Get Mystery Box with random crypto!

📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

የቴሌግራም ቻናል አርማ fetaenbeel — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 ቤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fetaenbeel — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
የሰርጥ አድራሻ: @fetaenbeel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.00K
የሰርጥ መግለጫ

📚📚እንኳን በደህና መጡ📖📗🧾
➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የ አማርኛ እና English መፅሀፍትን በ 📙 Pdf እና ትረካዎችን እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛሉ።
📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️
B-) :-መረዳዳት ቢኖር ሁሉም ቢተባበር
100K ይደርስ ነበር ።
For any comment @Meki3

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-05-20 21:45:47 ፅናት

ክፍል 35

ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ(የሸዋ ልጅ)
.
.
.

፨ያቤፅ "ምን ማለት ነው ቆይ ይሄ ምንድነው?" አለ። ሶስናም "እስቲ አንሽው
እባክሽ" አለቻት። ፅናት "አይ አይ አይሆንም ደግሜ አላነሳውም" አለች። ስልኩ
ተዘጋ።ያቤፅ ስልኩን ከሊባኖስ እጅ ወስዶ በተደወለው ስልክ መልሶ ደወለ።
ስልኩ አይሰራም ልክ ሲደውል የጥሪም ሆነ የምንም ድምፅ ሳያሰማ ይዘጋል።
ያቤፅ መንጎራደድ ጀመረ። "ሊባ ስትመጣ ስለ እዚህ ነገር ታብራራልናለች።
አሁን መጨነቅ አያስፈልግም ሁሉም ሰው አብሮት ለሚኖረው ስው እራሱን
ማብራራት አለበት።"ግዴታ ስለሆነ በሉ አሁን ቡናዬን ማፍላት ልቀጥል እናቴ
አንቺ ደሞ ስለ ሁሉም ነገር እና እኔን እንዴት እንደተውሽኝ ንገሪኝ ከዛ በፊት ግን
ለፅኑ ስላንቺ ትንሽም ልንገራት"አለና እዝን ያለ እና ሳቅ ያለበት ፊት አሳየ ፅናት
አይኑዋን እና ጆሮዋን ያቤፅ ጋር አደረገች።
፨ያቤፅ እናቱን እያየ መናገር ጀመረ። "እኔና እናቴ ልክ እንደ ጎደኛ ነበርን እኔ እና
እናቴ ሁሉንም ነገር፤ እንወያይ ነበር፤ለወደፊት ምንአይነት ሰው ምን አይነት
ወጣት መሆን እንዳለብኝ ትነግረኝ ነበር።ማለቴ ያው ጥሩ እና ታዛዥ ሰው
እንደሆን በጣም ትመክረኝ ነበር፤የእኛ የቤተሰቡ ትልቁን ድርጅት ዋና መሪ
እርስዋ ነበረች።አባቴ ስራው እየዞረ ከእድሜ እኩዮቹ ጋር መጠጥ መጠጣት እና
ምግብ መብላት ብቻ ነው። ስራው ግን ደሞ እኔ ሁሌም እናቴ ለምንድነው አባቴ
