Get Mystery Box with random crypto!

💕 ፍቅርን በቃላት 💕

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrn_be_kalat — 💕 ፍቅርን በቃላት 💕 ፍ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrn_be_kalat — 💕 ፍቅርን በቃላት 💕
የሰርጥ አድራሻ: @fkrn_be_kalat
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.03K
የሰርጥ መግለጫ

💝 ፍቅርን በቃላት 💝
♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
💞የፍቅር ቃላት ሁሌም አሸናፊ ናቸው💞
For any promotion ➢ @Naolviva ✌
For spam 👇
@fkrn_be_kalat_bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-04-18 22:54:58 ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
በለጡ የከቤን የእንቢታ መልስ ከሰማች ቡኃላ የጠለቀ ሀዘን
ውስጥ ተዘፈቀች፡፡ሳቅ እና ጫወታ በማቆም እኔ ክፍል
ውስጥ መሽጋ ከቤተሰቡ ራሷን ለየች፡፡በዚህ የተነሳ እኔም
ጥልቅ እና አስፈሪ ጭንቀት ውስጥ ገባው፡፡ከቤን ደጋግሜ
ብለምናትም አሻፈረኝ አለች፡፡በዛ ላይ ጋሽ በቀለ ህመማቸው
ፀንቶባቸው በነፍስ እየተጠበቁ ነው፡፡ በጭንቅ ላይ ጭንቅ
ተደራረበብኝ ፡፡ኩየራ ልሄድ ከቤት ስወጣ ቡሩክቲ ከኃላ
ተከትላ አስቆመቺኝና፡፡
‹‹ውለታ ልውልልህ ፈልጌ ነበር››አለቺኝ እየተምነቀነቀች፡፡
‹‹የምን ውለታ?››ኮስተር እንዳልኩ
‹‹ከዚህ ጭንቀት ብገላግልህ ምን ታደርግልኛለህ?››
‹‹ከየትኛው ጭንቀት?››
‹‹በለጡ ከምትነፈርቅበት ነዋ፡፡እሷ በአይኖቾ ስታለቅስ አንተ
ደግሞ በልብህ እያነባህ ነው፡፡ ደስታችሁን ብመልስላችሁ
እንደፅድቅ ይቆጠርልኛል ብዬ አሰብኩ፡፡››
‹‹የሆንሽ ነገረኛ እና ጉረኛ ነገር ነሽ፡፡ለመሆኑ እንዴት አድርገሽ
ነው ያልሽውን የምትፈፅሚው?››
‹‹ከቤን እሺ እንድትል በማድረግ ነዋ፡፡››
‹‹አታሳኪውም እንጂ ሀሳብሽ ጥሩ ነበር፡፡››
‹‹ካሳካው ምን ታደርግልኛለህ?››
‹‹የፈለግሽውን››
‹‹ሀብል ትገዛልኛለህ?››
‹‹ሀብል...!!!?››
‹‹ምነው ….?ከዚህ ሁሉ ጭንቅ ገላግዬችሁ ሀብል
ያንስብኛል?››
‹‹እሺ ይሁንልሽ እገዛልሻለው››
‹‹እንዲያውም ቅድሚያ ግዛልኝ››
‹‹ትቀልጂያለሽ››
‹‹አልቀለድኩም፡፡ያልኩህን ማድረግ ካልቻልኩ መልሰህ
ትወስደዋለህ፡፡››
ሞባይል ስልኬን አወጣውና አንድ ወርቅ ቤት ያለው ጓደኛዬ
ጋር ደወልኩ፡፡ሠላምታ ከተለዋወጥኩ ቡኃላ ‹‹ብሩክቲ
የምትባል ልጅ አንተ ጋር እልካለው ..የፈለገችውን ሀብል
መርጣ ትውሰድ ፡፡ከወደደችው ነገ ጐራ ብዬ ሂሳቡን
እከፍልሀለው፡፡.ካልሆነም ሀብሉ ይመለሳል፡፡›› አልኩት
‹‹ላካት ››አለኝ፡፡አድራሻውን ነገርኮት፡፡‹‹ማታ ስመለስ ከቤ
ሀሳቧን ቀይራ ካልጠበቀችኝ ሀብሉን አውልቀሽ እጄ ላይ
ታስቀምጪያለሽ፡፡ደግሞም በዛ ብቻ አለቅሽም ግንባርሽን ነው
ምበረቅስልሽ››አልኳት እና በቆመችበት ጥያት መንገዴን
ቀጠልኩ፡፡
እሷም እየተመናቀረች ‹‹ይመቸኛል››አለችኝና ወደ ቤት
ተመለሰች::

ሆቴል ደርሼ ስራውን ከየው ቡኃላ በቀጥታ ወደ ኩየራ
አመራው፡፡ሆስፒታል ጋሽ በቀለን ለመጠየቅ፡፡ጋሼ የመጨረሻ
ደቂቃ ላይ እንደተቃረቡ ሁኔታው ያስታውቃል፡፡ ውጭ ሀገር
ላሉ ልጆቻቸው ተደውሎላቸው ሁለቱ ነገ ሀገር ውስጥ
እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡ፈጽሞ አይቼያቸው የማላውቃቸው
ብዙ ዘመዶቻቸው የተኙበትን ክፍል እና የሆስፒታሉን ኮሪደር
አጨናንቀውታል፡፡
ስምንት ሰዓት አካባቢ በለጡ ደወለች፡፡ ከግርግሩ መካከል
ገለል አልኩና ስልኩን አነሳውት ‹‹ደግሞ ምን ልትለኝ
ይሆን ?››የሚል ስጋት እንደቀሰፈኝ፡፡
ፍንጠዛ ባጨናነቀው የደስታ ድምፅ‹‹ደስ ብሎኛል››
‹‹ምን ተገኘ?››
‹‹ከቤ ተስማማች፡፡ሽማግሌዎቹ በሚቀጥለው እሁድ ይምጡ
አለች፡፡››
ደስታ ይሁን ሀዘን ለይቼ የማላውቀው ስሜት ወረረኝ
‹‹ምን..? እንዴት?››
‹‹እኔ እንጃ ..ብቻ ከብሩክቲ ጋር ሲንሾካሾኩ ከቆዩ ቡኃላ ነው
ጠርታ መስማማቷን የነገረችኝ››
‹‹ዋናው እሺ ማለቷ ነው፡፡ደስ ስላለሽ ደስ ብሎኛል፡፡››
‹‹ከእኔ ጋር አብረህ ስትጨነቅ ስለከረምክ በጣም አዝናለው፡፡
ሌላው ደግሞ ብሩክቲም ወደ አረብ ሀገር የመሄድ ሀሳቧን
ሰርዛዋለች፡፡››
‹‹ምን ተገኘ አለች?››
‹‹ለእኔም ምስጢር ነው፡፡... አሁን ነው የሰማውት፡፡››
‹‹አይ ሁሉም ነገር እንዲህ መስመር መያዙ ደስ ይላል፡፡››
‹‹አትመጣም እንዴ..?ትቆያለህ?››
‹‹ሳልቆይ አልቀርም፡፡ ኩየራ ነው ያለውት፡፡ጋሼ በጣም
ብሶባቸዋል፡፡ሁኔታውን አይቼ እደውልልሻለው፡፡››
‹‹ግን ምሳ በላህ?››
‹‹ትዝ አላለኝም ነበር… ቆይ አሁን ወጥቼ እበላለው፡፡››
‹‹አሁኑኑ ወጣ ብለህ ብላ፤ትጐዳለህ.::የምታመሽ ከሆነ
ደግሞ ደውልልኝ ፤ልብስ ይዤልህ እመጣለው››
‹‹እሺ እደውልልሻለው ....ቸው››
‹‹ቸው››ስልኩ ተቋረጠ
ከፋኝ…በጣም ከፋኝ፡፡በቃ ምፅአት ሊታወጅ ቀኑ ደረሰ…
ሰማያት ደም ሊለብሱ..ምድር በነጎድጓድ ልትናጥ …የእኔ
በለጡ ልታገባ ነው፡፡ከቤ እሺ ካለች ሁሉ ነገር አከተመ ማለት
ነው፡፡እሺ ምን ሊውጠኝ ነው..?፡፡ለመሆኑ ይህቺ የተረገመች
ብሩክቲ የምትባል ልጅ ምን ብላ ነው ከቤን ማሰማን
የቻለችው..?፡፡ሁሉ ነገር ድብልቅልቅ አለብኝ፡፡እራሴን
ማረጋጋት ሳልችል ሌላ ልብ ሰንጣቂ ሀዘን ተከሰተ……..
****
አስር ሰዓት ተኩል የጋሽ በቀለ እስትንፋስ ተቋረጠች፡፡
በህይወቴ የምጠላው ሰው ሞቶብኝ ያውቃል(የበለጡ
አባት )ይሄንን ጉዳይ ለማንም ከአፌ አውጥቼ ተናግሬ
ባላውቅም በወቅቱ በጣም እጠላቸው ነበር፡፡በጣም
የምወደው እና በዚህ መጠን የምቀርበው ሰው ሲሞትብኝ
ግን ይሄ የመጀመሪያ ገጠመኜ ነው፡፡ ጋሽ በቀለ ማለት ለእኔ
ከአባቴ በላይ ናቸው፡፡እጅግ በጣም ነበር የምወዳቸው፡፡
ሬሳውን ከሆስፒታል ወጪ አድርገን ወደ መኖሪያ ቤታቸው
ይዘን ሄድን፡፡ ዘመድ አዝማዶቻቸው አንዱ ለአንዱ እየደወለ
ከያሉበት በመሰባሰብ ጊቢውን አጥለቀለቁት፤እኔም ለእናቴ
እና ለበለጡ ደውዬ የተፈጠረውን ነገርኮቸው፡፡ ከግማሽ ሰዓት
ቡኃላ እናቴ ፤አባቴ ፤በለጡ እና ከቤ ተከታትለው እያለቀሱ
ገቡ፡፡ እነሱን ሳይ እነደ አዲስ ሆድ ባሰኝ፤ እየጮኸኩ እና
እየተንሰቀሰቅኩ አለቀስኩ፡፡‹‹አባቴ... አባቴ››እያልኩ‹‹ደጉ
ሰው.... ደጉ ሰው››እያልኩ፡፡በእውነት ደግ አባቴ ነበሩ፡፡
በማግስቱ ሁለቱ ልጆቻቸው ደረሱ፡፡በሦስተኛው ቀን ተቀበሩ፡፡
ከልጆቻቸው እኩል ዕድሩ በደኮነው ድንኳን ሀዘን ተቀመጥኩ፡፡
ከልጆቹ በላይ ውስጤ በሀዘን ተኳማተረ ::
የጋሽ በቀለ የሀዘን ስርዓት ሳይጠናቀቅ እኔ ላይ ያነጣጠረ
ችግር ተከሰተ፡፡ የልጆቹ አጐት ነኝ ሚል አንድ ሀብታም
አዛውንት እኔ የምሰራበትን ሆቴል መግዛት እንደሚፈለግ
አዋጅ አስነገረ፡፡ልጆቹም ሀሳባቸው ተበታተነ፡፡መሸጥም
ፈለጉ.... እኔን ማፈናቀልም ከበዳቸው፡፡ ለሁሉም ኑዛዜው
ከተነበበ ቡኃላ መሆን ያለበትን አስበው እንደሚወስኑ
በመናገር ጉዳዩን በይደር አቆዩት፡፡እኔም ያወጣውትን ገንዘብ
እስክመልስ እና ሌላ የሚከራይ ሆቴል አፈላልጌ እስካገኝ
እንኳን ቢያንስ ለስድስት ወር እንዲታገሱኝ ጠየቅኳቸው፡፡
እንደሚያስቡበት ነገሩኝ፡፡
ሲጨንቀኝ ጋሽ በቄ በሞተ በ10ኛው ቀን … ከቀኑ 8 ሰዓት
አካባቢ አዳል ሞቲ ጋር ሄድኩ፡፡እቤቱ ነበረ ያገኘውት ፡፡
እንደተለመደው እዛችው ፍራሹ ላይ ቁጭ ብሎ አንድ አሮጌ
መጽሄት ያገላብጣል፡፡ የጋሽ ስብሀትን <ትኩሳት> መጽሀፍን
ከአሮጌ መጽሀፍ መሸጫ አግኝቼ ገዝቼለት ነበር የመጣውት፡፡
ስሰጠው ተቀበለና ርዕሱን ካነበበ ቡኃላ አንገቱን ጐንበስ ቀና
በማድረግ በምልክት አመሰግኖኝ ከጐኑ አስቀመጠው፡፡
አዳልሞቲ ምግብ ሳመጣለት፤ልብስ ሳመጣለት ምንም
ባመጣለት መልሱ ዝምታ ነው፡፡ የሚነበብ ነገር ሳመጣለት
ግን አንደበቱን ከፍቶ ቃላት አፍልቆ ባያመሰግነኝም ሁሌ
በግንባሩ ንቅንቅታ ስጦታዬ እንደተመቸው ከመግለፅ
አይሰንፍም፡፡
ለሃያ ደቂቃ በዝምታ ካሳለፍን ቡኃላ እንደተለመደው እኔ
መናገር እሱ ንባቡን ሳያቋርጥ የሚሰማ ሳይመስል ማደመጥ
ቀጠለ፡፡
