Get Mystery Box with random crypto!

💕 ፍቅርን በቃላት 💕

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrn_be_kalat — 💕 ፍቅርን በቃላት 💕
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrn_be_kalat — 💕 ፍቅርን በቃላት 💕
የሰርጥ አድራሻ: @fkrn_be_kalat
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.03K
የሰርጥ መግለጫ

💝 ፍቅርን በቃላት 💝
♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
💞የፍቅር ቃላት ሁሌም አሸናፊ ናቸው💞
For any promotion ➢ @Naolviva ✌
For spam 👇
@fkrn_be_kalat_bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-28 20:13:08 <<ጠይሙ ባሌ !>>

ክፍል.......4

(በእውነተኛ ታሪ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.
ባሌ የምግብ ጠረጴዛው ላይ የተቀመጠ ወረቀት ተመስጦ ያገላብጣል:: አይኖቼ ዋናው በር አጠገብ የተቀመጡት ሁለት ሻንጣዎች ላይ አረፉ...ብዙም አልተገረምኩም:: ላለፉት ሶስት አራት ወራት እኛ ካለንበት ከተማ ወደ 150 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚርቅ አገር ለስራ ቢያንስ በየሁለት ሳምንቱ እየተላከ መስራት ጀምሯል:: ከእኛ ጋር የሚያሳልፈው አንድም የእረፍት ቀን ስለሌለው መጀመሪያ ላይ በጣም እነጫነጭ ነበር...ሁዋላ ግን ጭራሽ ለመድኩትና እንደውም ከኩርፊያውም: ከንትርኩም: ከመገፋፋቱም እንደእረፍት እየወሰድኩት ደስ ደስ ይለኝ ጀምሯል::

ዛሬ ግን እንደወትሮው ልብሱን እንዳዘጋጅለትም ሆነ የሚወደውን የሀበሻ ምግብ እንድሰንቅለት ቀድሞ አልነገረኝም:: ደግሞስ ሁለት ትልልቅ ሻንጣ ምን ያደርግለታል?  "ቁጭ በያ!" አለ ፊት ለፊቱ ያለውን ወንበር እያመለከተኝ::
"ምንድነው ሻንጣው?" አልኩ ፊቴን ከስክሼ...ከቆምኩበት ሳልነቃነቅ:: አደን ላይ እንደተገናኙ አውሬዎች ተፋጠጥን:: "መጀመሪያ ቁጭ በይና በጥሞና እንነጋገር" አለኝ በመለማመጥ ድምፅ:: ውስጤን የማላውቀው ስሜት ሲነዝረኝ ተሰማኝ...ቁጣ አልለው ንዴት: ሽብር አልለው ፍርሀት...ብቻ ድብልቅልቅ ያለ::

ወንበሩን ሳብኩና ጫፉ ላይ ተንጠላጥዬ ተቀመጥኩ...በድንገት ለመሮጥ የተዘጋጀሁ ይመስል::  "እናት..." አለ ንግግሩን ሲጀምር:: እናት ብሎ ከጠራኝ ኧረ በሙሉ ስሜ እንኩዋን ከጠራኝ ወራት አልፈዋል...ሽብር አናወዘኝ:: "እናት...ጥሩ ሰው ነሽ: ደግ ልብ አለሽ:: ለልጆችሽ ሙዋች ነሽ...በራሴው ልጆች አንቺን የመሰለ እናት ስላደላቸው እ-ቀ-ና-ባ-ቸ-ዋ-ለ-ሁ" አለና ጉሮሮውን ሲቃ ሲተናነቀው የኔ እንባ ቀድሞ መዥጎድጎድ ጀመረ...ገባኝ: በጣም ገባኝ...አንድም ቃል አልተነፈስኩም::
ንግግሩን ቀጠለ:: "እኔ ላንቺ የምገባ ሰው አይደለሁም..." አቁዋረጥኩት "ምን ማለት ነው?" አንባረቅሁበት "ዲስኩርህን አቁምና በቀጥታ ለማለት የፈለከውን ተ-ና-ገ-ር" እንባ ተናነቀኝ:: "ይኸውልሽ...ዋነኛው ችግርሽ መደማመጥ የሚባል ነገር አታውቂም..." አለና በብሽቀት ሲያገላብጥ የነበረውን ወረቀት ወደኔ አሽቀነጠረው::

