Get Mystery Box with random crypto!

👳𝐅𝐔𝐀𝐃 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐏𝐎𝐒𝐓

የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadislamic — 👳𝐅𝐔𝐀𝐃 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐏𝐎𝐒𝐓 𝐅
የቴሌግራም ቻናል አርማ fuadislamic — 👳𝐅𝐔𝐀𝐃 𝐈𝐒𝐋𝐀𝐌𝐈𝐂 𝐏𝐎𝐒𝐓
የሰርጥ አድራሻ: @fuadislamic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.12K
የሰርጥ መግለጫ

በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል
በአላህ ፍቃድ በዚቻናል😘👇
🔶አስተማሪና አዝናኝ ቂሷዎች
🔶አለማቀፍ Islamic መረጃ
🔶ሰለ technology መረጃ
🔶ሀላል mem😁
🔶islamic ስነፅሁፎች
🔶አነቃቂ ምክሮች
📧የ technology መረጃዎች
🔶.......እና ሌሎችም..........🔶
..... ጥቆማ or
አስተያየት @fuaislamicpost_bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-30 20:47:15 አልፋና ከሪማ

ክፍል ሰባት
(የምዕራፍ 1 የመጨረሻ ክፍል)
(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ )

አልፋም ቤቴ ሆነ ፡ ከሪማም ባለዳ፣
ነፍሴም ተሸነፈች ፡ በእንስቷ ጓዳ።

የእሁዱ ቀን ደረሰ...በሚያምር አለባበስ ፊትለፊት በኩራት ተቀምጫለሁ። ፕሮግራሙ ጀመረ። ብዙ ሰዎች መናገር ጀምሩ...እዚ ድርጅት ላይ በገንዘብ እና በአስተሳሰብ የምትለወጠው ስልጠናውን ወደሂወትህ አምጥተህ ስተገብር ነው። አእምሮህ ሲከፈት፣ ብዙ የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ከውስጥህ ስታስወግድ፣ የቀድሞ ልምድህን እርግፍ አርገህ ስትተው፣ ከፈጣሪህም ከሰዎችም ቅርብ ትሆናለህ።
" ዛሬ ላይ በዚ 21 ቀን ውስጥ በደንብ የመጀመሪያውን ፓኬጅ ሰልጥነው የተመረቁ ልጆች እንመርቃለን። " አለ ሌሎችም ብዙ ሰዎችም ንግግር አደረጉ። ከዛም ወደመድረኩ ሁላችንንም ጠራን...

የዛሬዋ ቀን ትለያለች 12 አመት ምናምን ተምረን ምንመረቀው ምርቃት እኮ ሂወቴን ቀጣይ ምን ላርገው የሚል ጭንቀት ነው ምናተርፈው። በሂወትህ በለውጥህ ስትመረቅ ደስ አይልም ?

በዛ ላይ የሰራነው ዶላር ተነገረ በዚ ወር የበለጡኝ አሉ ግን እኔ ዶላሩ ብዙም አያሳስበኝም። " ወደቀጣዩ ፓኬጅ ስዘዋወር ነው ንግግር ማረገው " ብዬ እዛው ቦታዬ ተመለስኩ። ዛሬ ፉአድም ከድሬ መጥቷል። በጣም ደስተኛ ነበርን! በዚሁ የደስታ ሞራሌ ከሪማን እንደምወዳት ብነግራት ደስ ባለኝ ፣ ግን ፈራሁ። ከፕሮግራሙ መጠናቀቅ በኋላ ምሽቱን ስንጫወት እንደሙሽራ ሲያረጉኝ አመሸን። በጣም ደስ አለኝ ሂወቴ በአንድ ወር መቀየሩ ሀሴት ውስጥ ከተተኝ።

በርግጥ እንዲቀየር የአብዱ ስልጠናም ጠቅሞኛል እንጂ ከመጀመሪያው ፓኬጅ ይልቅ 2 ሶስተኛው ትልቅ ተፅዕኖ አለው። ሁለተኛው ሶስተኛው ከገዛኸው መጀመሪያ ከምታገኘው በላይ በዛ ያለ ተቆራጫም አለው።

ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ነገር አብዱም ከሪማም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ማሂር እና አብዱ ለምን ስለተለያየ የዲን አመለካከት ይጣላሉ?? ለምን ሀሳባቸውን አይከባበሩም። ለምን ማሜ ዛሬ ድረስ እዛች ሱቅ ይፈጋል? ፉአድንስ 1 አመት ግቢ ከተማረ ይበቃዋል ሂወቱን እዚ ለምን አይቀጥልም?

ብዙ ብዙ ውስጤ የነበሩ ሀሳቦችን በግልፅ አወራንባቸው። ያለንን የባህሪ ክፍተት ደፍነን ወደፊት እንደትልቅ Group ብዙ ነገር ከድርጅቱ ጋርም ተያይዞ ከዛ ውጭ መስራት እንደምንችል ተማመንን።

ለአላማችን መኖር እንዳለብን እና ከዚ በኋላ የደስታ ሂወት ለመኖር አሰብን። ዛሬ ከመሸ እኔና ማሂር አብዱ ቤት ልንሄድ ፈልገናል እሱ ግን መሽቷል ምን ትሰራላቹ ብሎ ላለመውሰድ ሞከረ። እኛ ግን አንሰማም አልነው። እሱም " ዛሬ ቤት አላድርም ማዘርን ደውዬላታለሁ አምሽተን ስንገባ ደስ አይልም ዛሬ አንሄድም " ሲለን አርፈን ተቀመጥን። ማታውን በአሪፍ ሁኔታ አሳለፍነው ድንገት ከመሃላችን ማሜ አንድ ቤት ተከራይተን መኖር እንዳለብን ሀሳብ አመጣ በጣም ገራሚ ሀሳብ ነው። አብዱ ደስተኛ አለመሆኑን ስናይ ተውነው።

አብዱና ማሜ ወደነማሂር ቤት ሊያድሩ ሄዱ። እኔ ወደቤት ተቀነጠስኩ ።

ቤት በጣም መሽቶ ነበር ስገባ አባዬን ዘየርኩት ሊቆጣ ሲል.ም ዛሬ የጀመርኩትን የስኬት ጅማሮ በፎቶ አሳየሁት በቀጣዩ ስመረቅ እጋብዛቹሃለው አልኩት። ሁሉም ተደሰቱ። የነሱን ደስታ ሳይ ከልቤ ተደሰትኩ። አሁን በአጎቴ ምክንያት ከተፈጠረው ችግር አንፃር የአሁኑ የነሱ ደስታ ትልቅ ቦታ አለው ለኔ።

ሰአቱ በጣም ሄደ 6:35 ይላል። እነኡሚን አስተኛኋቸው እና ዛሬ ይህን ትልቅ ውለታ ለዋለልኝ ጌታ ለይል ሰግጄ አመስግኜ መተኛት እንዳለብኝ ተረዳሁ። ለይል ሰግጄ ውብ እጆቼን ወደሰማይ ዘረጋሁ ።

ከልቤ አመሰገንኩት የእናቴን ደስታ አሳየኝ ብዬ እየተንሰቀሰቅኩ ለመንኩት የሂወቴን መጨረሻ አሳምረው! የአብዱንም የማሂርንም የሌሎችን ሂወት አሳምረው! በወንድማማቾች መሀል ማንም እንዲገባ አትፍቀድ። ከነሱ ውጭ ማንም የለኝም!

ጀሊሉ በጨለማ ውስጥ ብርሃንን ታሳያለህ! በሞተ ልቦና ነፍስ ትዘራለህ። የታል ሚለምነኝ ምሰማው ባልከው የከበሩ ቃላት ይዤሃለው የከሪማን ነገር አደራ ብዬ አነባሁ!