‹‹መቼስ ያለወትሮዬ ፀጉሬን ተላጭቼ ጥቁር የሀዘን ኮፍያ
አድርጌ ስታየኝ ምን ሆነሀል ብለህ ማሰብህ አይቀርም፡
በጣም ነው የተጐዳውት፡፡በህይወቴ ወሳኝ የሆነው ሰው ነው
የሞተብኝ፡፡ ስለእሱ ብዙ ጊዜ ስላወራውህ ትዘነጋዋለህ ብዬ
አልገምትም፡ጋሽ በቀለ ነው፡፡ጋሼ እኔ በህይወቴ ሁለት
ቅዱሳንን አውቃለው አንተንና እሱን፡፡
5.2K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 13:31:35 ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
1999ዓ.ም
ባለ መኪናም ብቻ ሳልሆን ባለሆቴልም ሆኜያለው፡፡የጋሽ
በቀለን ሆቴል ተከራይተው እየሰሩበት የነበሩ ሰዎች ከስረናል
ብለው ስለለቀቁ ጋሼ ሌላ ተከራይ እንድፈልግላቸው
ሲያማክሩኝ ራሴው ልሰራበት እንደምፈልግ ስነግራቸው
ሳያንገራገሩ በሀሳቤ ስለተስማሙ ፍቃድ አውጥቼ የሆቴል
ስራ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ፡፡
የቅርቦቼ የምልቸው ሰዎች ሁሉ በወቅቱ ‹‹ይቅርብህ አንትም
ትከስራለህ ››ብለው መክረውኝ ነበር፡፡ ልሰማቸው ግን
አልፈለኩም፡፡ ለስራው ከፍተኛ ጉጉት አደረብኝ፡፡ ደፈርኩ፡፡
እራሴን ሰማውት፡፡ሦስት የዝግጅት ወር መደብኩ፡፡
በመጀመሪያ በጥሩ ደሞዝ በሆቴል ማናጅመንት የተመረቀ እና
ጥሩ የስራ ልምድ ያለው ስራ-አስኪያጅ ፈልጌ ቀጠርኩ፡፡
የተወሰነ ገንዘብ መድቤ የሆቴሉን ውስጥ እና ውጩን
አሳደስኩ፡፡ቀጥሎ አብሮ አደጐቼ ሆነው ስራ በማጣት
በየሰፈሩ ይንከራተቱ የነበሩ እና ለስራው ፍላጐት ያላቸውን
ስምንት ሴት እና አራት ወንድ ወጣቶችን ሰብስቤ በምግብ
ዝግጅት እና በመስተንግዶ ለ3 ወር እንዲሰለጥኑ ኮሌጅ
አስገባዋቸው፡፡
ከስራ-አስኪያጁ ጋር በመነጋገር በሦስት ወር ውስጥ
አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ ተጠናቆ ሆቴሉ በአዲስ መልክ ሥራ
ጀመረ፡፡ ወደ ኮሌጅ ያመሩት የሰፈሬ ልጆችም ስልጠናውን
አጠናቀው ከሌሎች ልምድ ካላቸው ጋር በመሰባጠር ወደ
ስራ ተሰማሩ፡፡ስራ በጀመርን በሳምንት ጊዜ ውስጥ እቤቱ
በከተማዋ ተመራጭ እና ተወዳጅ ሆነ ፡፡በተለይ በምሳ እና
በእራት ሰዓት መቀመጫ ሁሉ ያንሰን ጀመር፡፡ሚኒባሴን
ለልጅነት ጓደኛዬ ለዳዊት እንዲሰራበት ስለሰጠው የሆቴሉን
ስራ በቅርበት እየተቆጣተሩኩት ነው፡፡በእውነት በአጭር ጊዜ
ውስጥ ከጠበቅኩት በላይ ተሳካልኝ፡፡በዚህም ግማሹ ሰው
ሲያደንቀኝ እና ሲያበረታታኝ፤የተቀረው በሀሚት ይሰነጣጥቀኝ
ጀመር፡፡በተለይ የሰፈሬ ሰዎች፡፡
‹‹እድሜ ለቆሪጥ ይበል…ልጆቻችንን ሁሉ ሰብስቦ ሳሀን
አጣቢ አደረጋቸው››
‹‹እናቱ ባሰራችለት መተት የሰፈሩን ሁሉ ሳንቲም
በመስለቡ በከተማው ነገሰበት (የእኛ ሰፈር ኑዋሪ ጠቅላላ
ሀብት እኮ ቢሰበሰብ አንድ ውይይት ታክሲ አይገዛም፡፡)
በዛው ልክ ደግሞ የሚመርቀኝ፤ ለአብሮ አደግ ጓደኞቼ የስራ
ዕድል በመፍጠሬ የሚያመሰግነኝ የሰፈሬም ሆነ የከተማው
ኑዋሪ መዓት ነው፡፡ብቻ እኔ በምርቃቱና በምስጋናውም ብዙ
ሳልኮፈስ በሀሚቱና በእርግማኑም ብዙ ሳልሸማቀቅ ሁሉንም
አቻችዬ በመቀበል ወደ ፊት እየገሰገስኩ ነው፡፡ምክንያቱም እኔ
ባለ ራዕይ ነኝ፡፡ሀብታም እንደምሆን ልጅ ሆኜ ለበለጡ ቃል
ገብቼላት ነበር፡፡ለእሷ የተገባ ቃል ደግሞ መተግበር አለበት፡፡
በዚህች አጭር ዓመት የስራ ዘመኔ ሦስት አይነት ሰዎች
እንዳሉ ተረድቼያለው፡፡
-አንደኛ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ምንም ዓይነት
ርዕይም ሆነ የወደፊት ተስፋ የሌላቸው፤ዛሬን ብቻ እንደነገሩ
የሚኖሩ ሰዋች ሲሆኑ
ሁለተኛዎቹ -በቁጥር በጣም ብዙ የሆኑ የህብረተሰብ
ክፍሎችን የሚወክሉ ሲሆን ሽርፍራፊ እና በቀላሉ ሊደረስበት
የሚችል ርዕይ ያላቸው፤ለምሳሌ ስራ መቀጠር፤መኖሪያ ቤት
መስራት ፤ሚስት ማግባት፤ልጅ መውለድ እና ማሳደግ
የመሳሰሉትን የእየለት ተራ ክንውኖች፡፡
ሦስተኞቹ - በቁጥር በጣም ጥቂቶች ሲሆኑ ባለግዙፍ እና
ጠሊቅ ብሎም በቀላሉ ሊደረስበት የማይችል ውስብስብ
ራዕይ ባለቤቶች ናቸው፡፡እነዚህኞቹ ምንም ነገር ማድረግ
ይቻላል ብለው የሚያምኑ፤በራስ የመተማመን ችሎታቸው
ከፍተኛ እና መንፈሰ ጠንካሮች የሆኑ ናቸው፡፡በመጀመርያ
ዕቅዳቸው ልብወለድ የሚመስል፤ እንደ እብድ
የሚያስቆጥራቸው እና እንደመንግስተ ሰማያት ከዕይታ የራቀ
ነው፡፡የሚገርመው ግን መዳረሻው እሩቅ፤መንገዱ ወጣ ገባ
የበዛበት፤ሂደቱ ትዕግስት የሚፈትን ይሁን እንጂ ያሳኩታል፡፡
እንደታዘብኩት እነዚህ ሰዎች የገዘፈ ዓላማቸውን አንግበው
ለስኬታቸው ተግባራዊነት ጉዞ ሲጀምሩ በራሳቸው ጥረት ብቻ
አይደለም ከህይወት ግባቸው ጫፍ ላይ የሚፈናጠጡት፡፡
ብዙ ርዕይ አልባዎች እና ሽርፍራፊ ርዕይ ያላቸው ሰዎችን
ከጐናቸው ያሰለፍሉ፡፡የህይወት ጉዞቸውን ከእነሱ ርዕይ
መሳካት አንፃር እንዲቃኙት ያደርጎቸዋል፡፡
እንዳልኰችሁ የባለርዕይዎች ድንቅ ችሎታ ወደ ስኬታቸው
ጫፍ የሚወስዳቸውን የተዋጣለት እቅድ መንደፍ ብቻ
ሳይሆን የነደፉትን ዕቅድም ሌሎች ሰዎች
ተረባርበው፤ላባቸውን አንጠፍጥፈው ወደ ተግባር
እንዲቀይሩላቸው የማሳመን፤የማስተባበር እንዲሁም
የማደራጀት ድንቅ ችሎታ አላቸው፡፡ የእያንዳንዱ ነጠላ
ዕቅዳቸው መተግበር ድምር ውጤት እነሱን ደረጃ በደረጃ ወደ
ፊት እየገፋ ከመጨረሻው ስኬት እርካባቸው ላይ
እንዲፈነጠጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ለእነሱ ውጤት መሳካት ትልቅ
ድርሻ የነበራቸው፤ለዓመታት ጉልበታቸውን እና ዕውቀታቸውን
የገበሩ ባለ ሽርፍራፊ ባለርዕይዎች ወይም ርዕይ አልባዎች
ደግሞ እነሱ ገድበው ፤አጠራቅመው ህያው ካደረጉት ባህር
ላይ በማንኪያ እየተቆነጠረ ምላሳቸውን ለማራስ እና
ጉሮሮአቸውን ለማርጠብ ያህል ብቻ እየተመጠነ
በሚታደላቸው ጠብታ ይኖራሉ (ብዙውን ጊዜ መጠኑ
በባለርዕይው መልካም ፍቃድ ላይ የተመሰረተ
ይሆናል፡፡)በዚህም የተነሳ ህይወታቸው ተደጋጋሚ እና አሰልቺ
በሆነ ሁኔታ ይቀጥላል፡፡ይሄንን የዓለም ሁኔታ ሳስተውል
ከሦስቱ የየትኛው ቡድን አባል ብሆን ይሻላል? ብዬ እራሴን
ብዙ ጊዜ በመጠየቅ ያገኘውት መልስ የልቤ መሻት
ሦስተኛው ላይ ነው ያረፈው፡፡ ባለራዕይ መሆን….፡፡

ሰሞንኑ በጊዜ ነው ወደ ቤት የምሮጠው፡፡ምክንያቱም በለጡ
የሁለተኛ ዓመት ትምህርቷን አጠናቃ ለእረፍት መጥታለች፡፡
ከእሷ ጋር ለማውራት፤ከእሷ ጋር ለመላፋት ሁሉ ነገር ጥዬ
በጊዜ ወደ ቤት እበራለው፡፡ ዛሬ ኩየራ ቆይቼ ነው የመጣውት
፤ሆስፒታል፡፡ጋሽ በቀለ ታመው አልጋ ከያዙ ሳምንት
ሆኖቸዋል፡፡ እሳቸው ጋር ማደር ነበረብኝ፡፡ግን ብዙ
ዘመዶቻቸው አብረዋቸው ስላሉ እና ከአንድ ሰው በላይ ማደር
ስለማይፈቀድ ወደ ቤት ተመለስኩ፡በዛ ላይ በለጡ ከቀን
ጀምሮ እየደወለች ወደ ቤት ፈጠን ብዬ እንድመጣ
ስትጨቀጭቀኝ ነበር፡፡
እቤት እንደደረስኩ ሁሉም ሳሎኑን ሞልተው ሲንጫጩ
ደረስኩ፡፡ ሰላም ብዬቸው ተቀላቀልኩ፡፡ በለጡ በተስገበገበ
ስሜት ገና ልቀመጥ ጐንበስ ከማለቴ ክንዴን አፈፍ አድርጋ
እየጐተተች ወደ ጓሮ ይዛኝ ሄደች፡፡ በመገረም ዝም ብዬ
ያለተቃውሞ ተጐተትኩላት፡፡
ከቤ‹‹ኸረ ደክሞት ነው የዋለው ምን አድርግ ትይዋለሽ?››
አለች
‹‹ምን ይመናቀሩብናል››ብሩክቲ ነች መርዝ ምላሶን
ያስወነጨፈችው፡፡
‹‹ምነው ምን ሆነሻል?››
‹‹አንተ ምን አባህ ነው እፈልግሀለው እያልኩህ እስከአሁን
የቆየኸው…?ነው ወይስ ፍሬንድህ አለቅህ አለችህ?››
‹‹ባክሽ እኔን ማን ይጠብሳኛል ብለሽ ነው?››
‹‹ኸረ ባክህ !!አንተን የመሰለ ቆንጅዬ ልጅ፤ ለዛውም የልጅ
ሀብታም አግኝታ ማነች የምትምረው?››
በለጡ እንዳለችው በተለይ በዚህ ዓመት ብዛት ያላቸው
ሴቶች በተለያየ ዘዴ እየተፈታተኑኝ ነው፡፡ አንዳቸውም ግን
ውስጤን አስደንግጠውት ወይም ከእኔ ጥሩ ምላሽ አግኝተው
አያውቁም፡፡የእኔን ትኩረት በጠቅላላ ይህቺ ፊቴ የተገተረችው
ጉርድርድ ኮረዳ ሰልባዋለች፡፡አንዷ እንደውም ሞክራ ሞክራ
ሲደክማት ሰው ፊት ‹‹አንተማ ስልብ ነህ..ምንም የለህ፡፡››
በማለት እልክ ልታስገባኝ ሞክራ ነበር፤የሚገባኝ ዓይነት
መስሏት፡፡
በወቅቱ የልጅቷን ንግግር ከሰሙት ሰዎች መካከል
የተወሰኑትም ‹‹እውነቷን ሳይሆን አይቀርም›› በማለት
እንሾካሽከውብኝ እንደነበርም ሰምቼያለው፡፡
በለጡ ቀጠለች….
