Get Mystery Box with random crypto!

💕 ፍቅርን በቃላት 💕

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrn_be_kalat — 💕 ፍቅርን በቃላት 💕 ፍ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrn_be_kalat — 💕 ፍቅርን በቃላት 💕
የሰርጥ አድራሻ: @fkrn_be_kalat
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.03K
የሰርጥ መግለጫ

💝 ፍቅርን በቃላት 💝
♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
💞የፍቅር ቃላት ሁሌም አሸናፊ ናቸው💞
For any promotion ➢ @Naolviva ✌
For spam 👇
@fkrn_be_kalat_bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-04-10 06:23:45 ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
ጉዞውን ቀጥለናል…..
ኮፈሌ..ሄረሮ...ዶዶላ… አለፍን፡፡ አዳባ ከተማ ስንደርስ
መኪናዬን መንገድ ዳር ምቹ ቦታ በማቆም 15 ደቂቃ የሻይ
እረፍት አድርገን መንገዳችንን ቀጠልን ፡፡ከተማውን ወጥተን
ኬላ ስንደርስ የዲንሾ ቆሎ እና ውሃ ገዝተን ተራራማውን
የሰብስቤ ዋሻ ተያያዝነው፡፡ በነገራችን ላይ የዲንሾ ቆሎ ዝም
ብሎ ቆሎ አይደለም፡፡በጣም የሚጣፍጥ ዝነኛ የገብስ ቆሎ
ነው፡፡ማንም ተጓዥ በዚህ አካባቢ የማለፍ እድል ካገጠመው
ይሄንን ቆሎ በመግዛት እሱም ቆርጥሞ ለቤተሰቦቹም ቋጥሮ
መሄድ የተለመደ ነው፡፡
ሰብስቤ ዋሻን እንደተያያዝን ሁለቱ የፍቅር አክተሮች
በአድናቆት እና በመፍዘዝ አስደማሚውን ተፈጥሮ ይቃኙ
ጀመር፡፡ከግራ በኩል ቅጥልጥል ተራራ፤ከቀኝ በኩል ጭው
ያለ የሚያስፈራ ሸለቆ ይታያል፡፡ሸለቆ ውስጥ እዚህም እዛም
የተራራቁ ጎጆዎች እና የተበጣጠሱ የእርሻ ቦታዎች ይታያሉ፡፡
መንገዱ ጠመዝማዛ እና አስፈሪ ነው፡፡መቼስ ቀልቤ እነሱ ጋር
ስለሆነ ዓይኔ አያርፍም በእስፖኪዬ እንደለመድኩት ወደ ኃላ
ስቃኝ እስክንድር ከንፈሩን አሞጥሙጦ ወደ እሷ ዚጓዝ ፊቷን
ታዞርበታለች ብዬ ስጠብቅ ይባስ ብላ መሀከል ድረስ ሄዳ
ተቀበለችው፡፡ተጐራረሱ፡፡የእሱ ዓይኖች ሲጐለጐሉ የእሷ
ደግሞ ተስለመለሙ፡፡
ቅናቴ ከጭንቅላቴ ሞልቶ ሲፈስ የሆነ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ፡፡
ለምን የፍቅሬን መቅደስ ሌላ ባዕድ ሰው ገብቶ
ይቀድስበታል….?ለምን በህይወት እያለው ልቤ በቅናት
ቀልጦ ወደ ፈሳሽነት ይቀየራል…? ለምን እለተ ምፅአት ዛሬ
አይታወጅም…?ለምን ፍቅሬን ከእስክንድር ነጥቄ ይዤያት ወደ
መንግስተ ሰማያት( ሲኦልም ቢሆን ግድ የለኝም)
አልኮበልልም..?ለምን በዛኛው ዓለም ሌለኛውን እድሌን
አልሞክርም?፡፡
የመኪናዋን ማርሽ ወደ አራተኛ ቀየርኩ…አምስተኛ ላይ
አስገባው‹‹ቀስ በል እንጂ… ኸረ ቀስ››የበለጡ ድምፅ ከሩቅ
ይሰማኛል፡፡ አሁን ተላቀዋል፡፡በፊልም ላይ ብዙውን ጊዜ
አንደማየው ጠመዝማዛውን መንገድ በአየር ላይ በሚባል
ሁኔታ እያሽከረከርኩ ነው ፡፡መኪናዋ በጣም ስለተጨነቀች
ልዩ የድረሱልኝ ድምጽ እያሰማች ነው፡፡ አንድ ሚኒባስ ወደእኛ
አቅጣጫ እየመጣች ነው ፡፡ግማሽ ኪ.ሜትር ርቀት
በመሀከላችን አለ …400ሜ ደረሰ… 300ሜ… 200ሜ…
50 ሜ ተጠጋጋን ፤ሀሳቤን ቀየርኩ እና አለፍኩት፡፡ ከባድ
መኪና መሆን አለበት፡፡ ይህቺኛው ፍጻሚያችንን ሙሉ
አታደርገውም፡፡ ተሸራርፈን እና ተቦዳድሰን ልንተርፍ
እንችላለን፡፡ፀጥ እንድንል ነው የምፈልገው፡፡ተያይዘን ወደ
ሌላው ዓለም እንድንሸጋገር፡፡ በመጨረሻ ፍጥነት ነው
እየበረርኩ ያለውት፡፡ከኃላ ጭንቀት ያዘለ ጫጫታ ይሰማኛል፡፡
ካፊት ለፊት የምፈልገው ዓይነት የጭነት ተሳቢ መኪና ወደ
እኛ እያዘገመ ነው፡፡እኔ ወደ እሱ እየፈጠንኩ ነው…
እየተጠጋጋን ነው…አዎ ከእሱ ጋር በጐን እላተምና አስፈንጥሮ
ሲገፈትረኝ ያው እየተገላባበጥን ሸለቆ ውስጥ በመግባት
ብትንትናችን ይወጣል፤የእኛ ብቻ ሳይሆን የመኪናዋም
ጭምር..አዎ ልንላተም ነው…ተጠጋግተናል ፡፡በመሀከል
ስልኬ ጠራ፤ በጐሪጥ አየውት፤ጋሽ በቀለ ናቸው የደወሉልኝ፡፡
የሆነ ነገር በፍጥነት በአዕምሮዬ ሲሰርግ እና ቅዝቃዜ
ሲረጭብኝ ተሰማኝ፡፡ማርሹን ወደ አራተኛ ቀነስኩ፤ወደ ሦስተኛ
መለስኩ፡፡ወደ ዳር አወጣውና አቆምኩ፡፡ስልኩን አነሳው‹‹ጋሼ
ሠላም ነው?››
‹‹ሠላም ነው ልጄ መምጣቴን ልነግርህ ነው››
‹‹በጣም ደስ ይላል ፡፡እንኳን በሰላም መጡ፡፡ሻሸመኔ ገቡ?››
‹‹አይ አልገባውም አዲስ አበባ ነኝ፡፡ሰሞኑን እመጣለው፡፡››
‹‹እሺ እጠብቆታለው››
‹‹ቸው››
‹‹ቸው ጋሼ››እኚህ ሰውዬ እኔን ሁሌ በቀኝ ጐዳና እንደመሩኝ
ነው፡፡ የእሳቸው መንፈስ የእኔ ጠባቂ መልአክ ሆኖ
እንዲያገለግለኝ በአምላክ የተመደበልኝ ይመስለኛል፡፡
ስልኩን ዘጋውና ወደኃላ ዞሬ አየዋቸው፡፡የቅድሙ ወዛቸው
ጠፍቶ አመድ የተነፋባቸው መስለዋል፡፡የሁለቱም ዓይን
ፈጧል፡፡የእስክንድር ለምቦጭ ከበፊቱ ያበጠ መሰለኝ፡፡
በፍርሀት ሳይነክሳቸው አልቀረም፡፡
‹‹ምነው..?ምን ሆናችሁ?››
‹‹ያምሀል እንዴ ….እብድ ነህ?››
‹‹ምን አደረግኩ?››
‹‹ምን አረኩ ትላለህ እንዴ ?ልትገለን ሀሳብ አለህ እንዴት…?