በወንጀል የቆሸሸ ባሪያህ ከፊትህ ተደፍቶ ያነባል .. ያልተፈቀዱለትን ልቅ ነገሮችን ያየበትን አይን አብስለት! በዘረጋው እጁ አንተን ያመፀበት እጁቹን ማሀርታ ለግሳቸው። ያልሰገዳቸው ሰላቶች፣ ትእዛዝህን የደፈሩ ውሳኔወች.. .ነገ የፍርዱ ቀን አንገት ያስደፋዋልና ዛሬ ማንም ሳያውቅ ከመዝገቦቹ ሰርዘው። ወንጀሉን ምረህ ፍላጎቱን አሳካለት። በልኩ የተሰፋችውን ሀዋ ለግሰው ከከሪማ ጋር በዱንያ የጀነትን ሂወት አሳየው ።
ያረሂም እዘንልኝ! ያ ከሪም አክብረኝ! ያ ወዱድ ውደደኝ! ሰዎች ዘንድም አስወድደኝ ያገፋር ወንጀሌ በኔና ባንተ መካከል ይቅር። የቀድሞዬን ሂወት ለመተው አንተው እርዳኝ! ቃልህን እንድሸመድድ አገዘኝ! በስንዝር ስቀርብህ በክንድ ተጠጋኝ! የደካሞች ደካማ ነኝ እና አንተው አበርታኝ። ብዬ ዱአዬን ጨረስኩ።

አገጬ ላይ ከተርገፈገፈው እንባ ባሻገር ሀሴት ተሰምቶኝ የመኝታ ዚክር ብዬ ተኛሁ።

በነገው ቀን ሲረፋፍድ ከማሂር ጋር እነ አብዱ ቤት ሄድን። የአብዱን እናት ዘየርናት እና ያሰብነውን ዋና ነገር ባማረ መልኩ አደረግነው...
የአብዱን ትንሽ እህት ኢልሃንን ብዙ ልብሶች ገዝተን ሰርፕራይዝ አደረግናት። በጣም ተደሰተች እየሮጠች ስትጠመጠምብኝ እንባ ነበር የቀረኝ በጣም ተደሰትኩ የህፃንን ደስታ ማየት እንዴት ያስደስታል።

የአብዱ እናት እያለቀሰች አቀፈቺን ዱአም አደረገቺልን።

እነማሜ እና ፉአድ ሲመጡ ዛሬ ኢልሃንን ቦሌ ስናዝናናት እንዋል ተባብለን ወደቦሌ አመራን። ልክ እንደገባን የፈለገችውን የጨዋታ አይነት እንድትጫወት ቆርጠንላት ጩሀት እና ጫጫታ ውስጥ ገባን።
ማሂርም ከኢልሃን ጋር መኪና ውድድሩን ተያይዘውታል። አብዱና ማሜ የእጅ ኳስ እየተጫወቱ ነው ማሂር ወደኛ መጣና እየጮኸ " ማታ ትልቅ የሚነገርህ ነገር አለ። ደስ ሚል የምናወራበት ልዩ ጉዳይ አለ " አለኝ እኔም ደስ አለኝ።
በዛውም የከሪማን ጉዳይ ዛሬ ማታ ልነግራቸው ስለሆነ ማለት ነው።
ቀን ሙሉ ስንዝናና ውለን ማታውን እነአብዱ ቤት ኢልሃን ስለተኛች አብዱ ተሸክሞ አስገባት።
እዛው እነአብዱ ሰፈር ወዳለ ካፌ እንደምናመሽ ተነጋገርን ወጣን። የዛሬው ቀንማ ሰኞ አይመስልም መግሪብ ሰግደን እራት እየበላን እዛው ሆንን።

ማሂር እየፈጠነ " ዛሬ ሚነገር ትልቅ ነገር አለ " አለን (እኔም በውስጤ የሰራውን ዶላር ሰርፕራይዝ ሊያረገን ነው ብዬ አሰብኩ)
ግን ወዲያውን ከተፍ ብዬ " እኔም የምነግራቹህ ነገር አለ " አልኩ። ፉአድ " ከማሂር እንጀምር ወይስ ከሰሚር? "ሲል ጠየቀ?

ማሜ " ከማሂር ይጀመር... የሰሚር ትልቅ ነገር ይመስላል መጨረሻ ላይ ብንሰማው ይሻላል " አለ። አብዱ ቁጭ ብሎ ለብቻው እየተሽኮረመመ ይስቃል ... ማሂርም በቃ ላውራ ብሎ ጀመረ ..

የሆነ ሰው እያለ ወደአብዱ እየሳቀ እያመለካተ (እኛም አብዱ ምን ? ብለን ሰፍ አልን ) ማሂርም " አብዱሻ ኡስታዛችን ፎንቃ ገብቶለታል! ፍቅር ነገር እያጫወተው ነው " አለ ማሜ " ተመስጦ ምን? ማንን ማንን? " አለ። እኔም ማንን ነው ስል ?

ማሂር " ያቺ ቆንጆዋ የመድረሳቸው ሀላፊ ልጅ... አደበኛዋ... ሁሌ ጥቁር ሂጃብ የምትለብሰው ልጅ... እንዳለ .. ማሜ " ከሪማን!? " አለ
610 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:04:59 ያ ጀሊሉ ያረበና
እዝነትህን ለግስና
ያ ማሊኩ ያረበና
በፍቅር ወደደና
አላህ አላህ ያዳኢሙ
ጨምርልን ከማድ ኢልሙ
ያ ኸፋሩ ያኻሊቁ
በዲናችን አርገን ንቁ
ያ ረህማኑ ያ ወዱዱ
አስጨልፈን ከመደዱ
ያ አዚዙ ያከሪሙ
ማረን አልነህ ያ ረሂሙ
።።።።።።።።።።።
ስንቱ አማረ ቢባል ቢስሚላህ
አሸበረቀዉ ከዉናትን ሁላ
በስሙ እኮ ነዉ ያለዉ በረካ
ላመሰገነዉ ይለዋል እንካ

እጁን ዘርግቶ ከአላህ ደጅ
ሚመለስ የለም በባዶ እጅ
አጂብ እዝነቱ የአላህ ሙሚቱ
ስንቱ አምፆት ቢቀርብ ተፊቱ
ይለግሰዋል ከሰፊ እዝነቱ
እያበሸረዉ በሽልማቱ

ቂም በቀል አያዉቅ የአለሙ ጌታ
ፍቅርን ይሰጣል የመጡ ለታ
ዛቱም ሲፋዉ የለዉ አምሳያ
መዉጁድ እኮነዉ ያለ ከይፍያ

አልሃምዱሊላህ ያረከኝ ካንተ
ከፅልመቱ ደጅ ስበህ ወዳንተ
አበራህልኝ አለሜን አንተ
ወድቄ ነበር ባትሰበኝ አንተ

በሲር እኮ ነዉ የኛማ ጌታ
አይከልለዉም ጣራ ኮረብታ
ወድቄ ነበር እኔስ በከንቱ
ባይኖርልኝ የአላህ እዝነቱ

አንደ ስራችን ከሆነ የኛ
ይደፋ ነበር ምድሩ በኛ
መቼም ትግስቱ ይልቃልና
ይምረናል ረሂም ነዉና

ምድር አታሰምጥ ሰማይ አይወድቅ
ኻፊዝ እኮ አላህ ኻሊቅ
አጋዥ የለዉም ኻሊቁ የኛ
አሀድ እኮ ነዉ ኗሪ ብቸኛ

አለን አድኡኒ በቸርነቱ
ቅሮት የለዉም ለሰጪነቱ
የሚጓዘዉን በአላህ ተስፋ
ኻሊቁ አይፈቅድም አንገት ሊደፋ

ወንድሜ አብሽ ከአላህ ተጠጋ
የጨለመብህ ቀኑ እንዲነጋ
አብሽር እህቴ አላህ አላህ በዪ
ፅልመቱ ጠልቆ ብርሀን እንድታዪ

ሌላዉን ትቼ ብዞር ወዳንተ
አለሜ ፈካ ጌታዬ ባንተ
ከእዝነቱ ደጃፍ እርቄ ስማትር
ደርሶ መለሰኝ የእዝነቱ ብትር
{ Fuad}


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
810 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:15:17 ከዚ ቀደም የነበረውን ማንነቴን አሳታወስኩ። ሰላት አልሰግም ነበር። ለማየውም ለምሰማውም ነገር አልጨነቀም። አላማዬ ገንዘብ እንጂ ሌላ አልነበረም። ጀናባ ሁኜ እንኳን ከአባዬ ጋር መስጊድ እሄድ እና ከሰዎች ጋር ተቀላቅዬ እሰግድ ነበር!! ሰው ለመናቅ ለከት አልነበረብኝም። ምኞቴ ውስጥ መጥፎ ነገር እንጂ ሌላ አልነበረም የጀሊልን ወሰን ሳምፅ ያሳለፍኩት ጊዜ አሳመመኝ።
-----------

ታሪክ ነበረኝ ፡ ውስጡ የገነነ፣
ባሪያውን ያጠፋ ፡ ስሜትን ያመነ።
እጁ ተጨማልቆ፡ ድጋሚ ላይፀዳ፣
ታሪክ ነበረኝ ፡ እኔስ  ተስፋን 'ሚከዳ።
ማንነትን ያልተረዳ ፡ ግዝፈትን ያቀለለ፣
ጊዜያዊን ደስታ ሰጥቶ ፡ ስብእናን ያጎደለ።
መንገዱ ሲከፈት ፡ ብሩህ የመሰለኝ፣
ዘልአለም መዋዠቅ፡ ልቤ ያታለለኝ፣
ምነው ጊዜው ከረፈደ፡ አሁን  ታወቀኝ?

