Get Mystery Box with random crypto!

💕 ፍቅርን በቃላት 💕

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrn_be_kalat — 💕 ፍቅርን በቃላት 💕 ፍ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrn_be_kalat — 💕 ፍቅርን በቃላት 💕
የሰርጥ አድራሻ: @fkrn_be_kalat
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.03K
የሰርጥ መግለጫ

💝 ፍቅርን በቃላት 💝
♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
💞የፍቅር ቃላት ሁሌም አሸናፊ ናቸው💞
For any promotion ➢ @Naolviva ✌
For spam 👇
@fkrn_be_kalat_bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 19:58:44 @phylosophy_gora
@phylosophy_gora
@phylosophy_gora
285 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, edited  16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:48:01 <<ጠይሙ ባሌ !>> ክፍል.......9 የመጨረሻው ክፍል (በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ) አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት . . . .....ግራ ግብት ብሎኝ ተገትሬ ቀረሁ...ባል እንዴት ይሸኛል? ደህና ሁን ወይስ መልካም እድል ተብሎ? ይጨበጣል: ይታቀፋል ወይስ ይሳማል? ወዳጅ ነው ጠላት? ውስጤ ከሚተራመሰው ሙግት ባሌ ተመለሰና…
492 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:07:58 <<ጠይሙ ባሌ !>>

ክፍል.......9

የመጨረሻው ክፍል

(በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.


.....ግራ ግብት ብሎኝ ተገትሬ ቀረሁ...ባል እንዴት ይሸኛል? ደህና ሁን ወይስ መልካም እድል ተብሎ? ይጨበጣል: ይታቀፋል ወይስ ይሳማል? ወዳጅ ነው ጠላት? ውስጤ ከሚተራመሰው ሙግት ባሌ ተመለሰና ገላገለኝ::
የደም ስሮቹ ግንባሩ ላይ ተግተርትረዋል...ስንብቱ ለሱም ቀላል አልሆነም:: እንዴት ይሆናል? በዚች አለም ላይ አለኝ የሚለውን ነገር ሁሉ ተሰናብቶ: ቁልፉን አስረክቦ ለመጨረሻ ጊዜ በሩን አቁዋርጦ ሊወጣ ነው:: 

"በ-ቃ...መ-ሄ-ዴ...ነ-ው" አለ በተሰባበረ ድምፅ: አንጀቴ ተላወሰ: ቅር ልለው ግን በፍፁም አልፈለኩም: ኧረ በጭራሽ:: ኩራቴ የት ሄዶ: ሌላ ሴት ጋ ለመሄድ የተነሳን ወንድ ከምለምን ሞቴን እመርጣለሁ: አዎን ለምወዳቸው ልጆቼ ስል እንኩዋን የማላደርገው አንድ ነገር:: 

"ም-ን...እ-ን-ደ-ም-ል-ህ...አ-ላ-ው-ቅ-ም....መ-ል-ካ-ም...እ-ድ-ል?
ያባራው እንባዬ መዥጎድጎድ ሲጀምር እሱም ግራ ተጋብቶ ቆመ::

"እ-ና-ት-ዬ...ይ-ቅ-ር-ታ" ምንም አልመለስኩለትም:: እያመነታ ወደበሩ ተራመደና ሻንጣዎቹን እያነሳ ዞር ብሎ አየኝ: ከቆምኩበት አልተነቃነቅሁም:: "በ-ሩ-ን...ቆ-ል-ፊ-ው"

ሲቃ እየተናነቀኝ ወደበሩ ሄድኩ: አንድም ቃል አልተናገርኩም... ምን ልናገር እችላለሁ? ስልኩ የወደቀበት እንዲታየው የውጪውን መብራት አበራሁለትና በሩን ዘጋሁት: ቆለፍኩት: ተደግፌው ወደመሬት ተንሸራተትኩና ጮኬ አለቀስኩ: ለትዳሬ: ለራሴ: ለባሌ: ለልጆቼ...አዎን ለልጆቼ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ:: ለምን ያህል ጊዜ እንደቆየሁ አላውቅም: እዛው በሩ ስር እንደተቀመጥኩት ቤቴን መቃኘት ጀመርኩ: ግድግዳው ላይ የተሰቀሉት ፎቶዎቻችን ላይ አፈጠጥኩ: ከዛም አይኔ እዛ ወረቀት ላይ አረፈ::