እንዴት ነው የምትነዳው?››
ነገሩን በማቃለል‹‹እሱ ነው እንዴ ያስደነገጣችሁ ?››አልኩ፡፡
‹‹ችሎታዬን እኮ አይታችሁ እንድታደንቁኝ ነበር››
በከረረ መኮሳተር‹‹ችሎታህን እዚህ ሲኦል አፋፍ ላይ ነው
የምታሳየን? ከቤ ትሙት ከአሁን ቡኃላ ብትደግመው
እንጣላለን፡፡››ብላ አስጠነቀቀችኝ፡፡
‹‹እሺ ተቀብዬለው..አሁን ልንዳ?››
እስክንድር ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገረ‹‹ሽንቴን…. ››
‹‹ውረድና ሽና››አልኩት…. ሊሸና ወረደ
‹‹አይ እስክንድር…!!እህቴ ጀግና ባል ያላት መስሎኝ ነበር?››
አልኳት
‹‹ባክ ዝም በል..እንዲህ አይነት ጀግንነት የለም፡፡›› ከአንጀቷ
ተበሳጭታብኛለች፡፡
ሸንቶ መጣና ጉዞችንን ቀጠልን፡፡ዲንሾ ተቃረብን ፡፡ መንገዱን
ተጠግቶ በ300 ሜትር ርቀት ከሚገኘው በደን የተሸፈነው
ሰንሰለታማ ተራራ ውስጥ በመውጣት በሜዳወ ላይ ሳር
የሚግጡ የሀገራችን ብርቅዬ እንስሳ ዋሊያዋች እዚህም
እዛም ይታያሉ፤ዝንጀሮዎች መንገዱን
ወረውታል፤ከርከሮዎችም የአካባቢው ድምቀቶች
ናቸው፡፡‹‹በሌ አየሻቸው ዋሊያዎቹን?›› ምንም
አልመለሰችልኝም ..ዝምብላ ብቻ ወዳጠቆምኳት አቅጣጫ
አይኖቾን ላከች እስክንድርም ተመሳሳዩን አደረገ፡፡ እጅ ለእጅ
እንደተያያዙ ናቸው፡፡ ፍራቻውና ድንጋጤው አሁንም
ከውስጣቸው የወጣ አልመሰለኝም፡፡ዲንሾ ከተማን አልፈን
ሮቤ ስንደርስ ከምሽቱ 12 ሰዓት ሆኖ ነበር::
12፡10 ላይ ጐባ ገባን ::ጎባ ከአዲስ አበባ ከተማ በደቡብ-
ምስራቅ አቅጣጫ 446 ኪ.ሜ እንደተጓዙ የሚያገኙት ከባህር
ጠለል በላይ 2743 ሜትር ላይ የሚያገኞት ነባር ከተማ ነች፡፡
ከጎባ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በ10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
የባሌ ብሔራዊ ፓርክ ይገኛል፡፡ቱሪስቶች እና ታዋቂ እንግዶች
ወደ አካባቢው ሲመጡ በሚያርፉበት ዋቤ ሸበሌ ሆቴል
በራሴ ገንዘብ አልጋ ያዝኩላቸውና ጥዋት ሁለት ሰዓት መጥቼ
እንደማገኛቸው በመናገር ተለየዋቸው፡፡ አብሬያቸው እስከማታ
እንድቆይ ሁለቱም ጠይቀውኝ ነበር፡፡ኸረ እንደውም በለጡ
ከእነሱ ጐን አልጋ እንድይዝ አሳስባኝ ነበር፡፡ግን ከምችለው
በላይ መሸከም ስለሌለብኝ አልተስማማውም፡፡
ቀጥታ ወደ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ነበር የሄድኩት ፡፡
መኪናዋን ቦታ አስይዤ በማቆም ወደ ውስጥ ገባው ፡፡
አልተሳለምኩም፡፡ድንዝዝ ብዬለው፡፡ተቀመጥኩ ፡፡በግምት
ለአንድ ሰዓት ተጐለትኩ፡፡ ከራሴ ጋር ብዙ
ተከራከርኩ፤ከእግዜያብሄር ጋር ብዙ ተጨቃጨቅኩ፡፡
ያለምንም እልባት ግቢውን ለቅቄ ወደ ከተማ ተመለስኩ፡፡
ወደ አያቴ ቤት መሄድ አልፈለግኩም፡፡ከበለጡ ጋር
እንመጣለን ብዬ ምን ብዬ ብቻዬን እሄዳለው? በዛ ላይ አሁን
እየተሰማኝ ባለው ጨለማ ስሜት ከአያቴ ጋር ተገናኝቼ
ልረብሻት አልፈለግኩም፡፡
በከተማው መሀል ከሚገኘው ባቱ ተራራ ሆቴል አልጋ ያዝኩ ፡፡
ምሽቱን ጭምልቅ አልኩበት፡፡የከተማዋ አንድም ጭፈራ
ቤቶች አልቀሩኝም፡፡ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ብዙ
መጠጥ ጠጣው፤ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ብዙ ሴቶች
ጐነተልኩ፤በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ከብዙ ሴቶች ጋር
ደነስኩ፤በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ገዝቼ ወደ ቤርጐ
ይዤ ገባው፡፡
እንደገባን በራፉም ሳይዘጋ ልብሷን ማወላለቅ ጀመረች፡፡
በራፉን ዘጋውና ጥግ ላይ ያለው ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ
አልኩ፡፡ፓንቷ ሲቀር ዕርቃኗን ቀረች፡፡ብስል ቀይ ነች፡፡የሰውነቷ
ቅርፅ በጣም ያምራል፡፡ ዕንብርቷ
2.3K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 11:09:49 ....ትወጂኛለሽ አወቃለው
አይንሽ ይናገራል

𝑗𝑜𝑖𝑛 & 𝑠ℎ𝑎𝑟𝑒
°@kmemuwaaa
@kmemuwaaa
2.4K views ᴍᴇʟɪɴᴀ , 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 21:57:56 ‍ ደግሞ አሁን እኛ ቤት ከገባህ በሁዋላ አይምሰልህ ያፈቀርኩህ፡፡…ድሮ ድሮ ልጅ እያለን አዲስ
ጀምስ ፓንት ገዝተህ በየሰፈሩ እየዞርክ ሱሪህን ዝቅ
እያደረግክ ለጓደኞችህ ስታሳይ እኔም የማየት እድሉ
አጋጥሞኝ ነበር፡፡ከዛን ጊዜ ጀምሮ አፈቅርሀለው፡፡ቶሎ ማደግ
እመኝም የነበረው አንተን ለማፍቀር ነበር፡፡››ብላኝ ሌላ መልስ
ከእኔ ሳትጠብቅ ቀድማኝ መንገድ ጀመረች፡፡ ሂሳብ በጥድፊያ
ከፍዬ ተከተልኳት፡፡ ተኰራርፈን እቤት ደረስን፡፡
ከቀን ውስጥ አንዳንድ መአተኛ ቀን አለ፡፡ከጫንቃችን አቅም
በላይ ሸክም የሚጫንብን፤ ከአዕምሮችን አቅም በላይ መከራ
የሚደርስብን፤ የቀን እርጉም፤እንደዛሬ ዓይነት ቀን፡፡ከአንድ
ጓዳኛዬ ለሦስት ቀን የተዋስኩትን ላንድ ክሩዘር መኪና
እየነዳው ነው፡፡ እራሴ እየሾፈርኩ ከሻሸመኔ ወደ ባሌ-ጎባ
እየተጓዝኩ ነው፡፡ከኃላ ወንበር ላይ እስክንድር እና በለጡ ጐን
ለጐን ተጣብቀው እየተጐሻሸሙ ይሳሳቃሉ፤ ያሽካካሉ፡፡ ወደ
ጎባ የምንሄደው ለምን ይመስላችኃል? በመጀመሪያ እኔ እና
እሷ ብቻ ሆነን የእኔን አያት ለመጠየቅ፤እግረ መንገድን