መመለሻ የሌለው መንገደኛ የዋለለ
መድረሻውን ሳያውቅ ከልካዩ የሌለ
ለጥፋት መሪ እንጂ ከጥፋቱ ዝቅታ
አስተካካይ የለው ከዝቅጠቱ ኮረብታ
ወንጀል ነው ተቃራኒው ፅንፍ  ያልተሰማ
ውርደት ነው አልታየም የልእልናው ሸማ።
--------

ከሪማ ምን ያህል ሂወቴን ትቀይረዋለች?
ብጠይቃት እሺ እባላለሁ ወይስ?
አሁን ላይ ለምን ለሷ ተገቢ አልሆንም?

"ቁርአን ሂፍዝ ጀምሬያለሁ ፤ የሰላት ጊዜዬን መስጊድ ነው ማሳልፈው (በርግጥ እሷ በእውቀት ትበልጠኛለች።)
ከገፅታም ሚያምር መልክ እና ቁመና ተሰጥቶኛል.. .የፈለገ ሂወቴ ቢበላሽ ከሌላ ሴት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም።

አላማዬን አውቂያለሁ በምን ምክንያት ላትቀበለኝ ትችላለች? አላውቅም ብቻ ያቺ ጥቁር ሂጃብ ምትለብሰዋ ቀዯ ባለ ሃያእ እንስት ሌላ ነገር ለማሰብ ጊዜም አልሰጠቺኝም።

-----------
እውቀት ለመቅሰም ድርሴን ብወድም
ልሰማ ማልጄ  መድረሳ ብሄድም፣
ጌታዬን ላወድስ እልፍ ብፈልግም፣
...........እኔ ግን አልችልም

ካንቺ ሌላ እንዳስብ ሺ ምክንያት ባገኝም፣
አንቺን አለማሰብ ሀሳብ አይመስለኝም፣

አይ እኔ ምስኪኑ፣
ካንቺ ጋር ሆነና ልቤ ቃልኪዳኑ፣
በስምሽ ተሳስሮ ድምፄ እና ልሳኑ፣
ከሀለቃው ቁጭ ብሏል ስጋዬ በድኑ፣
፡
አስተማሪው እየለፈለፈ ባየውም፣
አይኔን ለአፍታ እንኳ ዳሩ ባልከድነውም፣
እውነት አልሻለሁ ምንም አላየሁም፣
--------

..ያንንም ይሄንንም እያልኩ ሂወቴ ቀጥሏል.. ማሂር ከስልጠናው ይልቅ የአልፋን ኩባንያ ለሰዎች ሼር ማድረግ ተያይዞታል። ማሜን ወደድርጅቱ አስገባው። የክላስ ልጆቹን በሙሉ አስገባቸው በዛ ሁሉ ሰው ምን ያህል ዶላር እየቆጠረለት እንደሆነ አሰብኩት። እነሱ ያስገቡትም ሰው ጥቅሙ ወደላይ ይወጣል ደሞ ታሳቢ ሚደረገው ገንዘብ ብዙ ነው። በ6 ሰው ብቻ ሀብታም ይሆኑ የለ?

እሱማ የወሩ ከግሩፓችን ሳይሆን ከሙሉ ድርጅቱ ልዩ ተሸላሚ እንደሚሆን እጠብቃለሁ። ዛሬ እኛ ቤት መጦ ስልጠናውን በ online ፉአድን አስገብቶት የድሬ ልጆች እንደገቡ ነገረኝ እና ፉአድም ማሂርም ምን ያህል እንደሚሰሩ አሰብኩት በአንዱ የድርጅቱ ሲስተም ብቻ።

የእሁዱ የአልፋ ቀን አጓጉቶኛል የምመረቅበት ቀን ነው በ21 ቀን ስልጠና በ online መሰልጠን ስላቆምኩ አካውንቴ የቆጠረውን ብር አላየሁትም ማየት እፈልጋለሁ ግን እሁድ ላውቀው ብፈልግም አላስቻለኝም አየሁት...
887 ዶላር ሰርቷል !!! በሀገራችን እስከ 40 ሺ ምናምን ማለት ነው።
በማሂር በኩል የዘረጋሁት መስመር ምን ያህል እንደጠቀመኝ አወቅኩት። ግን ማሂር ስንት ሰርቶ ይሆን ? የሱን ብር እሁድ እነግርሃለው ብሎኛል። ጓጓሁ እስኪመረቅስ ስንት ይሰራ ይሁን??

አላውቅም እኔኮ ማሂርን ስልጠናው ላይ አተኩር። ስልጠናው ሂወትህን ሲቀይረው አእምሮህን መጠቀም ትጀምራለህ ። ቢዝነሱ ይደርሳል ምናምን ስለው አይሰማኝም ነበር። አይ ማሂ ታዋቂነቱን እና ምላሱን ተጠቅሞ ሸቅሎታል።

እሁድ ቀን ሱፍ ለብሰን እንድንመጣ ታዘናል። የዛሬ ወር እዚ ቦታ ላይ ስኬታማ ሰዎችን አይቼ መች ነው እንደነሱ የምሆነው ብዬ ነበር። እሁድ ደሞ እኔ ወጥቼ ልናገር ነው ..

የእሁዱ ቀን ደረሰ ....

ክፍል 7 ይቀጥላል...


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
655 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , edited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:15:17 አልፋና ከሪማ

ክፍል ስድስት
(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ)

ሂወት ላይ ስኬታማ ሰዎች እርሃብተኞች ናቸው።ህልማቸው ከሌላው በተለየ መልኩ የሚርባቸው!!!

... ይህ የእቃዎች የአቅርቦት ሂደት ነው።

እና ይህ ከሆነ የድርጅቱ ልጆች እና ድርጅቱ ምን ያህል ሚና ይጫወታሉ? ምንስ ግንኙነት አላቸው ስንል ደሞ...

አሁን ይሄን በስልክ መሰልነው... ከስልክ ውጭ ያሉ እቃዎችም አሉ እና ድርጅቱ እቃዎች ላይ በቀጥታ አምራች እና ገዢ የሚገናኝበት ሲስተም ዘርግቷል። ለዛውም በተለየ መልኩ! ብዙ አቅርቦቶች በቅርብ ጊዜ ይጀምራል።

ለጊዜው ግን ስልጠናውን በራሱ እንደ አንድ ሽያጭ አርጎታል ማለት ትምህርቱ ራሱ ሽያጭ ነው። ምክንያቱም ይህ ስልጠና ከአስፈላጊም በላይ ነው።
" ለምሳሌ የጓደኞችህን ስም ንገረኝ " አለኝ።
እኔም " ማሜ፣ ማሂር፣ አብዱ..." አልኩት። ይህን ስልጠና ለማሜ ነገርከው። አእምሮው እንዲታነፅ ስለቢዝነስ አጠቃላይ ነገር እንዲያውቅ ብለህ ድርጅቱን አስገነዘብከው። ራሱን ለመገንባት አልፋን ለተቀላቀለው አላማውን እና ግቡን እንዲቀርፅ ላደረከው አንተ በጣም ብዙ ብር ታገኛለህ ( ምክምያቱም ወጣቱን ስለ ስራ ማስገንዘብ ስለሆነ አላማችን)
ከዛ ደሞ ማሜ ሄዶ ጓደኞቹን፣ ዘመዶችን ወደ ድርጅቱ ሲጠራ አንተም ታሳቢ ይሆንልሃል። ከማሜ አንዱ ጓደኛ ሰውን ከጠራ ደሞ አንተም ማሜም ተጠቃሚ ትሆናላችሁ። አሁንም ወደታች በወረደ ቁጥር ከላይ ያለኸው አንተ ተጠቃሚ ትሆናለህ። በማሜ በኩል የጀመርከው ዝርጋታ ማሜንም አንተንም ውጤታማ ያረጋል። ይህ በማሜ ብቻ ነው የዘረጋሀው ።
በአንድ በ5 ሰው ሰው ብቻ ከዘረጋኸው ስኬታማ ያረግሃል። እነሱ በጠሩ ቁጥር ላይኞቹ እየተጠቀሙ ነው። ሳታስበው አካውንትህ ላይ ብዙ ቆጥሮ ታገኘዋለህ። ስኬት ላይ የወጡ ሰዎች አብዛኞቹ ይህን የድርጅቱ አንዱ ሲስተም ተጠቅመው ነው ለዚ የደረሱት።
ከዚ በላይ ውጤታማ እና ሁሉም የሚሰራው ደሞ...

ድርጅቱ ውስጥ ያለውን ስልጠና በበቂ ሁኔታ ተምረህ እዛው የተወሰነ ለስራ የሚሆን በጀት ሰብስበህ ከዛ በተማርከው ትምህርት እና ባወቅከው እውቀት የያዝከውን ብር ወደ ስራ፤ ክህሎትህን ወዳፍላጎትህ አጠቃቀሙን አውቀህ ትጠቀመዋለህ። ከዛ በተረፈ የራስህን group ምስረታ የገለፃ ቢዝነሶች አሉ። እነዛን ሁሉ ስትገባ ነው የምታውቃቸው። በውጭ ሳትገባ ልነግርህ የምፈልገው ይሄን ብቻ ነው።

ሰአቱ መሸ ቤት እንዳይጨነቁ ሰጋሁ። ብዙ ስላወራን ተሰነባብተን ተለያየን..

