Get Mystery Box with random crypto!

👳𝐅𝐔𝐀𝐃 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐏𝐎𝐒𝐓

የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadislamic — 👳𝐅𝐔𝐀𝐃 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐏𝐎𝐒𝐓 𝐅
የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadislamic — 👳𝐅𝐔𝐀𝐃 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐏𝐎𝐒𝐓
የሰርጥ አድራሻ: @fuadislamic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.12K
የሰርጥ መግለጫ

በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል
በአላህ ፍቃድ በዚቻናል😘👇
🔶አስተማሪና አዝናኝ ቂሷዎች
🔶አለማቀፍ Islamic መረጃ
🔶ሰለ technology መረጃ
🔶ሀላል mem😁
🔶islamic ስነፅሁፎች
🔶አነቃቂ ምክሮች
📧የ technology መረጃዎች
🔶.......እና ሌሎችም..........🔶
..... ጥቆማ or
አስተያየት @fuaislamicpost_bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-26 20:23:06 ይህ ነው የነሱ እቅድ ከ3000 እስከ 5000 በ አንድ ወር እየተከፈለኝ መኖር

ይህ ነው የአላማየ የስኬቴ ጫፍ በቃ ?

ከዚ ጊዜ በኋላ አረጋገጥኩ ቤተሰብ ሚያይበት ምንገድ ለኔ እንደማይሆን የነሱ ውስን አላማ ከኔ ልዩ የሂወት ፍላጎት ጋር ሊገጥም አይችልም !!
ክላሶችን መግባት ከምላችሁ በላይ አስጠላኝ ደባሪ ሳምንት እያሳለፍኩ ነው እንዳሰብኩት ግሩፕ ላይ አላወራችም ግን አንድ ሀሳብ መጣልኝ የሆነ ኢስላሚክ ፅሁፍ ሼር አርጌላት መልካም ጁምአ ይሁንላቹህ ብየ ፅፌ ለሁሉም እንደ መልካም አስታዋሽ Inbox መላክ

ለሷ እንደሌሎች ላኩላት አጠር ያለች ምክር ናት ከሆነ ቻናል ያገኘኋት
ጀዛከላህ ሚል መለሰች ነበር የተርቢያ ልጅ መሆኗን ጠየቅኳት አወ ካለቺኝ በኋላ ወደሰላምታ በመግባት ለመግባባት ሞከርኩ በዚ ሳምንት ከችግሮች ባሻገር በየቀኑ ከከሪማ ጋር ውሎ እንዴት ነው ምሽቱስ የሚሉ የቴሌግራም ወሬወች ደስታ ይሰጡኛል ።
ይህን ሳምንት ቤት ስላስጠላኝ ብዙውን ጊዜ እነማሂር ቤት ያሳለፍኩት ።
የቅዳሜዋ የተርቢያ ትምርት እስክትመጣ ቸኮልኩ ከሪማንም ለማየት የአብዱም ትምርት በመጠኑ አጓጉቶኛል .

የማይደርስ የለም እና በቅዳሜ ጠዋት ከነማሜ ጋር መድረሳ ተገናኘን ሁሉንም ሰላም አልኳቸው ጁምአ ከማሜ እና አብዱ ጋር አልተገናኘንም ነበር ክላስ ገባን ትምርቱም ቀጠለ ከሪማ መምጣቷን አለመምጣቷን ለማረጋገጥ ልጠይቃት ትምርቱም መጀመሩን ለመንገር ቴሌግራም ገባሁ ተጀምሯል መጠሻል ወይስ? ብየ እንደአሰባሳቢ ኮሚቴ text ፃፍኩላት አፍወን ሰሚር ዛሬ ትልቅ ፕሮግራም አለኝ ለአብዱ ነግሬዋለሁ ብላ ወዲያውኑ መለሰች።

