Get Mystery Box with random crypto!

Transit ማለፊያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ transit_leasons — Transit ማለፊያ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ transit_leasons — Transit ማለፊያ
የሰርጥ አድራሻ: @transit_leasons
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 241
የሰርጥ መግለጫ

<<እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል!>> እንዲሉ አበው በተሳከረው የማህበራዊ ኑሯችን፣ ፖለቲካችን እና የምጣኔ ሀብት ጉዳዮቻችን ውስጥ ስለ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ጠቃሚ መረጃዎችን፣ ማስታወቂያዎችን እና የማለፊያ ወጎችን በዘርፍ በዘርፋቸው አሰናድተን እንጠብቃቹሀለን። ሊንኩን ይጫኑ https://t.me/joinchat/AAAAAE7hGRJr7dKTmtFqIg
እና ደግሞ ይመቻችሁ!

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 10:56:19 የአፋልጉኝ ማስታወቂያ!

ትናንት ሀሙስ ነሀሴ 19, 2014 ምሽት ላይ ከጠሮ አራት መንታ ወደ አዲስ ሰፈር / አስኮ በሚሄድ ታክሲ ውስጥ ተሳፍሬ እያለሁ በጥቁር ፌስታል ውስጥ ይዤው የነበረውን የይስሬሸ ሪል እስቴት የመመስረቻ ፅሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ጥዬ የወረድኩ በመሆኑ ፋይሉን ያገኘ ሰው ከታች ባለው ስልክ ቁጥሬ ደውሎ ቢያሳውቀኝ ወሮታውን እከፍላለሁ።

ፈላጊ
ሲራጅ ሸሪፍ
0912 163775
0910 175417
67 views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 15:21:57 ሸገር ሼልፍ - 171ኛው ሆስፒታል በአንዷለም ተስፋዬ

https://bit.ly/3bClphL

#Andualem_Tesfaye #ShegerShelf #ሸገርሼልፍ #DanielKibret

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqzG
ሸገር FM

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
136 views12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 14:20:36
ቲክቫህ እስፖርት

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እስፖርታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
109 views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 13:50:07 በጉራጌ ዞን የተፈጠረው ምንድን ነው?

በዛሬው እለት በጉራጌ ዞን የተለያዩ ከተሞች የስራ ማቆም አድማ መኖሩን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከዞኑ ነዋሪዎች ያገኝው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዛሬው ዕለት ከክልል እንሁን ጥያቄ ጋር በተያያዘ በዞኑ መቀመጫ በወልቂጤ ከተማ የስራ ማቆም አድማ መመታቱ ተሰምቷል።
ከወልቂጤ ከተማ በተጨማሪም “ጉብሬ ጉንችሬ” እንዲሁም “እምድብር” ከተሞች ላይም የስራ ማቆም አድማ መመታቱን ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም በስልክ ተናግረዋል፡፡

በነዚህ ከተማዎች ባንኮች ፣ የተለያዩ መ/ቤቶች፣ የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንደቆመ የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረዉናል።
የእዣ ወረዳና የአገና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞችም የህዝቡ ጥያቄ ይመለስ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ መሆናቸውን በስልክ ሀሳባቸውን የሰጡን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የዞኑ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄው ረጅም ጊዜን ያስቆጠረ መሆኑንና ለጠየቀው ህጋዊ የሆነ ጥያቄ ህጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው፣የ"ጉራጌ ክልል" አደረጃጀትም ተግባራዊ እንዲሆንለት በተለያየ መንገድ እየጠየቀ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ ነግረዉናል፡፡

የአካባቢ ነዋሪዎች መንግስት በሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ እየተጠየቀ ላለው የክልልነት ጥያቄ ህጋዊ መልስ እንዲሠጥ ነው የስራ ማቆም አድማ ዋነኛ አላማዉ ሲሉ ነዋሪዎች ለጣበያችን ተናግረዋል፡፡