ስራ የማያግዝሽ ስላት እናቴ አባትህ በጣም ቸልተኛ ሰው ነው ቸልተኝነቱ ገብቶት
እስኪያግዘኝ ድረስ ትግስት ያስፈልገና ትለኛለች "አለና ብናውን ቀድቶ
ለሁለቱም ሰጥቷቸው ወደ ቦታው ተመልሶ ማውራት ጀመረ።
፨"እና እኔም በጣም እናደዳለሁ ለምን አንድሆነ እንዲህ እሚሆነው እጠይቀው
ነበር። አባቴ ግን በጠየኩት ቁጥር አንድ ነገር ነው የሚለኝ አፈክን ዝጋ ብቻ እኔ
ተወልጄ ነብስ ካወኩበት ጊዜ ጀምሮ እናቴ ሁሌም ከእኔ ጋር ነው
እምትተኛው።ልጅ እያለሁ ምንም ነገር ሰለማላውቅ እናቴን ምንምነገር
አልጠይቃትም ነበር ነገር ግን ነብስ ሳውቅ እናቴ ለምንድነው ከአባቴ ጋር
አብራቹ እማትተኙት ስላት እኔ አንተን በጣም ስለምወድህ ካንተ ጋር ነው
እምተኛው ትለኝ ነበር።እኔም እናቴን ላለማስጨነቅ ዝም እል ነበር። በእዚህ
መሀል ነበር እናቴን ጥዬ ልክ እንደ እብድ መኖር የጀመርኩት። እኔ ከ ቤት
ከወጣው ብዙ ሳይቆይ በምን ተአምር እንደሆነ ባላቅም ጠንካራዋን እና ሁሉን
ቻይዋን እናቴን የ ትንሽዬ ሱቅ ሻጭ ሆና አገኘዋት። ያየእናቴን ልጅነት ወስዶ እኔን
በ15 አመትዋ አግብታው እንድትወልድ ያረጋት ጨካኑ አባቴ ግን ያን ትልቅ
ድርጅት እየመራ አገኘውት።
፨ከመቅፅፈት ነበር ሁሉ ነገር የተቀያየረው" አለና ያቤፅ ተቆጣጥሮ ያቆየውን
እንባውን አረገፈው ፅናት እና ሶስናም ማልቀስ ከጀመሩ ቆይተዋል። ያቤፅ
እንባውን በሀይል በሁለት እጁ ጠርጎ በድጋሜ ወደ ወሬው ተመለሰ "እኔ እኮ
እናቴን እዛች ሱቅ ማየቴ ውስጤን ጎድቶታል ግን እንዴት እንደሆነ ምንም የገባኝ
ነገር የለም። እናቴ የኔ እናት ያኔ የጮኩብሽ እኮ በጣም ስለምወድሽ ነው ያኔ
የጮኩብሽ እኮ ባንቺ ተስፋ አረጌ ነበር እንደምታድኝኝ ሁሌም ተስፋ አረግ
ስለነበር እና አንቺ ብቻ ትረጅኝ ስለነበር ያልተረዳሽኝ ስለመሰለኝ ነው።ግን አሁን
ሁሉንም ነገር እንድትነግሪኝ እፈልጋለሁ አዳምጥሻለሁ" አላት። ሶስና ማልቀሷን
ሳታቆም "ልጄ አባክህ መጥፎ ሰው ነው መካድ አልፈልግም እንዲህ ባልልህ
በጣም ደስተኛ እሆን ነበር።አንተ ቤቱን ጥለህ ከወጣህ በኋላ እንዴት እንደሆነ
ባላውቅም ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እራሴን መሆን ከበደኝ"ብላ ይበልጥ ማልቀስ
ጀመረች።
፨ፅናትም አረጋግታ እንድትናገር ገፋፋቻት ሶስና መናገር ጀመረች። "አባትህ
ገጠር ውስጥ ልክ ብዙ ባለ ሀብቶች እንደሚያረጉት ትልቅ ከ 9ነኛ ክፍል ጀምሮ
መማሪያ ሊሰራ ከአባቱ ጋር መጣ። እኔ በጣም ቀልቃላና ከሰው ጋር ተግባቢ ልጅ
ሰለነበርኩ በቀላሉ ነበር ከአባትህ ጋር የተቀራረብኩት ከዛም ወደ ከተማ ይዜሽ
ልሄድ አባቴን እናገረዋለሁ። አለኝ።
፨እኔም ምንም ሳላቅማማ ነበር። የተቀበልኩት ምክንያቱም እኔ ከተማ መሄድን
በጣም እፈልግ ስለነበር። ከዛም
ቤቴ እህል እየፈጨው በአጥሩ በኩል መጥቶ እንድመጣ ምልክት ሰጠኝ እና
ወደሱ ሄድኩኝ አባቱን እንዳሳመነ ነገረኝ። እሱ እና አባቱ ድርጅት ውስጥ
ካስተማረኝ በኋላ እንደሚቀጥረኝ ነገረኝ መሪነትን አጥብቄ እፈልግ ነበረ ስለዚህ