ዛሬ ከሪማን ባለማየቴ እየተናደድኩ አርፌ ወደ ትምርቴን ቀጠልኩ የዛሬው ክላስ ይለያል በርግጥ ምን አይነት ሃጃ ግጥሟት ነው ብየ አስባለሁ ባለፈውስ ለምንድነው ያረፈደቺው ሌላ ተርቢያ አላት ወይስ ስራ ቤት ጫና ይፈጥሩባታል ?.. ብየ አሰብኩ ተርቢያው አልቆ ወጣን ዛሬ ቤት ያለው መደብዘዝ እንዲጠፋ ብየ እነማሜ እኛ ቤት እንዲመጡ ጠራኋቸው። ስለአጎቴ ምንም አያውቁም ቤት መጠን ከዛች ጠባብ ክፍሌ ቤቱን አጨልመን ሻይ እያፈላን ፊልም አየን ስንጨርስ ወደሳሎን ኡሚ ጋር እንድንጫወት ሄድን
ስናውከው ዋልን ቤቱን ማሂር ሳቅ በሳቅ አረገን ።እናቴ በጣም ነው ምትወደው አይ ማሂር ወረኛ የሆነ ልጅ ምንም ጭንቀት ያለበት አይመስልም እኮ ። ከሱጋ ስውል እኔንም ጭንቀቴን እረሳለሁ ማለት ይቻላል ።
ቤት አምሽተን ማታ ሸኝቻቸው ተመለስኩ ወዲያውኑ ቴሌግራም ገብቼ ከሪማን ለምን እንዳልመጣች ጠየቅኳት ።

እሷ ወዲያውኑ መለሰች " የአልፋ ልዩ ገፅታ ገንቢ ላይ ነበርኩ አለችኝ"

ግራ ገባኝ ።
" የምን አልፋ ? የምን ገንቢ ? አልፋ ምንድነው ? አልኳት

እሷም ሰሚር.. ሂወት ላይ ትልቅ አላማ እና ህልም አለህ አለቺኝ?

እኔም ግራ በመጋባት በጣም ትልቅ አላማ ነው እንጂ ያለኝ ሂወት በምፈልጋት ምንገድ አልሄድም አለች እንጂ ግን ለምን ጠየቅሽኝ አልኳት ?

እሷም ጥያቄ አታብዛ ነገ እሁድ 5 ሰአት ታላቅ ፕሮግራም አለ ለጥያቄወችህ እንዳለ መልስ ታገኛለህ ያልጠበቅከውንም ልዩ ነገር ታገኛለህ ና አለቺኝ

ምንድነው ምትለው ይቺ ልጅ ??
ፕሮግራም ና !
የምን ፕሮግራም? ? ጥያቄ አታብዛ ስላለቺኝ እንደምመጣ እና የት እንደሆነ በደንብ አድራሻውን ነገሪኝ አልኳት ።

እሷም ቦሌ የሆነ ሆቴል እንደሆነ ነገረቺኝ ነገ ማርፈድ እንደሌለብኝ እና ፕሮግራሙን ለመግባት ለሆቴሉ 150 ብር ክፍያ አለው እኔ እጋብዝሃለው አታስብ ግን እንተ በፍፁም እንዳታረፍድ ብላኝ ከ Online ወጣች

ፕሮግራም ወከባ ሰው የበዛበት ቦታ ምናምን ብዙም አይመቸኝም ። ከሪማን ለማየት ብቻ ነው ምሄደው ለሊቱ አልነጋልህ አለኝ ምን አይነት ፕሮግራም ነው የጠራችኝ ለምንስ ጠየቀቺኝ? በዛ ላይ ነገ ከሪማን ላያት ነው ።

