International Trade/አለምአቀፋዊ ንግድ ምንድነው? ስንት አይነት የክፍያ ስርአቶችስ አሉ? ዋና ዋና የሚባሉ የአለምአቀፍ የክፍያ ስርአቶችን የሚዳኙ ህግጋት የትኞቹ ናቸው? ህግጋቶቹን ማን ነው የሚያወጣቸው? _ ዓለምአቀፍ ንግድ/International Trade በተለያዩ ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ገዢና ሻጭ የሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ ሲሆን ከአንደኛው ሀገር ወደሌላው ሀገር የክፍያ/Payment እና የእቃና አገልግሎት ፍስሰትን/Flow of goods & Services የሚያስከትል ነው። በዓለምአቀፍ ንግድ ገዢዎችና ሻጮች የየራሳቸው ስጋት/Risks አሏቸው። ገዢው የሚል ስጋት ያለበት ሲሆን ሻጩ ደግሞ የሚል ስጋት አለበት። ____ በዓለምአቀፍ ንግድ ውስጥ ስንት አይነት የክፍያ ዘዴዎች/Modes of payment/ አሉ? _ በአለምአቀፍ ንግድ ውስጥ 5 ዋና ዋና የክፍያ ዘዴዎች/Modes of Payment/ አሉ። 1. ቅድሚያ ክፍያ/Advance Payment ገዢ ለሻጭ በቅድሚያ ክፍያ ከፈጸመ በኋላ ሻጩ እቃውን የሚጭንበት አሠራር 2. የዱቤ ሽያጭ/Open Account ሻጩ እቃውን ከላከ በኋላ ገዢው ክፍያውን የሚፈጽምበት አሠራር 3. Consignment የክፍያ ዘዴ ሻጩ /Consignor/ መሀል ላይ ከሚገኝ ገበያ አፈላላጊ /Middlemen, Consignee/ ጋር ውል ፈጽሞ እቃውን ለConsignee የሚልክበት፣ Consignee ገዢ ፈልጎ የሚሸጥበት የክፍያ ዘዴ 4. የመተማመኛ ሰነድ /Letter of Credit/ ገዢና ሻጭ በባንኮቻቸው አማካይነት ሰነድ የሚላላኩበት እንዲሁም ክፍያ የሚፈጽሙበት መንገድ ነው። ሻጩ በመተማመኛ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ቅድመ-ሁኔታዎች /Conditions/ አሟልቶ ሰነዱን በወቅቱ ካቀረበ ክፍያውን የመተማመኛ ሰነዱን ከሰጠው /Issuing Bank, Importer Bank/ ክፍያውን የማግኘት መብት የሚሰጥ የክፍያ ስርአት ነው። 5. CAD/Documentary Collection የክፍያ ዘዴ በእዚህ የክፍያ ዘዴ ሻጩ እቃውን ከጫነ በኋላ የኤክስፖርት ሰነዶችን በባንኩ /Remitting Bank/በኩል ለገዢው ባንክ /Collecting or Presenting Bank/ የሚልክበት፣ ገዢው ለCollecting Bank ክፍያ በመፈጸም ሰነዱን የሚረከብበት የክፍያ ዘዴ ነው። በእዚህ የክፍያ ስርአት የሚሳተፉት የገዢና የሻጭ ባንኮች ሰነድ ከማቀባበል እና ክፍያ ከተፈጸመ ከማቀባበል የዘለለ ኀላፊነት የለባቸውም። ____ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈቀዱ የክፍያ ስርዓቶች ____ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ክምችት ለመቆጣጠር በህግ በተሰጠው ስልጣን መሠረት አስመጪዎች የቅድሚያ ክፍያ /ከ5 ሺህ ዶላር ያልበለጠ በእራሳቸው ኀላፊነት ወስደው ከእዚያ የበለጠ ክፍያ ለመክፈል ደግሞ በሀገር ውስጥ ባንክ የተረጋገጠ የውጪ ጋራንቲ /Advance payment guarantee counter guaranteed by local banks/ በማቅረብ ክፍያ እንዲፈጽሙ ይፈቅዳል። ከእዚህ በተጨማሪ የመተማመኛ ሰነድ/Letter of Credit እና ጥሬ-ገንዘብ ተከፍሎ ገንዘብ የሚለቀቅበት/Cash Against Documents የክፍያ ዘዴዎችን በመጠቀም የዓለምአቀፍ ንግድን እንዲፈጽሙ ይፈቅዳል። ለወጪ ንግድ/Exports ደግሞ ላኪዎች በቅድሚያ ክፍያ/advance payment፣ በመተማመኛ ሰነድ/Documentary Letter of Credit፣ በDocumentary Collection/Cash Against Documents እንዲሁም የሚበላሹ እቃዎችን (ሥጋ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ፣ አበባ፣ ጫት፣ እንጀራ) ለሚልኩ ላኪዎች Consignment የክፍያ ስርአቶችን እንዲጠቀሙ ይፈቅዳል። የዱቤ ግዢ/Open Account/ ለገቢም ሆነ ለወጪ ንግድ አይፈቀድም። በብሔራዊ ባንክ የSuppliers Credit/የአቅራቢ በዱቤ የመግዛት መብት የተሰጣቸው አምራች ላኪዎች/Manufacturer Exporters/ እና ላኪዎች /Exporters/ የመተማመኛ ሰነድ/LC ወይም Documentary Collection የክፍለ ዘዴዎችን በመጠቀም በዱቤ እንዲገዙ ይፈቀዳል። የክፍያ ስርዓቶቹ በየትኛው የአለምአቀፍ ህግጋት ይዳኛሉ? _ ከላይ ከተጠቀሱት 5 የክፍያ ስርአቶች መካከል ሁለቱን (Documentary Letter of Credit እና Documentary Collection) ተቀማጭነቱን በፓሪስ ያደረገው International Chamber of Commerce /ICC/ ባወጣቸው UCP-600 እና URC-522 የተባሉ ህጎች የሚገዙ ናቸው። __ Tilahun Girma Ango, FCCA Part-time trainer at NBE Trade services Specialist @goferebusiness 932 views17:22