Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም ብቻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ getem0 — ግጥም ብቻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ getem0 — ግጥም ብቻ
የሰርጥ አድራሻ: @getem0
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.80K
የሰርጥ መግለጫ

የፍቅር_ግጥሞች
የፍቅር_ታሪኮች
የሙዚቃ_ግጥሞች
የተለያዩ_ግጥሞች
ጠቃሚ_መረጃዎች/አዲስ_ነገር
ቻናላችንን join በማረግ ይቀላቀሉን
@Getem0
ለማንኛውም አስተያየት/ግጥም ለመላክ
@dada_KL
@dada_KL

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-21 22:42:38
የቴዲ አፍሮ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ

#ዳጉ_ጆርናል
1.1K viewsDada 1, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 22:11:46
ባሳለፍነው ሳምንት በጊምቢ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ በግፍ ህይወታቸውን ላጡ እጅግ በርካታ ንፁሀን ዜጎቻችን ሀዘናችንን ለመግለፅ ቢያንስ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ይህንን ምስል በማጋራት እናስባቸው!

ሲሆን ሲሆን የሀዘን ቀን ታውጆ እና ባንዲራችን ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ መደረግ ነበረበት።

ነፍስ ይማር ወገኖቼ!

#አትግደሉን #ፍትህ
1.0K viewsDada 1, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 11:39:49 ይብላኝለት ለኔ
።።።።።።።።።።።

ያልወረደ መና ፣
ልቡን ለሰቀዘው፣
ያልተበላ ዳቦ፣
፣አንጀቱን ለያዘው።
ባልተጠጣ ወተት ፣
ምናቡ እያገሳ፣
ስጋው ሲደነድን፣
ልቡ ለሚከሳ።

ይብላኝለት ለኔ...
ኖርኩ እያለ ሲሞት፣
አፈር ለማይለብሰው፣
ይብላኝለት ለኔ
በነፍስና ስጋ፣ ድንበር ተገትሮ፣
መኖር ላልቀመሰው።
ዛሬ ቀኑ ፀሀይ ፣ ነግ ደሞ ዳመና፣
ታቻምና ረሀብ ነው ፣ አሁን ብልፅግና።
ፍቅር ይተኮሳል፣ ከወዲያኛው ማዶ፣
ዘመድ ይገናኛል፣ ተራራው ተንዶ።
ምናምን ምናምን...
ይሉት እንቶፈንቶ...

ቢያገኝ ለሚበላ ፣ቢያጣ ለሚጋደም፣ ተመስገኑን በልቶ፣
ምን ሊፈይድለት፣ አንዱ አደረ ቢባል፣ በሰው ስጋ አግስቶ?

ይብላኝለት ለኔ...
ከሰው አብራክ ወጥቶ ፣
ሰው ለማይናፍቀው፣
ዕልፍ ችግኝ መሀል፣
ተስፋው ለደረቀ
እኔን ባይ ለራቀው።
ይብላኝለት ልቤን ፣
ይብላኝለት ገላ፣
ብርድ አያውቅ ሙቀት፣
የአፍላነት ዘለላ።
እንባ የለው ዐይኔ፣
ላብ የል ከአካላቴ፣
እንዲህ ያል ድርቅናን፣
ከማን ሸመትኩ እቴ?
ሳቅ እማያስቀኝ ፣
ሰቆቃ እማይገደኝ፣
ምን ያል የሰው አውሬ ፣
አምጦ ወለደኝ?

ይብላኝለት ዐይኔን ...
የሱ ብጤ በርባን፣
አማትሮ ለሚያጣ፣
ውንብድናው አንሶት፣
አምላክ ለሚቀጣ።
ባልሰመረ ቅኝት፣
ለሚደክር ከንፈር፣
መሳም ላልታከተው
ያለመተፋፈር።
ለማይደክም እግሬ፣
በየብስ ባህሩ፣
ንዳድ ለሚነዳው
አልፎ ከድንበሩ።
ይብላኝለት ለኔ...
ሰው ተብሎ ላልሞላው፣
የ "ሰ"ን አንድ ቅኔ።
ይብላኝለት ለኔ!

