Get Mystery Box with random crypto!

“አማራ ነን እንጂ፤አማራ እንሁን አላልንም!” -የጠለምት አማራዎች በሰሜን ጎንደር ዞን በምስራቅ | ግዮን-አማራ

“አማራ ነን እንጂ፤አማራ እንሁን አላልንም!” -የጠለምት አማራዎች

በሰሜን ጎንደር ዞን በምስራቅ ጠለምት ወረዳ ነዋሪዎች መንግስት ከአካባቢው የአማራን አስተዳደር በማፍረስ ለትግራይ ክልል ሊያስረክብ ነው መባሉን ተከትሎ በምስራቅ ጠለምት የማንነት ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

በሰልፉ የጠለምት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ነጋ ካሳና አባላቱ የተገኙ ሲሆን በማንነት ሕዝባዊ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

❶የጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ የፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው!

❷አማራ ነን እንጂ፤አማራ እንሁን አላልንም!

❸አማራዊ ማንነታችንና የወሰን አስተዳደር ግዛት በሕግ አግባብ ይከበር!

❹መንግስት በጀታችን ይልቀቅልን!

ለትኩስ መረጃዎችን የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!
https://t.me/Gionamhara