‹‹ይሄውልህ የፊታችን ቅዳሜ…››
3.6K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 06:33:44 ‍ ቢኒያምና ዋሲሁን ደብተራቸውን
እያገለባበጡ ይንሾካሹካሉ፡፡ ወንበር ስቤ ዋሲሁን ጐን
ተቀመጥኩ፡፡
‹‹ምነው ዛሬ በጊዜ አንቀላፋህ?››
‹‹አይ ትንሽ ስለደከመኝ ነው፡፡እስቲ ቡና አፍይልኝ፡፡››
‹‹ኸረ ባክህ!!››የብሩክቲ ፀባይ ይገርመኛል፡፡ምንም ነገር
ሳትነጫነጭ ስትሰራ አይቼያት አላውቅም፡፡
‹‹የግድሽን ታፈያለሽ ፡፡ተነስ ቢኒያም ከዋሲሁን ጋር አብራችሁ
ሂዱና ግማሽ ኪሎ ቡና ፤ግማሽ ኪሎ ስኳር፤ እጣን፤ ሰንደል፤
ሻማ፤ለስላሳ..ሌላ..ሌላ››
እስኪሪብቶና ወረቀት እያቀበለኝ ‹‹ኸረ ይሄ ሁሉ ይጠፋብኛል
ፃፍልኝ››አለኝ
ቡሩክቲ‹‹ምነው ድግስ አደረከው ፤ እኔ ግን ለስላሳ
አልጠጣም፡፡››አለች
‹‹እና ምን አባሽ ፈለግሽ?››
‹‹ለስላሳ ለልጆች ነው፤ እኔ ወይን ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹የእኔ ዱርዬ ተማሪ ወይን አይጠጣም፡፡››
‹‹ነገ እኮ እሁድ ነው በናትህ ወይን አምሮኛል፡፡ ከገዛህልን እኮ
ቆየህ..የእኔ ምንተስኖት፡፡››
ጋሽ በቀለ ባወጡልኝ ስም እያሾፈች፡፡ከቤ ወይን ስለምትወድ
አልፎ አልፎ እገዛላቸው ነበር፡፡ በዛን ወቅት ታዲያ ብሩክቲ
ከእናቷ እኩል ነው እየተሸማች የምትጠጣው፡፡ እነቢኒያም
የሚገዙትን ዕቃ በዝርዝር ፅፌ ወረቀቱን ከብር ጋር ሰጠዋቸው
፡፡እነሱም እየተፍለቀለቁ ሊሸምቱ ተያይዘው ወጡ፡፡
‹‹እስከዛሬ ጠጥተህ የማታውቀውን ቡና ነው የማጠጣህ፡፡
በመጀመሪያ ግን ልብሴን ልቀይር››ብላ ጓዲያ ገባች፡፡ለብሳ
የነበረውን ጅንስ ሱሪ አውልቃ የሚያምር ሮዝ ቀለም ያለው
ድርያ ለብሳ ወጣች፡፡ ድርያው ይበልጥ ውብ አደረጋት፡፡
ሲኒውን አቀራርባ ሳትጨርስ እነዋሲሁን ከተላኩበት መጡ፡፡
ቡናው ተቆልቶ ፤ተወቅጦ ዱቄቱ የተጣደው ጥቁር ጀበና
ውስጥ ከተጨመረ ቡኃላ እስኪፈላ ድረስ ብሩክቲ እራት
አቅርባ እየተጐራረስን በላን፡፡ቡናው ተጠጥቶ ካበቃ ቡኃላ
ወይኑ ተከፈተ፡፡እኔ እና ብሩክቲ ወይን ፤ ወሲሁን እና ቢኒያም
ደግሞ ለስላሳ መጐንጨት ጀመሩ፡፡ልጆቹ ግን ተቁለጨለጩ፡፡
ከቤ እንደምታደርገው በሻይ ብርጭቆ ለሁለቱም ቀድቼ
ሰጠዋቸው፡፡በደስታ ተቀብለውኝ በሦስት ትንፋሽ ነበር
ያጋቡት፤ አልጨመርኩላቸውም፡፡ ተቁለጭልጨው…
ተቁለጭልጨው ተስፋ ሲቆርጡ እና እንቅልፋቸው ከቁጥጥር
በላይ ሆኖ ሲያስቸግራቸው ተያይዘው ወደ መኝታቸው ሄደው
ተኙ፡፡
አስር ለሚሆኑ ደቂቃዎች ፊት ለፊት እየተያየን ያለምንም
ንግግር ከቆየን ቡኃላ ብሩክቲ ድንገት ተነስታ ወደ መኝታ ቤት
ገባች፡፡ ከአምስት ደቂቃ ቡኃላ ተመልሳ ስትመጣ ቤቱ በአንዴ
ነበር የታወደው፡፡ በሽቶ ታጥባ ነበር የመጣችው ማለት
ይቻላል ፡፡ረስቼ የነበረውን ሻማ ለኮሰችው፡፡መብራቱን
አጠፋችና‹‹ፊልም እንይ?›› አለችኝ ፡፡ ሰዓቱ ወደ አራት ሰዓት
እየተጠጋ ነው፡፡
በጊዜ ተኝቼ ስለነበር መሰለኝ የእንቅልፍ ስሜት እየተሰማኝ
ስላልሆነ እልተቃወምኳትም፡፡ ‹‹እንቅልፍሽ ካልመጣ ደስ
ይለኛል››አልኳት፡፡
ከደብተር መያዣ ቦርሳዋ ውስጥ ቪሲዲ አወጣች እና ዴክ
ውስጥ ጨምራ ሪሞቱን እና የወይን ብርጫቆዋን ይዛ
በመምጣት ቦታዋን ቀይራ ጐኔ ተቀመጠች፡፡ ሽቶዋ ጭንቅላት
ይነቀንቃል፡፡ሪሞቱን ተጫነች፡፡ አማርኛ ፊልም መስሎኝ ነበር
እንግሊዘኛ ነው፡፡ፊልሙ የወሲብ ፊልም ነው፡፡‹ሄሮይክ›
የሚል ርዕስ አለው፡፡አንድ ወጣት ከሚዜው ጋር ከአንድ
የአሜሪካ ግዛት ወደ ላስ ቤጋስ ለሰርጉ ይጓዛል፡፡እንደ ዕድሜ
ልክ ፍርድ አስፈሪ አድርጐ ወደ ቀረፀው ጋብቻ ውስጥ
ከመግባቱ በፊት ግን ያለችውን ሽርፍራፊ የነፃነት ሰዓት
ከተለያዩ ሴቶች ጋር በየመንገድና በደረሰበት ቦታ ሁሉ ልቅ
ወሲብ ይፈጽማል፤ ሚዜውም ያግዘዋል፡፡ላስቤጋስ
የምትጠብቀው እጮኛውም ተመሳሳዬን እያደረገች ነው እሱን
የምትጠብቀው፡፡
አቁሚው ማለት ብፈልግም ቃላት ከአንደበቴ ላወጣ
አልቻልኩም፡፡ ወይኑን በላይ በላይ እየተጓነጨው ፊልሙን
እየኰመኰምኩ ነው፡፡ ሰውነቴ ተወጣጥሯል፡፡በዛ ላይ
ብሩክቲ እራሷን ጥላ እኔ ላይ ተደግፋለች፡፡አውቃ ይሁን
እንዳጋጣሚ አላውቅም የለበሰችው ድርያ ወደ ላይ
ስለተሰበሰበ ጭኖ ለእይታ ተጋልጧል፡፡እጆቾ በሸሚዜ ክፍተት
አልፈው ሰውነቴን እያተረማመሱት ነው፡፡ እንደምንም
ከገባውት ስሜት ወጥቼ ቀልቤን ገዛውና ሪሞቱኑ አንስቼ
ፊልሙን አጠፋውት፡፡ ብሩክቲ ምንም አልተናገረችም፡፡ቀስ
ብላ እጇን ሰብስባ ወይኗን አንስታ ጨለጠችው፡፡ድንዝዝ
ብላለች ፡፡አይኖቾ ይበልጥ ስልምልም ብለዋል፡፡ እኔም
የቀረችኝን ወይን በአንድ ትንፋሽ አጋባውና፡፡‹‹በይ ቸው
ልተኛ››ብዬ ወደ መኝታ ክፍሌ ገባው፡፡
ከአስር ደቂቃ ቡኃላ ገርበብ ያለው ክፍሌ ተከፈተ፡፡ልብሴን
አወላልቄ በፓንት ብቻ ከውስጥ ገብቼ ተኛቼ ነበር፡፡ተአምር
ነው የማየው ፡፡ ብሩክቲ ዕርቃኗን ፍዝዝ ብላ አይኖን
እያስለመለመች ስልታዊ በሆነ አረማመድ እየተራመደች ዘልቃ
ወደ እኔ እየቀረበች ነው፡፡አቤት ቅርፅ፤አቤት ውበት፤እንዴት
አድርጐ ነው አሳምሮ የፈጠራት፡፡ደግሞ ፒኪኒ ፓንት ነው
ያደረገችው ፡፡ኸረ ይሄንን ፓንት አውቀዋለው፡፡አዎ አስታወስኩ
ከጎባ ጉዞ መልስ ለበለጡ ለመስጠት ከገዛው ብኃላ ምን
ብዬ እንደምሰጣት ግራ ገብቶኝ ሻንጣዬ ውስጥ ደብቄው
የነበረ ነው፡፡ይህቺ እርኩስ ምን ስታደርግ ጐርጉር
አገኘችው….?እኔ ጋር ደረሰች ፡፡ኸረ አልጋ ላይ ወጣች፡፡ብርድ
ልብሱን ገልጣ ገባች፡፡ ሰውነቷ ከሰውነቴ ተነካካ፡፡ሰው
እንዲህ ይደነዝዛል፡፡ ደነዘዝኩ፡፡ብርታቱን ማን እንደለገሰኝ
አላውቅም በደመነፍስ ተነሳውና ቢጃማ ለብሼ ተመልሼ
ተኛው፡፡ አቀፍኳት፡፡ ታቀፈችልኝ፡፡ያ ሁሉ ምላሷ፤ያ ሁሉ
ተሳዳቢነቷ ድራሹ ጠፍቷል፡፡እርግብ ሆናለች፡፡ትንፋሿ በጣም
ይጋረፋል፡፡.ልክ እንደ ኤርታሬ እሳተጐመራ ጉድጓድ ፡፡
ያንተራሳት ክንዴ በእንባዎቾ ጅረት እየራሰ ነው፡፡እያለቀሰች
አንገቴን ትስማለች፤ግንባሬን ትስማለች፤ ጆሮዬ አካባቢ
ትስመኛለች፡፡በመጨረሻ መሳሟን ሳትገታ ከንፈሯ ጉንጬ ላይ
እንደተጣበቀ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡እኔ ግን ስካሬም፤ እንቅልፌም
ብን ብለው… ፀጥ ካለው ለሊት እና ዝም ካለው ጨለማ ጋር
ብቻዬን ጥለውኝ ጠፋ ፡፡

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot ❥❥________⚘_______❥❥
3.3K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 06:33:13 ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
ከ6 ወር ቡኃላ
በለጡ ድሬ ደዋ ከገባች ስድስት ወር አለፋት፡፡ሁለት ጊዜ
በመመላለስ ሄጄ አይቼያታለው፡፡ ያም ሆኖ በጣም
ትናፍቀኛለች።በየቀኑ ሁለት እና ሦስት ጊዜ በስልክ
ባወራትም ውስጤ አይረካም፡፡ ግማሽ አካሌ ከእሷ ጋር
ተቦጭቆ የቀረ ይመስለኛል፡፡
በተረፈ በኑሮዬ በጣም ስኬታማ እየሆንኩ ነው፡፡እናትና አባቴን ከአንድ ክፍል የቀበሌ ቤት አውጥቼ ባለአንድ መኝታ
ቤት ኮንደሚኒዬም ተከራይቼ አስገብቼያቸዋለው፡፡የቀበሌ
ቤቷን የሸቀጣ ሸቀጥ ችርቻሮ ሱቅ ከፍቼ ለአበቴ በመስጠት
እንዲተዳደሩበት አድርጌያለው፤እራሳቸውን በቋሚነት
እንዲችሉ፡፡
ለበለጡ በየወሩ 800ብር በባንክ ቁጥሬ አስገባላታለው፡፡
ለትዬ ከቤም አልፎ አልፎ ለቡና መጠጫ ሸጐጥ መድረጌን
አልዘነጋም፡፡ብሩክቲ ግን በቃሏ እንደፀናች ነው፡፡ከእኔ ምንም
ላለመቀበል አሻፈረኝ ብላለች፡፡ወደ ስራ ለመሰማራት
የሚፈልግ የሰፈር ልጅ የሚያማክረው እኔን ነው፡፡የሰፈሩ