ተነስቼ ወደጠረጴዛው አመራሁና አገላበጥኩት: እንደተነጋገርነው የባንኩን ድርድር ለውጦታል:: ግን ያ ድርድር አሁን ፋይዳ የለውም: አሁን ባለሙሉ መብትዋ እኔ ነኝ:: ግን ደግሞ መልሼ አሰብኩ: እንኩዋን ብር እሱም ሄዷል:: ብእር ከቦርሳዬ አወጣሁና እያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማዬን አኖርኩ::
በአንድ ፊርማ የገባሁበትን ትዳር በአምስት ፊርማ ተሰናበትኩት:: የመጨረሻው ፊርማዬ ላይ ማህተም ይመስል እንባዬ ተንጠባጠበበት::

ልጆቼን ቃኘሁና በራቸውን ክፍት ትቼ ወደራሴው መኝታ ቤት ገባሁ:: ቅድም ለግብዣው እየለካሁ ያሽቀነጠርኩዋቸው ልብሶች አልጋው ላይ ተከምረዋል:: በቁሜ ዘፍ ብዬ በጀርባዬ ተዘረጋሁባቸውና ጣራው ላይ አፈጠጥኩ:: ቅድም ልብሶቼን ስለካ የነበረኝ ህይወቴና የአሁኑ ህይወቴ አራምባ ቆቦነት አስገርሞኝ "ተ-ፈ-ፀ-መ" ብዬ አንሾካሸኩ:: ከቃሉ ጋር የሆነ እንግዳ ስሜት ተናነቀኝ:: "በ-ቃ...ተ-ፈ-ፀ-መ" አልኩኝ ደገምኩና ከፍ ባለ ድምፅ:: የሚተናነቀኝ ስሜት ፈንቅሎኝ ሊወጣ ታገለኝ::

"ማበዴ ነው እንዴ?" እራሴን ጠየኩ....በዚች ቀውጢ ሰአት እንዲህ አይነት ስሜት...አፌን አፍኜ ያዝኩት:: ግን አልቻልኩትም...አሸነፈኝ...አልጋዬ ላይ እንደተዘረርኩ ለቀቅሁት:: "ቂቂቂቂቂቂ.....ካካካካካካካካ" ሳቄ ቤቱን አናጋው ::

አዎን ተ-ፈ-ፀ-መ! በቸር ያገኛኘ?ን!
እወዳችኋለሁ !!!

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥
590 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:41:45 <<ጠይሙ ባሌ !>>


ክፍል.......8

(በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.
"እውነቱን ማወቅ ትፈልጊያለሽ?" አለኝ ካንጋጠጠበት ተመልሶ: የባሰ አጥብቆ እየያዘኝ:: 
"እጄን ልቀቀኝ" አልኩ እንደመታገል እያልኩ:: 
"እንግዲህ ምን የሚያደባብቀን ነገር አለ? ማወቅ ትፈልጊያለሽ ወይ?" በድጋሚ ጮሆ ጠየቀኝ: ፍርሀት ሰውነቴን አንዘፈዘፈው: በአዎንታ እራሴን አወዛወዝኩለት:: 

"ልጆቻችን ከመወለዳቸው በፊት የህይወትሽ እምብርት እኔ ነበርኩ: ትሰጪኝ የነበረው ፍቅርና እንክብካቤ....ኦህህ" አለ አይኑን አቡዞ "ከስራ ስገባ ፈገግታሽን ለማየት እንዴት እቸኩል ነበር" የትዝታ ፈገግታ ላፍታ ፊቱ ላይ ብልጭ አለች::

"ልጆቻችን ሲመጡ ግን ያ ሁሉ እልም ብሎ ጠፋ...በልጆቹ ታጠርሽ:: ሁልጊዜ ደክሞሽ: ሁልጊዜ ተኮሳትረሽ: ሁልጊዜ እራስሽን ጥለሽ ሆነ የማገኝሽ" መሬት መሬቱን አየ "የሚያሙዋሙዋኝ ፈገግታሽን የማየው ከልጆቻችን ጋር ስትጫወቺ ብቻ ሆነና እራሴን አገለልኩ: ለገዛ ቤተሰቤ እንግዳ ሆንኩ" ዝም አለ:: 
"ጨርሰዋ!" አፈጠጥኩበት:: 

"አህህህ...እናት... ሌላ ምን ልበልሽ? የማልወጣው ማጥ ውስጥ ገባሁና አረፍኩት" አይኖቹን ከአይኖቼ አሸሻቸው::
"የምን ማጥ? ፍቅር ያዘህ? ሌላ ሴት አስረገዝክ?" እንደው አፌ ለፈለፈ እንጂ እውነቱን መስማት አልፈለኩም: የቆሰለችው ነፍሴ ልትሸከመው አትችልም: እሱም አልመለሰልኝም::