እኔም በማታ ወደሰፈሬ ተጓዝኩ። በመንገዴ ላይም የሆነ ነገር አሰብኩ ...

እኔ እቃ የማስመጣት እና እዚው የማስረከብ ፍላጎት አለኝ። ይህን ህልሜን ከኔ በመቀጠል ትልቅ ሚና ሊጫወትልኝ የሚችለው ድርጅቱ ነው። ስልጠናውን በደንብ ወስጄ ከማን ጋ እና በምን መልኩ ነው የምሰራው? እሱን ማወቅ አለብኝ። ለበጀት የምይዘውን ብር እንዴት ወደስኬት እቀይረዋለሁ? ብዬ አሰብኩ። ከዛ ውጭ በራስ መተማመኔ እንዲመጣ እና የነበረኝን ማንነት መተው እፈልጋለሁ።

ለመግባት ወሰንኩ፤ ግን እንዴት ይህን የመጀመሪያ ፓኬጅ ክፍያ ላግኝ? ከጥቅሞቹ አንፃር ትንሽ ነው፤ ግን ያም ገንዘብ ለኔ ከባድ ነው! የመጀመሪያውን ፓኬጅ 5000 ምናምን ብር ከየት ላምጣው? ከአብዱ ልበደር አሰብኩ ወይስ በዚ ጭንቀት ሰአት ኡሚን ልጠይቃት ወይስ የሆነ አሪፍ ነገሬን ልሽጥ አላውቅም ብቻ ግራ ተጋባሁ።

ቤት እንደገባሁ ሻወሬን ወሰድኩ። ልብስ ቀያይሬ የት እንደነበርኩ ተጠየቅኩ መናገር አልፈለኩም? እነሱን ሳያቸው ግን እነሱን ተለውጦ የመለወጥ ጉጉቴ ጨመረ። ካለንበት ችግር እና ከሂወቴ ውጣ ውረድ በቃኝ ማለት እንዳለብኝ ተረዳሁ።
ጭንቀት በቃኝ !! ማጣት በቃኝ !! ሀዘን በቃኝ። በባህሪ መተቸት በቃኝ። ትልቁን ሰሚር ተመኘሁት። ለህልሙ የሚኖረውን ሰሚር...
Risk ወስጄ መሞከር አለብኝ። ለህልሜ ስል ብጎዳ ራሱ መቆፈር እና መዳፈር መወሰን መምረጥ!

ስኬት ላይ እንደሚያወጣ አወቅኩ። ሀሳቤ አብዛኛውን ሰአት እንቅልፍ ነስቶኝ ለሊቱ አለፈ። ህልማችንን በምናባችን መኖር እንዴት ነው የሚያስደስተው!

በነገው ቀን ስለድርጅቱ ለአብዱ ሳልነገርው ብር እንዲያበድረኝ ጠየቅኩት። ለምን ብሎ አልጠየቀኝም። ያለኝን እንካ ብሎ 3000 ብር ሰጠኝ።
ከማሜ 1000 ብር አገኘሁ። የቀረው 1700 ብር በራሴ እና ከኡሚ የተወሰነ እንደምንም ብዬ ተቀበልኳት። ብሩ ሀሙስ ቀን እንደሞላ ስልጠናውን በ Online እና በአካል ጀመርኩት። የአላማህን እና የእቅድህን ፎርም ያስሞሉሃል ራስህን እንድትገነባ መንገድ ይጀምሩልሃል።

በመጀመሪያው ስልጠና ስለሂወታችን ግብ፣ ስለምንኖርለት አላማ፣ ስለተፈጠርንበት፣ ስለህልማችን፣ ነገረን አረ ብዙ ብዙ ነገር ... በከሰአቱ መድረሳ ሂጄ አብዱ ሚለውን ሰማሁት ... የመጀመሪያው ስልጠና ብቻ ሂወቴ ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል ምን ላይ ነኝ? ምን እየሰራሁ ነው? ለምን አልሰግድም? ለምን ዲናዊ ሂወቴን አልኖረውም? ነገ እኮ ሁሉንም ትቼ እሄዳለው!!

ስልጠናውን እየተገበርኩ ስለስራም እያወቅኩ ሳምንታት አለፉ። መሀል ላይ ግን ሰውን ለመጥራት አሰብኩ ማሜ ሱቅ አለው። ሱቁን በምን መልኩ መጠቀም እንደሚችል ከድርጅቱ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ተረዳሁ። ማሂር ቁምነገረኛ ሰው እንዲሆን ቀልዱን በመጠኑ እንዲያረገው እና ህልሙን መቅረፅ እንዳለበት ተረዳሁ። አብዱም ከዱንያው ሂወት የራቀ እንደመሆኑ ውጪውን አለም እንዲያየው ፈለኩ። በዛውም በነሱ የማገኘው ጥቅም ስላለ ያን ጥቅም ለቀጣዮቹ ስልጠናዎች እና ብድሬን ለመክፈል ይረዳኛል።

ሁሉንም የአልፋ ፕሮግራም ጋበዝኳቸው። ማሜ ግን አልተመቸውም ነበር ለመምጣት። እነ አብዱ በጣም ወደዱት። ከዛም አብዱ " ስልጠናውን የምሰለጥነው ያንተን መለወጥ አይቼ ነው። ሂወትህ ላይ ትልቅ ነገር ፈጥሯል ማሻአላህ አሁን መሆን ያለብህን ሁነሃል! " አለኝ ማሂርም አሽቃበጠለት ትንሽ ..
ይህን ስሰማ በጣም ደስ አለኝ። አብዱ የኔ ሁብ ስወደው እኮ የራሴ የምትለው ምርጥ ወዳጅ ሲኖርህ፤ ወንድማማችነትህ ሲጠነክር ዱንያ ላይ ትልቁ ሀብት ወንድምነት ነው ትላለህ እኔም ወደስልጠናዬ ከከሪማ ጋር እየተመላለስኩ መውሰዴን ቀጠልኩ....

ውይ ሳልነግራቹ ከከሪማ ጋር ነው ስልጠናውን የምወስደው። በሷም ነው የገባሁት። በጣም ጎበዝ ናት። ለማንም ፊት አትሰጥም። ከኔጋም እንመላለሳለን እንጂ ስንመጣም ስንሄድም ኤርፎኗን ሰክታ ትመሰጣለች። ሁሌ ብቻዬን ነው የምቀረው። ምን አይነት ግፍ ነው በረቢ! ግን አይኗን ብቻ ማየቴ በቂ ነው። አንዳንዴ ላለመክፈል ነው ኤርፎን የምትሰካው እል ነበር። መጎዳቴ ሲበዛባት ነው መሰል ታክሲ ውስጥ ስንገባ መክፈል ጀምራለች ። በስኬት ጉዞ ብዙ ነገር ያጋጥመናል።

ከአንድ ሳምንት በኋላ እነማሂር ተቀላቀሉ።

ከደርሱ ከትምርቶቹ በስተጀርባ ከሪማ እኔ ላይ ኩራት ማሳየቷ እና ልዩ ስብእናዋ በጣም እንድወዳት አርጎኛል። የአልፋ ስልጠና ሂወቴን ሰጦኛል ሙሉ ለሙሉ ሀሳቤን ለሱ ነው ማድረግ የምፈልገው።

እና እንደምወዳት መንገር አለብኝ ።
ባለኝ ሁኔታ የወጣትነት ሂወትን ባላይም ኒካህ ብቻ ባስራለት እድሜዋ ደርሷል ታገባለች ብዬ ከምፈራው ትልቅ ጭንቀት እድናለሁ፤ ግን እፈራለሁ።
ከሪማ ሂወቴ ላይ ብትገባ ምን ያህል ሂወቴ እንደሚስተካከል አሰብኩ።
683 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:35:37
ሙህተላ በሆነቺው የፍልስጥኤም ምድር غዛ ላይ የሰማነው ኸበር እጅግ የሚደንቅ ነው። ከቀናቶች በፊት ከ580 በላይ የሚሆኑ የአላህን ቃል የተሸከሙ(ሁፋዞች) በአንድ መስጂድ ጥላ ስር ተሰብስበው ከፈጅር ሰላት አንስተው እስከ መغሪብ ድረስ በአንድ ጀልሳህ ሁለት ሁለት እየሆኑ ቁርዐንን ሙሉ ለሙሉ ተደማምጠው በግማሽ ቀን ማጠናቀቅ ችለዋል። ሱብሀነላህ! የሚገርመው በዚህ ፕሮግራም ወንዱም ሴቱም፣ ትልቁም ቲኒሹም የተካፈሉ ሲሆን፣ ከ12 አመት ታዳጊ አንስቶ እስከ 63 አመት የሚደርሱ ትልልቅ አባቶች ጭምር ተሳትፈዋል።