በማዕዶት ያየህ
18/09/2014 ዓ.ም.

@getem0
@getem0
@getem0
1.4K viewsDada 1, edited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 11:39:49 የሚገርመኝ
ቄስ አግዞ ፣ መለኮት
መንፈስ ቅዱስ ፣ ውሃን ባርኮት
እውር አይኑ ፣ ሲበራለት
ሽባ እግሩ ፣ ሲተረተር
ከተዓምር ፣ ሲቆጠር።

"የሚደንቀኝ"
ለብቻዋ ፣ ሳለች እናት
ወይ መለኮት ፣ ሳይወግናት
በእውር አለም ፣ ስታበራ
በሽባ ምድር ፣ ስትመራ
እንደተራ ፣ የሚቆጥሩት
እንደ ታምር ፣ ማያወሩት።

"የምመኘው"
በየገዳም ፣ በየደብሩ
ተጋድሎሽን ፣ እንዲያወሩ
ፈወስሽኝ ስል ፣ ከ እውር ጽልመት
አዳንሽኝ ስል ፣ ከመቆመጥ
ልጅነቴን ላጠነክር፣
ገድልሽን ልመሰክር።

[ ቃለ መወድስ ]

እናትነት
ቢሳለሙት ፣ እንደ ዳዊት
ቢተሻሹት ፣ እንደ እምነት
ትርፉ ድህነት።
ቢጻበሉት ፣ እንደ ጠበል
ቢያወድሱት ፣ እንደኪዳን
ዋጋው መዳን።


@getem0
@getem0
@getem0
1.0K viewsDada 1, edited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 11:39:48 በማርያም !

(ሚካኤል.አ)

ሸልምልኝ አደራህን 

ፊት አትንሳ ፍጥረትህን

ለፍርሀት ሳያረግዱ 

"ሲኦል... ሲኦል" በመንገዱ

የሚል ጩኸት ሳይጨንቃቸው

አንተን ፈርተው ዘፈን ወደው 

ከሰባኪ ተሸሽገው ...

ለሚሞቱ ...

ደግሞ ለዛ ደፋር... ለዛ ጉምቱ 

ተፈላስፎ ... ተመራምሮ ...

.......ዓለሟ ላይ ተራቆባት ለሚሄደው

ከራሱ ሀሳብ ሳይወሸክት ለሚነጉደው

አለ ሲሉት ሲኦል ሰይጣን አለ ሲሉት ሲኦል እሳት

ነፍሱን ፊት ሳይሰጣት.. .

ፍልስፍናን ወድዶ... ቅድሚያውን ለቸራት

ለዛ ብርቱ ... የአቋም ሰው 

ለድፍረቱ ብቻ ገነትን አውርሰው !

@getem0
@getem0
@getem0
1.6K viewsDada 1, edited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 11:39:48 #ተነድፈሽ_ክበሪ
:
:
እኔ አልነደፍም የሚለው ፉከራ፤
በገዛ አንደበትሽ በኩራት ሲወራ፤
ካንዴም አስር ጊዜ ደርሶ ሰምቻለው፤
ትክክል ነው ብሎም የሚያጎበጉብ ሰው በቅርብ አይቻለው።
:
:
እውነት ነው ወይ ብዬም በዙሪያሽ ያሉትን ዞሬ ሳጤናቸው፤
መላከፍ ነው እንጂ መንደፍ የማይችሉ ተራ ዝንቦች ናቸው።
:
:
አፍኜው ነው እንጂ ድሮም ያንቺ ነገር ያንገበግበኛል፤
ከንቱ ፉጨት ከቦሽ መኩራትሽ ገርሞኛል።
:
:
ከ ዐጀቦችሽ አንፃር መደምደምሽን ሳይ አናገረኝ እንጂ የሆዴ መከፋት፤
ባንቺ አልተጀመረም አደባባይ ቆሞ በጀሌ ተከቦ አጉል ጉራ መንፋት።
:
:
እውነት እውነት ስልሽ ያለመነደፍሽን ሚስጥሩን ላወቀው፤
ልክ እንደኔ ሁሉ ሆድ ቢብሰው እንጂ ቅንጣትም አይደንቀው።
:
:
ይልቁን አንቺ ሴት አንዣባቢሽ በዝቶ እንዳትዘናጊ፤
የማሩን እንጀራም ያንቺ እንድታደርጊ፤
ተነድፎ ለመክበር በይ ከንብ ተጠጊ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem0
@getem0
@getem0
911 viewsDada 1, edited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 15:22:29 በስሜትሽ በስሜቷ
አምባር ክንዷ ዋንጫ አንገቷ
እየረታኝ እርቃን ቃሏ
እያሰረኝ ልቅ አካሏ
ብዕር ቁልቁል እያደላ
ልገጥምለት ላ'ልቦ ገላ