እጄን ለቅቆ ጃኬቱን ከወንበሩ አንስቶ እየለበሰ 
"እንግዲህ ሁሉም በእጅሽ ነው" አለ ወረቀቱን እያየ "ስልኬን ብትሰጪኝ ደስ ይለኛል: ቁልፍሽ ይኸው" ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው:: ምንም አልተናገርኩም: ከቆምኩበትም አልተነቃነኩም:: 
"ልጠብቅ? ልሂድ?" አለ በሚለማመጥ ድምፅ...የመኪናውን ቁልፍ ከመስቀያው እያወረደ:: አመነታሁ: ስልኩን ያዝኩ አልያዝኩ ዋናው ሰው እየሄደ አይደል:: ባሌ ላይ አፈጠጥኩ...እንግዳ ሆነብኝ:: 
"የቤቱን ቁልፍ ስጠኝ...አንተ ጋ ያለውን" አልኩ እጄን ዘርግቼ:: 
"ም-ን?"

"አሁን ሌላ ቤት አለህ: የቤቴን ቁልፍ ስጠኝ" እጄን አላጠፍኩም "ከዛ ስልክህ የት እንዳለ እነግርሀለሁ"
ጭንቅላቱን እያወዛወዘ አንድ ቁልፍ እጄ ላይ አስቀመጠልኝ:: 
"የጉዋሮውንም" አልኩ እጄን ሳላጥፍ: ሌላ ቁልፍ አስቀመጠልኝ::
"ኦ እረስቼው...የመኪናዬንም" በረጅሙ ተነፈሰና ከቁልፍ መያዣው ጋር እየታገለ በትዝብት አይን አየኝ:: ቁልፎቹን ከተቀበልኩ በሁዋላ ስልኩ ያለበትን ነግሬው በሩ አጠገብ ቆሜ እስኪወጣልኝ ተጣደፍኩ:: 

"ልጆቼን ልሳም?" ሲቃ የተናነቀው ጥያቄው ከምጋልብበት የእልህ ፈረስ በድንገት አፈረጠኝ:: አህህ...ልጆቻችን! ምኑንም የማያውቁት: ምኑም ውስጥ የሌሉበት: ግን ደግሞ ከሁለታችንም በላይ የሚጎዱት ምስኪኖች:: ወደመኝታ ቤታቸው ሲሄድ እንባ ባቆሩ አይኖቼ ሸኘሁት:: 

ይቀጥላል .....



የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥
306 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:20:30 ፍቅርን በቃላት

"ምንም አይነት ስሜት ከሌለህ ያፈቀርክ አታስመስል!
ምክንያቱም ፍቅር እኛ ልንቆጣጠረው የምንችለው ሃይል አይደለምና"


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄



አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@fkrn_be_kalat
ፍቅርን በቃላት
┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
511 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:12:41 ፍቅርን በቃላት

በማንኛውም ፍቅር ውስጥ ጦርነት አለ። ሴቷ መዋጋቱንም ሆነ ማፈግፈጉን በሚገባ ስታውቅበት፤ ወንዱ ግን ጦርነት ውስጥ መሆኑን እንኳን ከነአካቴው አያውቀዉም። ለዚህም ነው የሚጠጣ ካገኘ ባይጠማውም ይጠጣል። ሴት ካየም ባያፈቅርም ፍቅርን መስራት ይችላል። ሴቷ ግን ቢጠማት እንኳን የምትጠጣውን ትመርጣለች ከማፍቀሯም በላይ መፈቀሯን አጥብቃ ትከታተላለች።

የአሜሪካ የሳይኮሎጂ "አባት" ዊልያም ጀምስ


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄



አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@fkrn_be_kalat
ፍቅርን በቃላት
┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
487 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:05:03 ፍቅርን በቃላት

ፍቅር ማለት በምትወዱት ሰው ነፍስ ውስጥ ራስን መግደል ነው!"
-ኦሾ


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄



አሁኑኑ ሼር አድርጉ

@fkrn_be_kalat
ፍቅርን በቃላት
┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
440 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, edited  06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 06:39:48 <<ጠይሙ !>>


