድ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.34K
የሰርጥ መግለጫ

💰 የቢዝነስ ዕውቀትን ማዳበር እንዴት ይቻላል❔
💰 ቢዝነስ መስራት እና ማሳደግስ እንዴት ይቻላል❔
💰 ትርፋማ የቢዝነስ ሀሳብ እንዴት ማግኘት ይቻላል❔
💰 ኦንላይን ስራ እንዴት ይሰራል❔
💰 አነስተኛ የንግድ ስራ እንዴት መጀመር ይቻላል❔
💰 አንድ የቢዝነስ ሰው ምን አይነት ችሎታዎች ሊኖሩት ይገባል❔
📥 ADMINs: @Fekadu_G21 @fromsisgebi

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-29 10:37:59 በአንድ የልብስ ስፌት ማሽን ሥራ
አምባሳደር ሪል እስቴት፤ አምባሳደር ሆቴልና አምባሳደር ሞል ...

#Ethiopia | የአምባሳደር ልብስ ስፌትና ንግድ ኃ/የተ/የግል ማህበር ታሪካዊ አመጣጥና እውነታዎች

የድርጅቱ ታሪካዊ አመጣጥ
አምባሳደር ልብስ ስፌትና ንግድ በድርጅት ደረጃ ከመቋቋሙ በፊት የዛሬ አርባ አመት ማለትም በ1974 ዓ.ም በአንድ የልብስ ስፌት ማሽን ስራ የጀመረ ሲሆን ከአመታት ልፋትና ጥረት በኃለ ከመስከረም 1989 ዓ.ም ጀምሮ በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ደረጃ ተቋቁሟል፡፡

ድርጅቱ ከእለት ወደ እለት እያደገ በመምጣት አምባሳደር ሪል እስቴት፤ አምባሳደር ሆቴልና አምባሳደር ሞል በሚል ስያሜ የሚጠሩ ድርጅቶችን ማፍራት የቻለ ሲሆን በስሩም በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰራተኞች የስራ እድልን ከመፍጠሩም ባለፈ ለመንግስት ተገቢውን ታክስና ሌሎች ህጋዊ ግዴታዎችን በመወጣት ለሀገሪትዋ ኢኮኖሚ ማደግ የራሱን አስተዕጾ ማበርከት የቻለ አንጋፋ የንግድ ተቋም ነው፡፡

የአምባሳደር ሞል እውነታዎች
አምባሳደር ሞል በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ከፓርላማ ፊት ለፊት በ3700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ባለ ሁለት ቤዝመንትና G+4 የሆነ የገበያ ማዕከል ሲሆን ዘመናዊ ሊፍትና እስካሌተሮችም የተገጠሙለት ህንጻ ነው፡፡ የገበያ ማዕከሉ በውስጡ የአዋቂና ህጻናት አልባሳት፤ የስጦታ እቃዎች፤ዘመናዊ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢዎች፤ካፌዎች፤ ሬስቶራንቶች፤ ባንኮች፤ ፉድ ኮርቶችና ጌም ዞኖችን አካቶ የያዘና በአንድ ጊዜ ከ120 (አንድ መቶ ሀያ) በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል የፓርኪንግ ፋሲሊቲ ያለው ህንጻ ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪም በሰከንድ 10 ሊትር ማምረት የሚችል የከርሰ ምድር ውኃ እንዲወጣና አገልግሎት እንዲሰጥም ተደርጓል፡፡

የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ
አምባሳደር ሞል በግንባታ ወቅት ከ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድልን የፈጠረ ሲሆን ህንጻው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኃላ ደግሞ ከ 200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድልን ፈጥሯል፡፡

የህንጻው የግንባታ ወጪ
የህንጻው ግንባታ እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎበትና የውጪ ሀገር ባለሙያዎች ጭምር እንዲሳተፉበት ተደርጎ የተሰራ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው ብር 500,000,000 (አምስት መቶ ሚሊዮን) በላይ ነው፡፡