የዩኒቨርሲቲ ማለፊያ ውጤት ከመጣሽ የእናቴን ሀገር
አሳይሻለው ብዬ ከስድስት ወር በፊት ቃል ገብቼላት ስለነበረ
ያንን ቃሌን ለማክበር ነበር ከቤን አስፈቅጄ ከቤት ይዤያት
የወጣውት ፡፡ በመሀል ግን ያልታሰበ ዕቅድ ታከለበት፡፡አጅፕ
ቆሜ ነዳጅ እየሞላው ሳለ‹‹ሰርፕራይዝ...››አለቺኝ
እየፈነጠዘች፡፡
‹‹የምን ሰርፕራይዝ?››
‹‹እስክንድር ከእኛ ጋር ይሄዳል!!››መርዶ ከመቼ ወዲህ ነው
ሰርፕራይዝ የሆነው..?እንዲህ ዓይነት ዜና እንዴት መንፈሴን
እንደሚያጠቁር መረዳት ያቅታታል?፡፡
‹‹እስክንድር የት..?...ባሌ!!?››
ጭራሽ በእሷም ብሶ ኮስተርተር እያለች፡፡‹‹አዎ ባሌ፡፡ምነው
ችግር አለው?››አለችኝ
‹‹አይ የለውም፡፡ግን እኮ ይህ የሁለታችን ለረጅም ግዜ
የታቀደ ፕሮግራም ነበር››
‹‹ይገባኛል ግን በናትህ..ለእኔ ስትል..በዛ ላይ...››ወደ ጆሮዬ
ጠጋ አለችና …‹‹ድንግልናዬን ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ እዛው
እናንተ ሀገር ልሰጠው ስለፈለኩ ነው ›› ብላኝ እራፍ፡፡
አቤት ጠቅላላ ውስጤን እንዴት አመመኝ መሰላችሁ፤ደሜ
በደም ስሮቼ መዘዋወር ያቆመ፤ሳንባዬ አየር መሳብ
የተሳነው፤ኩላሊቴ ከቦታዋ የጠፋች፤አዕምሮዬ የማሰብ
አቅሙ የተደመሰሰበት፤ በአጠቃላይ ሁለ ነገሬ ተኖ የጠፋ
ዓይነት ስሜት ነው በሰከንድ ሽርፍራፊ ውስጥ የተሰማኝ ፡፡
በቃ ጭልም ነው ያለብኝ፡፡እንደዛም ሆኖ ግን ‹‹እሺ››
አልኳት፡፡ ታዲያ እንዴት እምቢ ልበላት?፡፡በምን አቅሜ፡፡
አንዳንዴ ሳስበው ይህቺ በለጡ የምትባል ልጅ እኔን
ለማሰቃየት፤ነፍሴን ለመቦርቦር፤ከገሀነም የተላከች የቅዱስና
እርኩስ ድብልቅ መንፈስ ትመስለኛለች፡፡
በደስታ ተጠምጥማ ሳመችኝ..ጉንጬን፡፡እቤቱ ድረስ ሄደን
ወሰድነው፡፡እናም ይሄው አሁን ሦስታችንም እየተጓዝን ነው፡፡
መኪናዋን በደመነፍስ እየነዳው ነው፡፡የሚያወርቱን አልሰማም
፡፡አልፎ አልፎ ግን በእስፖኪዬ ወደ ኃላ አያቸዋለው፡፡ሁለቱም
እስከመፈጠሬ እረስተውኝ የራሳቸው ዓለም ውስጥ
ሰርገዋል፡፡በፊታቸው ላይ የመጐምዠት ወዝ ቸፍ ብሎል፡፡
ሁለቱም ማታ ስለሚጠብቃቸው ወሲባዊ ደስታ እያሰቡ ፤
በምናብ አንዳቸው የአንዳቸውን ልብስ በማውለቅ
ዕርቃናቸውን በመተያየት ላይ መሰሉኝ፡፡

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot ❥❥________⚘_______❥❥
2.3K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 21:57:22 ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
መስከረም 15 -1998 ዓ.ም
አንድ አስደሳች ነገር ተከሰተ፡፡የእኔዋ በለጡ ጥሩ የዩኒቨርሲቲ
መግቢያ ነጥብ አመጣች፡፡ እኔንም እናቷንም አኰራችን፡፡ትንሽ
ሁለታችንንም ያላስደሰተን የተመደበችበት ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡
ድሬደዋ ፡፡ ቦታውን የጠላንበት ምክንያት ግን ለየቅል ነው፡፡
ፊቷን አጨማዳ ነገረችኝ፡፡‹‹ድሬደዋ ደረሰኝ ››
‹‹በስመ አብ ይርቃል እኮ!..እንዴት ነው ሚኮነው ?››እንዴት
ነው? ምሆነው ማለት ፈልጌ ነው ሚኮነው ያልኩት፡፡
‹‹ርቀቱ እኮ አይደለም እኔን ያስጨነቀኝ?››
ግራ ገብቶኝ ጠየቅኳት‹‹ታደያ ምኑ ነው?››
ያልጠበቅኩትን ወይም ትዝ ያላለኝን ምክንያት
ነገረችኝ፡፡‹‹ከእስክንድር መራቄ፤እሱ እኮ ሀዋሳ ነው
የደረሰው፡፡››ብላኝ እርፍ፡፡
መቼ ይሆን ከእኔ ህይወት እሷ፤ከእሷ ህይወት ደግሞ
እስክንድር የሚወጣው?‹‹አይዞሽ የሆነ መላ
እንፈጥራለን፡፡››አልኳት… እሷን ማጽናናት፤እሷን
ማስደሰት፤እሷን ማገዝ አይሰለቸኝ፡፡ ወድጄ አይደለም በእሷ
ደስታ መጠን ነው እስተንፋሴ ህያው የሚሆነው፤የልቤ ምቷ
የሚቀጥለው፡፡
‹‹ምን መላ አለ ብለህ ነው?››
‹‹በቃ ሚቀይርሽ ሰው ከተገኘ በገንዘብም ቢሆን
እንፈልጋለን፤ካልሆነ እና እዛ መሄድ ከደበረሽ በግል ኮሌጅም
ቢሆን ትማሪያለሽ ዋናው ውጤቱ መምጣቱ ነው፡፡አሁን ዘና
በይ አልኳት፡፡›› ዘና አለች፤ፊቷ በራ፤ደስታዋ ከተዳፈነበት
እየተገለጠ ሲነድ አስተዋልኩት፡፡ካዛ እኔም ተደሰትኩ፡፡
በዛው ሰሞን ከጋሽ በቀለ ጋር በተስማማነው መሰረት ነገሮች
ተስተካክለውልኝ ሚኒባሶን ልገዛ ቅድመ ከፍያውን በመክፈል
አዘዝኩ፡፡ከ15 ቀን ቡኃላ እጄ ትገባለች፡፡ጋሽ በቀለም
ጥቅምት ወር ውስጥ እንደሚመጡ ደውለው ነግረውኛል፡፡
እኔም በቃሌ ለመገኘት ተፍ ተፍ እያልኩ ነው፡፡ ሲመጡ
አዲሷን ታክሲ አስረክባቸውና አሮጌዋን በስሜ ያዞሩልኛል፡፡
አሮጌ ብትሆንም የአንድ ታክሲ ባለቤት ሆንኩ ማለት
አይደል?፡፡እንግዲህ ምንተስኖት ማለት እኔ ነኝ፡፡
ከዚህ ሁሉ አስደሳች ክስተቶች ውስጥ ግን መሀል ገብቶ
የተሰነቀረ አንድ ደስታዬን እየረበሸ ያለ ጉዳይ ገጥሞኛል
፤የብሩክቲ ጉዳይ ፡፡ ሁኔታዋ ሁሉ ተለዋውጦብኛል፡፡
ትነጫነጭብኛለች፤ትገላምጠኛለች፤
ትስቅልኛለች፤ትኮሳተርብኛለች፤ትቀርበኛለች፤ትርቀኛለች፡፡
እንዴት እንዴት እያረጋት እንደሆነ ሁሉ እየገባኝ አይደለም፡፡
ሁኔታዎቾ መቀያየር የጀመሩት ከባለፈው ክረምት ጀምሮ ነው፡፡
እናትዬው እትዬ ከበቡሽ (…ልጆቻቸው ከቤ ብለው ነው
የሚጠሯቸው ፤እኔም ከቤ ማለት ከጀመርኩ ቆየው) እንኳን
ታዝበዋት ‹‹አንቺ መንቃራ ምንድነው ልጄ ላይ
ምትምነቀነቂበት...አደብ ግዢ እንጂ፡፡››በማለት ከአንድም
ሁለቴ ቢገስፆትም እስከአሁን አደብ ልትገዛልኝ አልቻለችም
ወይም አልፈለገችም፡፡ከእህቷ ከበለጡም ጋር በተደጋጋሚ