አርአያ እና ሞዴል ወጣት ሆኚያለው፡፡
አሁን እስክንድር እፈልግሀለው ብሎኝ ላገኘው ወደ እሱ
እየሄድኩ ነው፡፡ የተቀጣጠርንበት ካፍቴሪያ ስደርስ ቀድሞኝ
አገኘውት፡፡ ሠላምታ ከተለዋወጥን ቡኃላ የየፍላጎታችንን አዘን
ወደ ጫወታችን ገባን፡፡
‹‹ምነው ትምህርት የለም እንዴ?››
‹‹ያው ቅዳሜ አይደል ፤ከቤተሰብ ጋር ላሳልፍ ብዬ ነው
የመጣውት፡፡››
‹‹አይ ጥሩ ነው፡፡የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጤት እንዴት
ነበር?››
‹‹እንደበለጡ ባልሰቅልም ጥሩ ነው››ከንግግሩ በበለጡ
ውጤት ከልቡ መደነቁን በቀላሉ መረዳት ይቻላል ፡፡
‹‹አይ ጥሩ ነው፡፡ታዲያ ምነው በሰላም ፈለከኝ?››
‹‹ይሄውልህ በላቸው አሁን እንደድሮው ሞኛ ሞኝ እና ፈሪ
አይደለውም፡፡አድርግ ያሉኝን አላደርግም ፤ተው ያሉኝን ዝም
ብዬ በፀጋ አልተውም፡፡››ንግግሩን ገታ አደረገ
የንግግሩ ጭብጥ በቀላሉ ሊገለፅልኝ ስላልቻለ‹‹ምነው
እስክንድር ሰላም ነው?›› አልኩት፡፡
‹‹ምንም ሰላም የለም ....አዕምሮዬ በብዙ ጥያቄዎች
ተወጥሯል፡፡እነዛን ጥያቄዎች እንድትመልስልኝ እፈልጋለው››
‹‹ማ እኔ?››
‹‹አዎ አንተ››
‹‹ምንን በተመለከተ?››
‹‹የእኔ እና አንተ የጋራ ጉዳይ በለጡ ነች፡፡እሷን የተመለከተ
ባንተ የሚመለሱ ብዙ ጥያቄዎች አሉኝ››
‹‹ጠይቀኝ ››አልኩት ኮስተር ብዬ
‹‹በለጡ ላንተ ምንህ ነች?››
ፊቴ ሲጠቁር ለራሴ ይታወቀኛል፡፡‹‹ምን ዓይነት ጥያቄ ነው?››
‹‹መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡ይሄውልህ በላቸው.. ድሮ እናንተ
ስታስፈራሩኝ ጩቤያችሁን ፈርቼ ነበር በለጡን የቀረብኩት፡፡
አሁን ግን ጩቤ አይደለም መትረየስ ብትደቅኑ ከእሷ መለየት
የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሼያለው፡፡ በጣም
አፍቅሬያታለው፡፡ላጣት አልፈልግም››
ግራ ገብቶኝ‹‹ታዲያ ምን ተከሰተ..?ተጣላችሁ እንዴ?››
ጠየቅኩት፡፡
‹‹ፈራው..አንተ ለእሷ ያለህን ነገር ሳስብ ሁሌ እፈራለው፡፡
የሥጋ ዝምድና እንደሌላችሁ አውቃለው፡፡ታዲያ ከልጅነት ጊዜ
አንስቶ እሰከአሁን ድረስ ይህንን ሁሉ
የምታደርግላት፤እንደእዚህ የምትሆንላት በምን ምክንያት
ነው?እንዲሁ በነፃ..?አይመስለኝም፡፡››
‹‹የግድ ምክንያት ያስፈልጋል እንዴ?››
‹‹አዎ፡፡ቆይ ታፈቅራታለህ››
ዝም አልኩት፡፡ምን ብዬ ልመልስለት፡፡አፈቅራታለው ልበለው፡፡
ማፍቀርማ እሱም ያፈቅራታል፡፡እኔ ለእሷ ያለኝ ስሜት ግን
እንኳን ከእሱ ከእናቷ ፍቅር ይበልጣል፡፡ከማፍቀር በላይ የእኔን
ስሜት የሚገልፅ ቃል ይኖር ይሆን..?እኔ እንጃ
‹‹ምነው ዝም አልክ?››
‹‹እስክንድር የእኔ እና የበለጡ ግንኙነት ከአንተ እና ከእሷ
ግንኙነት በጣም የተለየ ነው፡፡ ምንም የሚያገናኘው ነገር
የለም፡፡አትስጋ :: ፍቅረኛህ ነች፤አንተው ነህ የምታገባት፡፡››
‹‹አዎ አገባታለው፤ለቤተሰቦቼም ነግሬያቸዋለው፡፡ትምህርት
እስክጨርስ እንኳን ተረጋግቼ መጠበቅ ስለማልችል በዚህ
ክረምት ቀለበት ላስርላት ወስኜያለው፡፡ከዚያ በፊት ግን…››
‹‹ከዚያ በፊት ምን?››
‹‹ቀስ በቀስ ከህይወታችን እንድትወጣ እፈልጋለው፡፡ለእሷ
በየወሩ የምትልከውን ብርም እንድታቆም እፈልጋለው፡፡እኔ
ከቤተሰቦቼ ጋር ስለተነጋገርኩ ከእዚህ ወር ጀምሮ
እልክላታለው፡፡ሌላው ደግሞ ድሬ ድረስ እየሄድክ
የምትጠይቃትንም እንድታቆም…..፡፡››
‹‹ጨረስክ?››
‹‹ለጊዜው ጨርሼለው››
ከመቀመጫዬ ተነሳው፡፡ድፍን ሃምሳ ብር ከኪሴ አወጣውና
ጠረጴዛ ላይ በማስቀመጥ ጐንበስ ብዬ አፍጥጬ ዓይን
ዓይኑን እያየውት ‹‹ስማ.... ያልከኸውን ሁሉ እርሳው፡፡
በእርግጠኝነት ልንገርህ… እንኳን አሁን ይቅርና ካገባሀት
ቡኃላ እንኳን የጠየቅከኝን ነገር ይሆናል ብለህ ፍጹም
አትጠብቅ፡፡ አግብቼያታለው ብለህ እሷ ላይ ተፅዕኖ
ብልታደርግ ወይም ከእኔ እይታ ልትሰውራት ብትሞክር
የገባህበት ገብቼ ነው የማጠፋህ ፡፡ሞክረውና እግዚያብሄር
እንኳን ሊያድንህ አይችልም፡፡ በበለጡ እምላለው
አጠፋሀለው፡፡ ትሰማኛለህ፡፡››ጠረጴዛውን በእጄ ጐ..ጐ
አደረግኩ ፡፡ሲፎክር የነበረው ሰውዬ ከአይኖቼ የሚወጡት
ገሀነማዊ የንዴት ጨረር ሲገርፉው ደንግጦ መሰለኝ ወደ ኃላ
ሸርተት አለ፡፡ሰውነቴ ከመንቀጥቀጥ አልፎ ወደመንዘፍዘፍ
እየተሸጋገረ ስለሆነ ከዛ በላይ አጠገቡ ከቆየው ያልታሰበ
አደጋ ላደርስበት እችላለው ብዬ በመፍራት እንደምንም
እራሴን ተቆጣጥሬ በፍጥነት አካባቢውን ለቀቄ ሄድኩ፡፡
ቀጥታ ወደ ቤት ነው ያመራውት፡፡ከቤም ብሩክቲም
አልነበሩም… ዋሲሁን ብቻ ነበር የሚታየኝ ፡፡አልፌ ወደ ክፍሌ
ገባው እና ዘግቼ ተኛው››ከብዙ መገላበጥ ቡኃላ እንቅልፍ
ወሰደኝ፡፡…ቅዠት የታጨቀበት እንቅልፍ ፡፡
የስልክ ጥሪ ነበር የቀሰቀሰኝ፡፡ ዓይኖቼን ሳልገልጥ ሞባይሌን
በዳበሳ ፈልጌ አነሳውት፡፡
‹‹ሰላም ዱርዬው››
በለጡ ነች‹‹እሺ ደህና ነሽ?››
‹‹ምነው ድምፅህ?››
‹‹ተኝቼ ነበር››
‹‹አመመህ እንዴ?››
‹‹ትንሽ ራሴን››
‹‹በእናትህ ዱርዬው..ለእኔ ስትል ይቅር በለው፡፡አሁን
ደውሎልኝ ነበር ፡፡ ሲነግረኝ ተጣልተን ነው ስልኩን
የዘጋውበት፡፡በጣም ነው ያናደደኝ፡፡ አንዳንዴ ዝም ብሎ
በማያውቀው ነገር ገብቶ መዘባረቅ ይወዳል፡፡ በእናትህ
አትበሳጭ፡፡››
ደስ አለኝ‹‹እሺ አልበሳጭም››አልኳት በመረጋጋት ስሜት፡፡
ከእኔ መወገኗ ሠላም በውስጤ እንዲረጭ አደረገ፡፡
‹‹በል አሁን ተነስ፡፡እቤት ማንም የለም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ፡፡ከቤ የለችም አላባ ለቅሶ ሄዳለች፤ዛሬ
አትመጣም፡፡የልጆቹ ድምፅ ግን ይሰማኛል ፡፡››
‹‹በቃ ብሩክቲን ቡና አፍይልኝ በላት፡፡ቆይ እንደውም እኔ
ደውልላታለው፡፡››
‹‹እሺ በቃ አታስቢ ወደ ጥናትሽ ተመለሺ››
‹‹እሺ ወንድም አለም፡፡ከመዝጋቴ በፊት ግን አንድ ነገር
ልንገርህ፡፡መቼም ቢሆን መቼ ከማንም ጋር የማልደራደርበት
አንድ ጉዳይ ቢኖር ያንተን ወንድምነት ነው፡፡ያንተን ወንድምነት
የሚያሳጣኝ ከሆነ ምንም ነገር ጥንቅር ብሎ ሊቀር ይችላል፡፡
ገነትም ቢሆን፡፡›› ዘጋችው፡፡
ይህን ዓይነት የሚያጥለቀልቅ ደስታ በመላ ሰውነቴ
እንደተሰራጨ መገመት አትችሉም፡፡የመጀመሪያ ጀምስ ፓንት
የገዛው ቀንም ፤የመንጃ ፍቃዴን የተቀበልኩ ቀንም ፤ ጋሽ
በቀለ አዲሷን ሚኒባስ የሰጡኝ ቀን እንኳን እንዲህ አይነት
ደስታ አልተሰማኝም ነበር ፡፡ዕድሜዬን ሙሉ ለበለጡ ብዙ ብዙ
ነገር ሳደርግላት ኖሬያለው፡፡ እሷ ግን ይሄን ሁሉ ውለታ ሰላሳ
ባማይበልጡ ቃላት መልሳ ከፈለቺኝ፡፡ ከመጀመሪያው
ይበልጥ በጥልልልልቀቀቀቀቀቀትትት
አፈፈፈፈቀቀቀቀቀቀርርርርርርርኳት፡፡
****
‹‹ከመኝታዬ ተነስቼ ወደ ሳሎን ወጣው፡፡ሦስቱም አሉ፡፡ብሩክቲ
በተንተረከከ የከሰል ፍም ላይ የሸክል ድስት ጥዳ ሽሮ
እያንተከተከች ነው፡፡
3.1K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 20:42:33 ‍ ጠርዝ ላይ ቁጭ ትላለች።ስድሥት ሰባት የሚሆኑ ጓረምሶች ዙሪያዋን ከበዋት
ይቀመጣሉ፡፡ በየሰሀን እየዘገነች የምትሰጣቸውን ስማቸውን
ማወቅ ያልቻልኳቸውን የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች
እየተቀበሏት ቁጢጥ ባሉበት በልተው ጨርሰው ሶስት ወይም
አምስት ብር ሰጥተዋት አፋቸውን እየጠራረጉ ይሄዳሉ ፡፡
የበላው ሲሄድ የራበው ደግሞ በቦታው ይተካል፡፡ በዚህ
ዓይነቱ አነስተኛ የመንገድ ላይ ርካሽ ተንቀሳቃሽ ምግብ ቤቶች
ድሬደዋን ከእኛዋ ሻሸመኔ ጋር እንደምትመሳሰል መታዘብ