የመጀመሪያው ገፅ ላይ የተፃፉት የህግ ቃላት ብዙም አልገቡኝም:: የሱ ስም ከላይ: የኔ ስም ከታች...እንደካሳሽና ተከሳሽ አይነት ነገር...ከስሩ ደግሞ የልጆቻችን ስም እና የተወለዱበት ቀን...ከዛ ደግሞ የቤታችን አድራሻ...ቀጥሎ የመኪኖቻችን አይነትና የተሰሩበት አመተምህረት...ባንካችን ውስጥ ያለው ገንዘብ መጠን...ያለብን እዳ...ግራ በተጋባ መንፈስ ባሌን ቀና ብዬ አየሁት: እሱም አፍጥጦ እየጠበቀኝ ነበርና አይን ለአይን ተገጣጠምን:: "ምንድነው ይሄ?" ብዬ አንሾካሸኩ...ጥያቄው ለሱ ይሁን ለኔ አላውቅም...እሱም አልመለሰልኝም:: 

ሁለተኛው ገፅ 1ኛ 2ኛ እያለ ንብረት ያከፋፍል ጀመር:: ሰበብ የማይሻው እንባዬ እንደጉድ እየተዥጎደጎደ ደረቴን አራሰው...አይኖቼን እየጨመቅሁ ማንበቤን ቀጠልኩ...ይህ የልጆቼ ህይወት ወሳኝ ጉዳይ ነው: የራሴም ህይወት ጉዳይ ነው: የማልቀሻና የመቅለስለሻ ጊዜ አይደለም...እንባዬ ግን አሻፈረኝ አለ::
ማንበቤን አላቁዋረጥኩም....ቀናም ብዬ ወደባሌ አላየሁም...ቤቱ: መኪኖቹ: የሱ ደሞዝ: የባንክ ገንዘባችን እንደቅርጫ ስጋ ተሸንሽኖዋል...ያልጣመኝ ነገር አለ: ግን አሁን ዋናው ጉዳዬ እሱ አይደለም...ማነብነቤን ቀጠልኩ...ሶስተኛ: አራተኛ: አምስተኛ ገፅ...የልጆቼን ስም ሳይ ልቤ ቀጥ አለች...አዎን ሁሉም ገደል ይግባ: አባታቸውን ጨምሮ ...ግን...ግን...ከልጆቼ ከአንዳቸውም ከተነጠልኩ ሁሉም ነገር አለቀ...እሱም እኔም እናውቀዋለን::

የቻልኩትን ያህል አየር ስቤ ማንበቤን ቀጠልኩ...ሲተናነቀኝ የነበረውን ሲቃ በጭራሽ ልቆጣጠረው አልቻልኩም...ሰውነቴን እያንዘፈዘፈ ፈነቀለኝ...አዎን...መርዶ የተረዳሁ ይመስል ጮኬ ማልቀስ ጀመርኩ...ለነገሩ ይህ ሁሉ ዱብ እዳ መርዶም አይደል::

ይቀጥላል .....



የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥
707 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 07:46:08 << ጠይሙ ባሌ! >>

ክፍል.......3

(በእውነተኛ ታሪ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.
እቤት እንደገባን ወዲያውኑ ልብሴን ቀያይሬ ወደተለመደው ስራዬ ገባሁ:: ዛሬስ እራትም አያስፈልገን...ልጆቼንም ቅድም ወደግብዣ ስንሄድ ነው ያጣጠብኩዋቸው...ግን ደግሞ ማታ ማታ ገንዳውን እየሞላሁ መንቦራጨቅ አስለምጃቸዋለሁ::
ለኔ ይሁን ለነሱ የሚዘፈዘፉት ግን አላውቅም...ብቻ ጢም ባለው አረፋ ውስጥ እየተንቦራጨቁ ክትክት ብለው ሲስቁ ነፍሴን ይመግቡዋታል...ተስፋ ይሰጡኛል...ያጠነክሩኛል:: "እ-ፎ-ይ!" አልኩኝ በረጅሙ እየተነፈስኩ...ዛሬ እንቅልፌን ጠግቤ ልተኛ ነው::