በእኔው ጉዳይ ላይ ተጨቃጭቀዋል፡፡
ብሩክቲ ፀባዬ ብቻ አልነበረም የተቀየረው የሰውነቷ ቅርጽም
ተቀይሯል፡፡ ጡቶቾ መጠናቸው ጨምሮ ወደፊት
አሞልሙለዋል ፤ ዳሌዋ ሰፋ ሰፋ ብሎ ከዓይን ሞልተው
መትረፍ ጀምሮል፤መቀመጫዋ ወደ ኃላ ወጣ ማለቱ ብቻ
ሳይሆን ስትራመድም በስልት ታስደንሰዋለች፤ዕድሜዋም ወደ
16ቱ ተጠግቷል (ከቤ እንደነገረችኝ)፡፡ ግራ ስለተጋባኝ ዛሬ
ላናግራት ወስኜያለው፡፡በግዜ ወደ ሰፈር መጥቼ ይዤያት
ወጣው፡፡ እየተቆናጠረች ተከተለችኝ፡፡ ከሰፈራችን ብዙም
ወደማይርቅ አንድ ኬክ ቤት ወሰድኳት፡፡እሷ ጭማቂ እና ኬክ
አዛ እየተጠቀመች እኔ ለስላሳ በብርጭቆ በመቀነስ
እየጠጣው ጭውውታችንን ቀጠልን፡፡
‹‹ብሩክቲ ስለ እኔ ምን ታስቢያለሽ?››ጠየቅኳት
‹‹ምን ታስባለች አሉህ..?ምንም፡፡››
‹‹‹በግልፅ እንድናወራ እፈልጋለው፡፡የምትጠይኝ
ይመስለኛል፡፡ እቤታችሁ በመኖሬ ደስተኛ አትመስይኝም፤ምክንያት አለሽ?›› እንደመደንገጥ አለችና
ልትጎርሰው አፎ አካባቢ ያደረሰችውን ኬክ ወደ ሳህኑ
በመመለስ
‹‹ከቤ ትሙት አልጠላህም፡፡››አለቺኝ፡፡
‹‹ታዲያ ለምንድነው ግራ የምታጋቢኝ?››
‹‹እራስህ ነሀ፡፡››
‹‹እኔ ምን አደረግኩ?››
‹‹አንተ እኮ ከበለጡ ሌላ ለሌላ ሰው ደንታ የለህም
፤ለእናትህም ቢሆን ደንታ ያለህ አይመስለኝም፡፡እስቲ እኔ
ከእሷ በምን አንሳለው?››
የድንጋጤ ጥያቄ ጠየቅኳት‹‹በምን አንሳለው ማለት ምን
ማለት ነው?››
‹‹በምን አንሳለው ማለትማ በመልክ ብትል፤በዕድሜ ያንተ
እኩያ እንደውም ታናሽህ በመሆን ብትል፤በእስታየል ብትል፡፡
ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ላንተ አልታይህም ፡፡ልብስ ብትገዛ
ለእሷ፤ደብተር ብተገዛ ለእሷ፤ቅባት ብትገዛ ለእሷ፤ምትስቀው
ለእሷ፤እስቲ በደንብ እየኝ እና መልስልኝ እኔስ ምን ያንሰኛል?››
ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳገኘዋት ሁሉ ትዕዛዟን አክብሬ በትኩረት
አየዋት፡፡ጠይም ዓሳ መሳይ የምትባል ዓይነት ነች፤ዓይኖቾ
በጣም ጐላ ጐላ ያሉ እና የሚስለመለሙ ናቸው፡፡ አፍንጫዋ
ያረዘመ ያላጠረ ነው፡፡በቃ ሰዓሊ ቢያገኛት ሊስላት የሚመኛት
ዓይነት ነች፡፡ ከሁሉም በላይ ቁመናዋ እና የሰውነት ቅርፆ
የሞዴሎች ዓይነት ነው፡፡አብዛኛውን ነገሮቾን ከአባቷ ነው
የወረሰችው፤በለጡ ደግሞ የከቤ ፎቶ ኮፒ ነች፡፡ቀላ ብላ
ጉርድርድ ያለች፡፡የበለጡ ፀጉሯ እና ፈገግታዋ ነው ልዩ፤
ሌላው እንደነገሩ ነው፡፡ማንም ሰው ሁለቱን ቢያወዳድር
ለበለጡ 5/10 ሰጥቶ ለብሩክቲ 10/10 ይሰጣል፡፡
አወዳዳሪው እኔ ስሆን ግን ለብሩክቲ 10/10 እሰጥና
ለበለጡ 100/10 አስታቅፋታለው፡፡ምክንያቱስ ብሎ
ሚጠይቀኝ ካለ እኔ እንጃ መልሴ ነው፡፡ልክፍት ነው ልትሉኝ
ትችላላችሁ፡፡አዎ!! እስከ ጥግ ማፍቀር ልክፍት ከሆነ ትክክል
ናችሁ፤በበለጡ ተለክፌያለው፡፡
ከብዙ ትካዜ እና ማሰላሰል በኃላ ወደ መልሴ
ተመለስኩ፡፡‹‹ቆይ ምን አይነት የሠይጣን ሀሳብ ነው በልብሽ
የተሰነቀረው…? እኔ እና በለጡ ምን እንደሆን ነው
ምታስቢው?››
‹‹ኪ..ኪ..ኪ ከቤ እንዳምታስበው እህት እና ወንድም ናችሁ
እንድልህ ትፈልጋለህ?››
‹‹ታዲያ ምንድነን .... ?እሷ ፍቅረኛ እንዳላት አታውቂም?››
‹‹አውቃለው ባክህ፡፡የሚገርመኝም እሱ ነው፡፡ትምህርት ቤት
እስክንድርን እቤት ደግሞ አንተን በጥበብ ያለምንም መደናበር
አቻችላ ማፍቀር መቻሏ ሁሌ ያስደንቀኛል፡፡››
‹‹አንቺ አፍሽን ዝጊ ...ስለማታውቂው ነገር አትቀባጥሪ፡፡››
‹‹አልቀባጠርኩም፡፡ እስኪ በለጡ ትሙት አላፈቅራትም
በለኝ፡፡››
‹‹ለምንድነው በበለጡ የምምለው?››
‹‹ምክንያቱም በውሸት በእሷ ስም የመማል አቅም እንደሌለህ
አሳምሬ ስለማውቅ ነዋ፡፡››
‹‹ከገመትኩሽ በላይ ነገር ሸራቢ እስስት ልጅ ነሽ፡፡››
‹‹እሱ ያንተ ግምት ነው፡፡በነገራችን ላይ እኔ ምንም ዓይነት
ፍቅረኛ የለኝም፡፡የሚጠይቀኝ ወንድ አጥቼ እንዳይመስልህ፤
በቀን ሦስት አራት ወንድ ነው ሰድቤ ከስሬ የማባርረው፡፡››
‹‹ታዲያ ይሄ ለእኔ ምን ይረባኛል?››
‹‹ዓይንህን ከፍተህ ምርጫህን እንድታስተካክል ነዋ፡፡ታናሽህ
ነኝ፤ቆንጆ ነኝ፤አማላይ ነኝ፡፡ በማንኛውም ሰዓት ወደ እኔ
ከመጣህ ልቀበልህ እየጠበቅኩ ነው..፡፡››
‹‹ይሄውልሽ ብሩክቲ..በአዕምሮሽ የተሰነቀረው ሀሳብ አጉል
ህልም ነው፡፡በለጡ ሆነች አንቺ እህቶቼ፤ከቤ ደግሞ እናቴ
ነች፡፡ሁሉን እርሺውና ትምህርትሽን አርፈሽ ተማሪ፡፡
እንደበለጡ ጐበዝ ሆነሽ ዩኒቨርስቲ ግቢ፡፡ እኔም ለበለጡ
አደርግላት የነበረውን ሁሉ ለአንቺም አደርጋለው፤ምክንያቱም
እህቴ ስለሆንሽ፡፡››
ከመቀመጫዋ ተነሳች‹‹በቃ… በቃ… ተነስ እንሂድ፡፡ እኔ ፍቅሬ
ነሽ ብለህ ወደእኔ እስክትመጣ ሽራፊ ሣንቲም ካንተ
አልፈልግም፡፡ልብ እስክትገዛ እና ዓይንህ እስኪከፈት
በትዕግስት እጠብቅሀለው፤
2.4K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 06:20:33 ‍ ምነግራችሁን ታሪክ በለጡ ነች በቁጭት የነገረችኝ፡፡በሰፈር ስለእኔ የሚወራውን
እትዬ እልፌ የሰፈራችን ቁጥር አንድ ወሬኛ‹‹በላቸው
ሀብታም የሆነው ከልጆቻችን የተለየ ጐበዝ ስለሆነ አይደለም
›› አሉ ፡፡
‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው?››
‹‹እናቱ ቆሪጥ ጋር ሄዳ አስረታለት ነው፡፡››
ሌለኛዋ አዳናቂ እትዬ ዘውዴ ትጠይቃለች፡፡‹‹ቆሪጥ… የት?