ችያለው ፡፡ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ሁለቱም ደሀ
እንዳቅሙ የሚኖርባቸው ከተሞች ተብሎ ሚነገርላቸው፡፡
ጫት
ስለድሬዎች እና ጫት ግንኙነት እዚህ ከመምጣቴ በፊትም
ቢሆን የተወሰነ መረጃ ነበረኝ፡፡ እንደተባለውም የሚገርም
ነው፡፡ጫት እንደሌላው ሀገር በጥቁር ፔስታል ተጠቅልሎ
በጋዜጣ ተሸፍኖ ባዛ ላይ ትልቅ ጃኬት በመልበስ ከውስጥ
ተሸጉጦ አይደለም ከሚሸጥበት ወደ ሚቃምበት ቦታ
የሚጓጓዘው፡፡ ጫቱ በነጭ ስስ ፔስታል ይገዛል፤ ጫፎን
አንጠልጥሎ አስፓልት ላይ ወሬውን እያወራ ዘና ብሎ
ይጓዛል፤ምንም የሚያሳፍር ምንም የሚያሸምቅቅ ነገር
የለም፡፡የመቃሚያም ቦታ ብዙ አያስጨንቅም፡፡ማንኛውም
የድርጅት በረንዳ፤አስፓልት ዳር የሚገኝ ጥላ ስፍራ እና
መሳሰሉት ቦታዎች ከ6 ሰዓት ቡኃላ በቃሚዎች እንደተሞላ
ነው፡፡ይህ ትዝብት ድሬዎች ለእውነት እንጂ ለይሉኝታ
እንደማይኖሩ ማረጋገጫ ሆኖኛል፡፡
በረዶ ውሃ
ድሬ በጣም ትሞቃለች ፡፡በዚህም የተነሳ የውሃ ፍጆታ በጣም
ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይ ላለመዳት እንግዳ ሰው ቀዝቃዛ ውሃ
ከምግብ በላይ አስፈላጊ ነው፡፡ታዲያ ፍሪጅ ባይኖሮትም
ድሬዎች ለዚህ ጥሩ መፍቴ ዘይደዋል፡፡ ውሃ ሲጠማዎት
ማንኛውም ኪወክስ ጐራ ይሉና በረዶ ብለው ይጠይቃሉ፡፡
በ50 ሣንቲም በነጭ ላስቲክ ጠጥሮ ነጭ ድንጋይ የመሰለ
አንድ ኪሎ አካባቢ የሚመዝን ነጭ በረዶ ይሰጦታል፡፡ ከዛ
እቤት በመውሰድ በመለስተኛ ባልድ የፈላውን የቧንቧ ውሃ
በመሙላት በረዶውን ውስጡ ይጨምሩታል ፡፡ከ10 ደቂቃ
ቡኃላ ያስፈለጐትን ያህል ቀዝቃዛ ውሃ በብርጭቆ እየቀዱ
እስኪረኩ ማንደቅደቅ ነው፡፡
እንግዲህ የድሬን ቆይታዬን አገባድጄ ዛሬ የመልስ ጉዞ ላደርግ
ነው፡፡ ከበለጡ ጋር ድሬ መነኸሪያ ነው ያለነው፡፡እየሸኘችኝ፡፡
‹‹እንግዲህ ጠንካራ ሁኚ ፤አትልፈስፈሺ፡፡እንደዚህ ስልሽ ግን
ነገሮች ከአቅምሽ በላይ ሆነው ከደበረሽ ጥለሽው ነይ፤ያለኝን
ነገር ሁሉም ከፍዬ አስተምርሻለው፡፡››
እንባዋ በጉንጮቾ ላይ ቁልቁል አቋርጦ ወረደ፡፡ተንጠራርታ
ጉንጬን ሳመችኝ ‹‹ከንፈሯ ይሞቃል››በዛ ቅፅበት ከኪሴ
ያዘጋጀውላትን የመሰነባበቻ ስጦታ አወጣውና እጇ ላይ
አስቀመጥኩላት፡፡ ሞባይል ነበር፡፡አንድ ሺ አምስት መቶ ብር
ነው የገዛውት ፡፡ ለእሷ ብዬ አይደለም ፤ ለራሴ ስል ነው ፡፡
ቢያንስ በቀን አንዴ ድምጾን መስማት ካልቻልኩ እንዴት
በህይወት መቆየት እችላለው?፡፡
‹‹ደግሞ ምንድነው?››
‹‹ሲምም ሚሞሪ ካርድም አለው፡፡ካንቺ የሚጠበቀው ከፈት
አድርገሽ መደወል ብቻ ነው፡፡ደግሞ ጐረምሶችሽ ጋር
እየደወልሽ እንዳትጀናጀኚበት››በማለት ለመቀለድ ሞከርኩ፡፡
አልሳቀችልኝም ፡፡ በዚህ መካከል ‹‹ግባ ልንሄድ ነው አለኝ..››
ሹፌሩ፡፡ ከፍዘቷ ባነነችና‹‹ያንተ ነገር ከአዕምሮዬ በላይ
እየሆነብኝ ነው፡፡ ታውቃለህ ጓደኞቼ ስለአባቶቻቸው ሲያወሩ
አንተ ነህ ትዝ የምትለኝ፡፡ በቃ ምርጥ አባቴ መስለህ
ትሰማኛለህ፡፡አባቴ በህይወት እያለ ሊያደርግልኝ ያልቻለቸውን
ነገሮች ሁሉ አንተ አድርገህልኛል፡፡ላንተ ወንድምነት ብቻ
ሳይሆን አባትነትም ያንስብሀል፡፡በቃ እንደአምላኬ
ትገዝፍብኛለህ፡፡››
‹‹በይ ቸው ››ብዬ ጐንበስ በማለት ጉንጮቾን ልስም
ስደነባበር ከንፈር ለከንፈር ተነካካን፡፡እኔ ደነገጥኩ እሷ ግን
ያስተዋለችውም አልመሰለኝ፡፡ ጉንጬንና ግንባሬን ስማ
እያለቀሰች ተሰናበተችኝ፡፡ እኔም ወደሚኒባሷ ገባውና ጉዞ
ጀመርን፡፡ደንገጐ ስደርስ ስልኬ ጠራ ‹‹አቤት ማን ልበል?››
በለጡ ነበረች፡፡‹‹ሙከራ 1...2….3 የት ደረስክ ?››

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot ❥❥________⚘_______❥❥
2.9K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 20:42:31 ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
.
ጉዞ ወደድሬ
ከበለጡ ጋር ወደ ድሬደዋ እየሄድን ነው ፡፡የሚቀይራት ሰው
ከተገኘ ልንሞክር ካልሆነም እዛው ተመዝግባ እንድትቀጥል፡፡
አገር ስለማታውቅ ብቻዋን ግር ይላታል ተብሎ አኔ
እንዳደርሳት በቤተሰቡ ተመረጥኩ፡፡ የእኔን ከእሷ ጋር መሄድ
ብሩክቲ ብቻ ነበረች የተቃወመችው ፡፡ ‹‹እውርን እውር
ቢመራው ምን ፋይዳ አለው፡፡ብቸዋን ብትሄድ ምን እንዳትሆን
ነው?›› በማለት በብስጭት የታሸ ተቃውሞዋን አሰምታ ነበር ፤
የሰማት ሰው ግን አልነበረም፡፡
እውነትም ብሩክቲ እንዳለችው እኔም ከሞጆ ቡኃላ ያለውን
ሀገር አላውቀውም፡፡ግን ግድ የለኝም፡፡ ከእሷ ጋራ ከሆነ ሁሉ
ነገር ቀና ነው፡፡ሻሸመኔ ተነስተን ነጌሌ-አርሲ፤አዳሚቱሉ፤ዝ
ዋይ፤መቂ፤ሞጆ የመሳሰሉትን ከተሞች አልፈን ከረፋዱ
አምስት ሰዓት አዳማ ደረስን፤አዳማ ታምራለች፡፡አየሯ ግን
ትንሽ ይሞቃል፡፡ገና ካለንበት መኪና ሳንወርድ ድሬደዋ፤ ሀረር
የሚሉ ደላሎች ተረባረቡብን፡፡ከመኪና ወደ መኪና
ተገለበጥን፡፡በውስጤ ግን አዳማን ሌላ ጊዜ በተረጋጋ ሁኔታ
ተመልሼ እንደምጓበኛት ለራሴ ቃል ገባው፡፡
ጭንቅላቷን ወደ እኔ ዘንበል አድርጋ ትከሻዬን በመደገፍ
‹‹አሁን የሚቀይረኝ ሰው የማገኝ ይመስልሀል?››በለጡ
የጠየቀችኝ፡፡
‹‹በተስፋ ፀልይ… ክርስቲያን አይደለሽ?››
‹‹አንተም ፀልይልኝ››
‹‹ድሬም እኮ ምርጥ ከተማ ነች፡፡ባይሳካም ያን ያህል የከፍ
አይደለም››
‹‹ቢሆንም አርባ ምንጭ ወይም ወላይታ ቢሆንልኝ ደስ ይለኝ
ነበር፤ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜም ቢሆን ከእናንተ ጋር
መገናኘት እፈልጋለው፡፡››
ሚኒባሳችን እየተስፈነጠረች መተሀራ ደርሳለች፡፡አየሩም
በጣም ይሞቃላ፡፡‹‹ከእኛ ጋር ነው ወይስ ከእስክንድር ጋር?››
‹‹ያው ነው …ምን ነገር ታጣምማለህ፡፡››
የወሬ አቅጣጫዬን ቀየርኩ‹‹ለመሆኑ የብራንባሩ ነገር አንዴት
ሆነ?››
‹‹ከጋብቻ ቡኃላ እንዲሆን ተወስኗል..በፊትም አንቺ ስላልሺኝ
እንጂ እኔ አልፈለኩም ነበር አለኝ››
‹‹ቆይ እሱም ድንግል ነው እንዴ?››
‹‹ከአንድ ሁለት ሴቶች ጋር ወጥቶል መሰለኝ››
‹‹ታዲያ አንቺ ጋር ሲደርስ….››
‹‹የዛን ቀን አንደኛ ሰክሮ ነበር፤በተጨማሪም እኔ
የተመቸውት አይመስኝም፡፡የቀዘቀዘ ስሜቱን ለማነሳሳት
ከመጣር ይልቅ ሳመነጫጭቀው ነበር፡፡ይሄ ደግሞ ይበልጥ
ስሜቱን ያጠፍበት እና በራስ የመተማመን ኃይሉን ያወረደበት
ይመስለኛል፡፡ ይሄ ሁሉ ቢሆንም ግን አሁንም እሱን ብቻ ነው
የማፈቅረው፡፡ሁሌ የእሱ ብቻ ነው መሆን የምፈልገው፡፡ ››
አለቺኝ ፡፡በዚህ ጊዜ አዋሽ ደርሰናል፡፡ ተደግፋኘም
ስለምታወራ ትንፍሿ እየሞቀኝ ነው፡፡ሰውነቴ ሁሉ
ተወጣጥሯል፡፡በዚሁ በጅቡቲ በኩል እስከወዲያኛው ከሀገር
ይዤያት ብጠፋ ደስ ይለኝ ነበር፤አጉል ምኞት፡፡ዝም ተባባልን፡፡
በቆረጣ ሳያት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዶታል፡፡ በመስኮት
አሻግሬ መልካ-ምድሩን እየቃኘው መተከዜን ቀጠልኩ፡፡
እውነት እክንድር እና በለጡ እስከ ጋብቻ የሚዘልቅ የፍቅር
ታሪክ ይኖራቸው ይሆን? ከሆነስ መቼ ይሆን የሚጋቡት?
ደግሼ የምድራቸውስ እኔ እራሴ እሆን? ወይስ በሰርጋቸው
እለት እሷ ቬሎዋን እሱ ሙሉ ሱፉን ከነከረባቱ ለብሶ ሽክ
ብለው በሚዜዎቻቸው ታጅበው እያለ በድንገት ሽጉጤን
መዝዤ የሁቱንም ግንባር አፍርሼ እንደ ቴድሮስ በገዛ እጄ
ጥይት በመጠጣት ከዚህ የዓለም ጣጣ እገላገል ይሆን?
ነው ወይስ እሷ እስክንድርን በምታገባበት ቀን እኔም ብሩክቲን
ለማግባት ወስኜ በአንድ ድግስ ፤በአንድ ድንኳን እንዳር ይሆን?