ግን ደግሞ ልቤ ክብድ ነገር...እንደው ቅር ቅር ነገር ብሎታል...ከባሌ ጋር መኩዋረፌን ስላወኩት ይሆን?  የልጆቼን ልብስ አወላልቄ ወደመታጠቢያ ቤት በሰልፍ ስንገባ አባታቸው ከሁዋላዬ ሲናገር ሰማሁት:: "ልጆቹን ካስተኛሽ በሁዋላ ላነጋግርሽ እፈልጋለሁ" ኮስተር ያለ ድምፅ:: መልስ አልሰጠሁትም..."ደግሞ ምንድነው የሚያነጋግረኝ?" አልኩ በልቤ:: ሽብሬን የሚያባርረው ይመስል የገንዳውን አሸንዳ በሰፊው ከፈትኩትና ሳሙና ሞጀርኩበት...አቤት የልጆቼ ደስታ! ጊዜ አላጠፉም...ውስጡ ገብተው እንደውሀ እናት መርመስመስ ጀመሩ::

"ማሚ...ማሚ...ማሚ...ኪኪኪኪ" ከዛ ደግሞ ቡርጭቅ...ወዲያው "ይሄኛው አረፋ የኔ ነው" ብሎ መጣላት...መካሰስ...መልሶ በሳቅ መንከትከት:: ይህ ትርኢት ሱሴ ከሆነ ከራርሞዋል...ከሱስም መደበቂያዬ ልበለው መሰል:: ብቸኝነቴን ፈፅሞ ያስረሳኛል...አዎ ከሰው ጋር እየኖርኩ የሚወርሰኝን ብቸኝነት::  ዛሬ ግን ልቤ እየተከፈለ አስቸገረኝ:: ምን ይሆን ደግሞ ሊያነጋግረኝ የፈለገው? ሀሳብ መፍተሌን አላቆምኩም:: ቤቱ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሲል ኮቴው አልፎ አልፎ ይሰማኛል...ምን እያደረገ ይሆን በዚህ በምሽት? ልጆቼን እያጣደፍኩ አለቀለቅሁዋቸው...እንደተለመደው እያንገራገሩ በአሳር ከገንዳው ወጡልኝና በፎጣ ጠቅልያቸው ወደመኝታ ቤታቸው ተግተለተልን::

እየተሽቀዳደሙ በየአልጋቸው ላይ ወተው መዝለል ጀመሩ...ለብሰው የነበሩት ፎጣም በየቦታው ወደቀ:: አይ ልጅነት...ፈገግ አልኩ:: ግን ደግሞ ዛሬ ለዚህ ፍልስፍናዬ ጊዜ የለኝም...አዎን የተጣደፍኩበት ጉዳይ አለብኝ:: የሌሊት ልብሳቸውን አለባብሼ አልጋቸው ውስጥ አስገባሁዋቸውና ወደበሩ ሳመራ እንደወትሮው አብሬያቸው ስላልቆየሁ ተቃውሞ አሰሙ:: ቆጣ ብዬ እንዳይነሱ አስጠነቀኩና እንዳይፈሩ በሩን ገርበብ አድርጌላቸው ወደሳሎን አመራሁ::

ይቀጥላል .....


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥
820 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:52:04 ጠይሙ ባሌ !