ባሁኑ ሰአትም በወልቂጤ ከተማ የመከላከያ፣ የፌደራል እንዲሁም የክልሉ ልዩ ሀይሎች በብዛት መግባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡
ከስራ ማቆም አድማው በተጨማሪ በጉንችሬ እና በጉብሬ ሰላማዊ ሰልፎች እየተደረጉ ይገኛሉም ብለውናል፡፡
እስካሁን የተፈጠረ የጸጥታ ችግር አለመኖሩን የተናገሩት ነዋሪዎቹ የመንግም ሆነ የግል ሰራተኞች ስራ አለመግባታቸውን ነዉ የሚናገሩት፡፡

በደቡብ ክልል ያሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለሁለት ተከፍለው በሁለት አዲስ ክልሎች ለመደራጀት በየምክርቤቶቻቸው ወስነው ውሳኔውን ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረባቸዉን ከዚህ ቀደም ማስታወቃቸዉ ይታወሳል፡፡

በጋራ በአዲስ ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ውሳኔ አሳልፈው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄውን ካቀረቡት መካከል ግን የጉራጌ ዞን እንደሌለበት መጠቀሱ ይታወቃል።
ከሰሞኑ ዞኑ ከአጎራባቾቹ ስልጤ ፣ ከምባታ ጠምባሮ ፣ ሀዲያ፣ ሀላባ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ ጋር ነበር በአንድ ክልል ይደራጃል ብሎ መንግስት አቅጣጫ አስቀምጦ የነበረው።
ነገር ግን የዞኑ ም/ቤት እስከ ዛሬ ድረስ በጉዳዩ ላይ አልተወያየም፤ አዲሱን አደረጃጀት አላፀደቀም ፤ ከዚህ በፊት ዞኑ እንደገለፀው የክልልነት ጥያቄን ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ ነው።
መንግስት በአሁን ሰዓት ዞኑን በክልል ለማደራጀት እንደሚቸገር በመግለፅ ከአጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳ ጋር ክልል እንዲሆን ሀሳብ እያቅረበ መሆኑም ተሰምቷል።


በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ FM

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
93 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 13:43:28
በጎፋ ዞን በአራት ቀናት ውስጥ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ 60 አህዮች መሞታቸው ተነገረ

በጎፋ ዞን በሶስት ወረዳዎች ምንነቱ ባልታወቀ ተላላፊ በሽታ በአራት ቀናት ውስጥ 60 አህዮች ሲሞቱ በርካታዎች በበሽታው እየተጠቁ እንደሚገኙ የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

ይህ ምንነቱ ያልታወቀውን ተላላፊ በሽታ እያጠቃ የሚገኘው አህዮችን ብቻ ሲሆን ምንነት ለማወቅ ወደ ወላይታ ሶዶ ላብራቶሪ ናሙና ተልዕኮ ውጤት ማግኘት እንዳልተቻለ ተጠቁሟል።

በሽታውን ለመለየት ወደ ሰበታ ላብራቶሪ ተልዕኮ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ እንስሳትና አሣ ሀብት ሀላፊ የሆኑት አ/ቶ ሙሉቀን ተመስገን ተናግረዋል።

በበሽታው የተጠቁ አህዮች የአንገት መርዘም ፣ የመንቀጥቀጥ ፣ አረፋ መድፈቅ ምልክቶች የሚያሳዩ ሲሆን በተያዙ በሰዓታት ውስጥ እንደሚሞቱ ተገልጿል።

በሽታው መከላከል የሚቻል በሽታ ከመሆኑ ባለፈ የጋማ ከብቶችን ከሚያጠቃው አፒታኖት ሲክነስ ከሚባል በሽታ ጋር የሚመሳሰል ሁኔታ የታየ በመሆኑ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ እየተሸጋገረ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት በበሽታው የተጠቁትን የመለየት ስራ እና ወደ ሌሎች እንዳይዛመት የማድረግ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ የበሽታው ምንነት እንደታወቀ ይፋ እናደርጋለን ሲሉ አ/ቶ ሙሉቀን ተመስገን ተናግረዋል ሲል ለብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።


ቲክቫህ መፅሔት

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
72 views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 13:17:33
ፊሊፕ ላህም ወደ ኳታሩ አለም ዋንጫ አይጓዝም !