የማይረባ መቋጫ የሌለው ግትልትል ሀሳቤ ራሴን
አሳመመኝ፡፡
አሰቦት፤ሚሌን አልፈን አሰበ ተፈሪ(ጭሮ) ስንደርስ
ሚኒባሳችን ለምሳ ቆመች፡፡በለጡም ከእንቅልፎ ተነሳች ፡፡
ጭሮ ብዙም ትልቅ የምትባል ከተማ ባትሆንም ሞቅ ያለች
ነች፡፡የ15 ደቂቃ የምሳ እረፍት አደረግን፡፡ ወደ ሚኒባሳችን
ስንመለስ ሁሉም ሰው ሹፌሩንም ጭምር ጫት ከኮካ
ጋር፤ጫት ከውሃ ጋር ይዘው ከቅድሙ በተሸለ ሁኔታ
ተነቃቅተዋል፡፡ አርበረከት፤አሰቦት፤ደበሶ፤ሚኤሶ፤ሀዳስ፤ቦረዳ
ካራሚሌ፤ ቆቦ፤ ጨለንቆ፤ ቁሉቢን አልፈን ደንገጐ ስንደርስ
ወደ ሀረር የሚወስደውን መንገድ ጥለን ወደ ግራ ታጥፈን ሃያ
ደቂቃ ያህል ከተጓዝን ቡኃላ ድሬ-ደዋ ገባን፡፡
ከዚራ ከሚገኘው ነፃነት ሆቴል ቤርጓ ያዝንና እራት በልተን
ተያይዘን ተኛን፡፡አንድ ክፍል ውስጥ፤አንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈን
ነው ያደርነው፡፡እሷ ሀሳቧን እኔ ላይ ጥላ የሰላም እንቅልፍ
ስትለጥጥ እኔ ደግሞ የእሷንም የእኔንም ሀሳብ በማብሰልሰል
ስገላበጥ ነጋ፡፡
ጥዋት ቁርስ ከበላን ቡኃላ 5 ሰዎችን በሚጭን ፎርስ ብለው
በሚጠሩት ገዘፍ ባለ ባጃጅ ተሳፍረን በከተማዋ በሌለኛው
ጫፍ ላይ ሳበያን የሚባል አካባቢ ወደሚገኘው ድሬደዋ
ዩኒቨርሲቲ ተጓዝን፡፡
ድሬ ደዋ አንድ ሳምንት ቆየው፡፡በለጡን ዩኒቨርሲቲ
የሚቀይራት ሰው ስላልተገኘ እዛው በመመዝገብ ዶርምም
ተረከበች፡፡
ድሬ-ደዋ ደቻቱ ወንዝን በጉያዋ አቅፋ 1213 እስኪዌር
ኪ.ሜትር ስፋት ላይ የተንጣለለች 340 ሺ በላይ ኑዋሪ ያላት
ከአዲስአበባ ቀጥሎ ሁለተኛዋ የፌዴራል መንግስቱ ከተማ
የሆነች ዘመናዊ ከተማ ነች፡፡ ከተማዋን አማርኛ ተናጋሪዎቹ
‹Dire Dawa› ኦሮሚኛ ተናጋሪዎቹ ‹Dirre Dhawaa ›ሲሎት
ሱማሊኛ ተናጋሪዎቹ ደግሞ ‹Dir Dhabe› እንደሚሏት አንድ
የአካባቢው ተወላጅ አስረድቶኛል..እንደውም ለመጀመሪያ
ጊዜ የባቡር ሀዲዱን ግንባታ ተከትሎ በፈረንሳዬች
በመንደርነት ስትመሰረት አዲስ ሀረር ተብላ እንደምትጠራም
ነግሮኛል፡፡ ኑዋሪዎቾ ሲያቋላምጦት ደግሞ በአጭሩ ድሬ
ይሏታል፡፡ሌላው ሀረር ከተማን እና ድሬደዋ ከተማን
የሚያገናኘውን መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰሩት በወቅቱ
የሀረር ገዢ የነበሩት የዐጼ ሀይለስላሴ አባት የሆኑት ራስ
መኮንን ነበሩ አሉ፡፡
በድሬ ቆይታዬ የተገረምኩባቸው ነገሮች
የአካባቢዎች ስያሜ
ገንደቆሬ፤መጋላ፤ሳቢያን፤ፈጢራ፤አሸዋ
ሰፈር፤ኮኔል፤ከዚራ፤ታይዋን፤ ግሪክ ካምፕ፤ አምስተኛ…. ወዘተ
እግር ኳስ እና ድሬ
ድሬ በሀገሪቱ እግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛ ስፍራ አላት፡፡እንደ እነ
ተፈሪ፤ሀዲድ፤ኮተን፤ ጨርቃጨርቅ፤ የመሳሰሉት ታሪካዊና
ስመጥር ክለቦች ባለቤት የሆነች ከተማ በእግር ኳስ
ተጫዋቾችም እነ ሉቻኖ ቫሳሎ፤ኢታሎ ቫሳሎ፤ግርማ
ዘለቀ፤ጌታቸው ወልዴ፤ሙሀመድ ኡስማን(ሚግ)፤ተካበ
ዘውዴ፤ዳኛቸው፤ሰምኦን አባይ፤ዬርዳኖስ አባይ ፤አሸናፊ ግርማ
የመሳሰሉትን የሀገሪቱን ፈርጦች ያፈራች ታሪካዊ ከተማ ነች፡፡
የሴቶች የውበት ሳሎን
በሚገር ሁኔታ በየሃምሳ ሜትር ልዩነት በሚያስብል ሁኔታ
የሴቶች የውበት ሳሎን ተመልክቼያለው፡፡ይህ ደግሞ ደማቅ
የንግድ ከተማ ይሁን ጭር ያለ መኖሪያ አካባቢ ከኪዬክሶች
ቁጥር ልክ የውበት ሳሎን ይገኛል፡፡ በኢኮኖሚክስ ህግ
ፍላጐት ሲኖር ነው አቅርቦትም ይኖራል ተብሎ ሚታሰበው ፡፡
በዚህ መሰረት የድሬ ሴቶች በውበት ሳሎን የመገልገል
ልምዳቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ግምት ወሰድኩ፡፡
ሽቶ
የድሬ ሴቶች ማታ የአስፓልቱን ጠርዝ ይዘው ነፋሻማውን
የቆላ አየር እየማጉ ወክ የማድረግ ልማድ አላቸው ፡፡ታዲያ
በዚያን ጊዜ በተመሳሳይ ሁኔታ በሚጓዝ በእንደእኔ ዓይነት
እንግዳ ሰው አፍንጫ ዙሪያ የሚበተነው ሽቶ የተለየ ነው፡፡በቃ
አይረብሽም ፤አይከረክርም …ብቻ ይስባል፡፡ልዩ ስሜት
ይፈጥራል፡፡በእውነት የድሬ ሴቶች የሚቀብትን ሽቶ መምረጥ
ይችላሉ፡፡
መንገድ ላይ ምግብ ቤቶች
ማታ ከ12 ሰዓት ቡኃላ ድሬ በመንገድ ላይ ምግብ ቤቶች
ይወረራሉ፡፡ አንድ ሴት ምግቧን ሰፋ ባለ ሰሀን ወይም
በዘንቢል ውስጥ ባለ ላስቲክ ይዛ አስፓልት
2.7K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 06:58:00 ‍ ሳር ቤቶች በተመጣጣኝ ስብጥር ይገኙባታል፡፡አምስት የሚሆኑ ሻይ ቤቶች እና ወደ
ስድስት ኪዮክሶች አሏት፡፡ መኪናችንን አቆምንና አንዱ ሻይ
ቤት ገባን፡፡ይዞታው እንደማንኛውም የገጠር ሻይ ቤት ነው፡፡
የአካባቢውን የባሀል ምግብ ጨጨብሳ አዘዝን፤በለጡ ጥቁር
የአበሻ ጐመን በቂጣ ሲበሉ አይታ አዘዘች ፤በትልቁ ብርጭቆ
በነፍስ ወከፍ ሻይ መጣልን፤ሻዩ ትኩስ መሆኑን በሚንቧለለው
እንፋሎት ማወቅ ቢቻልም በመዳፍ መሀል አድርገው ሙሉ
በሙሉ ሲጨብጡት ግን አያቃጥልም፡፡ከአካባቢው ነፍስን
ስልብ ከሚያደርገው ቅዝቃዜም አይታደግም፡፡ ሂሳባችንን
ከፍለን ጉዞችንን ቀጠልን ፡፡
ቀጥሎ ያጋጠመን ደግሞ እስከአሁን ከመጣንበት ፍፁም
ተቃራኒ ነው፡፡ከግራም ከቀኝም በሰማይ ጠቀስ ዛፎች
የተዋቀረ ጥቅጥቅ ደን፤ዓይን ባዶ ቦታ የሚመለከተው ከፊት
ለፊት ያለውን አስር ሜትር ስፋት የማይበልጠውን ጥርጊያ
የመኪና መንገድ ላይ ሲያርፍ ብቻ ነው፡፡ደግሞ የዛፎቹ ዓይነት
እና ብዛቱ…፡፡በንፋሱ ወዲህ ወዲያ እየዘመሙ ያልተበረዘ
በተፈጥሮ ልዩ ዜማ የሚመስጥ ሽብሻቦ እያሸበሽቡ ሰማያው
ዳንስ ከሚደንሱ የሸንበቆ ዛፎቹ ጋር ተሰባጥሮ እና ተዋህዶ
ሲታይ ያደነዝዛል፡፡ሦስታችንም በተመሳሳይ መመሰጥ ውስጥ
ስለተዘፈቅን ማንም የማውራት ፍላጐት ሳያሳይ ለሰላሳ ደቂቃ
ከተጓዝን ቡኃላ ድንገት በደመነፍስ የመኪናዬን ፍሬን
ሲጢጢ..ጢ አድርጌ አቆምኩ፡፡
በለጡ በግርምት የጠየቀችኝ‹‹ምነው
ምነካህ?››የበቀደምለታው የሰብስቤ ዋሻው ታሪክ ትዝ
ሳይላት አልቀረም፡፡
በእጄ እየጠቆምኩ‹‹ፊት ለፊት ተመልከቱ፡፡››አልኳቸው፡፡
የፍራቻ ይሁን ያድናቆት በማይለይ ድምፅ‹‹አንበ..ሳ››አለ
እስክንድር:: ሦስት ናቸ፡፡ሴቷ መሀል መንገድ ዘና ብላ
ተጋድማለች፡፡ ሁለቱ ግርማ ሞገሳቸው የሚያሰፈሩት ወንዶቹ
ከኃላዋ ጎን ለጎን ቆመው ይጐማለላሉ፡፡ፀሀይ እየሞቁ
መሰለኝ፡፡ሌላ አራተኛው ከእነሱ በቅርብ ርቀት ግማሽ አካሉን
ከጫካው በማውጣት አካባቢውን ይቃኛል፡፡
በሚንቀጠቀጥ ድምፅ ‹‹ምንድነው የምናደርገው?››በለጡ
ነች የጠየቀችው፡፡
‹‹ምንም ::ባለንበት የሚሆነውን መጠበቅ ነው››መለስኩላት
‹‹ለምን ወደኃላ አንመለስም?››እስለክንድር ነው የተሸለ
ያለውን ሀሳብ ያቀረበው
‹‹ያው ነው ወደፊት ሆነ ወደ ኃላ እንቅስቃሴ ስናደርግ
ከረበሽናቸው እና ከተቆጡ ሊተናኮሉን ይችላሉ፡፡››
እስክንድር መስታወቶቹን ሙሉ በሙሉ መዝጋት ጀመረ፤እኔም
ከእሱ በማየት ገቢናውን ዘጋው፡፡ ከ7 አስጨናቂ ደቂቆች
ቡኃላ ወንዱ አንበሳ የተጋደመችውን ሴት አንበሳ በእግሩ መታ
..መታ አደረጋት እና አስነሳት፡፡ተርገፍግፋ ሰውነቷን ካፍታታች
ቡኃላ ወደ ጫካ ጉዞ ጀመረች …ተከተሏት፡፡ ሦስታችንም
በአንድ ላይ በእፎይታ ረጅም ትንፋሽ ተነፈስን፡፡ሦስት የሚሆኑ
የመረጋጊያ ደቂቃዎችን ወስደን ባለንበት ካሳለፍን ቡኃላ
ጉዞችንን ቀጠልን፡፡ ይበልጥ በተጓዝን ቁጥር ቅዝቃዜው
እየጠፋ ፤ሙቀቱ እየጠነከረ፤መሬቱ ከጥቁርነት ወደ ቀይነት
እየተለወጠ መጣ፡፡ ከጫካው ውስጥ የወጡ ዝንጀሮዎች እና
ጉሬዛዎች መንገድን ሞልተውታል፡፡ጫካው ማለቂያ
የለውም፡፡ ሻዌ ወንዝ ድልድይ ደረስን፤ ይሄ ደሎ ከተማ
የመቃረባችን ምልክት ነው፡፡
በለጡ‹‹ቆይ ዱርዬው አማዞን ነው እንዴ
ያመጣኸን?››አለችኝ፡፡
እስክንድር‹‹እኔ ልጠይቀው የነበረውን ጥያቄ ነው
የጠየቅሽልኝ፡፡መች ነው ሚያልቀው?ኢትዬጵያ ውስጥ የዚህ
ዓይነት ማለቂያ የሌላው ደን ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡
አቤት የጦርነት ፊልም ቢሰራበት››አለ፡፡
ከቀጥታው መንገድ ወደ ግራ ሚታጠፍ ሌላ መንገድ ጋር
ደረስን ..የሆነ የደበዘዘ መፈክር የተፃፈበት ትክል ድንጋይ
አለ፡፡አልነበብ አለን:: ያለበት በአካባቢው ሰው ስለነበር አንዱን
ጠራውና በኦሮሚኛ ጠየቅኩት‹‹ይሄ መንገድ ወዴት ነው
የሚወስደው?››
‹‹ወደ ሻዌ እና አንጌቱ፡፡በእግር ከሆነ ግን ዲንሾ ወይም አዳባ
ድረስ መዝለቅ ይቻላል፡፡››አለን፡፡
‹‹ይሄ ምልክት ምንድው?››
‹‹በደርግ ጊዜ ትልቅ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ነበረ፤በዚህ
መንገድ ትንሽ ከሄድክ ታገኛዋለህ፡፡ በወቅቱ ከጠቅላላው
የሀገሪቱ ክፍለሀገር የተመለመሉ ወታደሮች ይሰለጥኑበት
ነበር፡፡በኢህአዲግ ዘመን ግን ማንም ዞር ብሎ ያየው የለም፡፡
በደሎ ከተማ እና በአካባቢው የገጠር ኑዋሪዎች ከ10 ዓመት
በላይ ተዘርፎል :: እንደዛም ሆኖ አሁን ቅሪቱ አለ፤
አላለቀም፡፡›› በማለት በቁጭት አብራራልኝ፤እኔም ወደ
አማርኛ መልሼ ለእነበለጡ አስረዳዋቸው:፡ጉዞችንን ቀጠልን
፡፡ሰውና ከብት እዚህም እዛ መታየት ጀመረ፤ መኪናችን ቀዩን
አቧራ እያነሳች ትረጨዋለች፡፡ጫካው በመጠኑ ቢሳሳም
ሳይቋረጥ ደሎ ከተማ ገባን፡፡ደሎ-መና በኦሮሚያ የባሌ ዞን
አካል የሆነች በብና ምርት የምትታወቅ ሞቃታማ የወረዳ
ከተማ ነች፡፡ ደሎ-መናን አንዳንዴ ደሎ-ቡና ብለው ይጠሮታል
(የቡና መገኛነቷን ለማመልከት ይመስላል፡፡)
የሳዕታት ዕረፍት ካደረግንና ከተማዋን ዞር ዞር ብለን
ከጐበኘናት ቡኃላ ጉዞችንን ቀጠልን ፡፡ በነገራን ላይ ይህቺ
ከተማ በወቅቱ በኢትዬጵያ ካሉ የወረዳ ከተማዎች ከራሷ
ያዶት ተብሎ ከሚታወቀው መሀል ሁለት ቦታ ሰንጥቆት
ከሚያልፈው ተስገምጋሚ ወንዝ ተጠልፎ በተገደበ ግድብ
የራሷን መብራት አመንጭታ ለራሷ ብቻ የምትጠቀም ብቸኛዋ
ከተማ ነች፡፡ ይሄንን ስጦታ ያበረከቱላት የቀድሞ ወታደዊው
የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት የነበሩት ናቸው የሚል መረጃ ከአንድ
የከተማው ኑዋሪ ተገልፆልኛል፡፡
በመዳ-ወላቡ አድርገን ነጌሌ ቦረነ ገብተን አደርን፡፡መዳወላቡ
የኦሮሞ የዘር ምንጭ መነሻ ቦታ እንደሆነ ይታመናል፡፡
በማግስቱ በሀዋሳ ዞረን ሀገራችን ሻሸመኔ ገባን፡፡

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot ❥❥________⚘_______❥❥
2.7K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 06:57:18 ሰማያዊ ልብ

ምዕራፍ

አዘጋጅ ➛ በፍቅርን በቃላት
.
