Get Mystery Box with random crypto!

ግዮን-አማራ

የሰርጥ አድራሻ: @gionamhara
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 86.76K
የሰርጥ መግለጫ

●ማንኛውንም ጥቆማ፤ አስተያየት እና የማስታወቂያ ስራ ካላችሁ 👇
@Haimonn ላይ ያድርሱን!

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-25 11:39:00 አቶ ብርሃኑ ከ8 ቀናት እስር በኋላ ተፈተዋል!

እኚህ አባት በበርካታ ጎረምሶች ተከበው ሲዋከቡ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መታየት ከጀመረ በኋላ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ለገጣፎ አቅራቢያ 44 ማዞሪያ ጅዳ ኩራ በተባለ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደነበር የተገለፀው ሲሆን ከሳምንት እስር በኋላ ትናንት መፈታታቸው ተገልጿል።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/Gionamhara
14.1K views , edited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 20:57:21
ከትላንት ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሲዘዋወር የተመለከትነው በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ውስጥ በምትገኘው ገጠራማ ቀበሌ ውስጥ ለ7 አመታት በ8.7 ሚሊዮን በመገንባት ላይ የነበረው ህንፃ ቤተክርስቲያን መመረቁን ተከትሎ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ደስታውን በጥይት ተኩስ መግለፁ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ልጁ ትጥቁን አውርዶ እንዲታሰር ተደርጓል።

ከዚህ በፊት የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በተለያዩ የእምነት ተቋማት በመገኘት ከወታደራዊ ዲሲፕሊን ውጪ ሲሆኑ ተጠያቂ ሲሆኑ አይታይም ነበር።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/Gionamhara
20.7K views , edited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 20:38:38
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከኤርፖርት በፖሊስ ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ ታስሯል።

አርቲስት አማኑኤል የአንድ ሰው ትያትር የሆነውን “ ዕብደት በህብረትን “ቲያትር ለማሳያት ከአዲስ አበባ ወደ እስራኤል ሀገር ሊሄድ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ለጥያቄ ትፈለጋለህ ብለው ፖሊሶች ይዘውት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ታስሯል።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/Gionamhara
19.8K views , edited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 20:26:06
“የእነዚያ ዘር” -በቅርብ ቀን!

ከስር ባለው የyoutube ቻናል ይለቀቃል!
https://www.youtube.com/@ategeremimtube7982
17.8K views , 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 11:39:12
ከአላማጣ እና የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን ተመድ አስታወቀ!

ግጭት ከተነሳባቸው የአላማጣ ከተማ፣ ዛታ እና ኦፍላ የራያ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ተፈናቃዮቹ የተጠለሉባቸውን የዞን ባለሥልጣናት ዋቢ አድርጎ ጽህፈት ቤቱ ሰኞ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት መሠረት ከተፈናቃዮቹ መካከል 42 ሺህ የሚሆኑ በሰሜን ወሎ በምትገኘው ቆቦ ከተማ እንዲሁም 8300 የሚሆኑት ደግሞ በሰቆጣ እና ዋግ ኽምራ ዞኖች ተጠልለዋል ብሏል።

በአብዛኛው ሴቶች፣ ህጻናት፣ ታዳጊዎች እና አረጋውያንን ያሉበት ተፈናቃዮች በማኅበረሰቡ ባሉ ቤቶች ለመጠለል እየሞከሩ እንደሆነ ገልጾ፣ ሌሎች ደግሞ ከቆቦ ከተማ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኝ ጋራ ሌንጫ በተሰኘው የኢንዱስትሪ መንደር ክፍት ቦታ ላይ ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል።

በዚህ ስፍራ የተጠለሉ ተፈናቃዮች በአስቸጋሪ ሁኔታ ለበልግ ዝናብ መጋለጣቸውን የጠቀሰው የመንግሥታቱ ድርጅት መግለጫ የተወሰኑትን ተፈናቃዮች ወደ ሌላ ስፍራ ለማዘዋወር እየተሞከረ እንደሆነ መሬት ላይ ያሉ አጋሮቹን ዋቢ አድርጓል ጠቅሷል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው!