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቁርዐን ኮፒዎች ሙሉ ለሙሉ ከምድረ-ገፅ ቢጠፉ በቀናቶች ውስጥ አንዲት ነጥብ ሳያጓድሉ እራሱን የሚመልሱልን ሁፋዞች አሉን። አልሀምዱሊላህ ይሄን እስልምና ውስጥ እንጂ የትም አታገኘውም። ሱብሀነላህ!!!
871 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:33:05 በነገዋ ሰኞ ማሂርን Class አገኘሁት። ስለ ትናንት ውሎዬ እና የት እንደነበርኩ ጠየቀኝ። እኔም ከሞላ ጎደል የትናንቱን ተአምራዊ ቀን ነገርኩት። እሱም በመገረም " ታዲያ አመንካቸው? " አለኝ። እኔም " አንተ ቀልድ ነዋ የያዝከው!? ወላሂ ቼኩን ሲሸለሙ ነው አይቼ የመጣሁት። በዛ ላይ ስለስልጥናው ይህ ባዶ ጭንቅላትህን አሳውቀው " አልኩት። እሱም " ቆይ ይህ አሰራር የት ነው የተጀመረው? " አለኝ።
እኔም " የተጀመረው ውጭ ሀገር ነው። አሰራሩ ከ20 አመት በላይ አስቆጥሯል። እኛ ሀገር 1 አመት ከ ምናምን ነው አሁን ላይ። " እሱም እየሳቀ " ቆይ ማነው የወሰደህ? " አለኝ። ስለከሪማ ለማውራት ደበረኝ እና " ፌስቡክ ላይ ነው ያገኘሁት " አልኩት ።

" አንተ ሚስኪን ዝምብለህ Facebook ላይ አገኘሁ ብለህ ማንንም ሳታማክር ትሄዳለሃ? ጊዜህን አትፍጅ ሊበሉህ ነው! " አለኝ።
አስደነገጠኝ ከንግግሩ በኋላ ግራ አጋባኝ ግን የጠራችኝ ከሪማ ናት እሷ ደሞ ልዩ ታማኝ ናት ብዬ የማሂርን ንግግር ከአእምሮዬ አስወጣሁት።

" ሂወት ውሳኔ ናት!! ማንም ሰው ስኬት ላይ ሲወጣ ከጎን የሚያደናቅፉት ብዙ ነገሮች አሉ! " የተባለውን አስታወስኩ። ከclass ስንወጣ አብዱ ጋር ደወልኩ።

ሰላምታ ሳይሰጥ " ትናንት የት ነበርክ? እሺ ዛሬ ማታ እንገናኝ..." ብሎኝ ስልኩን ቶሎ ዘጋው።
እኔ ወደ መገናኛ ሄድኩ። የtaxi መንገድ ያሰለቻል፤ ግን የማይደረስ የለም ደረስኩ ሰአቱ ግን ሂዷል። ኡሚ ከ class ሳልመለስ እንዳደነግጥ ደወልኩላት።

እነማሂር ቤት ነን እመጣለሁ አምሽቼ አልኳት 22 ቢሯቸው ውስጥ ገባሁ።

አዋራሁት...ደስ የሚል አቀባበል እና ስብእና ተላብሷል። ከዛ ስለ ስራው ዘልዬ ጠየቅኩት
እሱም እንዲህ አለኝ ..

" አንተ ስለ ስራው አታስብ ስራው ቀስብሎ ይመጣል። ዋናው ስልጠናው ነው ስልጠናው ስትወስድ ስለ ስራም ስለሂወትም ትሰለጥናለህ ..."

እኔም በቅርብ ጊዜ እንደምቀላቀል ገለፅኩለት እና እንዲህ አለኝ ..

" እዚህ ካንፓኒ ላይ ብዙ የስራ ሀሳቦች ሲኖሩ አብዛኛውን ይፕምትሰራው ስልጠናውን በደንብ ስትወስደው ነው ምክንያቱም ስልጠናው ስለ ቢዝነስ ስለሆነ አእምሮህ ወደሞላሀው ፎርም እና አላማ ታዞረዋለህ። እና በደንብ ብቁ ስትሆን ነው ያኔ በአመለካከት በራዕይ ስትጎለብት ወደራሳህ ስራ እና የሂወት መንገድ ትሄዳለህ ወይስ ከኛ ጋር በደንብ ሰርተህ የራስህን Team ትገነባለህ?

ያኔ ሚፈጠሩብህ ነገሮች ናቸው።

በተረፈ እነሱ ረዘም ያሉ የስራ እቅዶች ሲሆኑ ብዙዎቹን ስኬታማ ያረገውን እና ዋነኛውን አንድ ሃሳብ ሰፋ አርጌ ላካፍልህ። በቀላሉ ብዙ ዶላር እና ገንዘብ የሚሰራበትን ማለት ነው ።

ለምሳሌ 1 እቃ አለ ብሎ ከኪሱ ያለውን Smart phone ስልኩን አወጣው። ይህ ስልክ ከአምራቹ ስንት ይሸጣል ብንል እስከ 2500 ያወጣል። ከአምራቹ ተቀብለው ወደ ሚመረትበት ሀገር ለስራ እየመጡ ሚሸጡ አካላቶች ደሞ በተወሰነ መልኩ አትርፈው በ4000 ብር ይሸጡታል ምክንያቱም ግብር አለባቸው።

ውጭ ሀገር እየተመላለሱ ሚሰሩ አካላቶች ደሞ ወደሀገር ውስጥ አከፋፋይ ሲሸጡ ደሞ በ7000 ብር ይሸጡላቸዋል። ለምን ገንዘቡን አስወደዱት ስንል? የፕሌን ፣ የቀረጥ ፣ የግብር ... አለባቸው።

አከፋፋዮቹ ደሞ ለሱቅ መደብሮች በብዛት ሲያከፋፍሉ እስከ 8500 ብር ይሸጡት እና 1500 ብር ያተርፉበታል። የሱቅ መደብሮች ደሞ ዋና ነገር አለባቸው የኪራይ እና የግብር። ስለዚህ እነሱ በ10’000 ብር ለተጠቃሚ ይሸጡታል ከዛም በላይ ሊሆን ይችላል።

ይሄኔ የ2500 ብር እቃ 10,000 የሚገዛው ተጠቃሚ ይጎዳል ማለት ነው። እና አምራቹም በመጠኑ ይጎዳል መሀል ላይ ሳያመርቱ ከሚያገኙት ትርፍ አንፃር...ይህ የእቃዋች የአቅርቦት ሂደት ነው።

እና ይህ ከሆነ የዚህ ካንፓኒ ልጆች እና ካንፓኒው ምን ያህል ሚና ይጫወታሉ? ምንስ ግንኙነት አላቸው ስንል ደሞ. ..

ክፍል 6 ይቀጥላል...


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
785 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , edited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:33:04 አልፋና ከሪማ
ክፍል አምስት

(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ)

ይሄ ስልጠና ብትፈልግም ይለውጥሃል፤ ባትፈልግም ይለውጥሃል!!!!


ከዛ መድረክ መሪው" ቆይታ እንዴት ነበር? " ብሎ ወደቀጣይ ፕሮግራም እንሄዳለን በማለት የሆነች ሴት ለንግግር ጋበዘ...

ይገርማል! የጋበዛት ሴት ፊቷን የተሸፈነች ገና የ20ወቹ መጀመሪያ ኒቃብ የለበሰች ሙስሊም ሴት ናት ። ኮንፊደንሷ ደስ ይላል።
በኩራት ነው ወጥታ መናገር የጀመረችው ...
" ስሜ አሊያ ይባላል። የዚህ ካንፓኒ 3ኛ ፓኬጅ ሰልጣኝ ነኝ ። ብዙዎቻችን የሆነ ነገር አልተረዳንም እና አመለካከታችንን መቀየር አለብን። መጀመሪያ አእምሯችን ሲሰፋ እና ሲገነባ፤ እና አላማችንን ስናውቅ ነው ወደራሳችን ቢዝነስ የምንገባው። የራሳችንን ስራ ፈጥረንም ይሁን በተፈጠሩ ስራዎች ስኬታማ ልንሆን የምንችለው። እኛ ጭንቅላታችን ለስራ ምን ያህል ክፍት ሆኗል? ምን ያህልስ ስለስራ ግንዛቤ አለን?ይሄ ስልጠና ከምታስቡት በላይ ነው። አንድ ቀን ወስዳችሁት ራሱ ሂወታችሁ ላይ ልዩ ተፅእኖ ይፈጥራል ። ስነልቦናችሁን ያሰፋል፤ የገንዘብ አያያዝ እና የሰአት አጠቃቀም ያስተምራል። ሳናስበው የሆነ ሰአት ትምህርቱ ራሳችን ላይ ሰርቶ እናገኘዋለን ። ለራሳችን ያለን ግምት ይጨምራል፤ በሂወታችን ያለንን ግብ ያሳውቃል፤ ሂወታችንን ለማስመር ይሄን ስልጠና መውሰድ ግዴታ ነው!!!