መቼ?››
‹‹ከሦስት ዓመት በፊት ቢሾፍ ሄዳ ነው ያሰራችለት››
‹‹አበስ ገበርኩ..አበስ ገበርኩ... እርሷ ይሄንን ጉድ ከየት
ሰሙት?››
‹‹ምን አገር አይደል የሚያወራው፡፡አክስቴ ሞታብኛለች ብላ
ሄዳ አሰራችለት እና ለማስመሰል ጥቁር ለብሳ
መጣች፤ያለምንም እፍረት ዓይኗን በጨው ታጥባ
ከዕድራችንም ብር ተቀብላ በላች፡፡ሲፈጠርም እኮ አክስት
ኖሯት አያውቅም››(እንደተባለው እናቴ ከሦስት ዓመት በፊት
እኔ የማውቃት አክስቷ ሞታባት ቢሾፍቱ እንደሄደች
አስታውሳለው)
‹‹እውነትሽን ነው፡፡ይሄ ቁጭራ ሰፈር ያደገ ያረቄ ሻጭ ልጅ
በአንዴ ተነስቶ ባለ ጅንስ ሱሪ፤ባለ እስኒከር ጫማ፤ባለ ሌዘር
ጃኬት፤ባለ ሞባይል(በዚህ በእኛ ሰፈር ሞባይል ያለው
ብቸኛው ሰው መቼስ እሱ ነው)፤ባለ ታክሲ፤ባለ ዕቁብ እንዴት
ተሁኖ?›› ወይዘሮ ዘውዴ ጥልቀት ያለው ትንተና በማከል
ነገሩን አጩኸው አዳነቁ አሉ፡፡
ሌለኛዋ ሲቀጥሉ‹‹ኸረ ባሎንም ያቺኛዋን ሚስቱን ዞር በይ
ብሎ ጥሎ ወደ እሷ እንዲመጣ አስነክታው ነው ይባላል፡፡››
‹‹ኸረ እንደውም አዳልሞቲ ላይ ነው ያሰራው አሉ፡፡ አታዩትም
እንዴ እንደበተስኪያን እኮ በቀን በቀን ሳይሳለመው
አይውልም፡፡ … ውይ ጭካኔ!! ሰው በድመት እና በአህያ ላይ
ያሰራል…. እነሱ ቀን በጣለው እብድ ላይ››እትዬ ዘውዴ
የረሳችውን ታክልበታለች፡፡….ይሄን እና የመሳሰለው ወሬ በእኔ
እና በቤተሰቤ ዙሪያ ብዙ የእነ እትዬ ዘውዴ ዓይነቶቹ
እንደሚያወሩብኝ እሰማለው፤አውቃለው፡፡ይሄንን በተመለከተ
ከጋሼ ያገኘዋት አንዲት ፅሁፍ እንዲ ትላለች፡-
 ‹በውድቀትህም ሆነ በስኬትህ ጊዜ ህይወትህን
የሚያንፅው ወይም የሚያደቀው ወሳኙ ነገር ሰው ስለአንተ
የሚሰጠው አስተያየት ሳይሆን ….. አንተ ስለራስህ
የምታስበው ሀሳብ ወይም ለራስህ የምትሰጠው ግምት ነው
፡፡ስለዚህ ልጄ የስኬትህም ሆነ የውድቀትህ መሰረቱ
ሚመነጨው ከውስጥህ ነው…ለማግኘትህም ሆነ
ለማጣትህ ኃላፊነቱ የራስህ ብቻ ነው…› ነበር ያለኝ፡፡
እኔም የህይወት አስተማሪዬ ያለኝን በማመን ለውስጤ ድልን
እያበሰርኩት ለልቤ ስኬትን እየነገርኩት ወደፊት ቀጥያለው…
ወደፊት...