ክፍል.......2

(በእውነተኛ ታሪ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.
ከጋባዦቻችን ጋር የሞቀ ሰላምት ተለዋውጠን ልጆቻችንን ከታሰሩበት መቀመጫቸው ፈታንና ወደቤት ዘለቅን :: ከባሌ የሚያናድደኝ ዋንኛው ፀባዩ ሰው ፊት ሲሆን የሚፈጥረው ሸብ እረብ ነው ...ፍፁም የሆነ ባልና አባት ሆኖ ቁጭ ይላል :: ሌሎች ታድለሽ ሲሉኝ የሆዴን በሆዴ ይዤ ጥርሴ ኢኝ ይላል ...ድንቄም መታደል ::
ከሚስትነት ወርጄ ከሰውነትም ቀልዬ እንደቤት እቃ መቆጠር ከጀመርኩ ከራርሜያለሁ :: ምርር ሲለኝ "ለልጆቼ ስል " የሚል ሰበብ ለራሴ ሰጥቼ እፅናናለሁ ...ግን እስከመቼ ይሆን እንዲህ እንደ ግዑዝ ተቆጥሬ የምኖረው ? ስሜት አለኝ : መወደድ ... መታቀፍ ... መሳም ... መከበር ...የፍቅር ጨዋታ : አይዞሽ መባልን ...ደከመሽ እረፊ መባልንም እፈልጋለሁ ::
ግን ይህን የጎደለ ቀዳዳ በምን በማን ልሙላው ?  እንዳልኩት ወደ ቤት ስንገባ አባትና ባል ተብየው ፈጠን ብሎ የልጆቹን ጃኬቶች አወለቀና በስርአት ሰቀላቸው ::
"ወይ ድራማ " አልኩ በሆዴ :: አሁን በህይወቱ ኢምንት ለውጥ ለማያመጡ ሰዎች ይህ ሁሉ ትርኢት ለምን አስፈለገ ? ወደሳሎን ስንገባ ሁለት ፈረንጅ ባልና ሚስት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ትልቅ ሶፋ ላይ ተደርድረዋል :: "ሄይይይይ " አለ የኔው ጉድ በደስታ እየተፍለቀለቀ :: ሻነን ከሁዋላዬ "ሄንሪም የስራ ጉዋደኛቸው ነው " እለች ጀርባዬን እየነካች "እስዋም ባለቤቱ ነች ...ተዋወቁ "::
ሁለቱም ብድግ ብለው በፈገግታ ሰላምታ ተለዋወጥና እኔም ልጆቼን ይዤ ከፊት ለፊታቸው ያለው መሀከለኛ ሶፋ ላይ ተቀመጥኩ :: ባሌ እንዲቀመጥ ጠጋ ብልለትም እንዳላየኝ ሆኖ ደረቅ ወንበር ላይ ፈንጠር ብሎ ተኮፈሰ ::  አፍጥጬ አየሁት ...ኮፍያውንና ጃኬቱን ሳያወልቅ ተከምሮዋል ...አይቼ አልጠግበው እንዳልነበር ዛሬ አፈርኩበት ::
በአማርኛ "ኧረ ኮፍያህን እንኩዋን አውልቅ " ብዬ አንሾካሾኩ :: ለአንድ ሰከንድ ያህል አፈጠጠብኝና እንዳልሰማኝ ሆኖ ጨዋታውን ቀጠለ ::

ይህ ሰው ማነው ? እውነት ይህን ሰው ነው ወድጄ : ከንፌ : አብጄ ያገባሁት ? በቃ ትዳር ማለት ይኸው ነው ...የቁም ገሀነም ? ወዲያው ደግሞ አጠገቤ ሶፋው ላይ የሚተራመሱት ልጆቼ ላይ አይኔ አረፈና ላሰብኩት ተፀፀትኩ ::  ጨዋታው ደራ : ምግቡ ቀረበ : መጠጥ ተቀዳ : የሁላችንም ልጆች እየተሩዋሩዋጡ ቤቱን አደመቁት :: ሁለቱም ጥንዶች በየሰበባ ሰበቡ ሲጎሻሸሙ : ሲጎነታተሉ : ሲተቃቀፉና ሲሳሳሙ እያየሁ ቀናሁባቸው :: በዚህ ሁሉ መሀል ጠይሙ ባሌ ከነጮቹ መሀል ተደባልቆ አንዴም ወደኔ አልተመለከተም : እንዴም አላናገረኝም : አይኖቻችን በድንገት ከተገጣጠሙ እንኩዋን የሱ የኔዎቹን በፍጥነት ሲሸሹ አየሁዋቸው ::