የሰው ልጅ ሲፈልግ ተአምረኛ ሲፈልግ ሰበበኛ ነው። ተአምረኛ መሆን የፈለገ የሚከፈለውን መስዋትነት ከፍሎ አእምሮውን ያንፃል። ሰበበኛ የሆነ ደሞ በተለያዩ ሰበቦች ራሱን ከትልቅ ድግስ ያስቀራል። ነገሩን ሳያየው ሳያጣራ ውስጡ በፈጠርው ጥርጣሬ ከስኬት ይዘገያል ። በጣም እድለቢስ ሰው ማለት ለኔ እሱ ነው ።
እኛ ሀበሾች አዲስ ነገር አንወድም። አዲስ ነገር ስናረግ ምንጠፋ ነው የሚመስለን። ይሄንን ካንፓኒ ለመቀላቀል ስለካንፓኒው ግንዛቤ የሌለው ሰው እንጠይቃለን ነገር ግን አላወቅንም እሱ... የህልማችን ሰራቂ ነው! የኛን ስኬት ይመኛል፤ ነገር ግን በሱ አስተያየት እንድንመራ ይፈልጋል!!

አንተ በውስጥህ የምታልመውን ማንም አያልምም! አላማህን፣ እቅድህን ማንም ሊኖረው አይችልም! ካንተ በላይ ማንም አያውቀውም!!

ለምን ሌሎችን በሂወትህ ወሳኝ ታረጋለህ? ለምሳሌ እኔ ይሄንን ካንፓኒ ስቀላቀል ቤተሰብ ከልክሎኝ ነበር። የመጀመሪያውን ምዝገባ ለመቀላቀል ከብዙ ጓደኞቼ ተበድሬ ነበር የገባሁት ቤት በጣም እወቀስ ነበር።

ነገር ግን እኔ ቤተሰቦቼን በጣም ስለምወድ ሂወታቸውንም መቀየር ስለምፈልግ በራሴ የሂወት ምርጫ ላይ እንዲገቡ አልፈቀድኩም። አሁን ሂወቴ ላይ ለውጥ ሳመጣ፤ የቤተሰቦቼን ሂወት ስቀይር፤ በልጆቻቸው መንገድ መግባት እንደሌለባቸው ተረዱ። ዛሬ ላይ ፊት ለፊቴ ጋብዣቸዋለሁ!!

( ሁሉም አጨበጨበ) ቀጠለች ...

" በርግጥ ወላጆቻችን ከኛ የበለጠ የመኖር ልምድ አላቸው እናማክራቸዋለን፤ ነገር ግን ስለተጨባጩ ስላለንበት ዘመን እንደኛ ግንዛቤ የላቸውም። እነሱ የሚመለከቱት ባሰቡት የአእምሮ ልክ ነው። እኛን ለማሳደግ ብዙ ነገር አይተዋል! በቃቹህ አሁን የኛ ተራ ነው ማለት አለብን።
እኛ እነሱን ከፍ ለማድረግ ብለን ራሳችንን እንሁን!! ከቻልን እንጋብዛቸው። ከአሰልጣኞቹ ጋር እንዲያወሩ አርጓቸው ካልተረዱ ግን የራሳችሁን ሂወት ራሳችሁ ምሩ!!

አሁን ላይ በ5 አካውንት መስመሬን ዘርግቼ ምርጥ ተከፋይ ነኝ። በስልጠናው ተምሬ በተገነዘብኩት ልዩ የስራ ግንዛቤ ወደምመኘው አከፋፋይ ተቀይሬያለሁ። አልሃምዱሊላህ ይሄ ካንፓኒ ለካ ሂወት ነው። አሁን ደሞ ሰፈሬ ላይ የኢስላሚክ ትምርት ሚሰጥበት ልዩ ቦታ ልንገነባ ነው። " ብላ ንግግሯን ቋጨች ከሷ በኋላ አሰልጣኞቹ አወሩ ብዙ ብዙ ነገር አካፈሉን።

ያኔ እዚ ካንፓኒ እንደምገባ ውስጥ ሁኜ ወሰንኩ። ፕሮግራሙ ተጠናቀቀ።


ከከሪማ ጋር ወጣን። ብዙ ጥያቄ ውስጤ ላይ አለ እዛው ቦሌ የሆነ ካፌ ገብተን እንድናወራ ጠየቅኳት እሽ አለች..።

" ቢዝነሶቹ ምን አይነት ቢዝነስ ናቸው? እና ደሞ ስልጠናው እንዴት ነው ሂወት የሚቀይረው? አንቺ ገብተሻል ወይ? ምን አይነት ነገር ፈጠረብሽ? " የኔ ጥያቄወች ነበሩ።
ካፌ ላይ ቁጭ ብላ ያ የሚያምረው አይኗን ያለእፍረት እመለከታለሁ። እሷ ግን ሀያእ ( ይሉንታ) የሚያጠቃት ልጅ ስለሆነች በሙሉ አይኗ እንኳ አላየቺኝም። ምናልባት በቴሌግራም ስላወራን እንጂ አንድ ላይ ካፌ ለመቀመጥ እሽ ምትለኝ አይመስለኝም።

በለዘበ አንደበት ሰሚር ስልጠናውን የወሰደ አይተሃል።
እኔ ገና የመጀመሪያ ፓኬጅ ስልጠና ላይ ነኝ ይህ በራሱ ግን ዲኔ ላይ እና ከሰዎች ጋር ያለኝን ግንኙነት አሳምሮታል። በትንሽ ምክንያት ተስፋ ቆራጭ እና ተበሳጭ ነበረኩ፤ ገር ግን በማሳየው ፈገግታ እና ልዩ የአቀባበል ገፅታ ጓደኞቼ ቤተሰቦቼ ጋር ልዩ ትኩረት ስቤያለሁ ። ይበልጥ ለአላማዬ እንድኖር እና እቅድ እንድነድፍ አርጎኛል። ከዛ በተረፈ ስለቢዝነስ ለጠየቅከኝ ከኔ በላይ ነገ 22 መገናኛ የኛ Team መሪ ሂደህ አግኘው። ማታ ስልኩን በቴሌግራም እልክልሃለው እሱ በደንብ ይነግርሃል " ብላኝ ሀሳቡን ዘጋችው ከዛ እንዲ አለችኝ።

" ይሄ ካንፓኒ .. ሰውን አመለካከቱን በማሳደግ እና በራስ መተማመኑን በመጨመር ሀገራችንን እያሳደገ ያለ ካምፓኒ ነው። ከተከፈተ 2 አመቱ ሲሆን ውስጥ የገባ እና አእምሮውን የተጠቀመ ስኬታማ ይሆኑበታል። በደንብ ያላወቀው አላወቀውም ነው፤ ነገር ግን ትምህርቱ በተግባር የሚተገበርም ነው። የራሱ Workout አለው!" አለች " እና ሰሚሬ መሽቷል እንሂድ። የቦሌን ምርጥ ጎዳና ስታይ እዚው ማደር አማረሃ? " ብላ ሙድ ያዘችብኝ...

እኔም " አረ ቤተል ይግደለኝ..." ብያት ስለሸገር ሰፈሮች እያወራን ታክሲ ውስጥ ገባን። ስለቤተሰብ፤ ስለ መድረሳቸው ብዙ ብዙ ነገር አወራን ከጀሞ 3 ትንሽ ወደላይ ከፍ ብሎ ያለው ሰፈር ፉሪ እንደምትኖር ነገረቺኝ። ሜክሲኮ ላይ ተሰነባብተን ተለያየን። እኔም ስለራበኝ ሜክሲኮ እርጥብ ብለው ሚሸጡትን እየበላሁ ወደ ሰፈሬ አቀናሁ።

