Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ የልብስ ስፌት ማሽን ሥራ አምባሳደር ሪል እስቴት፤ አምባሳደር ሆቴልና አምባሳደር ሞል ... | GOFERE BUSINESS TIPS 💰

በአንድ የልብስ ስፌት ማሽን ሥራ
አምባሳደር ሪል እስቴት፤ አምባሳደር ሆቴልና አምባሳደር ሞል ...

#Ethiopia | የአምባሳደር ልብስ ስፌትና ንግድ ኃ/የተ/የግል ማህበር ታሪካዊ አመጣጥና እውነታዎች

የድርጅቱ ታሪካዊ አመጣጥ
አምባሳደር ልብስ ስፌትና ንግድ በድርጅት ደረጃ ከመቋቋሙ በፊት የዛሬ አርባ አመት ማለትም በ1974 ዓ.ም በአንድ የልብስ ስፌት ማሽን ስራ የጀመረ ሲሆን ከአመታት ልፋትና ጥረት በኃለ ከመስከረም 1989 ዓ.ም ጀምሮ በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ደረጃ ተቋቁሟል፡፡

ድርጅቱ ከእለት ወደ እለት እያደገ በመምጣት አምባሳደር ሪል እስቴት፤ አምባሳደር ሆቴልና አምባሳደር ሞል በሚል ስያሜ የሚጠሩ ድርጅቶችን ማፍራት የቻለ ሲሆን በስሩም በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰራተኞች የስራ እድልን ከመፍጠሩም ባለፈ ለመንግስት ተገቢውን ታክስና ሌሎች ህጋዊ ግዴታዎችን በመወጣት ለሀገሪትዋ ኢኮኖሚ ማደግ የራሱን አስተዕጾ ማበርከት የቻለ አንጋፋ የንግድ ተቋም ነው፡፡

የአምባሳደር ሞል እውነታዎች
አምባሳደር ሞል በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ከፓርላማ ፊት ለፊት በ3700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ባለ ሁለት ቤዝመንትና G+4 የሆነ የገበያ ማዕከል ሲሆን ዘመናዊ ሊፍትና እስካሌተሮችም የተገጠሙለት ህንጻ ነው፡፡ የገበያ ማዕከሉ በውስጡ የአዋቂና ህጻናት አልባሳት፤ የስጦታ እቃዎች፤ዘመናዊ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢዎች፤ካፌዎች፤ ሬስቶራንቶች፤ ባንኮች፤ ፉድ ኮርቶችና ጌም ዞኖችን አካቶ የያዘና በአንድ ጊዜ ከ120 (አንድ መቶ ሀያ) በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል የፓርኪንግ ፋሲሊቲ ያለው ህንጻ ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪም በሰከንድ 10 ሊትር ማምረት የሚችል የከርሰ ምድር ውኃ እንዲወጣና አገልግሎት እንዲሰጥም ተደርጓል፡፡

የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ
አምባሳደር ሞል በግንባታ ወቅት ከ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድልን የፈጠረ ሲሆን ህንጻው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በኃላ ደግሞ ከ 200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድልን ፈጥሯል፡፡

የህንጻው የግንባታ ወጪ
የህንጻው ግንባታ እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎበትና የውጪ ሀገር ባለሙያዎች ጭምር እንዲሳተፉበት ተደርጎ የተሰራ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው ብር 500,000,000 (አምስት መቶ ሚሊዮን) በላይ ነው፡፡


ጌጡተመስገን