ማይነጋ ለሊት ማይጠልቅ ጀንበር የለም ለሊቱ ነጋ ቁርስ በላልቼ ምርጥ ምለውን አለባበስ ለብሼ በጠዋቱ ተነሳሁ ።
5 ሰአት አካባቢ ቦሌ ደረስኩ እሷ ግን ትንሽ አረፈደች በርግጥ የጠራቺኝን የሆቴል አዳራሽ ለማግኘት መከራየን በልቻለሁ ቢሆንም ራሴን ላለማሰደብ ቀድሜ ተገኝቻለሁ
ሆቴሉ በር ላይ ትንሽ ጥብቂያት መጣች አየኋት
ደስ አለኝ በጣም ። እሷም ጎበዝ ቀጠሮ አክባሪ ነህ ብላ ትኬት ሰጠቺኝ ወደሆቴሉ ገባን የሆቴሉ ውበት ደስ ይላል 7ኛ ፎቅ ላይ ወጣን እንደገባን የሰጠቺኝን ትኬት ሰጠኋቸው ። ፕሮግራሙን ለመግባት ስሜ ወረቀት ላይ ተፅፏል ምንድነው ኮተት ሚፈጥሩት ብየ ገባን እሷ ብዙ ሰው ታውቃለች ሰላም ትላለች እኔ በገባንበት ቀለል ያለ የሆቴል አዳራሽ ውስጥ ተመስጫለሁ ሰወች ብዙ ናቸው ፕሮግራው ተጀምሯል ቀጥታ ፊትለፊት ወሰደቺኝ ፕሮግራሙ ምንድነው? ከራሴ ጋር ለመግባባት ጦርነት ገባሁ ።

እሷ በል ሰሚሬ ተከታተል እንቆያለን እዚ ብላኝ ራቅ ብላ ከጓደኞቿ ጋር ቁጭ አለች እኔም ጉዴን ለማየት ቁጭ ብየ ተመስጬ ትኩረቴን ወደፕሮግራሙ አረኩ
------------
ያኔ ሂወቴ እንደአዲስ ተጀመረ .. የሂወቴ መስመር ከዛች ቅፅበት በኋላ ነበር ነፍስ የዘራው ሰሚር ራሱን ያወቀው ለህልሙ መኖር የጀመረው ከዛች ጊዜ በኋላ ነው ለካ ሰሚር ሂወትን አያውቃትም አይ ያ ልዩ እለት..

ፕሮግራሙ ላይ አንድ ገፅታው ሚያምር ሱፍ የለበሰ ሰው ማውራት ጀመረ ..

ክፍል 4 ይቀጥላል ..........


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
973 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , edited  17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:23:06 አልፋና ከሪማ
ክፍል ሶስት

(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ)

ንጋቱም የራቀ ፣ ያልወጣልን ጀንበር
ለሊቱም ጨለማ ፣ ቀኑም ሌት ነበር

አባየን በጣም በመደናገጥ ምን ተፈጠረ ? የምን ወንድም ብየ ለማረጋጋት እየሞከርኩ ስልኩን ተቀበልኩት "አጎቴ ነበር። ሄሎ...ሄሎ አህመድ እያለ ነበር ። እኔም ሰሚር ነኝ ምነው ? ምንድነው የተፈጠረው?! አልኩት እሱም " ሰሚሬ አሁን ያለኝ ትንሽ ደቂቃ ነው ፖሊሶች እስር ቤት እየወሰዱኝ ነው አለኝ " ለምን ለምን ? ስለው ስልኩ ተዘጋ ደግሜ ደወልኩ ነገር ግን የውጭ ስልክ ነበር አልሰራ አለኝ ። አባየ ደንዝዟል ኡሚ ልታረጋጋው ትሞክራለች እኔ ደሞ የቤቱን ሁኔታ እያየሁ ምን ሁኔታ ላይ እንዳለሁ እንኳ ማወቅ አልቻልኩም ለሊቱ እንዲሁ ስንሆን ሊነጋ ምንም አልቀረውም። አባየን ነገ ምን እንደምናረግ እናወራለን ብየ እንደምንም አረጋጋውት
ኡሚም ይዛው መኝታቤት ወሰደችው ። የሳሎን መብራት አጥፍቼ ወዲያውኑ ክፍሌ ሄድኩ ዛሬ ማታ የተፈጠረውን ነገር ጭንቀታሙ ጭንቅላቴ ሊፈታው አልቻለም አጎቴ ለምን ታሰረ? ለምንስ ደወለ? ጊዜያዊ እስራትስ ቢሆን እኛን ለምን ይነግረናል? ምን አይነት ወንጀል ላይ ተሳትፎ አርጎ ነው? ውስጤ ተረበሸ ስልኬን ሳበራው ሰአቱ 9:17 ይላል የነገ ውሎየ እንዳይበላሽ መተኛት እንዳለብኝ ተረዳሁ ወዲያውኑ እንቅልፍ ወሰደኝ

ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ሰአቱ በጣም ሂዷል ፈጅር ለምን ኡሚ አልቀሰቀሰችኝም ለመነሳት ሁሌ ባሰቃያትም እንደሌላው ጊዜ መምጣት ነበረባት ብየ ሳጣራ እነሱ ራሱ ዛሬ ነግቶባቸዋል። የዛሬውን ቀን ከአባየ ጋር መዋል እንደፈለኩ ብጠይቀውም እሱ ግን ፍቃደኛ አይደለም። ወደትምርትህ ሂድ አለኝ ጭቅጭቅ ሳላበዛ ወደ ክላስ አመራሁ የዛሬ የትምርት ውሎ ጭንቀት ብቻ በሉት ምንም ነገር ልማር አልቻልኩም ቀኑን ሙሉ ፈዝዤ ዋልኩ ከክላስ እንደወጣን ማሜ እየሮጠ ሰላም ብሎኝ ዛሬ ምን ሁነው ነው ሰሚሬ? አለኝ " አረ ምንም አልኩት
እሱም ዋናው ሰላም መሆንህ ነው ብሎኝ ሄደ ።

ማሂርንም ዛሬ አብረን ሰፈር ለመመለስ ብጠብቀውም ቆየብኝ ዝምብየ ለብቻየ ተመለስኩ በምንገዴ ማሜን ቅድም ለምን ምንም እንዳልሆንኩ ዋሸሁት ? ብነግረውስ ምን እሆናለው አልኩ። መልሼ ግን የምነግርበት ጊዜውም አልነበረም ብየ ተውኩት ።

ሰፈር ስደርስ ከመቼው እንደቀደመኝ ማሂርን ከሴት ጓደኞቹ ጋር ሲሳሳቅ አየሁት ልክ እንዳየኝ እየሮጠ መጥቶ ዛሬ ቤተል እንሂድ ኳስ በዛውም እንይ አለኝ እኔም እደውልላሀለው ብየ ቤት ገባሁ ቤት አባየም ኡሚም አሉ ዘይሪያቸው ስለአጎቴ ዛሬ ምንም አዲስ ነገር የለም? አልኳቸው እነሱም እንደኔ ግራ ገብቷቸዋል ምንም ስልክም አልተደወለም አልሰራምም ።
ለምን እንደታሰረ ለምን እንደደወለ ? ምን አይነት ወንጀል ውስጥ እንደገባ ለማወቅ ምንም አይነት መፍትሄ የለም አላህ ነገሩን ያግራው ማለት እና ሚሆነውን ማየት ነው...