ጌጡተመስገን
1.1K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 20:38:39 ጥቆማ

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ሀገር በቀል የሆኑ፣ በኢትዮጵያውያን የሚደጋጁ ፣ የኢትዮጵያውያንን ስነ-ልቡና መሰረት ያደረጉ እና የሀገሪቱን አጠቃላይ እውነታ ተመስረተው የሚዘጋጁ አነቃቂ ፣ አስተማሪ እና ልምድ ተኮር የቢዝነስ የሚድያ ፕሮግራሞች የሉም ማለት ይቻላል። ያሉትም ቢሆን አብዛኛዎቹ የውጭ ሃገራት ባህል ተጽእኖ ያለባቸው፣ አንዳንዶቹም ሙሉ ለሙሉ ( ቢልጌትስ እንዴት ሃብታም ሆነ) አይነት የተኮረጁ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ። ይሄ ብዙ ጊዜ ውጤቱ ዜሮ ነው።

ምክንያቱም ቢዝነስ እና ስራ ፈጠራዎች በአንድ ሃገር አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ መልካቸውም እድሜአቸውም ይወሰናል። አንድ አሜሪካዊ ሰው በአሜሪካ ሰርቶ ሃብታም የሆነበትን መንገድ ቀጥታ ገልብጦ አምጥቶ አፍሪካ ውስጥ ወይ ሌላ ባህል እና ኢኮኖሚው የማይመስልበት ሀገር ላይ መተግበሩ ውጤታማነቱ እምብዛም ነው። ቀላል ምሳሌ....አሜሪካዊው በዶላር ቢዝነስ ይሰራል፣ ኢትዮጵያዊው ደሞ በብር ሲሰራ ልዩነታቸው ቀንድ እና ጅራት ይሆናል። ሌላ ምሳሌ የወሲብ ፊልሞች በምእራቡ አለም በቢዝነስ ደረጃ በአመት በቢልየን ዶላር ያንቀሳቅሳል። ይሄን አምጥቶ ሃይማኖት እና ባህል ያልሞተበት ሀገር ላይ ልተግብር ማለት እብደት ነው።

ይሄን ሁሉ ያልኩት እንደኢትዮጵያዊነታችን ኑሯችንን እና ኢኮኖሚያችንን የሚመስል ምክር እና መካሪ ስለሚያስፈልገን ነው። አንድ ትንሽዬ ካፌ ለመክፈት የሚንደፋደፍን ወጣት ስለ starbugs ወይ ስለ Mcdonald ታሪክ ከምንነግረው እሱ በኖረበት አገር እና ኢኮኖሚ ሰርቶ የተሳካለትን ሰው ብንጠቁመው ይበልጥ ትምህርት ያገኝበታልም፤ motivated ይሆንበታልም። ስለዚህ ይበልጥ ሀገራዊ እውነተኛ እና በተግባር ሰርተው የተለወጡ ሰዎች እኛን ሊስተምሩን እና ሊያነቃቁን የሚችሉት።

ይህንን ስራ በየወሩ ስኬታማ ሰዎችን እየጋበዘ ተሞክሯቸውን እየጠየቀ ልምዳቸውን ለጀማሪዎች እና መነቃቃትን ለሚፈልጉ ሁሉ ፕሮግራም እያዘጋጀ ይሰራ የነበረ ወጣት ነበር።( ነብሱን ይማረውና ከሁለት አመት በፊት በመኪና አደጋ አጥተነዋል)። ነገር ግን የሰራቸው ስራዎች በሙሉ ከፍቶት በነበረው ዩቱብ ቻናል አሁንም ይገኛሉ።

ብትመለከቷቸው መማሪያም መነቃቂያም ይሆኗችኋል እና ልንጠቁማችሁ ወደድን።

የቻናሉ መጠሪያ " Mella " ይሰኛል።

መልካም አዳር።

Watch "Mella Monthly Episode 20: Selam Wondim, Co-Founder and CEO of GROHYDRO." on YouTube


1.3K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 10:40:18 ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች /ክፍል አንድ/


እና በገደብ ከገቢ ግብር ነፃ ያለገደብየተደረጉ ገቢዎች አሉ ከእነኚህ ውስጥ ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎችን ክፍል አንድ መረጃ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

1. ተቀጣሪ ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤

2. የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤

3. በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤

4. በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤

5. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው፡- ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ እና ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ

6. በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽልማት:-

• አንድን ቴክኖሎጅ ለማሻሻል፣ አዲስ የፈጠራ ስራ በመስራት ወይም ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ስራ ላይ በማዋል የሚሰጥ ሽልማት