በጣም ደስተኛ ሆንኩኝ እምወደውን አባቴን አብዝቼ ከምወዳት እና ከ እናትም
በላይ ሆና እናቴን ተክታ ያሳደገችኝን ምስኪኑዋን እንጀራ እናቴን እንደምንም
አሳምኔ ከ ያቤፅ አባት እና አያት ጋር ወደ ከተማ መጣን።
፨ቤታቸውን አየውት በጣም ግዙፍ ነው። እና ደሞ በጣም የሚያምር ነው።
ወዲያው ነበር የመሸው ከ ያቤፅ አባት ጋር ስንጫወት አልታወቀኝም 13 አመት
ከ 6 ወሬ ነበር። አባቴ እናቴ እኔን ስትወልድ ስለሞተች ጊዜውን በደንብ ያቀዋል
እና ለእኔም ይነግረኝ ነበር። አባቴ ቢያንስ 6ወር ቆይተሽ የእናትሽን አመታት እና
የተወተለድሽበትን ጊዜ ከእኔ ጋር ቆይ ብሎኝ ነበር። እኔ ግን ትምህርት ለመጀመር
ስለምፈልግ እና 6ወር ከቆየው ከተማ የትምህርት ምዝገባ ስለሚያመልጠኝ
አይሆንም ብዬ ነበር የመጣሁት።ማታ ላይ ልክ ከተማ እንደገባው በተሰጠኝ ትንሽ
ክፍል ውስጥ ተንጋልዬ ስለ ገጠር እያሰብኩኝ የያቤፅ አባት መጣ እና አጠገቤ
ልክ እንደኔ አልጋው ላይ ተጋድሞ ቆየና በድንገት መቀያየር ጀመረ።እና እኔን
መነካካት ጀመረ። ልብሴን በሀይል ገላለጠው በህይወቴ አንዴም አይቼው
ማላውቀውን ስቃይ አየው።አባትህን ላስቆመው አልቻልኩም ያ ሌሊት
አለፈ።የያቤፅ አባትም ጠዋት ላይ ነበር አስነስቶ ገላዬን አጠቧኝ እንድጠነክር
አረገኝ።ከ15ቀን በኋላ የያቤፅ አያት መጡ። የያቤፅን አባት ላለማሳጣት ምንም
እንዳልተፈጠረ ሆኩኝ።
፨ጊዜው እየገፋ መጣ። የያቤፅ አያት ጠረጠሩ እና ጠየቁኝ መደበቅ አልቻልኩም
የተፈጠረውን ነገረኳቸው። ከዛም የያቤፅ አባትን ጮከበት እንዴት እንዲህ
ታረጋለህ ብለው በጣም ጮሁ ግን በቃ እጣ ፋንታዬ ነውና ጊዜው ብቻ ሳይሆን
ሆዴም ከፈቶ ያቤፅን የመውለጃ ሰአቴ ደረሰ።ምጥ ያዘኝ በጣም መሰቃየት
ስጀምር የያቤፅ አባት እዛው ቤት ውስጥ አዋላጅ አመጣ።ስቃዬ በረታ ከዛም
ነረስዋ በምጥ ከወለድኩኝ እንደምሞት እና የግድ በኣፕራሲዩን መውለድ
እንዳለብኝ ተናገረች። አዋላጅዋ እንደዛ ስትል ነበር ልጄ ሹልክ ብሎ የወጣው።
በ14 አመት ከ3ወር ከ15 ቀኔ የልጅ እናት ሆንኩኝ። ነገር ግን በጣም ተሰቃይቼ
እና በሞትእና በህይወት መካከል ተፍልሜ ወደ ህይወት ተመለስኩኝ። አንድ
አመት ትምህርቴን ባቋርጥም በቀጣዩ አመት ግን የያቤፅ አያት አለ የተባለ
ትምህርት ቤት አስመዝግቦኝ ትምህርቴን መማር ጀመረኩኝ። ከትምህርት
ስመለስ ልጄን እማጠባው ጡት እንኳን የለኝም ማርገዜም አሁን አሁን ሳስበው
ተአምር ነው። እና ደሞ መውለዴን ሳስበው እውነትም አይመስለኝም። ትምህርት
ቤት በጣም ጥሩ ውጤቶችን አስመዘገብኩ በዛም ምክንያት 9ነኛ ክፍል ተምሬ
410 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:45:47 "ናፊባ"
ክፍል ~ ሠማንያ አምስት
በአምባዬ ጌታነህ
