2022-09-22 08:34:34
ሰላቱል-ፈጅር ደስታና አጅር ሰላት የኢማንና ክህደት መለያ ታላቅ ዒባዳህ ነው፤ሰላት የማይሰግድ ሰው ኢስላም ላይ ቦታና ድርሻ የለውም።
ሁሉም ሰላቶች በአግባቡ ከተሰገዱ ወደ አላህ የሚያቃርቡና ብዙ ዱንያዊም ኣኼራዊም ጥቅሞችን የሚያስገኙ ከመሆናቸውም ጋር ፈጅር ሰላት ግን ደረጃና ጥቅሙ ይበልጥ ላቅ ያለ ነው።
ፈጅር ሰላትን በሰዓትና በስርዓቱ መስገድ ከሙናፊቅነት ያርቃል፣ በአላህ ጥበቃ ስር ያደርጋል።
ፈጅርን በጀማዓህ መስገድ ሌሊቱን በሙሉ የለይል ሰላት ሲሰግድ ያደረን ሰው ምንዳ ያስገኛል።
ፈጅርን በስርዓቱ የሚሰግድ ሰው ቀኑን ሙሉ ልቡ ተረጋግቶ፣ በአላህ ተጠብቆ፣ ድብርትና ሸይጣን ከሱ ርቆ፣ ሌሎች ሰላቶችንም በአግባቡ ለመስገድ ታድሎ ይውላል።
በተቃራኒው ደግሞ ፈጅር ሰላትን በአግባቡ የማይሰግድ ሰው ቀኑን ሙሉ ተጫጭኖትና ደብሮት፣ ደስታ ርቆት፣ ሌሎች ሰላቶች ላይም እየተዘናጋ ይውላል።
ገና ከመንጋቱ ፈጅር ሰላት ላይ ቁርኣን መቅራትና መስማት የሙእሚን የቀን ሙሉ የልብ ቀለብ፣ የትም የማይገኝ ደስታ፣ ልዩ የንቃትና የጉልበት ምንጭ ነው።
ፈጅር ሰላትን በአግባቡ በመስገድ እነዚህንና መሰል ጥቅሞችን ማግነት እየተቻለ ፍራሽና እንቅልፍን አስበልጦ በስርዓቱ መስገድንና ጀማዓን መተው ትልቅ ኪሳራና ሞኝነት ነው።
አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸውና የዒባዳህ ጣዕምን ከታደሉ ባርያዎቹ ያድርገን። -ኣሚን!! ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
ረቡዕ 25/2/1444 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ
~~~~
በተጨማሪም የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኜት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
https://t.me/+TXxgo3xLnJgC5IuW
አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
32 viewsرسلان بن أحمد, 05:34