.
.
ማታ አስራ ሁለት ሰዓት አካባቢ የእናቴ ታናሽ ወንድም
መምጣታችንን ሰምቶ አያቴ ቤት መጣና ወደ ከተማ ወሰደን፡፡
ሊጋብዘን፡፡ከንግድ ባንክ ፊት ለፊት ባለው መንገድ ወደ
ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ የሚገኝ ፍላሚንጐ ሬስቶራንት
ይዞን ገባ፡፡ፊት ለፊት በረንዳ ላይ ከሚገኘው ሥጋ ቤት
በመስኰት ጐራ ብሎ ግማሽ ኪሎ ጥሬ ሥጋ እና ግማሽ
ኪሎ ጥብስ አዘዘና ወደውስጥ ገብተን ቦታ ያዝን ::የሚጠጣ
አኩስማይት ከኮካ ጋር ታዘዘ፡፡ወዲያው በሚያምር ሆኔታ
በትላልቁ ጐረድ ጐረድ ተደርጐ የተቆረጠ ጥሬ ሥጋ በዝርግ
ሰሀን ከሶስት ትናንሽ ቢላዎ ጋር ቀረበልን፡፡ጥቅል እንጀራ እና
የተቆረጠ ዳቦ ዙሪያውን አለው፡፡ እስክንድር እና በለጡ
አንበላም አሉ፡፡አጓቴ ሊሰማቸው አልፈቀደም፡፡
‹‹ጎባ መጥቶ ጥሬ ሥጋ ሳይበሉ መሄድ ነውር
ነው፡፡››አለቸው፡፡
እስክንድር መለሰ፡፡‹‹ሻሸመኔም እኮ ከዚህ በላይ የሚያምር
እና የሚያስጐመዥ ጥሬ ሥጋ አለ፤እኔ ስለማልወድ እንጂ፡፡››
‹‹የመሀል ሀገር ሥጋን ተወው፤አናውቅም እንዴ…? በሬውን
በኪኒን አደልበው እና ነፋፍተው፤ መልክ ብቻ፡፡ስትበላው እኮ
ውሃ ውሃ ነው የሚለው፡፡የኛዎቹ ግን በጭዱ እና በፍርሽካ
ነው ሚደልቡት፡፡እስቲ ቅመሰው››በማለት ቆርጦ አጐረሰው፡፡
እኔም አይቅርብኝ ብዬ በለጡን አስገድጄ አጐረስኳት፡፡ጥሬው
ተበልቶ ከተጠናቀቀ ቡኃላ ‹‹ይሄ ነገር ግማሽ ኪሎ
ይጨመርልን፡፡››አለ እስክንድር፡፡ አጐቴ በደስታ ተንከተከተ
‹‹አላልኩህም፡፡ይሄው ጥብሳችን መጣ እሱን ደግሞ
ቅመሰው፡፡››ጥብሱ በአመረ ሁኔታ በሸክላ ሞልቶ
ቀረበልን::የቤቱ ባለቤት የሆኑት ባልና ሚስቶች በየተራ
እየመጡ መስተንግዶቸው እንደተመቸን በትህትና
ይጠይቁናል፡፡
በመሀከል እስክንድር መጣው ብሎ ወጣና 20 ደቂቃ ቆይቶ
በቢጫ ኩርቱ ፔስታል ምንነቱን ያላወቅኩት ነገር ይዞ መጣ፡፡
ወደ ቤት ተመልሰን ስንገባ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡
አያቴ ብና አፈልታ ነበር የጠበቀችን፤የወተት ቡና፡፡ባሌ ውስጥ
ጥቁር ቡና ሚባል ነገር የጻም ቀን ካልሆነ በስተቀር ማንም
የሚጠጣ የለም፡፡የመጨረሻ ደሀ ቤት ቢሆንም ብና በወተት
ነው ሚጠጣው፡፡ቡናችንን እየማግን ሞቅ ያለ ጫወታ ይዘን
ሳለ ድንገት እስክንድር ከተቀመጠበት ተነሳና ቅድም ይዞት
የነበረው ፔስታል ካስቀመጠበት አነሳና ወደ አያቴ ተጠጋ፡፡
‹‹አኩዬ››
‹‹አቤት የእኔ ዶጮ››አለችው
እጁን ወደ ፔስታሉ ውስጥ ሰዶ ምን የመሰለ ነጭ ጥበብ
ቀሚስ ከነ ንጠላው አወጣና‹‹በሚቀጥለው እሁድ
ቤተክርስቲያን ስትሄጂ ይሄንን ልበሺና መርቂኛ፡፡›› አላት፡፡
አቤት አያቴ እና በለጡ ላይ ያየውት ፈገግታ፡፡የቀረ የምርቃት
ዓይነት የለም::ለሃያ ደቂቃ ያለማቋረጥ መረቀችው፡፡የያዕቆብ
እና የኤሳው ታሪክ ትዝ አለኝ፡፡ ኤሳውስ ምስር ወጥ አግኝቶል
እኔ አለው እንጂ ብኩርናዬን በነፃ የተነጠቅኩ፡፡ ተሰማኝ ፡፡ ይሄ
እስክንድር የሚባል ልጅ የእኔን ምርጥ ምርጥ ነገሮች
እስከመቼ ሲሰርቀኝ ይኖራል?እየደበረኝ ቢሆን ከሻሸመኔ ገዝቼ
ያመጣውትን፤ይደርሳል በሚል ስሜት እስከአሁን
ያላስረከብኮትን ቀሚስ ፤ሹራብ እና እናቴ የላከችላትን ጋቢ
አስረከብኳት፡፡ሁለት ደቂቃ መረቀችኝ፡፡ለሁለት ደቂቃ ብቻ፡፡
የነበራትን ምርቃት ሁሉ አስቀድማ ለዚህ እርጉም አሸክማ
ጨርሳዋለች መሰለኝ፡፡
በሦስተኛው ቀን የመልስ ጉዞ ጀመርን፤በመጣንበት መንገድ
አይደለም በተቃራኒው፡፡የተፈጥሮ ድንቅ ዝማሬ፤ቅጥልጥል
የተራራ ሰንሰለት፤ እንደ ሀይቅ የተንጣለለ ደን እኚ ሁሉ ገና
ከከተማ ሳንወጣ ነው ፊታችን የተጋረጡት ፡፡ሁለቱም ነቃ ያለ
ስሜት ላይ ቢሆኑም እኔ ደግሞ በተቃራኒው ትንሽ
ተደብቸያለው፡፡
እስክንድር‹‹አንተ በላቸው..ታድለህ!!!›› አለኝ
‹‹እንዴት?››
‹‹የምትወደድ አኩዬና ደስ የምትል የተትረፈረፈ ተፈጥሮ
የሞላት ሀገር አለችህ፡፡ ››አለኝ
‹‹አንተም ከእኔ በላይ ታድለሀል፡፡››አልኩት፡፡
በተራው‹‹አንዴት?›› አለኝ
‹‹በዓለም ላይ ቁጥር አንድ የሆነች ምርጥ ፍቅረኛ
አለህ፡፡››አልኩት
ዞር ብሎ በአትኩሮት ተመለከታት፡፡ንግግሬ እውነት መሆን እና
ያለመሆኑን እያጣራ ያለ ይመስላል፡፡እሷ በንግግሬ አፍራ
መሰለኝ ፊቷ ቀላ፡፡
‹‹አዎ፡፡እሱስ እውነትህን ነው፡፡››አለኝ አና የአካባቢውን ውበት
ወደመቃኘቱ ትኩረቱን መለሰ፡፡ ዳገቱ በጣም እየከበዳት
ስለሆነ መኪናዋ በዝግታ ነው የምትሄደው፡፡ መንገዱ ግራና
ቀኝ በባህር ዛፍ እና በጽድ ጥቅጥቅ ደን ተሸፍኗል፡፡ወደ ፊት
በተጓዝን ቁጥር ከፍታው እየጨመረ ነው የሚመጣው፡፡
የፓርክ ክልል ገባን ፡፡የቴሌ ማይክሮዌብ የተተከለበት አካባቢ
ስንደርስ ደን የሚባል ነገር ጠፋ፡፡ ሀይለኛ ቅዝቃዜ እና ትናንሽ
ቁጥቋጦ ብቻ፡፡በተራራው ላይ ሰፊ ሜዳ ይታያል፡፡አንገሶን
አልፈን ሳነቴ መሀል ላይ ስንደርስ መኪናዋን አቆምኮት እና
ሞተር ሳላጠፋ ወረድኩ፡፡‹‹ውረዱና ትንሽ ዘና በሉ
እንግዲህ፡፡››አልኳቸው፡፡
በለጡ ‹‹አንተስ አለች?››
‹‹እኔም ዘና እላለው፡፡››
‹‹አይ ሞተሩን አላጠፋሀውም ብዬ ነዋ?››
‹‹አታይውም እንዴ ቅዝቃዜውን፤እንኳን የሞተር የሰው ደም
ያቀዘቅዛል፤ብኃላ አልነሳም ቢለኝስ?››አልኳት፡፡ ከገቢና ጃኬት
አወጣውና ለበስኩ፡፡ሁለተኛውን ለበለጡ ሰጠዋት‹‹ልበሺ
ይበርድሻል›› አልኳት ውስጤ እየተደሰተ፡፡ምክንያቱም
እስክንድር በካኔቴራ እየተንዘፈዘፈ ነበር፡፡ ከሻሸመኔም ስንነሳ
ጃኬት ሚባል ነገር አልያዘም ፡፡እኔን በሁኔታዎች እንደጠበሰኝ
እሱም በዚህ ብርድ ይጠበስ::
ሲያናድድ ‹‹እኔ ገና ስንነሳም በርዶኝ ስለነበረ እንደ ቁም ሳጥን
ደራርቤ ለብሼያለው፤እንካ አንተ ልበሰው፡፡ ›› ብላ የሰጠዋትን
ጃኬት አስረከበችው ::የተወሰኑ ቀይ ቀበሮዋች ለምግብነት
አይጦችን ከጉድጓድ ሲወጡ አድፍጠው ሲጠባበቁ፤ሌሎቹም
ከወዲህ ወዲያ ሲራወጡ አየን፡፡በየቦታው የሚንኮለሉ ጥርት
ያሉ ምንጮችም ይታያሉ፡፡
‹‹ይሄንን እኮ ቀጥታ አሽገው ለገበያ ቢያቀርቡት ሰው ሁሉ
እየተረባረበ ነበር የሚገዛው፡፡›› በማለት የውሃውን ጥራት
አደነቀች በለጡ::እኔም ስለአካባቢው የማውቀውንም
የሰማውትንም ለሁለቱም ነገርኰቸው፡፡ ወደ መኪናችን ገባንና
ጉዞችን ቀጠልን፡፡በቅዝቃዜ የሚያደነዝዘው ሜዳማው የሳነቴ
ክፍል ካለቀ ቡኃላ ቁልቁለቱን ተያያዝነው፡፡እጅግ የሚያስፈራ
ከገነት ተራራ ወደ ሲኦል ሸለቆ የመውረድ ያህል ስሜትን
በአስጨናቂ ውጥረት ፈጥርቆ የሚይዝ ምትሀታዊ መልክአ
ምድር ከፊታችን ተዘረጋ፤መንገዱ እጅግ አስፈሪ እና
ቁልቁለታማ ከመሆኑም በላይ ጠመዝማዛ ነው ፡፡መኪናው
ሄዶ ሄዶ ይጠመዘዝና ተመልሶ እዛው ነው፡፡ከትናንት ወዲያ
ስንመጣ የሰብስቤን ዋሻ በተመለከቱበት ወቅት እንደዛ
ሲፈሩና ሲደነቁ የነበሩት ሁለት ፍቅረኛሞች ዛሬ ደንዝዘዋል፡፡
እዚህች ላይ አንድ የጋሼ ጥቅስ ትዝ አለቺኝ
‹‹እግዜር ይኖር ይሆን…..?ብዬ ምጠራጠረው
ስለአስደማሚው የተፈጥሮ ውበት ሳሰላስል ብቻ ነው፡፡
ተፈጥሮ የእግዚብሄር የህልውናው አሻራ፤የመዳፉ ንባብ
ይመስለኛል፡፡›› ነበር ያለው፡፡ እውነትም የእግዚያሄር አሻር …
እስክንድር‹‹አንተ ሊማሊሞን አይደል እንዴ
የሚመስለው?››አለ፡፡
‹‹ሊማሊሞን አይተኸዋል እንዴ?››ጠየቅኩት
‹‹አይ በቴሌቨዥን ነው ያየውት፡፡ያኛው አስባልት ስለሆነ ነው
እንጂ ተመሳሳይ ናቸው፡፡እንደውም ይሄኛው አስፈሪ ብቻ
ሳይሆን በጣም የሚያስደምም ነው››አለ
በጥንቃቄ እና በዝግታ ለአንድ ሰዓት ያህል ከነዳው ቡኃላ ሪራ
የምትባል አነስተኛ የገጠር ከተማ ደረስን፡፡ ይህቺ የገጠር
ከተማ በጎባ እና በደሎ መና መካከል የምትገኝ አማካይ ስፍራ
ነች፡፡የተወሰኑ ቆርቆሮ ቤቶች እና