ክፍል.......7

(በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.
ልጆቼ ጋር እንኳን አልገባሁም: የመኝታ ቤት በራቸውን ዘግቼ ብቻ ተመለስኩ:: የማጠፋው ጊዜ የለኝም:: ተንደርድሬ የእጅ ስልኩን ከጃኬቱ ኪስ ውስጥ አውጥቼ ወደ መታጠቢያ ቤት አፈተለኩ:: በሩን ቆልፌ መጨረሻ ላይ የደወለው ቁጥር ላይ አፈጠጥኩ: የከተማው ኮድ ለስራ ሲላክ ከሚያርፍበት ሆቴል ስልክ ቁጥር ጋር ተመሳሰለብኝ:: በአጉሉ ስለላዬ ከራሴ ጋር እየተሙዋገትኩ መልእክቱን ለመስማት አንደኛውን ቁልፍ ተጫንኩት:: ገና የሴት ድምፅ ስሰማ ልቤ ወደሆዴ ተንሸራተተች: አቅለሸለሸኝ: ወበቀኝ: አዞረኝ:: እንደምንም ብዬ የተከደነው መፀዳጃ ላይ ተዘረፈጥኩ:: "ቤቢዬ..." አለች ሙልቅቅ ባለ ድምፅ "ምነው ጠፋህ? ስልኩን መቼም ታጠፋዋለህ ብዬ ነው ደፍሬ የደወልኩት:: መንገድ ስትጀምር ደውልልኝ...እሙዋዋዋ!" ጆሮዬን አላመንኩም...የምትስረቀረቀውን ሴትዮ አፌን ይዤ ደግሜ ሰማሁዋት "ምን?!" ለራሴው አንሾካሸኩ:: ለካስ ገደሉም ውስጥ ገደል ኖሮልኛል: በጥቃት ላይ ጥቃት:: ይህን ሁሉ ጊዜ ባሌ ስራ እየሄደ ነው ብዬ ስንቅ እያዘጋጀሁ ሌላ ሴት ጋ ኖርዋል ስልክ የከረምኩት: ቅናት እራሴ ላይ ወጣ:: "አፈር አባትዋ ትብላና" እየዛትኩ ቁጥሩን ተጫንኩት:: "ቤቢዬዬዬዬ....." አለች የጠይሙ ባሌ ሞልቃቃ...ፍንድቅ ብላ ስልኩን እንዳነሳች:: ምላሴ ተሳሰረ: በህልሜ ይሆን? "ሀሎ?! ባክህ አትቀልድ...ቂቂቂ" ትንፋሼ እየተቆራረጠ ለመሳደብ ሞከርኩ "አንቺ...አ-ን-ቺ...ር-ካ-ሽ" ስልኩ ተጠረቀመ: እኔ ግን ጆሮዬ ላይ እንደለጠፍኩት አፌን ከፍቼ ቀረሁ::

ማሰብ አቃተኝ:: ባሌ ወደሳሎኑ ሲመለስ ኮቴውን ሰማሁ:: አሁን ምንድን ነው የምለው? አይኑን እንዴት ነው የማየው? ለሱ እኔ አፈርኩ:: ጊዜ እየተሽቀዳደመኝ ነው: የኔ አይምሮ ደግሞ ለገመ:: ይህንን ስልክ መደበቅ አለብኝ: ግን የት? የት? የት? ባሌን ለማታለል የመፀዳጃ ቤቱን ውሀ ለቀቅሁት:: ሳጥኑን ከፋፍቼ እቃውን ሁሉ በደቂቃ ውስጥ አማተርኩት: እሱ የማይጠረጥረው ቦታ አጣሁ:: ባሌ ሲጣራ ሰማሁት...ምን አስቸኮለው? ስልኩን አጥቶ ይሆን? "መጣሁ" አልኩ መስኮቱን ለመክፈት እየታገልኩ:: ስልኩን በፎጣ ጠቅልዬ ወደውጭ አሽቀነጠርኩትና መልሼ ዘግቼ ወደሳሎን አመራሁ::

ተመልሶ ተቀምጦዋል:: ቶሎ ብሎ እጆቼን አየ: እንደተሸበረ ያስታውቃል:: ጠረጴዛው አጠገብ ቆሜ ተፋጠጥን:: አሁን ለቅሶ የለም: ጥላቻ ብቻ: እጆቼ ተንቀጠቀጡ:: በድንገት እንጣጥ ብሎ ተነሳና ወደመታጠቢያ ቤት ሮጠ:: እኔም ፈጠን ብዬ ከእጅ ቦርሳዬ ውስጥ ስልኬን አውጥቼ የቤት ቀሚሴ ኪስ ውስጥ ከተትኩት: ለክፉም ለደጉም:: ቅድም ከፍቼው የነበረውን ሳጥን በሀይል ሲጠረቅመው ተሰማኝ:: 