• በአለም አቀፍ ደረጃ በሚደረግ ውድድር አገርን ወክሎ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በህግ በተቋቋመ ድርጅት በሚደረግ ማንኛውም ውድድር የሚሰጥ ሽልማት

• በፌደራል፣ በክልል፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር መንግስት የላቀ የስራ ክንውን ላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚሰጥ ሽልማት ሲሆን ሽልማቱ ከገቢ ግብር ነጻ ሊሆን የሚችለው ከፈጠራ ስራው ጋር ግንኙነት ያለው የመንግስት አካል ለፈጠራ ስራው እውቅና የተሰጠው ወይም የፈጠራ መብት ሲኖረው ነው

7. በተቀጣሪው ላይ በደረሰ ተቀር ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤

8. ስጦታው የመቀጠር፣ የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤

9. በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤

10. ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤

ክፍል ሁለት በቀጣይ ክፍል ይጠብቁን፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር

@goferebusiness
965 viewsedited  07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 17:02:04
#ዳሸን #ባንክ #ሥራፈጠራ

#goferebusinesstips
882 viewsedited  14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 05:15:35 ሰላም! እንዴት ቆያችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች?!

ረዘም ላለ ጊዜ በዚህ ቻናል ወደ እናንተ እናቀርባቸው የነበሩ የቢዝነስ ምክረ ሃሳቦች ቀዝቀዝ ብለው ነበር። ብዙ በጣም ብዙ ቤተሰቦችም በውስጥ መስመር "ምነው?" እያላችሁን ፤ አንዳንዶቻችሁም በግል ምክር እየጠየቃችሁ ነበር።

በቀናት ውስጥ በዚሁ ቻናል የቀዘቀዝንበትን ምክንያት ጠቆም አድርገን፣ እግረ-መንገዳችንንም
" ሃገራዊ አለመረጋጋት እና ቢዝነስ " በሚል ጽንሰ-ሐሳብ ዙርያ አጠር ያለ ማብራሪያ እና ምክረ-ሐሳብ በድምጽ ( Podcast ) ለማቅረብ አስበናል።

ፍቃዳችሁ እና ተሳትፏችሁ ከተጨመረበት ፡ ቀኑን ወስነን ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል። እስከዛው ቸር ያቆየን።

አምላክ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን
ለክርስትና እምነት ተከታዮች የጾማችሁትን ጾም የበረከት ያርግልን!
ለእስልምና እምነት ተከታዮች ቤተሰቦቻችንም እየመጣ ያለው የረመዳን ወቅት ጾምና ዱዓችሁን እንዲሁ ፈጣሪ ተቀብሎ ለሃገራችን ፍቅር አንድነትን ያውርድልን!
849 viewsedited  02:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 20:22:03 International Trade/አለምአቀፋዊ ንግድ ምንድነው? ስንት አይነት የክፍያ ስርአቶችስ አሉ? ዋና ዋና የሚባሉ የአለምአቀፍ የክፍያ ስርአቶችን የሚዳኙ ህግጋት የትኞቹ ናቸው? ህግጋቶቹን ማን ነው የሚያወጣቸው?
_
ዓለምአቀፍ ንግድ/International Trade በተለያዩ ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ገዢና ሻጭ የሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ ሲሆን ከአንደኛው ሀገር ወደሌላው ሀገር የክፍያ/Payment እና የእቃና አገልግሎት ፍስሰትን/Flow of goods & Services የሚያስከትል ነው።

በዓለምአቀፍ ንግድ ገዢዎችና ሻጮች የየራሳቸው ስጋት/Risks አሏቸው። ገዢው <<ገንዘቡን ቀድሜ ብከፍል /through Advance payment/ ሻጩ እቃውን ባይልክልኝስ?>> የሚል ስጋት ያለበት ሲሆን ሻጩ ደግሞ<<እቃውን አስቀድሜ ብልክለት ገንዘቡን ባይከፍለኝስ?>> የሚል ስጋት አለበት።
____
በዓለምአቀፍ ንግድ ውስጥ ስንት አይነት የክፍያ ዘዴዎች/Modes of payment/ አሉ?
_
በአለምአቀፍ ንግድ ውስጥ 5 ዋና ዋና የክፍያ ዘዴዎች/Modes of Payment/ አሉ።