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot ❥❥________⚘_______❥❥
2.5K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 06:18:48 ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
‹‹በውድቀትህም ሆነ በስኬትህ ጊዜ ህይወትህን የሚያንፅው
ወይም የሚያደቀው ወሳኙ ነገር ሰው ስለአንተ የሚሰጠው
አስተያየት ሳይሆን አንተ ስለራስህ የምታስበው ሀሳብ ወይም
ለራስህ የምትሰጠው ግምት ነው ፡፡››
1998ዓ.ም
‹‹ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም››
ሌለኛው መስከረም ጠባ፤መቼም ይህ መስከረም ሲጠባ እኔ
በጣም የተለየ ሰው ሆኜለው ፡፡ ሰውነቴ በጣም
ገዝፎል፤ጡንቻዎቼ ፈርጥመዋል፤የሃያ ምናምን አመት
ጐረምሳ መስያለው፡፡ መንፈሴ ጠንካራ፤ንግግሬ በቁም ነገር
የተሞላ፤ስራዬ የትልቅ ሰው ሆኗል፡፡ እናቴ እንደ ልጆ ሳይሆን
እንደምትፈራው ታላቅ ወንድሟ ታየኝ ጀምራለች፡፡ አባቴ
በፍቅር እና በአክብሮት ይቀርበኛል፤ ይንከባከበኛል፡፡ ለሰፈር
ጓደኞቼ አማካሪ እና የችግር ቀን ደራሻቸው፤ሲጨነቁ
አፅናኛቸው ሆኜያለው፡፡
ጋሽ በቀለ ወደ አሜሪካ ከሄዱ 5 ወር አለፋቸው፡፡የእኔም
ህይወት በውጥረት የተሞላ ና በኃላፊነት የታጠረ ቢሆንም
በዛው ልክ በውጤት የታጀበ ሆኗል፡፡የእኔን ፤ የቤተሰቦቼን እና
የበለጡን ወጪ ሸፍኜ በሳምንት 3ሺ ብር ዕቁብ እጥላለው፡፡
ጋሽ በቀለ የሰጡኝን ኃላፊነትም በትክክል እየተወጣው ነው፡፡
እስከ አሁን 60ሺ ብር ከተከራዬቹ በመቀበል በባንክ
ደብተራቸው አስገብቼ ደረሰኙን በእጄ ይዤያለው፡፡
አንዳንዴ ስለዚህች ዓለም ሳስብ እገረማለው፡፡ድንገት በክፋ
ሁኔታ ውስጥ ስንገባ ችግር፤ህመም፤ሰቆቃ ይፈራረቅብናል…
ደጋግሞ ይደቁሰናል...ቋቅ እስኪለን ያማርረናል ፡፡
እንደምንም ብለን ያንን በትዕግስታችን አልፈን፤ በፅናታችን
አሸንፈን ወደ ብርሀን ከወጣን ደግሞ ደስታው እና ገንዘብ
ተግተልትሎ እና ተደራርቦ ይመጣልናል፡፡ አሁን ዕቁብ መጣል
ከጀመርኩ እንኳን ገና ሁለት ወሬ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት
ዕጣ ወጣልኝ፡፡መቶ ሺ ብር ፡፡ይታያችሁ የበቆሎ ቂጣ በቀን
አንዴ እና ሁለቴ እየበላው ያደግኩ፤ሰልባጅ ልብስ እና
በረባርሶ ጫማ እየተጫማው ያደግኩ ልጅ፤አረቄ ሻጭ እናት
እና ተሸካሚ አባት ያለኝ ልጅ፤ሃያ ዓመት እንኳን ያልሞላኝ ልጅ
የመቶ ሺ ብር ዕቁብ ሲደርሰኝ፡፡ዕቁብተኞች ብሩን ለእኔ
ለመስጠት ፈሩ፤ ዋስ ሊሆነኝ የሚደፍር ሰውም አልተገኘም፡፡
እኔም ጭንቀታቸውን ከስሜታቸው አነበብኩ እና
ገላገልኮቸው፡፡
‹‹ዕቁቡን መሸጥ እፈልጋለው፡፡››ስላቸው በደስታ ሀሳቤን
ተቀበሉኝ ፡፡ ለቸገረው አንዱ ግለሰብ በ15 ሺ ብር ሸጥኩለት
እና ብሩን ተቀብዬ ባንክ ያለኝ ገንዘቤ ላይ ጨመርኩት፡፡
ነገሮች በህይወቴ ውስጥ እንዲህ እየተስተካከሉ ቢሆንም
አሁንም ግን በልቤ ትልቅ ሽንቅር አለ፤ጥልቅ የሆነ ባዶ
ቦታ፤የግራጫ እና ጥቁር ድብልቅ የሆነ ጨለማ የሞላው
ስፍራ፡፡ በለጡ የበሳችው፤የቦረቦረችው ፤ያሰፋችው ዋሻ….፡፡
በለጡ አሁኝ ለ12 ክፍል ማትሪክ ፈተና ወስዳ ውጤት
እየተጠባበቀች ነው፡፡ሰሞኑን ይለቀቃል ተብሎ ወሬ
እየተናፈሰ ስለሆነ የእሷም ሆነ የእኛ ልብ በጉጉት
ተንጠልጥሎል፡፡በለጡ ከበፊቱ በተሸለ ሁኔታ ጐበዝ ተማሪ
ሆናለች፡፡ጉብዝናዋ የጨመረበት ምክንያት( ሰው እራሷ
ስታወራ ሰማው ብሎ እንደነገረኝ)ጐበዝ መሆን ፈልጋ፤
ለወደፊት ህይወቷ መቃናት ተጨንቃ፤ወይም የቤተሰቦቾን ኑሮ
ለመቀየር ወጥና ሳይሆን፤ የእኔን ልፋት እና ውለታ ገደል
ላለመክተት ብላ ነው፡፡
ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም በእሷ መቀየር፤ በእሷ ምርጥ
መሆን እኔ ደስተኛ ነኝ፡፡ጓደኞቾ ሲያሞግሷት እና በጉብዝናዋ
ተመስጠው ሲቀኑባት ሳይ ነፍሴ ሀሴት ታደርጋለች፡፡
የሚገርመው በለጡ ጐበዝ ተማሪም ብቻ ሳትሆን ምርጥ
ተፈቃሪም ሆናለች፡፡ያ እስክንድር የሚባለው ልጅ በማስገደድ
ጓደኛዋ እንዲሆን እንዳላደረግነው ሁሉ ዛሬ ቀርቧት የውስጧን
ብሩህነት ..የነፍሷን ነጻነት ሲረዳ፤ከበፊቱ ይበልጥ ስትጐብዝ፤
ከበፊቱ ይበልጥ ለብሳ ሲያምርባት፤ፀጉሮን በውበት ሳሎን
ስትሰራ፤ጥፍሮቾን ቀለም ስትቀባ፤ቆዳዋን በውድ ቅባት
ስታለሰልስ፤ጠረኗን የሚቀይር ሽቶ በሰውነቷ ስታርከፈክፍ
(ይሄን ሁሉ የምገዛላት እኔው ነኝ) ለኸጩን እስኪዝረከረክ
ያፈቅራት ጀምሯል፡፡
ይሄ የእሱ ወደ ፍቅር ውስጥ መስመጥ በእኔ ልብ ጥልቅ
የሆነ ሀዘን እና ሰፊ የሆነ ደስታ እንዲፈጠር አድርጐል፡፡እሷን
አቅፎት ሲሄድ፤ከንፈሯን ሲስማት፤የሆነ ደበቅ ያለ ቦታ ግድግዳ
ወይም አጥር አስደግፎ እጁን ወደ ጡቶቾ
ሲሰድ፤ሲጨምቃቸው…ወዘተ ወዘተ ሳስብ ልቤ ትደክማለች፡፡
ጥልቅ ቅናት እና ጥቁር ሀዘን ይወረኛል፡፡እሷ ስለ እሱ አንስታ
ስትስቅ፤ፍቅራቸውን እያሰበች ስሬ ተቀምጣ ስትፍለቀለቅ፤
እሱን ከሌሎች ሴቶች ነጥቃ የግሎ ማድረግ በመቻሏ በራሷ
ኩራት ሲሰማት ሳይ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል ፡፡ነፍሴ
አብራት ትፈነድቃለች፡፡
