Get Mystery Box with random crypto!

#Business_Motivation ...ከሶቅራጥስ... How Bad Do You Want It | GOFERE BUSINESS TIPS 💰

#Business_Motivation

...ከሶቅራጥስ...

How Bad Do You Want It???

አንድ ዕውቀት እና ጥበብን የተራበ ወጣት ወደ ፈላስፋው ሶቅራጥስ ይሄድና እንዲህ ይለዋል።

"መምህር: እኔ ልክ እንዳንተ ሊቅ መሆን እፈልጋለሁ፤ አንተ የምታውቀውን ዕውቀት ሁሉ ማወቅ እፈልጋለሁ፤ ስለዚህ እባክህ አስተምረኝ?!"።

ይህን የወጣቱን ንግግር የሰማው ሶቅራጥስ በመገረም:-

"እኔ የማውቀውን ዕውቀት ሁሉ ማወቅ ትፈልጋለህ?" አለው።

ወጣቱም ቆፍጠን ብሎ "አዎን!" አለ።

ሶቅራጥስም ያን ወጣት አስከትሎ በአካባቢው ወዳለው ወንዝ ሄደ። ከዛም ወደ ወንዙ ገባ ብሎ ቆመና ወጣቱን ጠርቶ:-

"እስቲ መልክህን በውሃው ውስጥ ተመልከት" አለው።

ያ ወጣትም መልኩን ሊያይ ጎንበስ ሲል ሶቅራጥስ አንገቱን በመዳፉ ይዞ ወንዙ ውስጥ ደፈቀው። ወጣቱ ለመውጣት ቢንፈራገጥም የሶቅራጥስ መዳፍ ብርቱ በመሆኑ አልቻለም። ወጣቱ አየር ለማግኘት የሞት ሞቱን ሲታገል፣ ሲወራጭ ቆይቶ ሶቅራጥስ ሲለቀው ተስፈንጥሮ ወጥቶ ከልቡ ተነፈሰ። ግራ የተጋባው ወጣት እያለከለከ:-

"እንዴዴ...ምን ሆነሃል?! ምን አደረኩህ?!" አለ እየተንዘፈዘፈ።

ሶቅራጥስም:- "እኔ አሁን ያለኝን ዕውቀት ለማግኘት እድሜዬን ሁሉ እንዲህ ነው የተፍጨረጨርኩት እና የታገልኩት!! ታዲያ በድንገት መጥተህ 'ያለህን ዕውቀት ስጠኝ' እንዴት ትላለህ?! አየር ለማግኘት የታገልከውን ያህል፣ ሕይወትህን ለማትረፍ የታገልከውን ያህል ትግል ሳታልፍ እኔ ያገኘሁትን ዕውቀት አታገኝም!!" አለው ይባላል በታሪክ።

እኛስ??? ምንድነው ምንፈልገው? ተመራማሪ መሆን? አርቲስት? የተዋጣለት ድምጻዊ? የተሳካለት የቢዝነስ ሰው? የተባረከ የፍቅር ህይወት እና ትዳር? ውጭ ሀገር ሄዶ መማር? ቅን መንፈሳዊ አገልጋይ? ስመጥር አርክቴክት ወይስ የተጨበጨበለት ኢንጂነር መሆን? እነዚህን ሁሉ ለመሆን እንደዛ ወጣት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ፍላጎታችንን ተከትሎ የሚመጡ ውጣ ውረዶችን መጋፈጥ ግድ ይላል። ሴሊን ዲዮን " When you want it the most, there is no easy way out" ብላ ያቀነቀነችው ሙዚቃ አለ። ምንጊዜም ቢሆን በጣም የምንፈልገው ነገር አቅማችንን ይጠይቃል።

ለዚህ ማሳያችን ደግሞ በተግባር ተፈትነው ያለፉት ስኬታማ ሰዎች ናቸው። ክቡር ዶ/ር ቅጣው እጅጉ ካደገበት የገጠር መንደር ተነስቶ ናሳ (NASA) ለመድረስ እልሁን የተፈታተነ ጥናት እና ስራ ተጋፍጧል። እነ ሻለቃ ኃይሌ ዛሬ በዓለም መድረክ በብዙ ሺ ሰዎች ፊት ንግግር እንዲያደርጉ የሚጋበዙት ትናንት ማንም በሌለበት ጫካ እና ተራራ በብርድ በልምምድ ታሽተው ነው።

ካፕቴን አለማየሁ (የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አውሮፕላን አብራሪ ) በባዶ እግሩ በእረኝነት ከብት አግቶ፣በኩራዝ አጥንቶ ፣ተሰዶ ብዙ ፉክክር አልፎ ነው ለአየር መንገዳችን መመስረት መሰረት የጣለው። ክሪስ ጋርድነር (Pursuit of happyness ፊልም የተሰራለት ባለሀብት) Wall street stock market ውስጥ ገብቶ የመስራት ምኞቱ ትዳሩን ነጥቆታል፣ ከህጻን ልጁ ጋር ቤት አጥቶ የህዝብ ሽንት ቤት ውስጥ እስከመተኛት ዋጋ አስከፍሎታል።

አሁን ሁላችንም በቲቪ መታየት፣ፌስ ቡክ ላይ ብዙ ላይክ እና ኮሜንት እንዲኖረን፣ ሰዎች እንዲያወሩልን፣ መድረክ ላይ መቆም ወዘተ... ያምረናል( ሰዋዊ ባህርይ ስለሆነ)።ግን ይህን በረከት የሚያመጣልንን ከባዱን ስራ መጋፈጥ አንፈልግም።በቀላል አማርኛ በትምህርት ፈተና 100/100 ማምጣት እንፈልጋለን ግን ማጥናት አንፈልግም። ውፍረት መቀነስ እንፈልጋለን ግን ስፖርት እንጠላለን። ሀብት እና ክብር እንፈልጋለን ግን ዝቅ ብሎ መጀመር ያሸማቅቀናል።የፈጣሪን እርዳታ እንፈልጋለን፤ ግን አንጸልይም። ይህ እንዴት ይሆናል? ህይወት የመስጠት እና የመቀበል ህግን እንድንከተል ታስገድደናለች። አንድ የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት/ለመቀብል እኛ መጀመሪያ መስጠት ያለብን ነገር አለ። ነጮች "Nothing is for grant!" የሚሉት አባባል አለ። እናም የምናስበውን ነገር የማግኘት ፍላጎታችን ምን ድረስ ነው?? How bad do we want it??

አዘጋጅ እና አቅራቢ:- @Fekadu_G21 (Admin)

መልካም ጊዜ

@goferebusiness