ጀርመናዊው የቀድሞ ባየር ሙኒክ እና ጀርመን ብሔራዊ ቡድን አምበል ፊሊፕ ላህም የኳታሩን 2022 አለም ዋንጫ ለመመልከት ወደ ስፍራው እንደማያቀና ገልጿል ።

ላህም በሰብዓዊ መብት አያያዝ ብዙ ጥያቄዎች ወደሚነሱባት ሀገር መሄድ እንደማይፈልግ እና ጨዋታዎችን በቤቱ እንደሚመለከት ተናግሯል ።

" ወደ ኳታር የመሄድ ፍላጎት የለኝም ይልቁንም በቤቴ ጨዋታዎቹን መመልከት እመርጣለሁ " ያለው ላሀም " ስልጣኑ ባይኖረኝም ለአለም ዋንጫ አስተናጋጅነት ሀገራት ሲመረጡ ግን የሰብአዊ መብት አያያዝ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው ይገባል " በማለት ተናግሯል ።

ለኳታሩ የአለም ዋንጫ ስራዎች ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 6,500 ሰራተኞች ህይወታቸውን ማጣታቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ ።


ቲክቫህ እስፖርት

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እስፖርታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
60 views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 13:17:07 ነሐሴ 3፣ 2014

በላኒና ተፅዕኖ ምክንያት በመጠኑ የበረታው የዘንድሮ ክረምት በአንዳንድ አካባቢዎች በታሪክ ትልቅ የሆነ የዝናብ መጠን እንዲመዘገብ አድርጓል ተባለ፡፡

እንደ ቆቃ፣ ርብ እና ጣና ያሉ ግድቦች የውሃ መጠናቸው ከፍተኛ ደረጃ ስለደረሰ አስቸኳይ ክትትል ያስፈልጋቸዋል ተባለ፡፡

የክረምቱ ዝናብ በበርካታ ቦታዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ የመሬት መንሸራተትና ከፍተኛ ጎርፍ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡

የቀሪ ክረምት የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያና የቅድመ ጎርፍ መከላከል ሥራዎች ዙሪያ ዛሬ በቢሾፍቱ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ ሲነገር እንደሰማነው የክረምቱ ዝናብ በበርካታ ቦታዎች ላይ በያዝነው ወርም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የዝናብ ውሃና ጎርፍን በወጉ መቆጣጠርና ማስተዳደር ባለመቻሉ ትልቁ ፀጋ የኢትዮጵያ ስጋት እንደሆነባት ያነሱት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በዚሁ ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎችም ቦታዎች ጎርፍ ለሰው ሕይወት መጥፋት፣ ለንብረት መውደም ምክንያት እየሆነ ነው ብለዋል፡፡

የዝናብ ውሃን በሚገባ መያዝ ብንችል ለዝናብ አጠር አካባቢዎች መፍትሄ ይሆን ነበር ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

በመጪው ጊዜም የዝናቡ መጠን የመሬት መደርመስና ከፍተኛ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል እንደ አገር እንዴት እናድርግ ብሎ መነጋገር የግድ አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬው ዝግጅት ተሰናድቷል ብለዋል፡፡

የክረምቱን የአየር ትንበያ በተመለከተ ማብራሪያ ያቀረቡት የብሔራዊ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪው አቶ ታምሩ ከበደ በሰኔና ሐምሌ የጣለው ዝናብ በአንዳንድ አካባቢዎች በታሪክ ትልቅ መጠን ያለው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በምዕራብ እና ሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል የዝናብ መጠኑ ከፍተኛ እንደነበር ያነሱት ባለሙያው በትግራይና አማራ በሐምሌ ወር ብቻ እስከ 800 ሚሊ ሊትር የደረሰ ዝናብ ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