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/Gionamhara
14.8K views , edited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 19:20:14
ጋዜጠኛ ፍላጎት አብርሃም (የልጅ ማኛ) በድጋሚ ታስራለች።

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/Gionamhara
17.4K views , 16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 12:34:55 ለዚህም ወንጀለኞች በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲጠየቁ እንጠይቃለን!! የግፉዓን ጠበቃ ለመሆን በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የምትሰሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት፣ በጠለምት የአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል የፈጸሙ የሕወሓት አመራሮች ለፍርድ እንዲቀርቡ በምናደርገው ጥረት ከጎናችን ሁናችሁ ሰብዓዊ ውግንና እንድታሳዩን እንጠይቃለን!

3) በወራሪው ሕወሓት አገዛዝ ስር የነበረው የጠለምት አማራ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ከባድ የሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዷል፡፡ አያሌ ወገኖቹ በጅምላ ተገድለውበታል፡፡ በማንነቱ ሞትን የማስተናገድ መራር ዕጣ ፈንታ በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ገብቷል፡፡ እንዲሳደድና እንዲፈናቀል ተደርጓል፡፡ ሃብትና ንብረቱንም ተዘርፏል፡፡ ለዚህም በዓለማቀፍ ተሞክሮዎች መሰረት ለደረሰብን ግፍና በደል ካሣ እንጠይቃለን፡፡ የምንጠይቀው ካሣ ለሰላሳ ዓመታት በዘለቀው የሕወሓት የአፓርታይድ የአፈና አገዛዝ ያጣናቸውን በሺህዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ሕይወት ባይመልስልንም፣ ለደረሰብን ግፍና በደል እውቅናው ቁስላችንን ያሽረዋልና፣ የፍትሕና የካሳ ጥያቄችን ገፍተን እንቀጥላለን፡፡

4) በሕወሓት የግፍ አገዛዝ ተማርረውና በእርሱ አስገዳጅነት ከጠለምት እና አካባቢው የፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደቀደመ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የማድረጉ ስራ የፌዴራሉ መንግሥት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ሊሰራው የሚገባ ቁልፍ ተግባሩ እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡ የጠለምትን ሕዝብ በጀት በመከልከልም ሆነ የልማት ድጋፎችን በመንፈግ ለዘመናት የታገለለትን አማራዊ ማንነት ጥያቄ ማስጣል አይቻልምና የፌዴራል መንግሥት የመደበኛና የካፒታል በጀታችንን እንዲለቅልን እንጠይቃለን፡፡

5) እኛ የጠለምት አማራዎች አስተዳደራዊ ነጻነታችንን በተመለከተ ትላንትም ሆነ ዛሬ ቃላችን አንድ ነው፡፡ ወደኋላ ላንመለስ ነጻ ወጥተናል፡፡ ስለማንነታችንም ከእኛ በላይ ምስክር ሊሰጥ የሚችል አንዳች አካል የለም፡፡ ከእንግዲህ ከትግራይ ሊመጣ የሚያስብ የትኛውም አካል የእኛን አማራዊ ማንነትና አስተዳደር አምኖ ተቀብሎ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ከወንጀል ነጻ መሆኑን ሳናረጋግጥ የምናስተናግደው አንዳችም እንግዳ አይኖርም፡፡ ለእንግዶች እንጂ ለወንጀለኞች ቦታ የለንም!!

6) ተፈጥሯዊ ድንበራችን የሆነውን ተከዜ ወንዝን በጋራ የምንጋራው የትግራይ ወንድም ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች በጠለምትና አካባቢው በሠላምና በነጻነት መኖር ይችላሉ፡፡ ሕግና ሥርዓትን አክብረው ለሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ጠለምትና አካባቢው ክፍት ነው፡፡ ነገር ግን እኛ የጠለምት አማራዎች፣ ማንነታችን አማራ በመሆኑ አስተዳደራዊ ክልላችን የማንነታችን አካል ከሆነው የአማራ ክልል ጋር ሁኖ በሕግ እንዲጸናልን የፌዴሬሽን ምክር ቤትን አጥብቀን እንጠይቀለን፡፡

7) የጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄን መላው ፍትሕና ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይጋሩታል፤ ጥያቄውንም ጥያቄቸው አድርገውታል ብለን እናምናለን፡፡ የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች የጠለምት አማራ እየጠየቀ ያለው፣ ‹ማንነቴ አማራ ነው፤ ማንነቴም በአስተዳደራዊ ነጻነት ይከበርልኝ› የሚል መሆኑ ታውቆ ያደረ ነውና ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!