አጎቴ ችግር ላይ መሆኑ
በኢኮኖሚ በኩል እኛ ላይ ሚፈጥረው ተፅእኖ እንዳለ ግልፅ ነው !. ቀን ሙሉ ስጨነቅ ውየ አሁንም ስለሱ ማሰብ አልፈለኩም። ፈታ ለማለት እና ጭንቀቴን ለመርሳት መግሪብ ከአባየ ጋር ሰግጄ ወደ ቤተል ምሽቱን ለማሳለፍ አቀናሁ ማሂር ጋር እዛው ሰፈር ተገናኝተን አንድ ላይ ወክ ማረግ ጀመርን የማሂ ቤት እኛጋ ቅርብ ነው የማሜ ደሞ ትንሽ ራቅ ይላል የኛ አንፎ ነው የማሜ አለም ባንክ ዝቅ ብሎ ትሮፒካል በመባል ሚታወቀው ሰፈር ነው ። የአብዱ ግን በደንብ ይርቃል ማሜ ትንሽ ራሱን ስላመመው አብሮን እንደማይመጣ ለማሂ ነገሮታል። ከማሂር ጋር ምሽቱን ኳስ እያየን በዛውም ነገ ሚጀምረውን የነ አብዱ መድረሳ የተርቢያ ኮርሱን እሱም እንደሚጀምረው ነገረኝ ።
አብረን አምሽተን ወደቤታችን ገባን


በነገው እለት ከክላስ መልስ ቤት ሳልገባ መድረሳ ሄድኩ ። ገና ሳልገባ የ ማሂሬ ጩሀት ከሩቅ ይሰማል ።
እንደገባሁ ማሜ እያፈጠነ መጦ እ .ምን ልትሆን ነው ቆይ? ልትማር በቁምነገር ምናምን ብሎ ከሰላምታ በፊት ሙድ ያዘብኝ .
ፈገግ ብየ በውስጤ ይህ ደነዝ የትምርት ሰው አልሆንም ማለት ነው ምንድነው ሚለው አልኩ !!

ወደ ተርቢያ መስጫው ስንገባ ሰፋ ያለ ክፍል ነው መሀል ላይ የሆነ ግርዶ ነገር አለ የሴቶች እና የወንዶች መግቢያ መግቢያ በሩ ግን አንድ ነው ።
ትንሽ ቆይተን አስተማሪያችን አብዱ ገባ የተማሪወችን እንዳለ ስም ጠየቀ ትውውቅ ካረግን በኋላ ወደኮርሱ ተሸጋገርን ስለ ወጣትነት ማውራት ጀመረ በወጣትነት ዙሪያ ያልዳሰሰው እርእስ የለም የሆነ ትልቅ ተስፋ ውስጤ ላይ እየጫረ ይመስላል በዛ ላይ ሲናገር ይመስጣል በደንብ ሚናገረውን ስከታተል ነበር። መሀል ላይ ግን በሩ ተንኳኳ ሁለት ሴቶች አሰላሙአለይኩም ብለው ገቡ .. አንዷ ከሪማ ናት ። ድንግጥ አልኩ በእውነቱ ገርሞኛል እንዴት እንደሆነ ሳላውቅ እኛ ጀምአ ውስጥ ናት። ደስ አለኝ እሷ ከመጣች በኋላ አብዱ ትኩረቱን ወደሴቶች አብዝቶ አደረገ በዚህም ከሪማ ጎበዝ ተማሪ መሆኗን እና ልዩ ትኩረት እንደምስብ ተረዳሁ ለነገሩ የመድረሳው ሃላፊ ልጅ ናት ብዙም ሚገርም ነገር አይደለም ትምርታችንን እየተማርን እያለ የሆነ ሰው ክላስ ውስጥ ገብቶ ትልቅ መዝገብ ነገር አምጥቶ በየተራ ስማችንን ከስልክ ቁጥራችን አስመዘገበን እና ክላስ ማንመጣበት ቀናቶች ላይ ቴሌግራም እንደምንማማር Add ለማድረግ እንደሆነ አብዱ ማስተማሩን አቁሞ ነገረን የዛሬውን ተርቢያ በዚ መልኩ ጨረስን ዛሬ ፈታ እያልን ከመድረሳ ልጆች ጋር እናሳልፍ ብለን ምሳ ምርጥ ቤት በልተን እዛው ቁጭ ብለን ስንጫወት ዋልን ልጆቹ ደስ ሚል ባህሪ አላቸው ሰአቱ ወደከሰአት ሲል ወክ እያረግን ስንዛዛግ አመሸን ደስ ብሎኝ ቤት ገባሁ ቴሌግራም ላይ ስገባ የጀምአችንን ግሩፕ አየሁት ወደግሩፑ አባሎች እየሄድኩ ከሪማ ሚል አካውንት ፈለኩ .. ብዙም አልደከምኩም አገኘኋት እሷ መሆኗን በስሟ ሳረጋግጥ ወደፕሮፋይሏ በፍጥነት ሄድኩ ። ማይስቡ ፕሮፋይሎች ናቸው ዱአወች አረብኛ ጥቅሶች ምናምን ነገር ናቸው አንድ ብቻ የአባቷን ፎቶ አየሁ እና የሆነ የእርዳታ ድርጅት 10 ቀን ቀረው 5 ቀን ቀረው ይላል ።

