#ባርቶሊን #ሲስት # (Bartholin Cyst) #ባርቶሊን የምንለዉ | Feya Medical center Bale Robe
#ባርቶሊን #ሲስት # (Bartholin Cyst)
#ባርቶሊን የምንለዉ አተር የሚያክል መጠን ያላቸዉ የባሪቶሊን እጢዎች በግራ እና በቀኝ የሴት ብልት ክፍል ላይ የሚገኙ ሲሆን ብልት እርጥበቱን ጠብቆ እንዲቆይ ፈሳሽ ያመነጫሉ፡፡
#ይህ ባርቶሊን ሲስት የሚከሰተዉ ፈሳሹ ወደ ብልት በሚሄድበት ትቦ ላይ መዘጋት ሲከሰት መሄድ የነበረበት ፈሳሽ ወደ እጢዉ ይመለስ እና እብጠት ይፈጥራል፡፡
#አጋላጭ #ሁኔታዎች
ልቅ የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት
ከ20-30ዓመት የእድሜ ክልል
ከዚህ በፊት ባርቶሊን ሲስት ተከስቶ ከነበር
በዛ አካባቢ አደጋ ሲከሰት
ብልት አካባቢ የተደረገ ቀዶ ጥገና ካለ
#ምልክቶቹ
እብጠቱ ካልተለቀ ወይም ካልተበከለ ምንም አይነት ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ
በባክቴሪያዎች ከተበከለ (ካመረቀዘ) ከፍተኛ የሆነ ህመም ይፈጥራል
በጾታዊ ግንኙነት ጊዜ እና በሚራመዱበት ጊዜ ህመም መኖር
#የተበከለ (ኢንፌክትድ) #ባርቶሊን #ሲስት #የሚያሳዩት #ምልክቶች
ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት
ህመም ( በሚራመዱበት ፣ በሚቀመጡበት ወይም በማንኛዉም እንቅስቃሴ የሚባባስ
በብልት ላይ እብጠት መኖር
ፈሳሽ መዉጣት
#ህክምናዉ
ከ 40ዓመት በታች ከሆኑ እና ሲስቱ ምንም አይነት ህመም(ችግር) የማያስከትል ከሆነ ምንም አይነት ህክምና አያስፈልገዉም
በሙቅ ዉሃ ዉስጥ መዘፍዘፍ ሲስቱ በራሱ እንዲጠፋ ይረዳል (ይህን በተደጋጋሚ ለ 3-4 ቀን ማድረግ)
ፎጣ በሙቅ ዉሃ እየነከሩ ጫጫን ማረግ
የሚቀባ መድሀኒት
የአባላዘር በሽታ ካለ እና የቋጠረዉ ፈሳሽ ከተበከለ ፀረባክቴሪያ መድሀኒት ሊታዘዝ ይችላል
#መከላከያ
ጥንቃቄ ያለዉ ጾታዊ ግንኙነት (ኮንዶም መጠቀም)
ንጽህናን መጠበቅ
#ዉስብስብ #ችግሮች (complication)
አንዳንድ ጊዜ ባክቴሪያዎች ዉሃ ወደ ቋጠረዉ (ሲስት) ይገቡ እና መግል ይፈጥራሉ ይህም ህመሙ እንዲጨምር ያደርገዋል
#መግሉ በፍጥነት እየተስፋፋ ሲሄድ እነዚህ ምልክቶች ይታያሉ፡-
መቅላት
አከባቢዉ ላይ በሚነካበት ጊዜ ህመም መሰማት
በአከባቢዉ ላይ ሙቀት መኖር
በግንኙነት ጊዜ ህመም መሰማት
ትኩሳት
መቀደድ እና መፍሰስ
ፔጁን ሼር በማድራግ ለሌሎችም ያጋሩ።