8/ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለአጭር ጊዜም ቢሆን አንፃራዊ ሰላም አግኝቶ የነበረው የራያ ህዝብ ለአራተኛ ጊዜ በተደረገበት ወረራ በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል ንብረታቸው ተዘርፋል ወድሟል በርካታ የሰብአዊ  ግፍ እየተፈፀመባቸው ይገኛል። በዚህ የወራረ ተግባር በጠለምት 3 ቀበሌዎች በወራር ይዞ ከመገኘቱም በተጨማሪ ሌሎች  አካባቢወችንም ለመውረር ትንኮሳወችን እያደረገ ይገኛል።

ይህ የወረራ ተግባር እየተፈፀመ ያለው ደግሞ የህወሐት የታጠቁ ሐይሎች በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ትጥቃቸየውን አለመፍታታቸው ነው።
ይህ ትንኮሳ ህዝብ ተረጋግቶ ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንዳይዘጋች ከፍተኛ ስጋት ደግኖ ይገኛል። ስለሆነም መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተረድቶ  የወራሪውን ተንኮሳ እንዲያስቆም በጠለምት አማራ የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሜቴ ስም እንጠይቃለን።

የጠለምት አማራ ማንነት ትግል በከበረ መስዋዕትነታችን በዘላቂ ድል ይቋጫል!

ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕት

የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ

ሚያዚያ 13/2016 ዓ.ም.

ማይጠምሪ-ጎንደር

ኢትዮጵያ

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/Gionamhara
18.7K views , edited  09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 12:34:55 የጠለምት አማራ ማንነት በከበረ መስዋዕትነታችን በዘላቂ ድል ይቋጫል!

(ከጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)

                                               
በታሪክ፣ በሕግና በሞራል አግባብ ጠለምትና አካባቢው የበጌምድር ስሜን ጎንደር ክፍለ ሃገር ክፋይ ማንነት (አካል) ነው፡፡
“ጠለምት” ከነባሩ ጠለምትና አድርቃይ ወረዳዎች በተውጣጡ 25 ቀበሌዎች የተመሰረተ፣ 3 ወረዳዎችን (ማይጠምሪ ዙሪያ፣ ዲማ እና ማይጠምሪ ከተማን) ያካትታል፡፡ ይህ ቀጠና እንደ ወልቃይትና ጠገዴ ሁሉ በ1984 ዓ.ም በወረራ ተወስዶ የቆየ የጎንደር አማራ ግዛት ነው፡፡ ሕወሓት በ1968ቱ ማኒፌስቶው ጠለምትን የትግራይ አካል አድርጎ ቢያሰፍርም፤ ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ ነው፣ ተከዜ ወንዝን በመሻገር ቀጠናውን ለጦር ቤዝነት ያዋለው፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከ 2015 ዓ.ም መጀመሪያ ድረስ የጠለምት አካባቢ በሕወሓት አገዛዝ ሲሰቃይ ቆይቷል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት የጸደቀው በ1987 ዓ.ም ሲሆን፤ ሕወሓት እነዚህን አካባቢዎች ወደ ትግራይ ያካለላቸው ግን ከ1984 ዓ.ም በፊት ስለመሆኑ ነው፡፡ እኛ የጠለምት አማራዎች ያለሕግ እና ያለሕዝብ ይሁንታ በጉልበት ነበር ወደትግራይ ክልል በጭፍለቃ የተካለልነው፡፡

ከጠለምትና ከአድርቃይ ተቆርሰው በተወሰዱ ግዛቶች ውስጥ ህወሓት ብዛት ያላቸው ሰፋሪዎችን ባለማስፈሩ በአካባቢው ያለው የሥነ-ሕዝብ ስብጥሩም ሆነ የሥነ-ልቦናው ሁኔታ አማራነት የሚንጸባረቅበት ነው፡፡
ሕወሓት ጠለምትን እና አካባቢውን ለመውረር የፈለገበት ምክንያት አንደኛ አካባቢው ለወታደራዊ ስትራቴጅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጠለምትና አካባቢው ያለው የተፈጥሮ ሀብት እጀግ ብዙ ከመሆኑ ጋር ይያያዛል፡፡ የቦታው አቀማመጥም ለቱሪስት መስህብነት ያለው ፋይዳ፣ የልዩ ማዕድናት መገኛ፣ የደን፣እምነ-በረድና የእጣን ሙጫ ምርት፣ የእንስሳት ሀብቱ ብዛት የጠለምት በረከተ-ፀጋዎች ናቸው፡፡ በማዕድን ዘርፍ በተለይ የወርቅ ክምችቱ እጅግ ብዙ በመሆኑ ህወሓት ጠለምትን ሲያደማ እንዲኖር አድርጎታል፡፡ ለትግራዩ ሳባ የእምነ-በረድ ፋብሪካም ማዕድኑ የሚሄደው ከጠለምት መሬት ነው፡፡

