2022-04-18 13:40:19
#5ቱ ሀዘናት
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 5ቱ ሀዘናት አንድ አምላክ በሚሆን በአብ፣ በወወልድ፣ በወመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፭ቱ ታላላቅ ኀዘናት ማን ማን ናቸው ቢሉ? ።
፩ኛ - ስምዖን በቤተ መቅደስ ትንቢት በተናገረ ጊዜ።
፪ኛ - ከቤተ መቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ።
፫ኛ - በጲላጦስ አደባባይ በገረፉህ ጊዜ።
፬ኛ - በዕለተ ዓርብ በሰቀሉህ ጊዜ።
፭ኛ- ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው ወደ አዲስ መቃብር ባወረዱህ ጊዜ።
..
ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን
በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኅዘናት የትኛው ይበልጣል ብሎ በጠየቃት ጊዜ ???
እመቤታችንም ልጄ ወዳጄ ሆይ ባንተ ምክንያት ካገኙኝ ኅዘናት እነዚህን አምስቱ ይበልጣሉ ብላ እመቤታችን የጠቀሰቻቸው ታላላቅ ኅዘናት እነዚህ ሲሆኑ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እነዚህን ያንችን ኅዘናት እያሰበ የጸለየ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል።
፩ኛ - ስምዖን በቤተ መቅደስ ትንቢት በተናገረጊዜ።
..
ስምዖን የተባለው፦ አረጋዊው ስምኦን ነው የእመቤታችን ሐዘን የሚጀምረው ገና አንድዬ ልጇን ከመውለዷ በስምተኛው ቀን ነው ቤተመቅደስ ይዛው በሄደች ጊዜ አረጋዊው ስምዖን “በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል (ልጅሽ በቀራንዮ ይሞታል)” ሉቃስ 2፥34-35 ብሎ በነገራት ጊዜ ድንግል ማርያም አምርራ አዘነች አለቀሰች።
እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት። ሉቃ (2፡34-35)
፪ኛ - ከቤተ መቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ።
..
ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር። የአሥራ ሁለት ዓመ ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር። ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ። ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው። ሉቃ (2፡41-48)
፫ኛ - በጲላጦስ አደባባይ በገረፉህ ጊዜ።
በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤ እየቀረቡም። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር። ጲላጦስም ደግሞ
ወደ ውጭ ወጥቶ። እነሆ፥ አንዲት በደል ስንኳ እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ አላቸው። ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ዮሐ (19፡1-5)
፬ኛ - በዕለተ ዓርብ በሰቀሉህ ጊዜ።
..
ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ። ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም። የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ።ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ
በግሪክም ተጽፎ ነበር።ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን። እርሱ። የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት። ጲላጦስም። የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ። ዮሐ. (19፡17-22)
join us @helansane
፭ኛ- ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው ወደ አዲስ መቃብር ባወረዱህ ጊዜ።
..
ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ።የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት። ዮሐ (19፡38-42)
እነዚህን አምስቱን የእመቤታችን ሐዘናት እያሰበ ያዘነ ዝክሯን የዘከረ በአማላጅነቷ የታመነ ዋጋው ከቶ አይጠፋበትም፡፡
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
።።።አሜን አሜን።።።
ይህ ኦርቶዶክሳዊ ስብከቶችንና ጥበባዊ ጽሑፎችን የሚያገኙበት ምኅላፍ (ቻናል) ነው። ይቀላቀሉ! ያተርፋሉ! #ሄላንሳን ማለት #የክብር ልብስ ማለት ነው። በቃሉ ጸንተን የክብር ልብስን ለመደረብ ያብቃን።
join us @helansane
https://telegram.me/helansane
1.3K views10:40