"ስልኬ የታል?" ወደሳሎን እየገባ አንባረቀ:: "የምን ስልክ?" አልኩ ረጋ ብዬ "ቀስ ብለህ ፈልገው: ምን አስቸኮለህ?" የሸር ፈገግታዬን ብልጭ አደረኩ: ሞኚትዋ ሚስቱ:: ወደበሩ ተንደረደረና በግራ በኩል የተሰቀሉትን ቁልፎቼን አነስቶ ኪሱ ከተታቸው:: "ስልኬን ካልሰጠሽኝ ..." የቀረውን አልሰማሁትም: ጭንቅላቴ ውስጥ የታመቀው ነገር ሁሉ ፈነዳ: ብሶት: ቅናት: ጥላቻ: ንዴት: ፍርሀት:: አጠገቤ ያለውን ወንበር አንስቼ ወረወርኩበት: ወደጎን ፈንጠር ብሎ አሳለፈውና አፈጠጠብኝ:: ይቺኛዋን ሚስቱን በጭራሽ አይቶዋት አያውቅም: ኧረ እኔም አላውቃት:: በሚያስፈራ ድምፅ አጉዋራሁ:: "አንተ ከኔ ሳይሆን: እኔ ከእንዳንተ አይነቱ ቆሻሻ ፍቺ እፈልጋለሁ...ው-ሻ!" ወደሱ እየተንደረደርኩ "ቁልፌን አምጣ!" ጮህኩ: ኪሱ ውስጥ ልገባ እጄን ስዘረጋ ሁለቱንም እጆቼን ጠርቅሞ ያዛቸው: መነቃነቅ አልቻልኩም:: "አ-ን-ተ...ግ-ፈ-ኛ" እንባዬ መዝነብ ጀመረ "እ-ኔ...ከልጆቼ ጋር እየታገልኩ ስ-ን-ቅ...ስሰራ የ-ከ-ረ-ም-ኩ-ት... ለ-ለ-ው-ሽ-ማ-ህ... ኖ-ር-ዋ-ል" አቤት ፊቱ ላይ ያየሁትን ድብልቅልቅ ስሜት!..ድንጋጤ: እፍረት: ሀዘን: ቁጭት:...ምንም አልተናገረም: እጆቼን ግን አጥብቆ ጠርቅሞ ያዛቸው:: ለመሳሳም እንደተዘጋጁ ፍቅረኛሞች ፊት ለፊት ተፋጠን ቆምን:: "ም-ን... በ-ደ-ል-ኩ-ህ... ይ-ህ-ን-ን... ያ-ህ-ል...ግ-ፍ" ተንሰቀሰቅሁ "ቤ-ቴ-ን... ት-ዳ-ሬን... ባ-ል-ኩ" እንባዬም: ንፍጤም: ለሀጬም ተደባልቆ ተዝረከረከ:: "አንቺ ምንም አላደረግሽም: እ-ኔ-ው...ነ-ኝ" አለ በጎረነነ ድምፅ:: አይኖቹ እንባ አቅረዋል: እጆቼን ጠርቅሞ እንደያዘ ወደጣራው አንጋጠጠ::
ይቀጥላል ...........

ማሳሰቢያ:- ይህን ፅሁፍ ከናንተ ጋር እኩል ክፍል ላይ ነኝ አደራ እጁ ላይ ስላለ ያነባል ብላችሁ አታስቡ።



ይቀጥላል .....


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥__⚘_❥❥
548 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, edited  03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 00:01:36 <<ጠይሙ !>>


ክፍል.......6

(በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.
"ተግባባን ወይይይ?" አልኩ በድጋሚ ድምፄን ከፍ አድርጌና አጎንብሼ ፊቴን ወደሱ ፊት በጣም እያስጠጋሁ:: ብዙም አተኩሮ ሊያየኝ አልቻለም: ወንበሩን ወደሁዋላው አንሸራትቶ ራቀኝ::

"ተናገር እንጂ" "አይ አንቺ...ልብሽን እኮ አውቀዋለሁ:: እንኩዋን ሰው...." ፈገግ ለማለት ሞከረ:: "አሂሂሂሂ..." እኔም የብሽቀት ሳቄን ብልጭ አደረኩ::