Inbox ወሬ ለመጀመር ከበደኝ ሴት ልጅ በቴሌግራም ቀድሜ አውርቼ አላውቅም ምናልባት ካወሩኝ በመከራ ከመለስኩ ነው ። ከሴቶች ጋር ብዙም የማውራት ፍላጎቱም ልምዱም የለኝም ግን ግሩፕ ላይ ማውራት ከጀመረች ባወራችው እርእስ በመጠየቅ አስቀይሼ Chat መጀመር እንደምችል ተረዳሁ

ግን ግሩፕ ላይም ልታወራ አልቻለችም ።

ሰሞኑን ቤት ያለው ሁኔታ ደስ አይልም አጎቴ እንደታሰረ ከሰማን ወዲ የቤታችን ለዛ ጠፍቷል እኛ ቤት ላይ ከኢኮኖሚ አንፃር የፈጠረው ተፅእኖ መኖሩ እንዳያስጨንቀኝ ብሞክርም አልቻልኩም

የመጀመሪያም ብቸኛም ልጅ ነኝ የቤተሰቤን ሂወት መቀየር አለብኝ አባቴ እንደቀድሞው መስራት አይችልም ። የራሴ ሂወት አለኝ ገንዘብ ግዴታ ሁኖ ታየኝ ከበረንዳችን ወጥቼ ከኡሚ ጋር ስለሰሞኑ ሁኔታ አወራን እና መስራት እንዳለብኝ ራሷ ወሬ ጀመረች ደስ አለኝ ። በምን መልኩ መስራት እችላለሁ ብየ ጠየቅኳት እሷም ትምርትህን ተማር በተማርከው አሪፍ ስራ ታገኛለህ አለችኝ እንደመሳቅ ሁኜ በአካውንቲንግ ነው አሪፍ ስራ ማገኘው አልኳት ብዙም አልተረዳችኝም ዝምብላኝ ሄደች ተናደድኩ ..!!!!
872 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 08:43:28
አላህ ካለ ቀጣይ አመት እዚህ ለይ እንድንገናኝ

በ TV /Social media ለይ ብቻ ተመልካች ሁነንማ አንቀርም #Insha'allah

عيد مبارك በድጋሚ


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
266 viewsFNB, edited  05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:32:18 የኢድ ቀን አዲስ ልብስ ሲገዛላቹ እና ሳይገዛላቹ ያለዉን ስሜት አጋሩን ልጅ እያላቹ እንዴት ነበር ኢዱን ምታሳልፉት comment አርጉ
@fuaislamicpost_bot
467 viewsFNB, edited  11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:29:54 ዛሬ ኢድም አይደል እስቲ ዘና እንበል

በ በአል ቀን ያጋጠማችሁን ፈገግ የሚያስብሉ ወይም አስደናቂ የምትሉትን የገጠማችሁን ወይም የሰማችሁትን አጋሩን
በዚህ አድርሱን
@fuaislamicpost_bot
@fuaislamicpost_bot
415 viewsFNB, 11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:54:30 عيد أضحى مبارك :
#ኢደል_አድሀ_ሙባረክ

ለ1443ኛ ጊዜ ለሚከበረው የፅናትና የመታዘዝ ተምሳሌት ለሆነው ለኢድ አል_አድሀ አረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰሽ የኔ ዉድ ጓደኛ ዩስሪና?!