1. ቅድሚያ ክፍያ/Advance Payment

ገዢ ለሻጭ በቅድሚያ ክፍያ ከፈጸመ በኋላ ሻጩ እቃውን የሚጭንበት አሠራር

2. የዱቤ ሽያጭ/Open Account

ሻጩ እቃውን ከላከ በኋላ ገዢው ክፍያውን የሚፈጽምበት አሠራር

3. Consignment የክፍያ ዘዴ

ሻጩ /Consignor/ መሀል ላይ ከሚገኝ ገበያ አፈላላጊ /Middlemen, Consignee/ ጋር ውል ፈጽሞ እቃውን ለConsignee የሚልክበት፣ Consignee ገዢ ፈልጎ የሚሸጥበት የክፍያ ዘዴ

4. የመተማመኛ ሰነድ /Letter of Credit/

ገዢና ሻጭ በባንኮቻቸው አማካይነት ሰነድ የሚላላኩበት እንዲሁም ክፍያ የሚፈጽሙበት መንገድ ነው። ሻጩ በመተማመኛ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ቅድመ-ሁኔታዎች /Conditions/ አሟልቶ ሰነዱን በወቅቱ ካቀረበ ክፍያውን የመተማመኛ ሰነዱን ከሰጠው /Issuing Bank, Importer Bank/ ክፍያውን የማግኘት መብት የሚሰጥ የክፍያ ስርአት ነው።

5. CAD/Documentary Collection የክፍያ ዘዴ

በእዚህ የክፍያ ዘዴ ሻጩ እቃውን ከጫነ በኋላ የኤክስፖርት ሰነዶችን በባንኩ /Remitting Bank/በኩል ለገዢው ባንክ /Collecting or Presenting Bank/ የሚልክበት፣ ገዢው ለCollecting Bank ክፍያ በመፈጸም ሰነዱን የሚረከብበት የክፍያ ዘዴ ነው። በእዚህ የክፍያ ስርአት የሚሳተፉት የገዢና የሻጭ ባንኮች ሰነድ ከማቀባበል እና ክፍያ ከተፈጸመ ከማቀባበል የዘለለ ኀላፊነት የለባቸውም።
____
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈቀዱ የክፍያ ስርዓቶች
____
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ክምችት ለመቆጣጠር በህግ በተሰጠው ስልጣን መሠረት አስመጪዎች የቅድሚያ ክፍያ /ከ5 ሺህ ዶላር ያልበለጠ በእራሳቸው ኀላፊነት ወስደው ከእዚያ የበለጠ ክፍያ ለመክፈል ደግሞ በሀገር ውስጥ ባንክ የተረጋገጠ የውጪ ጋራንቲ /Advance payment guarantee counter guaranteed by local banks/ በማቅረብ ክፍያ እንዲፈጽሙ ይፈቅዳል። ከእዚህ በተጨማሪ የመተማመኛ ሰነድ/Letter of Credit እና ጥሬ-ገንዘብ ተከፍሎ ገንዘብ የሚለቀቅበት/Cash Against Documents የክፍያ ዘዴዎችን በመጠቀም የዓለምአቀፍ ንግድን እንዲፈጽሙ ይፈቅዳል።

ለወጪ ንግድ/Exports ደግሞ ላኪዎች በቅድሚያ ክፍያ/advance payment፣ በመተማመኛ ሰነድ/Documentary Letter of Credit፣ በDocumentary Collection/Cash Against Documents እንዲሁም የሚበላሹ እቃዎችን (ሥጋ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ፣ አበባ፣ ጫት፣ እንጀራ) ለሚልኩ ላኪዎች Consignment የክፍያ ስርአቶችን እንዲጠቀሙ ይፈቅዳል።

የዱቤ ግዢ/Open Account/ ለገቢም ሆነ ለወጪ ንግድ አይፈቀድም።

በብሔራዊ ባንክ የSuppliers Credit/የአቅራቢ በዱቤ የመግዛት መብት የተሰጣቸው አምራች ላኪዎች/Manufacturer Exporters/ እና ላኪዎች /Exporters/ የመተማመኛ ሰነድ/LC ወይም Documentary Collection የክፍለ ዘዴዎችን በመጠቀም በዱቤ እንዲገዙ ይፈቀዳል።

የክፍያ ስርዓቶቹ በየትኛው የአለምአቀፍ ህግጋት ይዳኛሉ?
_

ከላይ ከተጠቀሱት 5 የክፍያ ስርአቶች መካከል ሁለቱን (Documentary Letter of Credit እና Documentary Collection) ተቀማጭነቱን በፓሪስ ያደረገው International Chamber of Commerce /ICC/ ባወጣቸው UCP-600 እና URC-522 የተባሉ ህጎች የሚገዙ ናቸው።
__
Tilahun Girma Ango, FCCA
Part-time trainer at NBE
Trade services Specialist

@goferebusiness
932 views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 19:10:00 #Business_Motivation

...ከሶቅራጥስ...