ቤት እንደገባሁ ኡሚን ስሚያት ተጣጥቤ ቱታ ቀይሬ ከፋዘር ጋር ቤት ቡና መጠጣት ጀመርን። ዛሬ አባዬ ለምን እንደወጣሁም አልጠየቀኝም። ማታውኑ ተጫወትን አባዬም ትንሽ የአጎቴን ነገር እየረሳው ይመስላል ። ለነገሩ የቤታችን ኢኮኖሚ ሲያንስ ሳይወድ በግዱ ያስታውሰዋል። እዛው ቤት ኢሻ ሰግደን ወደክፍሌ ስገባ አብዱ 7 ጊዜ ደውሏል ማሂር 3 ጊዜ። ዛሬ ደሞ አዲስ ሰው ደውሏል ፉአድ ምርጡ እና የዋሁ ወዳጃችን ( አሁን ድሬድዋ ግቢ የሄደው) ነገ ስለምንገናኝ ከማሂር ጋር አንድ ላይ እንደውላለን ብዬ ተውኩት ለአብዱም አልደወልኩም። ወደቴሌግራም ስገባ የአሰልጣኙን ስልክ ከሪማ ልካዋለች። ቢመሽም ወዲያውኑ ደወልኩለት እና ነገ ከሰአት ከሱ ጋር መገናኘት እንደምፍለግ ገለፅኩለት እሱም ፍቃደኝነቱን ገለፀልኝ። እኔም ወደእንቅልፌ አቀናሁ።
774 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:34:41 ነገር ግን ይህ ኩባንያ ከሚታሰበው በላይ የገንዘብ በጀት ያለው ፤ እቅዱ ትልቅ የሆነ፤ በውጭ ሀገር የተመሰረተ እና አፍሪካ ላይ ይህ ኩባንያ ለብዙ ወጣቶች የስኬት ምንጭ የሆነ ነው። አስተምሮ፤ አሰርቶ ወጣቶችን ለማነፅ የሚሰራ ነው። ስልጠናው በውጮቹ ለብዙወቹ የሂወት መስመር እንዳሰመረላቸው እና በኛ ሀገር ልዩ ባለሀብት ባለሞያወች ሚሰለጥኑበት፤ እቅድ ያላቸው የሚያሳኩበት፤ እቅድ የሌላቸው እቅዳቸውን፣ ራዕያቸውን የሚቀርፁበት ሆኗል ። በተሟላ የቁጥር ሀይል እና በየ ሚዲያው ሼር ማይደረገው የራሱ የሆነ ልዩ የስራ ምክንያት እና አላማ ስላለው ነው።

ቤተሰቦች ዘመዶች በፍፁም ሊደግፉኝ አልቻሉም፤ ነገር ግን አልደነቀኝም። የሀበሻ ልዩ ባህሪያቶች አሉን ....

ባላየነው ባልሰማነው ባላወቅነው መፍረድ!!
ከጥሩ ጎኑ ይልቅ መጥፎ ጎኑን መፈላፈል ...

አእምሯችንን በአንድ ነገር ማጥበብ ፤ ራሳችንን ብቁ አይደለንም ብለን ማሳመን!

ብዙ የወረስናቸው መጥፎ ጥርጣሬ ሃሳቦች ወደኋላ አያስቀሩኝም ብዬ ለመመዝገብ ያለኝ አማራጭ ቤት ያለውን PC መሸጥ ነበር ከመበደር ይልቅ።

ምክንያቱን ብሩን ካንፓኒው ጋር በምሰራው ገንዘብ እመልሰዋለሁ። የመጀመሪያ ፓኬጅ ለመግዛት ሚያስፈልገኝን 5776 የኢትዮጲያ ብር ከፈልኩ።

ወዲያወኑ ስልጠና ጀመርኩ። ቢዝነሱንም ጀመርኩት ለቤተሰብ አትለወጥም ላለኝ በሙሉ ለማሳየት በቢዝነሱ ለፋሁ። ስልጠናውንም እየወሰድኩ 21 ቀናት አስቆጠርኩ በአልፋ ገቢ የተደረገልኝን አካውንት ሳየው ማየት ከበደኝ 237 ዶላር ሰራሁ ይህም በኛ ሀገር እስከ 11,000 የኢትዮ ብር ይደርሳል የ21 ቀን ስልጠናው ልዩ ምሩቅ ነበርኩ። ከኔ በላይ workout ተምረው የሰሩ እና ቢዝነሱንም በደንብ ያደጉበት ስለነበሩ ከ21 ቀን በኋላ ዛሬ ላይ ቁሜ በምናገረው መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመረቅኩ " አለ።

ያኔ ነው ቤተሰብ እና ጓደኞችን የጠራሁት። ያኔ እስቲ መጀመሪያ ተለወጥ እስቲ አትባክን አትለፍልፍ ያሉኝን ቤተሰቦቼ በአንድ በወር ብቻ ምሩቅ መሆኔን ለማሳየት ጠራኋቸው።

እኛ እኮ ስንት አመት ተምረን ስራ ለማናገኝበት ትምህርት ስንመረቅ ራሱ እንደዚ አንደሰትም፤ ነገር ግን እኔ ቆረጥኩ ውስጤን ብቻ ሰማሁ ከጎኔ ሚያሳንፉኝን አትበላ ያሉኝን ሰዎች አልሰማሁም !!

(ሲል ሰው እንዳለ አዳራሹ ላይ ያለው ሰው እየጮኸ አጨበጨበ። እኔ ምን አይነት አለም ውስጥ ነው የገባሁት ወይስ ህልም ነው ? ጥያቄ ላይ ነበርኩ...)

ሰውየው ንግግሩን ቀጠለ ...

በእለቱ የካንፓኒው ልዩ ስልጠና ግሩፓችንም አሸነፈ ያን እለት በ21 ቀን እስከ 600/ 700 ዶላር ( 35, 000) በስራት የበለጡኝ ጓደኞቼ እነሱን ሳይ በመናደድ ከዚ በላይ መስራት እንዳለብኝ እና አሁን ያገኘሁትን ብር ሁለተኛ ፓኬጅ ራሴን ስለሚገነባ እና የራሴን ስራ መፍጠር ስላለብኝ ልውሰድ በዛ ላይ ፖኬጄ ከፍ ሲል ገቢዬም ከፍ እያለ ነው ብዬ ወደሁለተኛው ተሸጋገርኩ። ቀስ በቀስ በአመቱ ልዩ ተከፋይ ሆኜ አረፍኩት ።

ፊትለፊት ምትታዩኝ ወጣቶች .. እኔ ከአዳማ እየተመላለስኩ ስኬታማ ሆንኩ። እድሜዬ ቢሄድም ተጠቀምኩት እናንተ። 20ወቹ ያላችሁ ሰዎች ምን አይነት የሂወት ደረጃ እና የከፍታ ማማ እንደምትወጡ ሳስብ ምናለ አልፋ ኢትዮጲያ በኔ እድሜ በገባ ብዬ አሰብኩ።

ሂወት ለወሳኞች ናት። ሂወት ምንድናት?
ምርጫ ናት ብሎ አንተ ግን ከኔ ትለያለህ አንበሳ ነህ! ከኔ በላይ መስራት ትችላለህ፤ ሂወትህን ቀይር ፤ ተናግረህ ሳይሆን አሳይተህ ጋብዘህ አሳምን ብሎ ከመድረኩ ወረደ!!

ወዲያውኑ ህዘቡ በጩሀት አዳራሹን ቀወጠው ።
ከዛ መድረክ መሪው " ቆይታ እንዴት ነበር? ብሎ ወደቀጣይ ፕሮግራም እንሄዳለን " በማለት የሆነች ሴት ለንግግር ጋበዘ...

ይገርማል የጋበዛት ሴት ፊቷን የተሸፈነች ገና የ20ወቹ መጀመሪያ ኒቃብ የለበሰች ሙስሊም ሴት ናት።

ንግግሯን ቀጠለች ....


ክፍል 5 ይቀጥላል....




#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
955 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , edited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:34:39 አልፋና ከሪማ
ክፍል አራት

(ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ )

ህልም ማለት ስትተኛ ምታየው ሳይሆን ..እንዳተኛ እንቅልፍ ሚነሳህ ነው !!!


ያኔ ሂወቴ እንደአዲስ ተጀመረ .. የሂወቴ መስመር ከዛች ቅፅበት በኋላ ነበር ነፍስ የዘራው። ሰሚር ራሱን ያወቀው፤ ለህልሙ መኖር የጀመረው ከዛች ጊዜ በኋላ ነው። ለካ ሰሚር ሂወትን አያውቃትም ! አይ ያ ልዩ እለት...

ፕሮግራሙ ላይ አንድ ገፅታው የሚያምር ሱፍ የለበሰ ሰው ማውራት ጀመረ። ለንግግሩ ትኩረት እንድታረግ የሱ አለባበስ እና በራስ መተማመን ይጋብዝሃል። በሚያምር ፈገግታ እና ሰላምታ ረዥም ንግግሩን ቀጠለ ....

" ህይወት ውሳኔ ናት... ሂወት ምርጫም ናት... የሰው ልጅ በፈለገው የሂወት መስመር እና መርህ መጓዝ ይችላል። የጉዞውን መንገድ የአላማውን ህልም መኖር ከጀመረ የጊዜ ትርጉም ገብቶት የሚንቀሳቀሰውን እንቅስቃሴ እንዳለ ወደ እቅዶቹ መቀየር ይችላል።
ብዙወቻችን ህልም አለን። ህልም ስላለን ነው እዚ የመጣነው... ወደፊት መኖር የምንፈልገው ህይወት አለ...በወጣትነት ማሳካት የምንፈልጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ...