"ልቤንማ አውቀኸው ነው የምትጨማለቅብኝ...አሁን ግን እስኪ ወንድነትህን ልለካው...እስቲ አንድ ልጅ ከኔ ለመንጠቅ ሞክር...በላ ሞክረኝ" የተናገርኩትን ለማስረገጥ በሌባ ጣቴ ጠረጴዛውን እየደጋገምኩ ተመተምኩት:: "ይገባኛል...በንዴት ብዙ ነገር ልትይ ትችያለሽ...እኔ ግን ለልጆቹም ቢሆን የሚሻለው....." አቁዋረጥኩት::
"ኖ-ኖ-ኖ-ኖ...ወዴት ወዴት...አንተን ብሎ ለልጆቹ አሳቢ:: እንደልብህ ለመንዘላዘል እንዲመችህ ነው እንጂ...አሁን የተባልከው ወንድ ከሆንክ አንዳቸውን ለመውሰድ ሞክር እስኪ ነው" ድንፋታዬን ቀጠልኩ...የሚጋልበኝን እንግዳ ስሜት ወደድኩት...እልህ: በቀል: አልጠቃም ባይነት... ምንም ሳይመልስልኝ ተፋጥጠን ቆየንና "እሺ ልክ ነሽ...ማንኛቸውንም አልወስድም" ከት ብዬ በንቀት ሳቅሁበት::
"በሞከርከኝ ኖሮ...አንተ ሽንታም!" ወንበሬ ላይ በኩራት ተመቻችቼ ተቀመጥኩ...አዎን ድል መታሁ::  እኔ እሱ ላይ: እሱ ወረቀቱ ላይ አፍጥጠን በዝምታ ተቀመጥን:: እንደዛ እወደው: ከመውደድም አልፌ አመልከው የነበረውን ሰው ለአይኔ ተፀየፍኩት:: "ጥዝ...ጥዝ...ጥዝ" የሚል ድምፅ በጣም በስሱ የወረሰንን ፀጥታ አቁዋርጦ ተሰማኝ...የአንዳችን የእጅ ስልክ መሆን አለበት...ግን ደግሞ የኔን ስልክ ድምፁን አላጠፋሁትም::
በአይኔ ፈለኩ...የማንኛችንም ስልክ በአካባቢው የለም:: የባሌ እጅ ግን በድንገት ሲንቀሳቀስ አየሁትና ወዲያው ድምፁ ፀጥ አለ::
ጠረጴዛው ቢከልለኝም እጁ ወንበሩ
መደገፊያ ላይ ወደተሰቀለው ጃኬት ኪስ እንደገባ ገምቻለሁ:: ቶሎ አይኔን ከባሌ ላይ አንስቼ ከጀርባው ያለው ግድግዳ ላይ አፈጠጥኩ...አላየሁም: አልሰማሁም ለማለት አይነት::
ወዲያው ባሌ ተነሳ:: ያን የፍቺ ወረቀት ወደእኔ እየገፋ "ተረጋግተሽ አንብቢውና ይስተካከሉ የምትያቸውን ነገሮች ነገ አስተካክያቸው ሁለታችንም እንፈርምበታለን" አለ እያመነታ:: የኔ ልብ ግን እዛ ስልክ ላይ ተንገዋሎ ቀርቷል...አሁን እንዳይሄድ መያዝ አለብኝ:: 
"አስተካክያቸው? ማን: አንተ?" አልኩ በለሰለሰ ድምፅ...ያ ሁሉ ማጉዋራት በፍጥነት ሲቀየር ገርሞት አፈጠጠብኝ:: "እእእ...አ-ዎ-ን...ጠበቃዬ ለማስተካከል እንዲመቸን ብሎ ኢሜይል አድርጎልኛል"  "ባንክ ያለንን ገንዘብ ግማሽ እስከተካፈልን ድረስ በሌላው ሁሉ እስማማለሁ...ልጆቼን እንደሁ ሰጥተኸኛል" ቀጠልኩ በዛው በለሰለሰ ድምፅ "ቅድም ስለጮህኩብህ ይቅርታ...የልጆቼን ነገር ታውቀዋለህ"  የባሰውን ግራ ተጋባ::
ከደቂቃት በፊት ልገለው ስዝት የነበርኩ ሴትዮ ከመቅፅበት ወደ ይቅርታ ጥየቃ ስገባ ጆሮውን አላመነም...ግን ደግሞ ወንድ አይደል...ሰተት ብሎ ወደወጥመዴ ገባልኝ:: "እና-ና-ና.....አሁኑኑ ላስተካክለው?" አለ ፈራ ተባ እያለ:: "አዎን...የባንኩን ብቻ አስተካክለው...ታዲያ ለኔም ቀሪ ኮፒ ስለምፈልግ እባክህ ፕሪንት አድርግልኝ" ጨዋነትና ትህትና የተሞላበት መልሴን ሰጠሁ "እስከዛ ልጆቼን አይቼ ልምጣ" ብዬ ወደመኝታ ቤታቸው አመራሁ...እሱም ኮምፒውተሩ ወዳለበት ክፍል ተጣደፈ::

ይቀጥላል .....