በአጠቃላይ፣ ትግራይ አብዛኛውን የማዕድን ሀብቷን የምታፍሰው ከጠለምት ቀጠና እንደነበረ መላው የአማራ ሕዝብ፣ ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲያውቁልን እንወዳለን፡፡ የአማራ ሕዝብና አመራሩ፣ ይህን እውነታ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ የትግራይ ሰዎች ከዐድዋ፣ አክሱምና መቀሌ ድረስ መጥተው፣ የጠለምትን ሁለንተናዊ እምቅ ሀብትና ጥቅም ተገንዝበው በወረራ መዝለቃቸው ባይጠፋቸውም ‹ጠለምት ወይም ሞት!› ብለው ከ30 ዐመታት በላይ ሲጠቀሙበት፤ ባለ ርስቱ ጎንደሬ፣ ባለቤቱ አማራ አካባቢውን ባለማወቅ ያላግባብ ጥቅሙን አሳልፎ ሰጥቶ ከርሟል፡፡ አሁን ግን መላ አማራ ነቅቷል፤ የማንነት ትግሉ ተወናይ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡
የጠለምትን የማንነት ትግል ገና ከጅምሩ ለማደናቀፍ ሕወሓት ከቅጥረኛ ወኪሎቹ ጋር ሆኖ ሰርቷል፡፡ በ1985 ሕዝቡ 80 ሽማግሌዎችን መርጦ ቅሬታውን ለአማራ ክልላዊ መንግሥት ለማቅረብ መወሰኑን ተከትሎ፣ ከመሃላቸው አራት ሽማግሌዎች በወቅቱ የክልሉ ፕሬዚዳንት ለነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ አቤቱታቸውን አድርሰዋል፡፡ አቶ አዲሱም አቤቱታ አቅራቢዎቹን የ80ዎቹን ወኪሎች ስም ዝርዝር እንዲሰጧቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለትግራይ አስተዳደር አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ የትግራይ አስተዳደርም ለመጀመሪያ ጊዜ አቤቱታውን ለአማራ ክልል መንግሥት ያቀረቡትን አራት ተወካዮች አስሮ በመውሰድ ረሸኗቸዋል፡፡ በሂደትም፣ ቀሪዎቹን 76 ተወካዮች አንድ ባንድ እየለቀሙ አጠፍቷቸዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ጠለምት መሬት ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የአማራነት ጥያቄ አንስቶ ፍትሕን መጠየቅ ከባድና የማይታሰብ በመሆኑ፤ ሌላ የትግል አማራጭ መፈለግ የግድ ሆነ፡፡

በዚህ አስገዳጅ እውነታ የተነሳ የመጀመሪያው የከፋኝ (ፋኖ) ተጋድሎ በጠለምት ተጀመረ፡፡ ጠለምት ውስጥ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ የአማራነት ጥያቄን ማንሳት የማይቻል መሆኑን ተከትሎ፤ በርካታ ተወላጆች ጫካ ገብተው ተፋልመዋል፡፡ በአርማ ደጋ በረሃ ውለው ማደሩን ተያያዙት፡፡ የጠለምት ፋኖዎች ሕወሓትን አብዝተው ፈተነው፣ እረፍት ነስተውታል፣ በወቅቱ ትግሉ የሚጠይቀውን ከባድ መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ወራሪው ኃይል የጠለምት መሬት የእግር እሳት እስከሚሆንበት ድረስ ዋጋ አስከፍለውታል፡፡