"የዛሬው የባሰ ነው " አልኩ በልቤ :: ከላይማ በውሸት ፈገግታ እየተፍለቀለኩ ሰዉን መምሰል ተክኜበታለሁ ::  ልጆቼ ብዙም አላስቸገሩምና ጥሩ ጊዜ አሳለፍን ...ከኔ አዲሱን የባሌን ፀባይ ከማፍተልተል በስተቀር :: አመሻሹ ላይ ጋባዦቻችንን አመስግነን እንግዶቹን ተሰናብተን ወደቤታችን አመራን :: ያው የተለመደው ፀጥታ መኪናችንን ወረሰው ...አቤት ድሮ ለማውሪያ ጊዜ ያላጠረንን ያህል ...የዛሬን አያድርገውና :: ቀስ ብዬ ወደባሌ ተመለከትኩ ::
መንገዱ ላይ አይኑን አቡዞ በሀሳብ የነጎደ ይመስላል :: የት ይሆን ያለው ? ምን ይሆን የሚያስበው ? "ቆንጆ ጊዜ አሳለፍን አይደል ?" አልኩት በድንገት የሄደበትን አለም ለማደፍረስ :: "አዎ " አጭር መልስ :: እኔ ግን ቀጠልኩ "ፈረንጆች ግን ደስ ሲሉ ...ፍቅራቸው አይደብቁም " ወዴት እንደምሄድ የገባው ባሌ "ሰው ፊት መላላስና መተቃቀፍ የኛ ባህል አይደለም " ቀጭ ያለች መልስ ወረወረልኝ ::

"ምነው ድሮ ታቅፈኝ ትስመኝ ነበር ?" ቁና ተነፈሰ ...አንዳችም አልመለሰም :: ብዙም ሳንቆይ ቤታችን ደረስን ::  በሩ አጠገብ መኪናውን አስተካክሎ አቆመና ...ልጆቹን ሳወርድ እንዳይከብደኝ መሆኑ ነው ...ዘሎ ወርዶ የቤቱ በርጋ ሲደርስ "አግዘኝ እንጂ " ብዬ አንባረቅሁበት :: "ምን አስጮኸሽ ...በሩን ልከፍት ነበር " አለና በንዴት በሱ በኩል ያለውን በር ከፍቶ ትልቅዋን ልጄን አንጠለጠላት ::

እጅዋ ተገነጠለ ብላ ነፍሴ ተሳቀቀች :: በድንገት እንባዬ ገነፈለና ትንሹን ልጄን ከታሰረበት ወንበር ልፈታ ጎንበስ ስል ድንቡሼ እግሮቹ ላይ ተንጠባጠበ :: እዛው እንዳጎነበስኩ "አምላኬ ሆይ አለህ ?" ብዬ አንሾካሾኩ :: አዎን ...ለሁለት ሳምንት የሚሆን ኩርፊያዬን መሰነቄ ልቤ ተረድቶታል :: እንዴታ ...እሱማ ባህላችን አይደል ! ጉዴን አላወቅኩ ... 

ይቀጥላል ...........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥
829 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:37:11 ጠይሙ ባሌ

ክፍል.......1

(በእውነተኛ ታሪ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
በተቻለኝ መጠን በዛ በማድረግ ለማቅረብ ሞክሪያለሁ መልካም ንባብ
.
.
ዛሬ የምሳ ግብዣ ነበረብን :: እንደው ከሰው ጋር ለመኖር ተብሎ የግድ ሆኖ ነው እንጂ ልጆቼን ከወለድኩ በኋላ ግብዣ የሚባል ነገር ጠልቻለሁ :: ከቤት ለመውጣት ያለው ትርምስ ...ልጆቼን አጥቦ : የክት ልብሳቸውን አልብሶ : ፀጉራቸውን ሰርቶ : ተይዞ የሚኬደውን ምግባቸውን ሆነ መጠጣቸውን እንዲሁም ተቀያሪ ልብስ በትልቅ ቦርሳ አጭቆ ...ሁህ ...ግብዣው ቦታ ከተደረሰ በሁዋላ ደግሞ ልጆቼ እቃ እንዳያጠፉ መከታተሉ : አንድ ነገር ሲደፉ መሸማቀቁና ማጽዳቱ : በር በተከፈተ ቁጥር ሾልከው ይወጡብኛል ብሎ መሳቀቁ ...ገና ሳስበው ብቻ ይደክመኛል :: 