How Bad Do You Want It???

አንድ ዕውቀት እና ጥበብን የተራበ ወጣት ወደ ፈላስፋው ሶቅራጥስ ይሄድና እንዲህ ይለዋል።

"መምህር: እኔ ልክ እንዳንተ ሊቅ መሆን እፈልጋለሁ፤ አንተ የምታውቀውን ዕውቀት ሁሉ ማወቅ እፈልጋለሁ፤ ስለዚህ እባክህ አስተምረኝ?!"።

ይህን የወጣቱን ንግግር የሰማው ሶቅራጥስ በመገረም:-

"እኔ የማውቀውን ዕውቀት ሁሉ ማወቅ ትፈልጋለህ?" አለው።

ወጣቱም ቆፍጠን ብሎ "አዎን!" አለ።

ሶቅራጥስም ያን ወጣት አስከትሎ በአካባቢው ወዳለው ወንዝ ሄደ። ከዛም ወደ ወንዙ ገባ ብሎ ቆመና ወጣቱን ጠርቶ:-

"እስቲ መልክህን በውሃው ውስጥ ተመልከት" አለው።

ያ ወጣትም መልኩን ሊያይ ጎንበስ ሲል ሶቅራጥስ አንገቱን በመዳፉ ይዞ ወንዙ ውስጥ ደፈቀው። ወጣቱ ለመውጣት ቢንፈራገጥም የሶቅራጥስ መዳፍ ብርቱ በመሆኑ አልቻለም። ወጣቱ አየር ለማግኘት የሞት ሞቱን ሲታገል፣ ሲወራጭ ቆይቶ ሶቅራጥስ ሲለቀው ተስፈንጥሮ ወጥቶ ከልቡ ተነፈሰ። ግራ የተጋባው ወጣት እያለከለከ:-

"እንዴዴ...ምን ሆነሃል?! ምን አደረኩህ?!" አለ እየተንዘፈዘፈ።

ሶቅራጥስም:- "እኔ አሁን ያለኝን ዕውቀት ለማግኘት እድሜዬን ሁሉ እንዲህ ነው የተፍጨረጨርኩት እና የታገልኩት!! ታዲያ በድንገት መጥተህ 'ያለህን ዕውቀት ስጠኝ' እንዴት ትላለህ?! አየር ለማግኘት የታገልከውን ያህል፣ ሕይወትህን ለማትረፍ የታገልከውን ያህል ትግል ሳታልፍ እኔ ያገኘሁትን ዕውቀት አታገኝም!!" አለው ይባላል በታሪክ።

እኛስ??? ምንድነው ምንፈልገው? ተመራማሪ መሆን? አርቲስት? የተዋጣለት ድምጻዊ? የተሳካለት የቢዝነስ ሰው? የተባረከ የፍቅር ህይወት እና ትዳር? ውጭ ሀገር ሄዶ መማር? ቅን መንፈሳዊ አገልጋይ? ስመጥር አርክቴክት ወይስ የተጨበጨበለት ኢንጂነር መሆን? እነዚህን ሁሉ ለመሆን እንደዛ ወጣት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ፍላጎታችንን ተከትሎ የሚመጡ ውጣ ውረዶችን መጋፈጥ ግድ ይላል። ሴሊን ዲዮን " When you want it the most, there is no easy way out" ብላ ያቀነቀነችው ሙዚቃ አለ። ምንጊዜም ቢሆን በጣም የምንፈልገው ነገር አቅማችንን ይጠይቃል።

ለዚህ ማሳያችን ደግሞ በተግባር ተፈትነው ያለፉት ስኬታማ ሰዎች ናቸው። ክቡር ዶ/ር ቅጣው እጅጉ ካደገበት የገጠር መንደር ተነስቶ ናሳ (NASA) ለመድረስ እልሁን የተፈታተነ ጥናት እና ስራ ተጋፍጧል። እነ ሻለቃ ኃይሌ ዛሬ በዓለም መድረክ በብዙ ሺ ሰዎች ፊት ንግግር እንዲያደርጉ የሚጋበዙት ትናንት ማንም በሌለበት ጫካ እና ተራራ በብርድ በልምምድ ታሽተው ነው።