የኔ ዉድ ዩስሪታ ለአላህ ብዬ ዉድድ አረግሻለዉ መልካም በአል EID MUBAREK አንቺን ለኔ አላህ ስለሰጠኝ አልሃምዱሊላህ ነፍ አመት ኑሪልኝ የኔ ዉድ ጓደኛዬ ዩስሪዬ
በአሉ የሰላም፣የፍቅር፣የደስታ፣የተቸገሩትን ምንረዳበት ያርግልን

አላህ ከጀነት ጥላ ስር ከሚሆኑት ጓደኞች ያርገን

የኔ ዉድ #ዩስሪታ ዉዴታዬ ከልብ ነዉ


አላህ ይቀበለን!!
ለመጭውም አላህ በሰላም ያድርሰን!

ዒዱኩም ሰዒድ!

ኢድ ሙባረክ
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

ለበይክ ነኝ ከ (ሎሚ ሜዳ) ለአላህ ብዬ ዉድድ አርግሻለሁ ጓደኛዬ ዩስሪ
F
ባማረ አቀራረብ እናደርስሎታለን
መልዕክት


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
367 viewsFNB, edited  10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:38:37 عيد أضحى مبارك :
#ኢደል_አድሀ_ሙባረክ

ለ1443ኛ ጊዜ ለሚከበረው የፅናትና የመታዘዝ ተምሳሌት ለሆነው ለኢድ አል_አድሀ አረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳቹ የኔ ዉድ ጓደኞች !


ጓዶቼ ለአላህ ብዬ ዉድድ አረጋቹዋለዉ መልካም በአል EID MUBAREK አናንተን ለኔ አላህ ስለሰጠኝ አልሃምዱሊላህ ነፍ አመት ኑሩልኝ የኔ ዉድ ጓደኞች
በአሉ የሰላም፣የፍቅር፣የደስታ፣የተቸገሩትን ምንረዳበት ያርግልን

አላህ ከጀነት ጥላ ስር ከሚሰበስባቸዉ ያርገን

የኔ ዉድ #ጓደኞች ዉዴታዬ ከልብ ነዉ


አላህ ይቀበለን!!
ለመጭውም አላህ በሰላም ያድርሰን!

ዒዱኩም ሰዒድ!

ኢድ ሙባረክ
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

ቢላል ነኝ ለአላህ ብዬ ዉድድ አረጋቹዋለሁ ዉዶቼ
F
ባማረ አቀራረብ እናደርስሎታለን
መልዕክት


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
460 viewsFNB, edited  10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 11:59:38 ከዚያ ከተራራ ከሩቅ ሀገር ግዛት
ከደጋጎች ሰፈር ከታሪክ ንቅሳት
የኋሊት ከዘመን ብጓዝ በምናቤ
ድንቅነትን በቁም ቃኘሁ ተገንዝቤ

እምነት ልብ ጠልቆ አብራክ ሲያስቤዛ
አምላክ በፈተና በጥበብ ሲገዛ
አይቷል ተመልክቷል ያ የአባቱ ሀገር
ካራ አንገቱ ደርሶ መላይካ ሲያናግር

አባቴ ትንሹ ሙላ ትዛዝ ህጉን
ወትሮስ መች ይጥላል ያሳጣል ማዕረጉን
ትዕዛዝህን ሙላ ትዕዛዝህን ፈፅም
ሁን ያለው ከመሆን ተዛንፎም አያውቅም

እንስፍስፍ ብርክርክ ጉልበት አቅም ባዶ
ባመሻሽ ቡራኬ ነፍስያው ታውዶ
ወንድነት ከንቱ ነው ከመስዋት በኩል
አብራኩን ላያኖር ከፈጣሪው እኩል