"ሙሉ አዳር አልወጣም። ሲመስለኝ መርዶው አልተነገረውም። የዋና ሳጅኑን መሞት ቢሰማ ኖሮ አስችሎት አይቆይም!" አለ የራሱን ፀጉር በጣቶቹ እየመነሸረ። ከእንቅልፍ መባነኑ እንዳይታወቅበት በተቻለው መጠን ሳይተኛ እንዳደረ ለማሳወቅ እየጣረ።" ተኝተህ በነበረበት ስአት ሄዶ ከሆነ ግን እኔ የለሁበትም!!" ንዴት የተቀላቀለበት ዱብዳ አነጋገር "ኧረ በጭራሽ ለሰከንድ ያህል እንኳን ልተኛ አላንቀላፋሁም።አይኔንም ከበራቸው አልነቀልኩም"አለ "እሺ ብቻ ለቅሶው ጋር ቀድሞህ ከተገኘ የሚያሳውቀኝ ሌላ አባል አለ" ብላ አስፈራራችውና ስልኩን ዘግታ አዲስ ነገር እንዳለ ለማወቅ ስልኳን ወደሌላኛው አሻንጉሊቷ ደወለች። የስልክ ተቀባይዋም ስልኩን አንስቶ ምንም ነገር እንደሌለና እስካሁን እንዳልመጣ ሲነግራት ከጥርጣሬዋ በመላቀቅ እፎይ አለች። ጥርጥሬ እንደምግብ የምታመሰኳው ነገር ነው። ለእሷ እያንዳንዱ ድርጊት ትልቅ ትርጉምና ዋጋ አለው። ይህን ምስጢራዊ ቡድን በሀላፊነት ስትመራ እያንዳንዱ ሰራተኛዋን በጥርጣሬ ነው የምትመለከተው። አንዳቸውንም የውሸት እንጅ የእውነቷን አታምናቸውም። ሁሉም የግቧ መውጫ መሰላላቸው እንጅ ሌላ አንዳች ጥቅም የላቸውም። ለዚህም በእነሱ ፊት ኮስታራ ፊቷን ነው ሰርክ የምታሳያቸው። አሁን ላይ ግን በርካታ ሰራተኞቿን በሞትና በክህደት ካጣች በኋላ ውስጧን ፍርሃት ቢገባውም ፍርሀቷን ግን በእነሱ ፊት አታሳይም።ቀን በቀን በወንድሟ እየተሳደደችም ፅንፍ ህልሟን ለማሳካት ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንዳለባት አውቃለች። በጥንቃቄና በብልሀት የተወጠሩት የሚሽን ክሯቿ ለመበጠስ እየመነመኑ ቢመስሉም ነገር ግን እሷ በፍፁም ተስፋ አልቆረጠችም። ነገር ግን ግማሽ ነፍሷ የተሸነፈች እንደሆነ ይነግራታል። ቢሆንም እስከመጨረሻው ድረስ እታገላለሁ በሚል ፅኑ ፍላጎት መንገዷን ቀጥላለች።
*****
ንጋት ከጨለማ ወስዶ መልዕይተ ቀኑን ለፀሐይ ካስረከበ በኋላ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው በማለዳ ቢነቃም ሀዘን እንዳጠላበት ነው። እስካሁን ፊቱ በጭራሽ የነቃ አይመስልም። የክብር ልብሱን አንድ በአንድ ከለበሰ በኋላ "በል ተሕሚድ ውሎዬ ለቅሶ ላይ ነው የሚሆነው።አንተ እንግዲህ የተለዬ ነገር ለማንኘት ሞክር የቻልከውን ያህል ጣር። ይሄ ሊሆን ይችላል ብለህ የጠረጠርከውን በሙሉ በማስታወሻህ ይዘህ ጠብቀኝ።የሕይወቴ ፈታኙና እጅግ ልዩ ትርጉም ያለው ምርመራዬን ነው የተጋራኸኝ። ከአንተ የሚጠበቀው ጥርጣሬዎችህነ ባገኘኽበትና ባሰብክበት ልክ ማስፈር ነው የሚጠበቅብህ ሌላ ከአንተ ምንም አይጠበቅም።ብሎ ትከሻውን መታመታ አድርጎት ትቶት ወጣ ።