ካፕቴን አለማየሁ (የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አውሮፕላን አብራሪ ) በባዶ እግሩ በእረኝነት ከብት አግቶ፣በኩራዝ አጥንቶ ፣ተሰዶ ብዙ ፉክክር አልፎ ነው ለአየር መንገዳችን መመስረት መሰረት የጣለው። ክሪስ ጋርድነር (Pursuit of happyness ፊልም የተሰራለት ባለሀብት) Wall street stock market ውስጥ ገብቶ የመስራት ምኞቱ ትዳሩን ነጥቆታል፣ ከህጻን ልጁ ጋር ቤት አጥቶ የህዝብ ሽንት ቤት ውስጥ እስከመተኛት ዋጋ አስከፍሎታል።

አሁን ሁላችንም በቲቪ መታየት፣ፌስ ቡክ ላይ ብዙ ላይክ እና ኮሜንት እንዲኖረን፣ ሰዎች እንዲያወሩልን፣ መድረክ ላይ መቆም ወዘተ... ያምረናል( ሰዋዊ ባህርይ ስለሆነ)።ግን ይህን በረከት የሚያመጣልንን ከባዱን ስራ መጋፈጥ አንፈልግም።በቀላል አማርኛ በትምህርት ፈተና 100/100 ማምጣት እንፈልጋለን ግን ማጥናት አንፈልግም። ውፍረት መቀነስ እንፈልጋለን ግን ስፖርት እንጠላለን። ሀብት እና ክብር እንፈልጋለን ግን ዝቅ ብሎ መጀመር ያሸማቅቀናል።የፈጣሪን እርዳታ እንፈልጋለን፤ ግን አንጸልይም። ይህ እንዴት ይሆናል? ህይወት የመስጠት እና የመቀበል ህግን እንድንከተል ታስገድደናለች። አንድ የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት/ለመቀብል እኛ መጀመሪያ መስጠት ያለብን ነገር አለ። ነጮች "Nothing is for grant!" የሚሉት አባባል አለ። እናም የምናስበውን ነገር የማግኘት ፍላጎታችን ምን ድረስ ነው?? How bad do we want it??

አዘጋጅ እና አቅራቢ:- @Fekadu_G21 (Admin)

መልካም ጊዜ

@goferebusiness
1.2K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 22:02:02 እጅግ በጣም ጠቃሚ መረጃ

ክሪፕቶከረንሲ (Cryptocurrency)

አንድ ራሱን የቻለ የገንዘብ አይነት ነው። በተለምዶ የነበረው የገንዘብ አይነት የወረቀት ወይም የክሬዲት ካርድ እና የሳንቲም ነበሩ። አሁን ላይ ደሞ Cryptocurrency የሚባል ዲጂታል ገንዘብ በብዛት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። ይህ ገንዘብ በእጃችን አንዳስሰውም፤ በአይናችን አናየውም። በመሰረቱ crypto ማለት kruptos ከሚል የግሪክ ቃል የወጣ ሲሆን ስውር፣ ምስጢር ማለት ነው። በመሆኑም crypto-currency ማለት የማንዳስሰው የonline digital currency ነው። ልክ ባንኮቻችን የውጩን ገንዘብ foreign currency እንደሚሉት ማለት ነው። ይህን ገንዘብ የምናንቀሳቅሰው ኢንተርኔት በመጠቀም ነው። መነሻውም ይሄው ኢንተርኔት ነው። Cryptocurrency የሚቆጣጠረው ማዕከላዊ ባንክ የለውም። ያ መሆኑ ደሞ ጥሬ ገንዘብ ወደ አንድ ወገን ብቻ እየሄደ የሀብት ልዩነት እንደሚፈጠርበት እንደዘልማዳዊው ስርዓት ከመሆን ያድነዋል። ይህ ዲጂታል ገንዘብ የሚንቀሳቀሰው በሚጠቀሙት ሰዎች እና በኢንተርኔቱ አማካኝነት ነው።

ስንት አይነት Cryptocurrency አለ?