በእኔ ውስጥ የሚፈጠር ሳቅና ለቅሶ፤ሀዘን እና ደስታ፤ፈገግታ
እና ብስጭት፤ተስፋ እና ጨለምተኝነት፤ክብር እና
ውርደት፤ዝቅጠት እና ከፍታ፤ውድቀት እና ስኬት፤ውበት እና
ፍዘት ሁሉም ስሜቶች ጐልተው ሚፈጠሩብኝ በሷው ነው፡፡
በእሷው ብቻ፡፡ሌሎች የህይወቴ ክፍሎች በእኔ ሚዛን ክብደት
የሌላቸው ቀሊሎች፤ውሃ ማይቋጥሩ ገለቦች ናቸው፡፡
****
በነገራችን ላይ በአሁኑ ወቅት የእናት እና የአባቴ ልጅ ብቻ
ሳልሆን የትዬ ከበቡሽ ልጅም ሆኜያለው፤የበለጡ ታናሽ
ወንድም አድርገው ተቀብለውኛል፡፡ከልጆቻቸው እኩል
ወደውኛል፡፡ሳመሽ ሁለት እናቶች ናቸው ሚጨነቁልኝ፤ሳጠፋ
ሁለት እናቶች ናቸው ሚገስፁኝ፤ሲያመኝ ሁለት እናቶች ናቸው
ሚዳብሱኝ፡፡ሲበርደኝ ሁለት እናቶች ናቸው በትንፋሻቸው
የሚያሞቁኝ፡፡ይሄ ሁኔታ የሆነ ደስ የሚል ምቾት ሰጥቶኛል፡፡
በተለይ በለጡን በፈለኩ ጊዜ እንደፈለኩ ለማግኘት ትልቅ
ነፃነት ፈጥሮልኛል፡፡
የእኔ መኖሪያ ክፍል የበለጡም የጥናት ክፍል ከሆነችም
ወራት ተቆጥረዋል፡፡ እህት እና ወንድሞቾ እየተንጫጩ
ስለሚረብሿት(ይህ ከፊል ሰበብ ነው)እስከምሽቱ አምስት እና
ስድስት ሰዓት አልጋዬ ላይ ወጥታ ስሬ ቁጭ ብላ ታነባለች፡፡
እኔም ልብወለዱንም ፤ፍልስፋናውንም፤ሳይኮሎጂውንም ብቻ
የተገኘውን መጽሀፍ እያነበብኩ እግረ መንገዴን አማሻታለው፡፡
እኔ የማነባቸውን መፃሀፎች በብዛት በለጡ ነች እየተዋሰች
የምታመጣልኝ፡፡ እኔም አልፎ አልፎ እገዛለው፡፡ታዲያ በለጡ
በሳምንት አራት እና አምስቱን ቀን እዛው እኔው ጋር ነው
የምትተኛው፡፡አንብባ አንብባ ሲደክማት‹‹ አንድ አስር ደቂቃ
አረፍ ልበል እና ትቀሰቅሰኛለህ›› ትለኛለች፡፡እንደማልቀሰቅ
ሳት ታውቃለች፡፡ግን ሁሌ እኔ ጋር መተኛት ስትፈልግ እንደዛ
ነው የምትለኝ:: እስክትተኛ እጠብቃታለው፡፡ ስለሚደክማት
በእንቅልፍ ለመዋጥ 5 ደቂቃ በቂዋ ነው፡፡ከዛ ቀስ ብዬ ልብስ
አለብስታለው እናም ከአስር እስከ ሃያ ደቂቃ አትኩሬ
በተመስጦ አያታለው፤በጥልቀት አስተውላታለው፤ስሬ እያለች
እራባታለው፤ እንዳልቀሰቅሳት ተጠንቅቄ ከጐኗ እተኛለው፡፡
አንዳንድ ቀን ደግሞ የእናቷ ትንፋሽ ሲናፍቃት ከለሊቱ ስድስት
ሰዓት አካባቢ ግንባሬን ስማኝ ጥላኝ ትሄዳለች ፤ ከእናቷ ጋር
ልትተኛ፡፡የዛን ቀን ሌቱ ምቾት አልባና ህልሜም ቅዠት
የበዛበት ይሆናል፡፡ ያለፉትን ሁለት ወሮች ግን እረፍት ላይ
ስለሆነች እና ጥናትም ስለሌለባት መጨናነቁንም አምሽቶ
መተኛቱንም ቀንሳለች፡፡
በነገራችን ላይ እኔ በተከራየውት ክፍል እና በእነ በነበለጡ
ቤት መካከል ባለው የጋራ ግድግዳ የነበረው የታሸገ የቆርቆሮ
በር እሽጉ ተነስቶ መተላለፊያ ሆኖል፡፡ ተቀላቅለናል፡፡
በእንደዚህ አይነት ጥልቀት ከበለጡም ሆነ ከቤተሰቦቾ
እየተዋሀድኩ መምጣቴ ወደ ፊት ምን ዓይነት መዓት
እንደሚያመጣብኝ እግዜር ይወቀው፡፡
ሌላው ጉዳይ በሰፈር ውስጥ ለውጤ አነጋጋሪ እንደሆነ
ቀጥሏል፡፡
2.4K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 06:19:42 ‍ ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
 ከሦስት ወር ቡኃላ
ዛሬ ቀኔ ነው፤18 ዓመት ሞልቶኛል ብዬ ከቀበሌ ባወጣውት
መታወቂያ፤በጋሼ በቀለ የገንዘብ እርዳታ ና በእኔ ከፍተኛ
ጥረት የ3ኛ ደረጃ የመንጃ ፍቃዴ በእጄ ማስገባት ችያለው፡፡
ይህንን ደስታዬን ከእናት እና ከአባቴ ጋር ለማክበር ወሰንኩ፡፡
ወዲያው ግን ሀሳቤን ቀየርኩ ፡፡ከበለጡ ጋር ነው ማክበር
ያለብኝ፡፡እሷ መቅደም አለባት፡፡
*
ከሁሉም በፊት ግን ወደ ጋሽ በቀለ ቤት በመሄድ ማመስገን
አለብኝ፡፡እቤታቸው ስደርስ ሳሎን ቁጭ ብለው መፅሀፍ
እያነበቡ ነው፡፡ስገባ በፍቅር ተቀበሉኝ፡፡መንጃ ፍቃዴን
ሰጠዋቸው፡፡ቀኝ እጄን በመያዝ ወደ ራሳቸው ጐተቱኝና
አገላብጠው ግንባሬን ሳሙኝ
‹‹ጐበዝ የእኔ ልጅ፡፡ገና ትልቅ ደረጃ ትደርሳለህ››በማለት
ስለወደፊቴ የሚታያቸውን ተነፈሱልኝ፡፡
‹‹ያው እግዜር ይስጥልኝ ለማለት ነው የመጣውት››
ኮስተር ብለው ‹‹ለምኑ….?››አሉ
‹‹እርሷ ገንዘቡን ባይከፍሉልኝ ከየት አመጣው ነበር?››
‹‹አንተ ደግሞ.... ይህቺ ምን አላት ?ብቻ ጐበዝ ሁን እንጂ
ገና ብዙ ነገር እንረዳዳለን፡፡በነገራችን ላይ ስፈልግህ ነበር
የመጣኸው››
‹‹ምነው…?በሰላም?››
‹‹ከሳምንት ብኃላ ወደ አሜሪካ ልሄድ ነው››
ደነገጥኩ‹‹እንዴት….?ምነው ? ››
‹‹አይ .....በሰላም ነው፡፡ልጆቼን አይቼ መምጣት ፈልጌ
ነው.፡፡››
‹‹ይቆያሉ?››
‹‹አንድ ዓመት ያህል ሳልቆይ አልቀርም››
እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ስራዬንም፤ታክሲዋንም፤ሀብታም
የመሆን ምኞቴንም አብረው ተሸክመው የሚሄድብኝ መስሎ
ነው የተሰማኝ፡፡ ‹‹አንድ ዓመት ሙሉ?››
‹‹አዎ ፡፡እንደምታውቀው ያመኛል፡፡ጤናዬን ለማስተካከል ጥሩ
ህክምና ማግኘት አለብኝ፡፡አሁን አንተን የፈለኩት አደራ
ልሰጥህ ነው››
‹‹የምን አደራ… ?የፈለጉትን ይዘዙኝ››
‹‹ይሄንን መኖሪያ ቤትም ሆነ ሸዋ በር አካባቢ የሚገኘውን
ሆቴሌን አከራይቼ ነው የምሄደው፡፡ ታዲያ የቤቶቹን ኪራይ
እንድትሰበስብልኝ አንተን ወክዬህ መሄድ ነው የፈለኩት፡፡››
መደነቅም ፤መገረምም፤መደንዘዝም አጋጠመኝ፡፡‹‹እንዴት... ?
