Get Mystery Box with random crypto!

#ወቅታዊ የኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይተዋወቁ! በቅርቡ ኢትዮ ቴሌኮም ይ | GOFERE BUSINESS TIPS 💰

#ወቅታዊ

የኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይተዋወቁ!

በቅርቡ ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ ያደረጋቸውን ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን በአጭሩ እናስተዋውቃችሁ።

ቴሌ ብር መላ

የቴሌብር ደንበኞቹን ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ በቀን እስከ 2,000 ብር፣ በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው።

ቴሌ ብር እንደኪሴ

በቴሌብር አማካኝነት ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ የቴሌብር ሂሳብዎ ከሚገዙት እቃ በታች ከሆነ ቀሪውን ክፍያ ጨምሮ ለሻጭ ይከፍልና ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ ከሂሳብዎ ላይ ተቀናሽ የሚያደርግ አገልግሎት ነው።

ቴሌብር ቁጠባ

ቴሌብር ላይ ካለው የገንዘብ መጠን ላይ መቆጠብ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን በሁለት አማራጮች ማለትም በወለድና ያለወለድ የቀረበ ነው። የወለድ መጠኑም 7% ሲሆን የወለዱ መጠን በቀን ተሰልቶ በሂሳብዎ ገቢ ይደረጋል።

#investorscafe #investors #investment #ethiopia #ethioinvestors

@investorscafethiopia