አሁን ላይ ኢንተርኔት ላይ ከ150 በላይ አይነት Cryptocurrency አይነቶች አሉ። ካሽ ገንዘብን ዶላር፣ ዩሮ፣ ፓውንድ፣ ዩዋን፣ብር፣ ሩጲ...እንደምንለው ሁሉ ብዙ አይነት ዲጂታል currency አሉ። ለምሳሌ bitcoin፣ ethurium፣ pi...ወዘተ። ነገር ግን የሁሉም ዋጋ ይለያያል። የእንግሊዝ ፓውንድ ከዩሮ፣ ዩሮ ደግሞ ከዶላር እንደሚበልጠው ማለት ነው። ይህ እንዲፈጠር የሚያደርገው ደሞ የተጠቃሚው ብዛት እና የኢኮኖሚው ጥንካሬ ነው። ዶላር ዩሮ እና ፓውንድ በአክስዮን ገበያው (stock market) ዋጋ ወቶላቸው እንደሚሸጡት ሁሉ Cryptocurrencyዎችም አክስዮን ገበያው ላይ ትልቅ ፉክክር ፈጥረዋል። አሁን ላይ ውዱ ክሪፕቶከረንሲ የሚባለው ቢትኮይን (bitcoin) ሲሆን የአንዱ ኮይን (1 coin) 40ሺ የአሜሪካ ዶላር ነው። ይህ የሆነው ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው። ከሱ ውጭ ያሉት እንደ Etheruem፣ USD coin፣ Tether፣ XRT ወዘተ የመሰሉት ከ 0.5 ዶላር በታች እና ከዛም በላይ ዋጋ አላቸው ። ልክ እንደ ጥሬ ገንዘብ ሁሉ ዲጂታል ገንዘብም inflation (የዋጋ አለመረጋጋት) ይገጥመዋል። ከፍም ዝቅም ይላል።


ይህ digital ገንዘብ እኔን ምን ሊጠቅመኝ ይችላል?

Cryptocurrency በመጠቀም ግዢዎችን መፈጸም እና ክፍያ መፈጸም ይቻላል። ነገር ግን online መሆን እና እቃ የምንገዛበት ተቋም ያን ዲጂታል ገንዘብ የሚቀበል መሆን አለበት። ለምሳሌ የጃክ ማ'ው #አሊባባ እህት ኩባንያ Aliexpress፣ ግዙፉ የቡና መሸጫ Starbucks፣ Amazon በተዘዋዋሪ በ eGift በኩል፣ Microsoft ኩባንያ፣ የአውስትራልያ አየር መንገድ፣ የአሜሪካው JP Morgan፣ አንዳንድ የእንግሊዝ እግር ኳስ ክለቦች ወዘተ...Cryptocurrency እየተቀበሉ ነው። አንድ ሰው ከአሊባባ ሞባይል መግዛት ቢፈልግ ድረ-ገጻቸው ላይ ገብቶ እቃውን አዞ፣ የክፍያ ዘዴ ምረጥ የሚለው ላይ Cryptocurrency የሚለውን በመምረጥ ከእሱ አካውንት (digital wallet) ወደእነሱ ትራንስፈር በማድረግ መክፈል ይቻላል።

Cryptocurrency እንዴት ሊኖረኝ ይችላል?

ጎረቤታችን ኬንያን ጨምሮ በዓለም ላይ በአሁኑ ሰአት ልክ እንደማንኛውም ሱቅ በየመንገዱ እየተከፈተ ክሪፕቶከረንሲ እየተገበያየ ይገኛል (ከላይ ፎቶዎቹን ይመልከቱ)።

ይህን ገንዘብ ለማግኘት Mining ማድረግን ይጠይቃል (በኢንተርኔት)። ለምሳሌ ወርቅን የመሰሉ ማእድናትን ከመሬት ቆፍረን እንደምናገኛቸው ሁሉ Cryptocurrencyም ከኢንተርኔቱ አለም ይቆፈራል( mining ይደረጋል)። ይሄ የ21ኛው ክፍለዘመን ምጥቀት (advancement) ነው። እናም አንድ ሰው mine ለማድረግ ወይ በዚህ ጠለቅ ያለ እውቀት ሊያስፈልገው ይገባል፤ አልያም ደሞ በስራው ላይ ላሉ ባለሙያዎች ከፍሎ mine ማስደረግ ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ሁለቱ መንገዶች ብዙውን ጊዜ ድካምም አላቸው፣ሰፊ ግብአት(resource) ይጠይቃሉ፣ ብሎም ለአጭበርባሪዎች ያጋልጣሉ።