2.6K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 06:24:50 ​በጣም ወደ ውስጥ የገባ
ነው፡፡እዛ አካባቢ ትንሽ ጉድጓድ የተቆፈረ ይመስላል፡፡ፀጉሯን
አወለቀች፡፡ደነገጥኩ፡፡ቅድም ሳገኛት እውነተኛ ፀጉሯ
መስሎኝ ነበር፡፡የእሷ ፀጉር በጣም አጭር ነው፡፡ ከሁሉም
ነገሯ የሳበኝ ያደረገችው ፓንት ነው፡፡ቀይ ፒኪኒ ፓንት ነው
ያደረገችው፡፡በፊልም ካልሆነ በስተቀር ሴት ልጅ ፒኪኒ ፓንት
አድርጋ በአካል ሳይ የመጀመሪያዬ ነው፡፡በቃ በጣም ነው
የሚያምርባት፡፡ በምናቤ ፓንቷን ከእሷ አውልቄ በለጡ ሰውነት
ላይ አጠለቅኩላት፡፡ በብልቴ ደም ታጨቀ፤አፌን ምራቅ
ሞላው፡፡‹‹ነገ ይሄንን ፓንት ለበለጡ እገዛላታለው›› ወሰንኩ፡፡
ልጅቱ አንሶላውን ገልጣ ከውስጥ ገባች፡፡መልሳ ተነሳች
ልብሷን ወደ አስቀመጠችበት ጠረጵዛ ሄዳ ከጃኬት ኪሷ
ኮንደም አወጣች እና አልጋው አቅራቢያ የሚገኘው ኮመዲኖ
ላይ አስቀመጠች፡፡ ብዥ እያለብኝ ነው፡፡ሰክሬያለው፡፡ግን
ደግሞ የምሰራውን ሁሉ አውቃለው፡፡ ልተኛ ወደ አልጋው
እየሄድኩ ሳለው ከቤ ትዝ አለችኝ‹‹የእኔ ልጅማ እንዲህ
አታደርግም…›› ስትል ሰማዋት፡፡በቃ የእውነት ሰማዋት፡፡
የገረመኝ ግን ከእናቴ ይልቅ የእሷ ድምፅ ለምን ቀድሞ
በመንፈሴ እንደሰረገ ነው?አልጋ ልብሱን ከላይ ገፈፍኩ እና
አንድ ትራስ ይዤ በተቃራኒው አቅጣጫ ተዘቅዝቄ ተኛው፡፡
ልጅቷ ተነስታ ቁጭ አለች፡፡ መልሳ ተኛች፡፡ ሁሌታዬ ግራ
ያጋባትም ያበሳጫትም መሰለኝ፡፡
‹‹ያምሀል እንዴ ..ምን እየሰራህ ነው?››
‹‹ምንሽ ተነካ ?አርፈሽ ተኚ፡፡ከደበረሽ ደግሞ መሄድ
ትቺያለሽ፡፡››
‹‹ሳልሰራ መብላት ይደብረኛል››አለችኝ ፡፡ንግግሯ በጣም
አሳቀኝ፡፡ ቀጠለች …‹‹ለሊት ግን ብርህ ሲቆጭህ መጥተህ
እንዳትረብሸኝ፡፡የምታደርገውን አሁኑኑ አድርግ እና ልተኛበት››
አልመለስኩላትም፡፡ አልጋ ልብሱን ተሸፋፈንኩ
ጥዋት የስልክ መንጣረር ነው ከእንቅልፍ ያባነነኝ‹‹አንተ ዱርዬ
የት ነህ?››በለጡ ነች፡፡
‹‹ተኝቼያለው››
‹‹በል ተነሳ እና እንሂድ››
‹‹ምነው ሰዓት ስንት ሆነ?››
ተነጫነጨች፡፡‹‹አንድ ሰዓት ነው …ግን በቃ ወደ አያትህ ጋር
መሄድ ፈለግኩ››
የሆነ ልክ ያልሆነ ነገር ሸተተኝ፡፡የማታውቃት የእኔ አያት
እንዴት እንዲህ ልትናፍቃት ቻለች?ልጅቷ በተኛችበት ሹልክ
ብዬ ጥያት ወጣው፡፡
ስደርስ ከሆቴሉ ፊትለፊት ባለው ሰፊ በረንዳ ቁጭ ብለው
የጥዋት ፀሀይ እየሞቁ የግቢውን አስደሳች ተፈጥሮ ሲቃኙ
ደረስኩ፡፡በተለያ በዛፎች እና በአበባዎች ያጌጠውን ውብ ግቢ
ቢያስደምማቸው አይገርምም ፡፡ አቀማመጣቸው ግን የሆነ
ችግር እንዳለ ያሳብቃል፡፡ በአንድ በኮንክሪት በተሰራ አግዳሚ
ወንበር ላይ ጐን ለጐን የተቀመጡ ቢሆንም በመካከላቸው
የ30 ሳ.ሜ ክፍተት አለ፡፡ ፍቅረኛሞች ልባቸው በ 30
ኪ.ሜትር ካልተራራቀ በስተቀር አካላቸው በ30 ሴ.ሜ
ሊራራቅ አይችልም፡፡የሆነ ደስ የሚል ስሜት ወረረኝ፡፡
ተጠጋዋቸው፡፡ሰላምታ ተቀያየርን፡፡ የበለጡ ፊት ጨልሽቷል፡፡
ያለቀሰችም ትመስላለች፡፡ መልሶ ከፋኝ::
‹‹ቁርስ በላችሁ?››
‹‹አልበላንም እየጠበቅንህ ነው››እስክንድር ነው በተጐተተ
ድምፅ የመለሰልኝ፡፡ኩምሽሽ ብሏል፡፡ትናንት ተነፋፍቶ
የነበረው ሰውነቱ ዛሬ ወደ ውስጥ የተሰበሰበ መሰለኝ፡፡‹‹ብር
አምባር መስበር እንዲህ ያከሳል እንዴ?ኸረ ባገኝም
አልሞክረው ›› አልኩ በውስጤ፤ከቅናት የተፀነሰ የውሸት
ፉከራ ፡፡ ወደ ሬስቶራንቱ አመርተን ቁርስ አዘዝን፡፡እጄን
ልታጠብ ስነሳ በለጡ ተከተለችኝ፡፡እየታጠብን ጠየቅኳት
‹‹እንዴት ነው? የደም ሻሹ ይሰጠና?››
‹‹ድንቄም የደም ሻሽ ማን ችሎት!››
‹‹ምነው?››
‹‹ባክህ እንትኑ በብረትም ቢደገፍም ሊቆም አልቻለም››
‹‹ወይኔ ወንድሜን እና በቃ..?››
‹‹አዎ እንዲሁ ስንቦጫጨር አደርን፡፡እንዴት ይደረግ፤በጣት
አይወሰድ፡፡››
‹‹ብርዱ አኮማትሮበት ይሆን?ወይ ነዶ…!!!የዚያን ጊዜ ሚዜ
ቢኖር?››
‹‹ሚዜማ አንተ ነበርክ፤ ወንድሜ ሆንክ እንጂ››
‹‹ታዲያ ምን አለበት? ሳራ እኮ ለአብርሀም ሚስቱ ብቻ
ሳትሆን እህቱም ነበረች፡፡››
‹‹እሱ ድሮ ነው፤ አሁን ግን አይፈቀድም፡፡››ብላኝ መንገዷን
ቀጠለች ፡፡ ተከተልኳት፡፡
*
ከቁርስ ቡኃላ ቀጥታ ማሪያም ሰፈር ወደሚገኘው የአያቴ ቤት
ነው ያመራነው፡፡ስንደርስ በእልልታ ተቀበለችን፡፡ስለበለጡ
ከዚህ በፊት ስለነገርኮት ለማስተዋወቅ ብዙም
አልከበደኝ፤እስክንድርን ምኔነው ብዬ እንደማስተዋውቀው ግራ
ገብቶኝ ‹‹አኩዬ ይሄውልሽ ይሄ እስክንድር ይባላል፡፡ በጣም
የምወደው ጓደኛዬ ነው፤ስላአንቺ ብዙ ጊዜ አጫውተው
ስለነበር ካላየዋት ብሎ ስላስቸገረኝ ነው ይዤው
የመጣውት፡፡››
‹‹ጐሽ ደግ አረክ፡፡እንኳንም ይዘኸው መጣህ፡፡ምን ዓይነት
ጀግና እና ጠንካራ እናት እንዳለህ በደንብ ይረዳል››በማለት
አገላብጣ በመሳም ሶስተኛ እንግዳዋ አድርጋ ተቀበለችው ::
አቤት ምርጥ ጓደኛዬ ነው ስል አፌን እንደመረረኝ፡፡
አያቴ የሰባ ስምንት አመት አዛውንት ብትሆንም የሚገርም
ጥንካሬ አላት፡፡ጥናካሬዋ ደግሞ የአካልም የመንፈስም ነው፡፡
በዛ ላይ ፍፁም የተረጋጋች እና ትግስተኛ ነች፡፡በምንም ነገር
ስትነጫነጭ እና ስትማረር ሰምቼ አላውቅም፤ በዚህ ጉዳይ
ከእናቴ ጋር ፍፁም ተቃራኒ ናቸው፡፡አኩዬ ብዬ ነው
የምጠራት..‹አኰ› የሚለው የኦሮሚኛ ቃል ሲሆን አያት
ለሚለው የአማርኛው ቃላ አቻ ፍቺ ነው፡፡ ‹አኩዬ› እንግዲህ
አያቴ ለማለት ነው፡፡
የሚገርም መስተንግዶ አደረገችልን ፤ትንሽ ከተረጋጋን ቡኃላ
በትልቅ ጓድጓዳ ሳሀን ገንፎ ቀረበልን፡፡መሀሉ በሰፊው
ተሸንቁሮ ከበርበሬ ጋር አንድ ላይ ተማስሎ የተደባለቀ ፈሳሽ
ቅቤ ተሞልቶበት፡፡በማንኪያ እየዛቅን መብላት ጀመርን፡፡
በተለይ የእስክንድር አበላል ሚያስደነግጥ ነው
‹‹አኩዬ እንዴት ይጣፍጣል መሰልሽ፤አንቺ ነሽ የሰራሽው?››
አላት፡፡ እንዴት በሸቅኩ መሰላችሁ አንደኛ አኩዬ ብሎ
መጥራቱን፡፡ሁለተኛ አንቱታውን መርሳቱ፡፡
በፈገግታ‹‹አዎ፡፡እኔ እናትህ ነኝ የሰራውት፡፡››አለቺው
‹‹አኩዬ ሙች እኔ እንዲህ የሚጣፍጥ ገንፎ በልቼ
አላውቅም፡፡ማንም ያንቺን ያህል መስራት እንደማይችል ምዬ
እናገራለው››አላት፡፡
ጣልቃ ገብቼ በንዴት ጠራውት፡፡‹‹እስክንድር››
ከአያቴ ጋር የጀመረውን ወሬ ስላቋረጥኩት ቅር እንዳለው
በፊቱ መጨማደድ እየነገረኝ፡፡‹‹አቤት›› አለ፡፡
‹‹አኩዬ አይደለም ስሞ፡፡ ኦሮሚኛ አታውቅ እንደሆነ አኩዬ
ማለት አያቴ ማለት ነው፡፡..ስሟ ጫልቱ ነው፤ እትዬ ጫልቱ
ብለህ ጥራት፤አንቱታንም አክልበት፡፡››
በለጡ ደነገጠች እና በእጇ የያዘችውን ባዶ ማንኪያ ወደ
ገንፎው ከመላክ አዘገየችው
‹‹ኸረ በናትህ በላቸው...ለአንተ አያትህ ከሆነች ለእኔም አያቴ
ነች፡፡አኔ በጣም ስለወደድኮት አንቱም ጫልቱም አልላትም፡፡
አኩዬ አይደል››አላት ድጋፍ በመፈለግ ወደ እሷ ዞሮ በዓይኖቹ
እየተለማመጣት፡፡
እሷም በፈገግታ ታጅባ‹‹ጐሽ የእኔ ልጅ በጣም ወደድኩህ፡፡
እሱን አትስማው ቀንቶ ነው:: አኩዬ ብለህ ጥራኝ፡፡ አንቺም
እንደዛው(ወደ በለጡ ዞራ)እስቲ ያልቅብህ እንደሆነ
እናያላን››በማለት በንዴት ላይ ንዴት ጨመረችብኝ፡፡ዝም ብዬ
በማንኪያዬ እየቆነጠርኩ መብላት ቀጠልኩ፡፡..እርጎ በትላልቅ
ብርጭቆ ተቀዳልን፡፡እኔና በለጡ አንድ አንድ ስንጠጣ
ከርሳሙ እስክንድር ሁለት ብርጭቆ ገለበጠ፡፡እንዳይተረተር
ፈራውለት፡፡

ይቀጥላል....

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot ❥❥________⚘_______❥❥
2.7K views★ ŊąøŁą şəłəçŧívę ★, 03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