ከዛ ደግሞ የራስ ዝግጅት አለ :: በስንት ጊዜ አንዴ ቢወጣ እንደአቅሚቲ መሽቀርቀር አይቀር :: ችግሩ ግን ለረጅም ጊዜ ተለብሰው የማያውቁት የክት ልብሶች ከደረት በታች አልወርድም : ከዳሌ በላይ አልወጣም ብለው ሲያሳፍሩ ነው :: አንዱ ይለካል ...አንዱ ይጠለቃል ...ሌላው ይሽቀነጠራል ...አልጋው የሳልቫጅ መሸጫ ሱቅ እስከሚመስል በልብስ ይሸፈናል ::
በስንት ፍለጋ ቦርጭንና ዳሌን ሸፈን የሚያደርግ ልብስ ይገኝና ተጠልቆ ወደፀጉር ስራ ይሮጣል :: 
"ጨረስሽ ?" ጠይሙ ባሌ ተጣራ ...ከኮምፒውተሩ ፊት ለፊት እንደተጎለተ የልጆቹን መልበስ ሲያይ ::

እንጀቴ በንዴት ኩምትር ..."ምናለ ብታግዘኝ ?" ሁልቀን የሚሰማው ብሶቴ ስለሆነ ቡዙም ጉዳይ አላለኝም :: "ስራ ይዤ ነበር ...በይ አንቺ እስክትጨርሺ ልጆቹን መኪና ውስጥ ላስገባ " ...በቃ የሱ ትልቅ ስራ እሱ ነው ...ይሁና !  ካውያም ሆነ ማለስለሻ ቅባት ነክቶት የማያውቀው ፀጉሬ ዛሬ በወጉ ላስይዝህ ብለው እሱም ግራ ገባው :: ተሰባብሮ ...ተንጨፍርሮ ...ኤዲያ !

"ጲፕ ...ጲፕፕ ...ጲፕፕፕፕፕፕ " የመኪናችን ጡሩንባ ሰፈሩን አናወጠው :: "ጀመረው ደግሞ " አልኩ የራሴኑ ፀጉር በንዴት እየነጨሁ ...እንደነገሩ ወደኋላ ለምጥጬ አስያዝኩትና እየተጣደፍኩ ያንን ትልቅ ቦርሳ አንግቤ ወደመኪናው ሮጥኩ :: 
"ዘገየን እኮ !" አለኝ ቆጣ ብሎ ...ገና በቅጡ እንኩዋን መኪና ውስጥ ገብቼ ሳልቀመጥ :: "እንደሱ ካልክ አታግዘኝም ነበር ?" የተሳለች መልስ ዱብ አደረኩለት :: ይህ የተለመደ እንኪያ ሰላንቲያችን ነው ...እንደውም አንዴ "በቃ አልሄድም " ብዬ የቀረንበት ግብዣ ሁሉ አለ :: እና እሱ ካልተወኝ የሚከተለውን ያውቃል :: በዝምታ መኪናውን አስነስቶ ጉዞዋችንን ጀመርን :: 
ከትልቁ ቦርሳ ውስጥ ኩልና የከንፈር ቀለሜን አውጥቼ ልኩዋኩዋል ከፊቴ የታጠፈውን የመኪና መስታወት ዘረጋሁት :: አይኖቼ ከሁዋላ የተኮለኮሉት ልጆቼ ላይ አረፉ ...አምረውና ደምቀው ተኮፍሰዋል :: ሁሉም ወደውጭ እያዩ ነበርና አላዩኝም ...አኔ ግን አየሁዋቸው : ወደድኩዋቸው : ቀለጥኩላቸው ...የልቤ አበቦች ...የነፍሴ ማረፊያዎች ...የህይወቴ ተስፋዎች :: "ግድ የለም ...እነሱ ብቻ በሰላም ይደጉልኝ " እራሴን አፀናናሁ :: 