ነገር ግን ቴክኖሎጂው እየተሻሻለ በመጣ ቁጥር ለሰዎች አጠቃቀም ቀላል ምቹ እና ቀላል የሆኑ ዘዴዎችም እየተፈጠሩ መተዋል። ለምሳሌ mine ማድረጊያ እንዲሆን develop ተደርጎ ለተጠቃሚ የቀረበው Pi network. የተባለ የስልክ መተግበሪያ(application) ትልቅ ትኩረት ያገኘው ነው። መተግበሪያው ከተለቀቀ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 4ሚልየን ሰዎች ወደ ስልካቸው አውርደው Cryptocurrency mine ያደረጉበት ሲሆን አሁን ላይ ( በሁለት አመት ውስጥ ) ተጠቃሚዎቹ ወደ 30 ሚልዮን ገብተዋል። ብዙ ኢትዮጵያንም እየተጠቀሙበት ነው። መተግበሪያው እንደ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ለመጠቀም በጣም ቀላል፣ ባትሪ የማይበላ እና ምንም ገንዘብም የማይወስድ መሆኑ አይን ውስጥ ከቶታል። ከሁሉ በላይ ደሞ mining ስራውን ለመስራት እኛ online እንድንሆን አለመጠበቁ ሌላው ደረጃውን ከፍ ያደረገለት ነው። አሁን ላይ አፕሊኬሽኑ እያመረተ ያለው የcryptocurrency አይነት Pi ይባላል። ከቢትኮይን እና ከሌሎቹ ጋ ሲነጻጸር ዋጋው ኢምንት ቢሆንም ግን ገበያውን ሰብሮ የገባበት መንገድ ከረንሲው ባጭር ጊዜ ውስጥ ማርኬቱ ውስጥ ውድ ዋጋ (value) ያስገኘዋል ብለዋል ባለሙያዎች። እነ ቢትኮይን እና ኢቱሪየምን mine ለማድረግ እንደ air fan, computer፣ strong wifi፣ complex system የሚጠይቅ ሲሆን "ፓይ Pi" ግን አንድ የስልክ መተግበሪያ ስልክ ላይ አውርዶ መጠቀምን ብቻ ነው የሚጠይቀው።

መተግበሪያውን ካወረዱ በኋላ install አድርገው እንዳበቁ ያለውን የአሰራር ቅደም ተከተል ባጭሩ እና በቀላሉ ራሱ ይመራናል። ከዛም እኛ ከተመዘገብንና mine ማድረግ ከጀመርን በየ24 ሰአት አንድ ጊዜ ብቻ በመክፈት እና "mine" የሚለውን ምልክት ነክተን መተግበሪያው ስራውን እንደጀመረ እኛ ዳታውን አጥፍተን ስልካችንን መዝጋትም እንችላለን።ነገር ግን የግድ በ24 አንዴ ከፍተን መንካት ይጠበቅብናል። መተግበሪያው online ባለው በነጻ server አማካኝነት 24 ሰአት mine ያደርጋል። መተግበሪያው google play, vidmate apps እና የመሳሰሉት ላይ ይገኛል። አውርዳችሁ mine ማድረግ ብትጀምሩና ብትሞክሩት መልካም ነው። ነጋችን (the future) ብዙ ነገሩ ኢንተርኔት ነክ ስለሆነ ከወዲሁ ከነገሮች ጋ መላመድ መልካም ነው። በመጨረሻም ማንም ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ መተግበሪያውን አውርዶ መጠቀም ለመጀመር who invited you? Inter your invitation code የሚል ጥያቄ መተግበሪያው ይጠይቀዋል እና የእኔን code መጠቀም ትችላላችሁ።

( fafi21 )

I am sending you 1π! Pi is a new digital currency developed by Stanford PhDs, with over 25 million members worldwide. To claim your Pi, follow this link https://minepi.com/fafi21 and use my username (fafi21) as your invitation code.

መልካም እድል!!!

@goferebusiness
1.2K viewsedited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 22:01:39
የዲጅታል ገንዘብ (Cryprocurrency) መገበያያ ሱቆች በኬንያ፣ ዱባይ እና ቱርክ
717 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