በሰኔና ሐምሌ የተመዘገበው የዝናብ መጠን እስከ 1 ሺህ ሚሊ ሊትር መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በላኒና ተፅዕኖ ምክንያት የዝናቡ መጠን በብዙ ቦታዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በዚህም ምክንያት የመሬት መደርመስ እንደ ተከዜ ፣ ሐዋሽና ግቤ ያሉ ወንዞች ደግሞ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል ተብሏል፡፡

የግድቦችና የወንዞችን የውሃ መጠንንም በጥንቃቄ መከታተል ይገባል ተብሎ ተመክሯል፡፡

በተለይ ቆቃ፣ ርብ እና ጣና ግድቦች የውሃ መጠናቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ስለደረሰ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋሉ፤ ግቤ 1 እና 3 እንዲሁም ከሰምና ተንዳሆም ክትትል ያስፈልጋቸዋል ተብሏል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ላኒና #የውሃና_ኢነርጂ_ሚኒስቴር

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqzG
ሸገር FM

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
52 views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 12:55:21 አዲስ አበባ አትገቡም ክልከላው ቀጥሏል

ግድቡ ሊያልቅ ሲል ግብጾች ተርበተበቱ

የኮለኔል መንግስቱ ፓርቲ ተመለሰ

የትግራይ ገበሬ ወደእርሻው ተመለሰ
===================
06/11/2014 ማክሰኞ
(17:14 min) 7.9 MB
=====================

መረጃው የ #Feta_Daily ነው
=====================
አዲሱን የመዝናኛ YouTube ቻናላችንን ይከታተሉ





ሀሳብ አስተያየት ወይም ጥቆማ ካላቹህ _bot ይላኩልን

መረጃው በቅንነት ሼር ያድርጉላቸው
=====================

ዋልታ

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
46 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 12:47:47


ኢትዮ FM

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
41 views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 11:48:18 የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው::

ከጳጉሜ 2 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ይቆያል የተባለው አለም አቀፍ ኤክስፖው፣ ዘመኑ የደረሰባቸውን ቴክኖሎጂዎች ለማስተዋወቅ የታቀደበት መሆኑን አዘጋጆቹ አስታዉቀዋል፡፡

በሮቦቲክስ፣ ኤሌክትሮኒክስ ክፍያዎች እና ቴክኖሎጂ ላይ የተሰማሩ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ድርጅቶችም እንደሚሳተፉበት ተጠቁሟል፡፡

በሶላር፣ ሳይበር ደህንነት፣ በግብርና እንዲሁም የቴሌኮም ዘርፉን ጨምሮ በ14 አይነት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል፡፡

ከአፍሪካ፣ አዉሮጳ፣ እስያ እና የሰሜን አሜሪካ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ኤክስፖ፣ ከ500 በላይ ድርጅቶች እንደሚመዘገቡ እና ከ45 ሺህ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅም ሰምተናል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ እንደዚህ ያሉ አለም አቀፍ መድረኮች ለሃገር መልካም ገፅታ ግንባታ ከሚኖራቸው ሚና ባሻገር የአፍሪካዊያንን ትብብር እና ትስስር እንደሚያጠናክር ተጠቁሟል፡፡

የቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግር ከዘርፉ ጋር ያለንን ግንኙነት ማሻሻል ይገባናል ያሉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ተቋማትም ለእንግዶች የተሻለ አገልግሎት እንዲያቀርቡ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

ከኤክስፖው በተጓዳኝ በተጋባዥ እንግዶች የሚቀርብ ሲምፖዚያም ማዘጋጀቱም ተነግሯል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ኢትዮ FM

ቻናላችንን በመቀላቀል ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን በጣቶ ስር ያድርጉ
@transit_leasons
@transit_leasons
@transit_leasons
36 views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