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥
527 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:46:45 <<ጠይሙ ባሌ!>>


ክፍል.......5

(በእውነተኛ ታሪ የተመሰረተ)

አዘጋጅ፦ ፍቅርን በቃላት
.
.
.
.... ባሌ ፊት ለፊቴ ከጠረጴዛው ባሻገር አገጩን እጁ ላይ አስደግፎ: አንገቱን ደፍቶ ጠረጴዛውን እያየ ተቀምጦዋል...ሊያባብለኝ አልሞከረም...እኔም አልፈለኩም:: አሁን አንድ ቃል ቢናገረኝ: ወይም ሊነካኝ ቢሞክር ጉሮሮውን ሳልይዘው አልቀርም::

እንደምንም እራሴን አረጋጋሁና ለመናገር ሞከርኩ:: "ይ-ህ-ን-ን...ሁ-ሁ-ሉ...ስ-ስ-ስ-ታ-ደ-ር-ግ...ለ-ም-ም-ን... አ-ል-ል-ል-ነ-ገ-ር-ከ-ኝ-ም....አ-ን-ን-ተ-ተ...አ-ን-ተ..." ለሱ የሚገቡ ስድቦች ስላጣሁ ትንሽ ቆም አልኩና ቀጠልኩ... "ጨ-ካ-ካ-ኝ....እ-እ-እ...ቆ-ሻ-ሻ-ሻ"ቀና ብሎ አየኝ...አይኑ ላይ ምንም አይታይም...ቁጣም: ቁጭትም: ንዴትም: ፍቅርም: በቀልም: ጥላቻም...እንደው ምንም ምንም...አስፈራኝ:: 
"ሌ-ላ ሴ-ት ወደድክ እንዴ?" ያላሰበውን ጥያቄ ዱብ አደረኩለት::  "እ-ን-ዴ-ዴ-ዴ-ዴ..." ድንገት ነቃ አለ...እጆቹን የሚያደርግበት ቦታ ያጣ ይመስል አወራጫቸው "ምን አይነት ጥያቄ ነው?" ወንበሬ ላይ ተደላድዬ ተደግፌ ተቀመጥኩና እጆቼን አጣምሬ አፈጠጥኩበት::
ላቡ ግንባሩ ላይ አቸፈቸፈ...ምላሱ ግን ትንፋሽ እያጠረው ቀጠለ  "እንዴት ብትገምቺኝ ነው? ባለትዳር ሆኜ...."  አቁዋረጥኩት "ምነው ታዲያ አላበህ?" ሌላ ጥያቄ::  "ቤቱ ይሞቃል..." እየተደናበረ ተነስቶ ጃኬቱን አወለቀና ወንበሩ መደገፊያ ላይ አንጠለጠለው:: በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ባሌን ጠረጠርኩት::  "ለፍች ምን አስሮጠህ ግን?" ያንን ሁሉ ለቅሶ በድንገት አቁሜ ወደ መስቀልኛ ጥያቄ ገባሁ...ከላይ የተረጋጋሁ ልምሰል እንጂ ልቤ ብትንትኑ ወጥቶዋል::  "በቃ ልንስማማ አልቻልንም...ሁሌ መኩዋረፍ ነው:: በተለይ ልጆች ከወለድሽ በሁዋላ ለኔ ብዙም ጉዳይ የለሽም...ተለውጠሻል" 

"እ-ን-ዴ!" አልኩ በመገረም አፌን ይዤ "ያንተው ልጆች እኮ ናቸው"  "ቢሆኑም...ለኔ ምንም ጊዜ የለሽም"  "ታዲያ ስንት ጊዜ የቤት ስራ አግዘኝ: ደከምኩ ብዬ ጠየኩህ?"  "አ-ይ-ይ-ይ...." አለና አመነታ  "ጨርሰው እንጂ...አይ ምን?"  "እኔ ቤታችን ውስጥ ምንም እንዳይጎድል...እንደውም ሞልቶ እንዲትረፈረፍ በሳምንቱ ውስጥ አንዳንዴ ሰባቱንም ቀን እለፋለሁ...ቤቴ ስመጣ