ታዘዘ ...
ፈፀመ ...
ከተራራ መሀል አለት ባ'ለት ከተኩራራ
ኢብራሂም ልጁ ላይ አሳረፈ ካራ

ለዝንቱ ስለቱ የማያጠራጥር
ዝም ...
እንቢ አላርድም
አለው ብዙ ሚስጥር

ከልቡ ላይ መንቀል ሆነና ታልሞ
ጅብሪል ከተፍ አለ .. አኺ ኢብራሂሙ
ያዝ ፊዳ ከጀና ምትክ ሰዋ ብሎ
አረጋው አምላኩ በታምር አባብሎ

አይታለች ሀገሩ የዛን ዘመን ፍጥረት
እንደው ከድሜ መዝገብ መንደሩ ብከሰት

መንገዱ ያባት ነው ትውልድ የዘለቀ
በኢብራሂም ፈለግ በሱና የደመቀ

ከቀንም በመልካም ኢድ ሆነ የደስታ
ለዝንት የማይከስም የላቀ ትዝታ


አይዳ አወል

@fuadislamic

# ዒድ_ሙባረክ
374 viewsFÑ, 08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 01:41:51 عيد أضحى مبارك :
#ኢደል_አድሀ_ሙባረክ

ለ1443ኛ ጊዜ ለሚከበረው የፅናትና የመታዘዝ ተምሳሌት ለሆነው ለኢድ አል_አድሀ አረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰሽ የኔ ዉድ ጓደኛ ሙኒራ !


የኔ ዉድ ሙኒራዬ ለአላህ ብዬ ዉድድ አረግሻለዉ መልካም በአል EID MUBAREK አንቺን ለኔ አላህ ስለሰጠኝ አልሃምዱሊላህ ነፍ አመት ኑሪልኝ የኔ ዉድ ጓደኛ?
በአሉ የሰላም፣የፍቅር፣የደስታ፣የተቸገሩትን ምንረዳበት ያርግልን

አላህ ከጀነት ጥላ ስር ከሚሆኑት ጓደኞች ያርገን

የኔ ዉድ #ሙኒራዬ ዉዴታዬ ከልብ ነዉ


አላህ ይቀበለን!!
ለመጭውም አላህ በሰላም ያድርሰን!

ዒዱኩም ሰዒድ!

ኢድ ሙባረክ
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

ፈትህያ ነኝ ለአላህ ብዬ ዉድድ አርግሻለሁ ጓደኛዬ ሙኒራ

F
ባማረ አቀራረብ እናደርስሎታለን
መልዕክት


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
428 viewsFNB, edited  22:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 01:37:39 عيد أضحى مبارك :
#ኢደል_አድሀ_ሙባረክ

ለ1443ኛ ጊዜ ለሚከበረው የፅናትና የመታዘዝ ተምሳሌት ለሆነው ለኢድ አል_አድሀ አረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰሽ የኔ ዉድ እህት ሃናኔ !


የኔ እህት ሃኒ ለአላህ ብዬ ዉድድ አረግሻለዉ መልካም በአል EID MUBAREK አንቺን ለኔ አላህ ስለሰጠኝ አልሃምዱሊላህ ነፍ አመት ኑሪልኝ የኔ ዉድ እህት ሀኒታ
በአሉ የሰላም፣የፍቅር፣የደስታ፣የተቸገሩትን ምንረዳበት ያርግልን

አላህ ከጀነት ጥላ ስር ያርገን

የኔ ዉድ #ሃኒታ ዉዴታዬ ከልብ ነዉ


አላህ ይቀበለን!!
ለመጭውም አላህ በሰላም ያድርሰን!

ዒዱኩም ሰዒድ!

ኢድ ሙባረክ
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

ሰብሃ ነኝ ለአላህ ብዬ ዉድድ አርግሻለሁ እህቴ ሀኒዬዬ
F
ባማረ አቀራረብ እናደርስሎታለን
መልዕክት


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
352 viewsFNB, 22:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