በዚህ ትግል ሂደት ውስጥ ሕወሓት የቻለውን ገደለ፤ አንዳዶቹን የነጻነት ታጋዮች ደግሞ በምህረት ስም እንዲገቡ አድርጎ ረሸነ፡፡ በዚህ የፋኖነት ዘመን በርካታ ጀግኖች የሕወሓትን ታጋዮች ጥለው ወድቀዋል፡፡ በወቅቱ ‹ሕወሓትን ስለማናምን በምህረት አንገባም› ብለው የቀሩት ፋኖዎች እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ አድራሻቸውን ሰውረው ገባ-ወጣ ያለ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው፣ ከጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም ጀምሮ አገራችን ከሕወሓት ጋር በገባችበት ጦርነትም ንቁ ተሳታፊ በመሆን፣ በጠለምት ግንባር የታሪክ አደራቸውን አስቀጥለዋል፡፡
በአጠቃላይ ትግሉ በሁለት ትውልዶች ቅብብል አሁን ያለበት ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፤ የቀደሙት ሰማዕታት ‹ትግላችሁ ከንቱ አልቀረም› ብለን ዘላቂ ድላችን በከበረ መስዋዕትነታችን ለማረጋገጥ ዛሬም ቃላችን እናድሳለን፡፡
በመሆኑም፡-

1) ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ጀሮ የነፈገው  የዘር ማጽዳት ወንጀል በጠለምት የአማራ ሕዝብ ላይ ተፈጽሟል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል የተፈጸሙ የዘር ማጽዳት ወንጀሎች አንዴ ተጀምረው በተወሰነ የጊዜ ገደብ የተጠናቀቁ ቢሆንም፣ በጠለምት ሕዝብ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል ግን በአይነትም ሆነ በድርጊት የተለየ ነው፡፡ ለሠላሳ ዓመታት ያለ ማቋራጥ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ እኛን የማጽዳት ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በሺህዎች የሚቆጠሩ አማሮች በማንነታቸው ተገድለዋል፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወገኖቻችን ወዳልታወቁ ስፍራዎች ታፍነው ተወስደው በእስር ሲማቅቁ ኑረዋል፤ ብዙዎችም ባሉበት አልፈዋል፡፡ በጥቅሉ በሠላሳ ዓመቱ የወያኔ አፓርታይዳዊ ዘመን በተለየ ሁኔታ በከተሞች በርካታ የጠለምት አማራ ከእርስቱ ተፈናቅሎ እንዲሰደድ ተደርጓል፡፡

ዛሬ የዘመናት ትግላችን ሂደትና የሁለት ትውልዶች ቅብብል መስዋዕትነታችን የጠለምት አማራ የተነጠቀ ማንነቱን ማስመለስ ችሏል፡፡  እኛ የጠለምት አማራዎች ያስመለስነው ማንነት እንጅ የነጠቅነው መሬት የለም!! የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም፤ የራሳችንንም አሳልፈን አንሰጥም!! ማንነታችን አማራ ድንበራችን ተከዜ ነው!!

2) የሕወሓት አፓርታይዳዊ አገዛዝ ከተዘረጋ ጀምሮ በጠለምት የአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል ታውጆ ተፈጻሚ ተደርጓል፡፡ በዋልድባ ገዳም ይህ ነው የማይባል ግፍና መከራ ደርሷል፡፡ መነኮሳት በብሔራቸው ምክንያት ሞት ታውጆባቸው ተሳድደዋል፤ ተፈናቅለዋል፡፡ በተገኙበት ታፍነው ተወስደዋል፡፡ በእኛ በኩል በዓለማቀፍ መመዘኛዎች ስንመለከተው በጠለምት  የአማራ ሕዝብ ላይ ዓለም ያልሰማው የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሞበታል፡፡
17.0K views , edited  09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 12:34:52
16.0K views , 09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 21:27:20
ጎሀፅዮን እና ገብረ ጉራቻ መካከል በቀን 11-08-2016 ዓ.ም አንድ ታታ ሙሉ ሰው በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል። አንድ ከታጋቾች መካከል ያለች እንስት ለቤተሰብ ስልክ ደውላ “ሁለት ቀን የእግር መንገድ ተጓዝን እጅግ ከፍተኛ ድካም ውስጥ ነን። የታገትነው ባሱ ውስጥ ያለን ሰዎች በሙሉ ነው። እንድንለቃችሁ ስልክ ደውላችሁ ብር አስልኩ ነው የሚሉን።” ብላለች!

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/Gionamhara
18.9K views , 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