እኔን?››
‹‹አዎ ለአንተ ውክልና እሰጥሀለው በየ3 ወሩ ኪራዬን
እየተቀበልክ ባንክ ደብተሬ ውስጥ ትከታልኛለህ››
‹‹ኸረ ይሄ ነገር ለትልቅ ሰው...ማለቴ ለዘመዶቾት አደራውን
ቢሰጡ ይሻላል፡፡››
‹‹የሚሻለኝን እኔ ነኝ የማውቀው፡፡በአሁኑ ጊዜ የእኔ የምለውና
ካንተ በላይ የማምነው ሰው የለኝም፡፡››
‹‹ካሉ እንግዲህ እሺ፡፡ግን ታክሲዋስ?››ዋናውን ጥያቄ
ጠየቅኳቸው፡፡የምኞቴን መንገድ…..፡፡
‹‹ታክሲዋን አንተ ያዛት፡፡ማለቴ አንተ ስራበት ፡፡እንዲያውም
እንዲህ አስቤያለው ልክ የዛሬ ዓመት ስመጣ ሌላ አዲስ
ታክሲ ገዝተህ ከጠበቅከኝ ይህቺኛዋን ለራስህ
ትወስዳታለህ፡፡.እሸልምሀለው፡፡››
ህልሜ በቅርብ እንደሚፈታ፤ሀብት ወደ እኔ እየተንደረደረ
እንደሆነ ተሰማኝ፡፡በሁሉም ነገር ተስማምተን ተሰናብቼያቸው
በራፋ ጋር ስደርስ ‹‹ልጄ ››ብለው ጠሩኝ፡፡
የመውጫውን በራፍ ለመክፈት የዘረጋውትን እጄን ባለበት
አንከርፍፌ‹‹አቤት››
‹‹ከዛሬ ጀምሮ ስምህ በላቸው አይደለም ‹ምንተስኖት
ብዬሀለው፡፡ምንም እንደማይሳንህ ስለማውቅ ነው ይሄን ሁሉ
ሀላፊነት የሰጠውህ ›› አሉኝ፡፡ድጋሜ አመስግኜያቸው
መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ወደ ሰፈር፡፡
*
ወደእናቴ ቤትም አልገባውም፡፡በለጡ ጋር ሄድኩና እናቷን
አስፈቅጄ ይዤት ወጣው፡፡ደስታዬን ከእሷ ጋር ላከብር፡፡ ሆቴል
ገብተን እንደተቀመጥን አስተናጋጅ መጣ፡፡‹‹ምን ልታዘዝ?››
‹‹አክሱማይት ወይን ከኮካ ጋር እና ደግሞ ሁለት እስፔሻል
ክትፎ››
‹‹እንዴ አንተ ልጅ..!!ዛሬ አብደኸል እንዴ?››
‹‹ምነው?››
‹‹የስንት ብር ምግብ እና መጠጥ እንዳዘዝክ አውቀኸል ?ነው
ወይስ እናትህ የምትሸጠው ሽሮ ና ጠላ መሰለህ?››
ደረቴን በኩራት ወደፊት ወጥሬ‹‹አትጨነቂ፤ዘና
በይ፡፡››አልኳት፡፡
‹‹እንዴት እንዴት ነው ዛሬ ..?እንዳልከውም ከአሁኑ ሀብታም
ሆንክ እንዴ?››
‹‹እንደዛው በይው፡፡በነገራችን ላይ 200 ብር ተቆራጭሽ
ከዚህ ወር ጀምሮ 400 ብር ሆኖልሻል፡፡››
ዓይኖቾ ፈጠጡ ‹‹ምን ተገኘ…?ደግሞ እኔ 200 ብሩ መች
አነሰኝ አልኩህ?››
‹‹አንቺ ስላልሺኝ ሳይሆን …ስለሚገባሽ ነው፡፡››
‹‹ምን እንዳገኘህ ለምን በግልፅ አትነግረኝም?››
የመንጃ ፍቃዴን ከኃላ ኪሴ አውጥቼ ሰጠዋት፡፡አነበበችው፡፡አ
ገላብጣ ጉንጬቼን ሳመችኝ፡፡ አስተናጋጁ ወይኑን አምጥቶ
አስጭሆ በመክፈት በእሷ ብርጭቆ ላይ ትንሽ ጠብ ካደረገ
ቡኃላ እንድትቀምሰው ሰጣት፡፡ቀመስ አድርጋ
አስቀመጠችለት፡፡የእኔንም የእሷንም ቀድቶልን ጥሎን ሄደ፡፡
ሴትን ስጋብዝ ሆነ ወይን ስጠጣ ዛሬ የመጀመሪያ ቀኔ ነው፡፡
እንደኮራችብኝ ከአንደበቷ በምታወጣቸው ቃላት ብቻ ሳይሆን
በፊቷ ፈገግታ እና በእጆቾ እንቅስቃሴ ጭምርም ልትገልጽልኝ
እየሞከረች
‹‹የእኔ ወንድም ጀግና እኮ ነህ!››አለችኝ፡፡ቀጠለችናም
‹‹አይዞህ በርታ በስድስት ወር ውስጥ ምርጥ ሹፌር
ትሆናለህ፡፡ ዓላማህም በቅርብ ይሳካል፡፡››
በእርካታ ዘና ብዬ‹‹ሆንኩ እኮ››አልኳት ፡፡
‹‹መንጃ ፍቃዱን አይደለም ያልኩት ስራውን ማለቴ መኪና
ይዞ መሾፈሩን››
‹‹ገብቶኛል.... ስራውንም አግኝቼያለው..ጋሼ ታክሲያችውን
ሰጥተውኛል››
‹‹እንድትነዳ?››
‹‹አይ ሙሉ በሙሉ ሰርቼ እንድጠቀምበት፡፡›› በማለት
ሁሉንም ነገር በዝርዝር አስረዳዋት፡፡በመገረም እና በደስታ
ነው ያዳመጠችኝ፡፡
‹‹..ደግሞ ሌላው...››
‹‹ሌላ ደግሞ ምን? ››
‹‹ጋሼ ‹ምንተስኖት› ብለው ስም አወጡልኝ››
‹‹ምንተስኖት...››
‹‹አዎ...ምንተስኖት››
‹‹እውነትም ምንተስኖት፤ይገልፅሀል፡፡በጣም ጣፍጭ ስም
ነው፡፡ ከዱርዬው ግን አይበልጥም››በማለት ለአዲሱ ስሜ
ያላትን አድናቆት ገለፀችልኝ፡፡እኔም ደስ አለኝ፡፡አሪፍ እራት
በአሪፍ መጠጥ እያወራረድን ስንጫወት አምሽተን ከሞቅታ
ባለፈ ከስካር ትንሽ ወረድ ባለ ስሜት ሆቴሉን ለቀን ወደ
ሰፈራችን አመራን፡፡
መንገድ ላይ ወደ ሥጋ ቤት ጐራ አልንና ሁለት ኪሎ ስጋ
ለየብቻ ገዛን፡፡ አንዱን ለበጡ ሰጥቼያት አንዱን ለራሴ ያዝኩ
፡፡ቀጥሎ ግሮሰሪ ገባውና አንድ ጠርሙስ የፈረንጅ አረቄ
ገዛው፡፡ በለጡን ከያዘችው ሥጋ ጋር ወደ ቤቷ ልኬ እኔ
ወደቤተሰቦቼ ቤት ጐራ አልኩ፡፡ሥጋውን ለእናቴ አረቄውን
ለአባቴ አስታቀፍኩ እና በቆምኩበት ሁሉንም ዜና በማጣፈጥ
ነገርኮቸው፡፡
እናቴ በእልልታ ሰፈሩን አናጋችው፡፡አባቴ ከተቀመጠበት
ሳይነቃነቅ እንባውን በደስታ ወደ መሬት አንጠባጠበ፡፡በቅርብ
እርቀት ያሉ ጐረቤቶቻችን የእልልታውን ምክንያት ለማጣራት
ተንጋግተው መጡ፡፡ የምስራቹ አጠር ባለ መልኩ በእናቴ
አማካኝነት ተነገራቸው፡፡ግማሹ ከልባቸው የተቀሩት ካንገት
በላይ አደነቁኝ፤መረቁኝ፡፡እቤታችን ደመቀ፡፡ ሥጋው
ተጠበሰ፤አረቄው ተቀዳ፤ሳቅ ጫወታ ደራ፤የቤቱ ንጉስ …
የሰፈሩ ምሳሌ ሆንኩ፡፡

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot ❥❥________⚘_______❥❥
2.6K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