2022-02-25 12:48:44
ከመሀፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና
ከማህፀን ውጪ እርግዝና የሚንለው እርግዝና ከማህፀን ውጪ ሲፈጠር ሲሆን ስንደ ስያሜው፣ በአብዛኛውን ደግሞ ይሔ የሚሆነው በማህፀን ቱቦ ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ የማህፀን ቱቦዎች ውስጥ እርግዝና ሲከሰት ፅንሱ እድገቱን መቀጠል የማይችል እና በቱቦዎቹ ውስጥ በቆየ ቁጥር ደግሞ በእናትየው ጤና ላይ አደጋ የሚያስከስት ነው፡፡
ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና በአፋጣኝ ሕክምና የሚያስፈልገው ሲሆን ፅንሱን ማስቀጠልም ስለማይቻል፣ ፈጥኖ ተገቢውን ህክምና ማግኘት ወደሚቻልበት የህክምና ማዕከል በመሄድ በመድሐኒት ወይም በቀዶ ህክምና ፅንሱን ማውጣት ተገቢ ነው፡፡
ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና ምልክቶች
ከማህፀን ውጪ እርግዝና ምንም ዓይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ይሔም ማለት እናቶች በፅንስ ክትትል ወቅት የፅንስ አልትራሳውንድ ምርመራ ሲያደርጉ የሚታወቅ ክስተት ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡
ከዚህ ውጪ በተረፈ ምልክቶቹ (ካሉ) የሚታዩት በአብዛኛው ከ4ኛ እስከ 12ኛው የእርግዝና ሳምንት ነው፡፡
እነዚህም ምልክቶች፡-
- የወር አበባ አለማየት
- ማቅለሽለሽ እና ሌሎች የእርግዝና ምልክቶች
- በአንድ ትከሻ ጫፍ ላይ ህመም ስሜት መሰማት
- በአንድ በኩል የሚያጋድል የሆድ ህመም
-ደም ወይም ቡናማ ፈሳሽ በማህፀን መፍሰስ
-በሚሸናበት ወቅት ምቾት መንሳት ሊሆኑ ይቸላሉ፡፡
ይሄ በዚህ እንዳለ እነዚህ ምልክቶች የማህፀን ውጪ እርግዝና ምልክቶች ብቻ አይደሉም፣ የሆድ ዕቃ/ጨጓራ መታወክን ጨምሮ ሌሎች ህመሞች ምልክቶች ናቸው፡፡
ሕመሙን መኖሩን የምናረጋግጠው ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች አይተን በሽንት የእርግዝና ምርመራ ካደረግን በኋላ የፅንስ አልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ነው፡፡
ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና መንስኤዎች ግልፅ ባይሆኑም አልፎ አልፎ ሲከሰቱ የሚስተዋለው ዋናው መንስኤ በማህፀን ቱቦዎቹ ውስጥ ያለ ችግር ምክንያት ነው፡- ይሄም ማለት ቱቦዎቹ ሲጠቡ ወይም በሆነ ምክንያት ሲዘጉ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ለሕመሙ ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
- በማህፀን ቱቦዎች ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን/ በአብዛኛው በአባላዘር በሽታዎች ምክንያት የሚመጣ፣
- ከዚህ ቀደም የተከሰተ ከማህፀን ውጭ እርግዝና- ይሔ ሲሆን ድጋሚ የሚከሰትበትን ዕድል በ 10 በ 100 ይጨምረዋል፡፡
- በቀዶ ህክምና ወቅት የሚደርስ የማህፀን ቱቦ ጉዳት - በተለይም የማህፀን ቱቦ መዘጋት
- የማህንነት ህክምና
- ማጨስ
- እድሜ መጨመር ፣ የእናቶች እድሜ ከ35-40 በላይ ሲሆን
ህክምናው
ሀኪምዎ ለእርስዎ የሚሆን የህክምና አይነት ከማህፀን ውጪ እርግዝናው እንደተከሰተበት ቦታ እና እንዳጋጠመው የጤና ውስብስብ ችግር ላይ ተመረኩዞ በመድሃኒት ወይም በቀዶ ህክምና ህክምና ያደርግሎታል፡፡
በመድሃኒት፡- ጊዜው ያልገፋ በማህፀን ቱቦ ውስጥ ለተከሰተ፣ ያልፈነዳ፣ ሊያድግ የማይችል ፅንስ ሲኖር
ቀዶ ህክምና ደግሞ በመድሃኒት ለመወገድ ትልቅ የሆነ ፅንስ ሲሆን ወይም ፅንሱ ያለበት የማህፀን ቱቦ የፈነዳ
ድጋፍ
ከማህፀን ውጪ እርግዝና ከተከሰተ በኃላ እናቶች ላይ ሀዘንን እና ትካዜን ማየት የተለመደ ቢሆንም ብዙ የሚቆይ ነገር ግን ሆኖ አይስተዋልም፡፡ ሀኪምዎ ጋር በመሄድ ስለወደፊት የእርግዝና እቅዶች እንዲሁም ስለ ስነልቦናዊ ድጋፍ ምክክር ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ስለተከታይ እርግዝና መሞከር
ተከታይ እርግዝና ከባለቤትዎ ጋር ለመሞከር ስታስቡ ሁለታችሁም አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡
-ከዛ በመቀጠል ሁለት ጊዜውን የጠበቀ ተከታታይ የወር አበባ ማየት ይመከራል ሙከራ ከማድረግዎ በፊት፡፡
-በመድሃኒት ከታከሙ፣ ተከታይ እርግዝናን ለመሞከር 3ወራትን እንዲጠብቁ ይመከራል፡፡ ይሄም መድሃኒቱ ፅንሱን እንዳይጎዳ ለማድረግ ነው፡፡
-በአብዛኛው እናቶች የማህፀን ቱቦ መወገድ ቀዶ ህክምና ተደርጎላቸው ራሱ ቢሆን ደግመው የማርገዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡
በአጠቃላይ ከ65 በ 100 የሚሆኑ ከማህፀን ውጪ እርግዝና የተከሰተባቸው እናቶች በ18ወራት ውስጥ የተሳካ እርግዝናን ያገኛሉ፡፡ አልፎ አልፎ የማህንነት ህክምና ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡
ከዚህ ቀደም የተከሰተ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ሲኖር ድጋሚ ከማህፀን ውጭ እርግዝና የሚከሰትበት ዕድል 10 በ 100 ሲሆን ይሄም በንፅፅር ትንሽ የሚባል ነው፡፡ ስለሆነም ተስፋ ባለመቁረጥ፣ ከሀኪምዎ ጋር በመመካከር ተከታይ እርግዝናን በጤናማ ሁኔታ ማግኘት ይችላሉ፡፡
86 views09:48