ስሽኮረመም ስግደረደር
ሐረግ ስኩል ስንኝ ስድር
ቢያስገርመኝ
ቢያስደምመኝ ሃቅ እውነታ
ለቃል ፊደል ሰጪ ጌታ
ለኔ አንቺን የሚነሳኝ
ከተሰጪ የሚረሳኝ
ምን ባጠፋ ምን ብበድል
ያሳነሰኝ ከቃል እድል
ምን ባይኖረኝ ምን ብጎድል?

እግዚአብሔሩስ እየሳሳሽ
ለሰው ላዳም የሚነሳሽ
ምን ብትሆኚ መከልከልሽ
ወይ አይድርሽ
ወይ አይኩልሽ

ለመላዕክት ለ ቅዱሳን
ማትገለጭ
ሚስጢር ድርሳን
ሂጃብ ነሽ ወይ?
ወይ ማህተብ
የእምነት ማጽኛ የእውነት ገደብ
መሐላ ነሽ? ወይ ቃልኪዳን
ላዳም ተስፋ ለሰው መዳን

ምን ነሽ አንቺ
ሚያስውብብሽ ሰይጣን መልኩን
ሚለካብሽ ውበት ልኩን
መስታዬት ነሽ? ንጹህ ውሃ
በረዶ ነሽ? ወይ በረሃ
እየቆየሽ ምትጠሚ
ዲያቢሎስን ምትጠቅሚ

ትዝታው ነሽ? ወይ ቅጽበቱ
ሳያዘቅጠው መተበቱ
ለነበረው ሰማይ ቤቱ
እንባ ካይኑ እየደማው
ያንን ስልጣን ያንን ግርማው
ሚስልብሽ ዘፈን ዜማው?

ላትገዝፊ ካንዲት ፊደል
ንጥል ሆኜ የምበደል
ጠንቋይ እንኳ ማይገምትሽ
እንደ እጣን የምትጨሽ
ማን ነሽ አንቺ
ምን ነሽ አንቺ
ቅኔ ነሽ ወይ ማትፈቺ?


@getem0
@getem0
@getem0
1.1K viewsDada 1, edited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 22:20:06 ጋይስ Make money reality ዌብሳይት ነው ተጠቀሙበት እቤቶ ቁጭ ብለው አኳውንት ከፍተው በቀን እስከ 200$ ይስሩ መልካም እድል
1.2K viewsDada 1, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 22:19:55 Do quizzes to earn US dollars, easily earn 1 US dollars in 1 minute, and anyone who logs in to our website will get 10 US dollars. https://en61.xyz/71112659563415461/?s=tg
1.1K viewsDada 1, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 17:16:09 ጋይስ Make money reality ዌብሳይት ነው ተጠቀሙበት እቤቶ ቁጭ ብለው አኳውንት ከፍተው በቀን እስከ 200$ ይስሩ መልካም እድል
1.2K viewsDada 1, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