ብዙም ሳንቆይ የተጋበዝንበት ቤት
ደረስን :: ሻነንና ስቲቭ ወጥተው ተቀበሉን :: የተዋወቅነው ወንዶቹ አብረው ስለሚሰሩ ቢሆንም : የበለጠ ያቀራረበን የሻነንና የኔ ጉዋደኝነት ነው :: አስተዋይ ወጣት ነች :: በተለይ ደግሞ ለኢትዮጵያ ባህል ያላት ክብርና ፍቅር የበለጠ እንድወዳት አደረገኝ ::
ቡና መቁላት : እንጀራ መጋገርና ዶሮ ወጥ መስራት ሳይቀር ...እቤቴ እየመጣች ተምራለች :: እኔ ደግሞ አገሬንና ባህሌን ስለወደደችልኝ አበባ የመሰለ ያበሻ ቀሚስ ሸልሜያታለሁ :: ከዛማ በቃ ...በሳምንት ሁለት ሶስቴ ልጆችዋን ይዛ ብቅ ትላለች ...አንዳንዴም ስራ ትረዳኛለች ::የስዋ ልጆች ስላደጉ ለኔ ታዝንልኛለች ...እኔስ እቤቴ ያጣሁት እሱን አይደል ! 

ይቀጥላል ...........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group

https://t.me/+Bpbeik0Cf-45ZWU0
╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥
859 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:34:17 https://t.me/+weJ5oZ70nFhlMWI0
JOIN AND SHARE
┄┄┄┄┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄┄
727 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:33:52 ፍቅርን በቃላት

የወደዱትን ማግኘት መታደል ነው፤
የወደደንን መውደድ ግን ብልህነት ነው፤
የኔ ካልሆነ ብሎ እራሡን መጉዳት ደግሞ በጣም ሞኝነት ነው።


┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄



አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@fkrn_be_kalat
ፍቅርን በቃላት
........... ••● ●•........ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
724 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:00:19 ፍቅርን በቃላት

​​ ለሚወዱት ሰው ፍቅርን መግለፅ መሸነፍ አይደለም
ማፍቀርም ሆነ መፈቀር ፀጋ ነው።ስላፈቀርሽው
አትዘኚ ያዘዘሽ ልብሽ እንጂ ሰው አይደለም
ለምትወዱት ሰው ፍቅራቹን ለመንገር
ምንም አይነት አጋጣሚዎችን ማባከን
የለባቹም።ምክኒያቱም ነገ የረፈደ ጊዜ ሊሆን ይችላልና.....



° ጠይሙ ባሌ° የተሰኘ አዲስ ትረካ በቅርቡ እንጀምራለን።


┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄



አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@fkrn_be_kalat
ፍቅርን በቃላት
........... ••● ●•........ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
956 viewsከማን ገጥመሽ ይሆን ✧ŊąøŁą ✧, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:39:39 ፍቅርን በቃላት

ሴት ልጅ ባንተ ምክኒያት ፈገግ ካለች ትወድሀለች...ባንተ ምክኒያት ግን ካለቀሰች እመነኝ ታፈቅርሀለች


┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@fkrn_be_kalat
ፍቅርን በቃላት
┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
848 viewsከማን ገጥመሽ ይሆን ✧ŊąøŁą ✧, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:31:33 ፍቅርን በቃላት

​ ፍቅር ለሴት ልጅ ሙሉ የህይወት ታሪኳ ሲሆን፤ ለወንዱ ግን የህይወቱ አንድ ትእይንት ነው::

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄



አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@fkrn_be_kalat
ፍቅርን በቃላት
┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
822 viewsከማን ገጥመሽ ይሆን ✧ŊąøŁą ✧, 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:27:38 ፍቅርን በቃላት

​ካንቺ በፊት እኔን ይውሰደኝ እንዳልል በኔ ሞት እንድትሰቃይ አልሻም

አንቺን ከኔ ቀድሞ ይውሰድሽ እንዳልልም ፈጣሪን ማማረርና በሞትሽ በቁሜ እየሞትኩ መኖርን አልፈልግም

ግን አንድ ነገር እመኛለሁ
በሞትኩባት ቅፅበት ከጎንሽ መሆንን እሻለሁ


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄



አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@fkrn_be_kalat
ፍቅርን በቃላት

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
795 viewsከማን ገጥመሽ ይሆን ✧ŊąøŁą ✧, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