ደግሞ ማረፍ ነው የምፈልገው..." "ሰባቱንም ቀን ማን ስራ አለህ...ፈልገህ እኮ ነው...ያለን መቼ አነሰን?"  "አንቺ ባታመሰግኚኝም ለልጆቼ የተሻለ ህይወት ነው የምለፋውና ምንም አይደል...ሳረጅ አርፋለሁ"  "እና መፍትሄ ያልከው ከምትለፋላቸው ልጆች መለየቱን ነው?"  "ወድጄ አይደለም...አንቺ ነሽ የገፋሽኝ...አሁን ግን በቃ ወስኛለሁ" ውስጤ ሲግል ተሰማኝ::  "እና አሁን በዚህ በምሽት የት ነው የምትሄደው?" 

"ለጊዜው አንድ የስራ ጉዋደኛዬ ጋ እቆያለሁ" ሰበቡ ሁሉ አልጣመኝም...አላመንኩትም...ግን ደግሞ እሄዳለሁ ካለ ጥርግ...ኩራቴ አሸነፈኝ: አልተለማመጥኩትም:: ፊቴ የተቀመጠውን ወረቀት ማገላበጥ ጀመርኩ:: 
"ይሄንን መቼ ነው እንድፈርምልህ የምትፈልገው?" ወሬውን ድንገት ቀየርኩት::  አመነታ..."እ..ዛሬም ብትፈርሚው ደስ ይለኛል...እኔና አንቺ ፍርድ ቤት እየተጉዋተትን ገንዘባችንን ጠበቃ ከሚበላው በሰላም ብንጨርሰው አይሻልም?"  "ለምንድነው ባንክ ያለን ገንዘብ እሩቡ ብቻ የሚደርሰኝ?"
ኮስተር ብዬ ጠየኩ "ይህን ገንዘብ እንደሴቱ ማማር መሸቀርቀር ሳያምረኝ የቆጠብኩት ነውና ሌላው ቢቀር ግማሹ ይገባኛል" ከሞኝዋ ሚስቱ ያልጠበቀው ጥያቄ ነበርና ትንሽ አሰላሰለ::
 
"ቤቱንና አዲሱን መኪና ላንቺ ሰጠሁሽ እኮ:: ለልጆቹም በየወሩ በቂ ተቆራጭ ተመድቦልሻል...ለኔም አስቢልኝ እንጂ"  "ቤቱና መኪናውን እኮ ከነባንክ እዳው ነው ያሸከምከኝ...ጣቴን የምጠባ ህፃን አረከኝሳ......ተቆራጩም በግድህ ነው...ከፈለክ የጡረታ ምናምን ገንዘብህን ቀቅለህ ብላው" ፊቱ ላይ አሽቀነጠርኩለት...አቤት ፊቱ ላይ ያየሁት መደናገጥ...ልቤ ሞላች:: 
"ልጆቹን በሙሉ ሰጠሁሽ እኮ...ምን ያህል እንደምትሳሽላቸው..."  እንጣጥ ብዬ ቆምኩና ጠረጴዛውን ነረትኩት::  "ስማ አንተ ቆሻሻ...በደንብ ስማኝ" የድምፄ ውፍረት እንኩዋን እሱን እኔንም አስደነገጠኝ...ቀጠልኩ..."እበትም ትል ይወልዳል:: አንድ ቀን ዞር ብለህ ያላየሀቸውን ልጆች ዛሬ ካንቺ ልነጥል ብትል አለቀልህ...አላማዬ አንተን ማጥፋት ይሆናል"
አንጋጠው የሚያዩኝ አይኖቹ ላይ አፈጠጥኩባቸው "በመኪና ነው የምወጣብህ...አንዴ አይደለም...እየተመላለስኩ ሀያ ጊዜ...ለዛች ለድሀ እናትህ የሚላክ እሬሳ እስከሚታጣ ድረስ...ተግባባን?" እነዛ ኩሩ አይኖቹ በሽብር ተርበተበቱ...ምራቁን ሲውጥ የአዳም ፍሬው ወደላይ ወደታች ብሎ አሳበቀበት::

ይቀጥላል .....


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group
@ethio_lifes_group


╔═══❖• •❖═══╗
@fkrn_be_kalat
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@fkrn_be_kalat_bot
❥❥________⚘_______❥❥
687 views✧ زوجة الفيلسوف ✧, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