የኔን ህልም ብትጠይቁኝ መኪና፣ ቤት እና እናቴን እየሩሳሌም መውሰድ ነው።
መኪናውን በፕሮግራሜ በመጓዝ አሳክቼዋለሁ። ቤትም መግዛት ባለብኝ ጊዜ በርግጠኝነት እገዛለሁ፤ምክኒያቱም የሂወቴን መስመር እና ለኔ የሚሆነውን ትክክለኛ መንገድ አልፋ አሳውቆኛል።

የሰው ልጅ የገንዘብ ሀብት ይፈልጋል፤ ነገር ግን የገንዘብ ሀብት እንዳለ ሁሉ የአእምሮ ሀብትም አለ... የአእምሮ ሀብታም ከሆንን የገንዘቡ በጣም ቀላል ነው። እኛ ሰዎች ፈጣሪ ልኩን ያላወቅነውን ትልቅ ጭንቅላት ሰጥቶናል አብዛኞቻችን አንረዳውም። መጠቀም ባለብን መንገድ አልተጠቀምነውም። ሰፋ ያለ አመለካከት ሊኖረን ሲገባ ሁሌ በአንድ መስመር ስራ እንፈልጋለን... ውጤታማ ለመሆን ረዢም ጊዜ ያዳግተናል።
የአብዛኞቻችን የሀገራችን ወጣቶች የሚኖሩት ኑሮ _ "ትምርታቸውን ይማራሉ... አንድ የሞያ አይነት Doctor, Engineer‌‌ .... የማርኬትም፣ የአካውንትም... የተለያዩ ነገሮች ሞያ ተምረን በተማርንበት ብቻ ስራ እንፈልጋለን። አእሞሯችንን በተማርንበት የመስራት አቅም ብቻ እንዳለን እንረዳለን።
ነገር ግን ብዙ የ Business‌‌ ሀሳቦች ብዙ መፍጠር ያለብን ስራወች አሉ።
ህልም ያለው ይቆፍራል... ህልም ያለው ይጥራል...በአጭር ጊዜ ምን እንደሚያሳድገው ለማወቅ ከፍተኛ ጥረት ያረጋል!

ስራ እና ሂወትን መለወጥ ሚለው ሀሳብ አእምሯችን ላይ ሲመጣ... ብዙ በጀት፤ ብዙ የገንዘብ Capital እናስባለን ነገር ግን የሰው ልጅ መንገዱን ካወቀ በጣም በአጭር ጊዜ መለወጥ ይችላል!!

ስለዚ ለተወሰነ ጊዜ ስለስራ ... ስላለንበት ተጨባጭ፣ ስለ ተጠቃሚ፣ ስለ ገዢ፣ ስለአከፋፋይ ማወቅ አለብን! እስቲ በሌላ ነገር... በወሬ፣በሙዚቃ የተሞላውን አእምሮ ስለ Business‌‌ እንዲያውቅ እናርግ ሁላችንም ለስራ ያለን እይታ ከስራ ትርጉም ፍፁም የተለያየ ነው።

በአእምሯችን ላይ ብዙ የስራ አመለካከቶች አሉ፤ነገር ግን አቅማችንን አናወጣውም። ለማውጣት የገንዘብ የሰው በጀት ያለ ይመስለናል ከእንቁ የስራ ሀሳባችን ጋር ወጣትነት ያልፈናል።

የብዙወቻችን ሂወት ይህ ነው ።
ነገር ግን ያልተረዳነው ነገር ወጣትነት ልዩ ሃይል እና ሁሉም ነገር የሚያምረው በወጣትነት ነው ።

እኔ ይሄንን ኩባንያ ስቀላቀል 29 አመቴ ነበር ነገር ግን አሁን በ 31 አመቴ ተለውጬ ስኬት ላይ ወጥጬ በወር እስከ 70,000/ 80,000 በአልፋ ተከፋይ ነኝ እሱም ቋሚ ላርገው እንጂ እጅግ በርካታ ገንዘብ በአካውንቴ የሚገቡት ብዙ ጊዜዎች ናቸው።

መጀመሪያ ይሄንን ኩባንያ መቀላቀል አልፈለኩም ነበር፤ ነገር ግን ጓደኛዬ ጋብዞኝ እንደምንም ተሳተፍኩ እና ስለአልፋ የBusiness‌‌ ስልጠና መውሰድ እንዳለብኝ ተረዳሁ ምክኒያቱም አልፋ ውስጥ ሁለት ትላልቅ ነገሮችን መጠቀም ስላለብኝ፡

አንደኛው ለቢዝነስ ያመጣልኝን ልዩ ሀሳብ ።
ሁለተኛው ቢዝነሱን በምን መልኩ መስራት እንዳለብኝ እና የራሴን እምቅ ሀሳቦች እንዴት ማውጣት እንደምችል...ከምን አይነት ሰው ጋር መገናኘት እንዳለብኝ እና የራሴን ክህሎት እንዳወጣ...በአጭር መልኩ አረገዋለሁ ያልከውን ማድረግ፤ እንዳለብህ ማመን፤ የአእምሮ ሀብታም፤ የተስፋ የህልምህን ስፋት የተመለከተ ከሰዎች ጋር ያለንን ቀረቤታ፤ ሀይማኖት ላይ ያለንን አመለካከት፤ ለአላማችን መኖር ሚባለውን ነገር ሰፋ አድርጎ ይፕሚሰጥ ልዩ ስልጠና ነው።

እነዚ ሁለት ነገሮች ( Business‌‌ እና ስልጠና) ለሂወቴ ትልቅ መስመር ናቸው ብዬ ከወሰንኩ በኋላ የካንፓኒውን ሰፊ ስልጠና ለመውሰድ የመጀመሪያውን ፓኬጅ ለመግዛት አሰብኩ።
ይሄ ካንፓኒ አራት አይነት ስልጠና አለው ትንሽ ረዘም ያለ ጊዜ ሲኖራቸው ...

የመጀመሪያው የገፅታ ገንቢ yellow ሲሆን አቅማችንን እንድናውቅ ህልማችንን እንድንቀርፅ ማንነታችንን እና መጓዝ ያለብንን መንገድ ለኔ የሚሆነውን የሂወት መስመር ይቀርፀዋል ።

ሁለተኛ ሶስተኛ እያሉ ይቀጥላሉ ሙሉ ስልጠናውን ከወሰድክ ስለ ማህበረሰቡ ስለ ሀይማኖትህ ስለ አካሄድህ ስለ አጠቃላይ Business‌‌ ሙሉ ግንዛቤ ይኖርሃል በአላማህ ተጉዘህ ከ6 ወር እስከ 1 አመት ባለው ጊዜ የስኬት ማማ ላይ ያወጣሃል ።
እና እኔ ይህን ስልጠና ለመውሰድ እና የአልፋ የBusiness‌‌ ሴንተር ውስጥ ለመግባት መመዝገቢያውን መጠየቅ እና ቤተሰብ ማማከር እንዳለብኝ ተረዳሁ።

የ Business‌‌ አቅርቦቱ ልዩ ስለሆነ መግቢያ ገንዘቡ አሁን ላለሁበት ሁኔታ ቢበዛ እንኳ ከየትም አመጣዋለሁ ብየ አሰብኩ ..

(ሰውየው ሲያወራ እየጮኸ ስለነበር በዛ ጊዜ ማንም ራሱን አያውቅም። እኔም ብሆን የስኬት ጫፍ ላይ እንደምደርስ በምናቤ አሳክቼዋለሁ) .. መድረክ ላይ የወጣው ሰውዬ ታሪኩን ቀጠለ ..

" ምክንያቱም አንዴ ሲስተም ውስጥ ከገባሁ የሚገኘው ገንዘብ እና ስለልቦናዊ የተሟላ ስልጠና ሂወትህን ይቀይራል ሰው ስለ ዘራችን፣ ስለ ኳስ፣ ስለ ታዋቂ ሰዎች በደንብ ያውቃል። ስለ Business‌‌ ያለን እውቀት ግን ውስን ነች። ይህ ነገር ግዴታ በሂወቴ አስፈላጊ ነው ።

ቤተሰብ ጋር ሂጄ አማከርኩ። በሞራል ነገርኳቸው ነገር ግን እነሱ ይህን ነገር ውድቅ አረጉብኝ፣አልደገፉትም። ይልቁንስ የተለያየ ነገር አርገው አጣጣሉብኝ። ጓደኛ ዘመድ እንዳለ .. ነገር ግን እኔ ያየሁትን የስኬትን በር ስለማያውቁ አጥበውም ነገሩን ስለሚመለከቱ ስራውን ስላልተረዱ ሞራል ሚያከስም አስተያየቶችን ላለመቀበል ወሰንኩ።

በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች የሚያነሱት ጥያቄ ...
" ለምን ይህ ሁሉ ወጣት እዚህ አልገባም?
ለምን በየሚዲያው አልተዋወቀም? "
828 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:28:19
كُلُّ نَفْسٍۢ ذَآئِقَةُ ٱلْمَوْتِ


#share_share_share
@fuadislamic @fuadislamic
925 views𝙵𝚞𝚢𝚎 , edited  09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