ሸዋንግዛው በሀሳብ ውስጥ ትክዝ እንዳለ ነው። በአንዳች ነገር ክንፉ ተሰብሮ ዋጋ ቢስ የማይረባ ንስር ስነልቦናን ሀያ አራት ስአት ባልሞላ ጊዜ ተላብሷል። አቅሙ እስከዬት እንደሆነ የነገሩት መሰለው። የነዚህ ምስጢራዊ ሰዎች ማንነትና ምንነት የውሃ ሽታ ሆነበት። ሁኔታው ከአቅሙ በላይ እንደሆነ እንዲያውቅ አውቆም እንዲያምን ያደረጉት መሠለው።በዚህ ሁሉ የራስ ጥያቄና መልስ ተወጥሮ ባለበት ዝም ብሎ የመሀሉን ስፖኪዮ ሲመለከት ከኋላው ባለ አንድ ቅያስ ላይ መኪና ቆሞ ተመለከተ። ሽጉጡን ከመሳቢው አቀባብሎ በማውጣት ቀስ አድርጎ ማርሹ ጋር ያለበት ክፍት ቦታ ቀስ አድርጎ አስቀመጠው። ሰረቅ አድርጎ ወደ ኋላ እየተመለከተ "እነዚህ ውሾች እኔንም እየተከታተላችሁኝ ነበር? የማትረቡ ብሎ ሊዞር ሲል አይኑ ላይ አንድ ነገር ተመለከተ። የሚከታተለው መኪና ላይ "ዓደይ ሞል" የምትል በራሪ ወረቀት ነገር የመኪናው መስታውት ላይ ተመለከተ። የምፀት ፈገግታ ፈገግ አለና "መች አጣኋችሁ የዚህን ሰው ማንነትና ምንነት ያወኩ ጊዜ ያኔ እኔ ኢንስፔክተር ሸዋንግዘው አይደለሁም ልጆቼን ይንሳኝ!" አለ ከንፈሩን ንክስ እያደረገ። ****
ንጋት ሲሐም ኤሌዝንና ብሩክታዊትን ትምህርት ቤት አድርሳ ከመጠች በኋላ ተሕሚድን ትተሻሸዋለች።"ኧረ ተይ የኔ ፍቅር ኢንስፔክተር በጣም ትልቅ ሀላፊነት ነው ሰጥቶኝ የሄደው"አለ የሚሰራውን ስራ አቁሞ አይኖቿን በስስት እየተመለከተ። " ትንሽ ጊዜ ብቻ ነው እኮ።ከዛ ስራዬን ስጨርስ ምንም ችግር የለውም።የፈለግነውን ጊዜ አብረን እናሳልፋለን"ብሎ ወደስራው ሊዞር ሲል ሲሐም መላፋቷን ስትቀጥል ትሕሚድ ቦግ አለበትና "እየነገርኩሽ አይደል ሲሓ! ምንድን ነው እንደ ህፃን ልጅ የምታዳግሚኝ"ብሎ ኮስተር አለባት። "እና ልትቆጣኝ ነው?" አለች እሷም ከመቅፅበት ኩስትር አለች። "የምገላው ባህሪሽ ይሄን ነው።በተደጋጋሚ ነግሬሻለሁ።ከዚህ በኋላ ግን ደግሜ አልነግርሽም እንዳታስቢው እሺ"አለና ዝም ብሎ ወደ ላፕቶፑ አይኖቹን ላከ። ሲሐም ጥፋቷ ታውቋት ይሁን በተሕሚድ ተናዳ በውል ባታስታውቅም እየተመናቀረች ክፍሉን ለቃለት ወጣች። የእሷን መውጣት ተከትሎ ትንሽ ጊዜ ከቆዬ በኋላ በሩን ከውስጥ ቆለፈው። መዘጋቱን የተመለከተችው ሲሐም ይበልጥ በመናደድ "ቆይ አሁን በሩን መዝጋት ምን ይሉታል?" ብላ አጉተመተመች።
****
በርካታ የፖሊስ መኮንኖች፣ የፖሊስ አባላት፣ የፌደራል ፖሊሶች፣የደህንነት ተወካዮች ሰቪሎች እና ሲቪሎች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ከሆስፒታል የአስከሬን የማውጣት ስነስርአትና በክብር እየተደረገለት ይገኛል። ሁሉም ፊት ላይ አንዳች ሀዘን ይነበባል። በተለመደው ዝግጅት በስነስርአት አስከሬኑ ወደ መኖሪያ ቤቱ ተሸኝቶ ዘመድ አዝማድ የስራ ባልደረባዎችና ጓደኞች በተገኙበት የማስተላለፍ ስራ ከተሰራ በኋላ የሁሉም የፖሊስ የደህንነትና የወንጀል ምርመራ ክፍል እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ ለስብሰባ እንዲገቡ የፍትሕ ምኒስቴሩና የደሕንነት ኃላፊው ለሁሉም መረጃውን አደረሰ።
ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ሀላፊዎች ሁሉም ተገኝተው ስብሰባው መካሄድ ሲጀምር ሁሉም በየተራ ሀሳብና አስተያየት መስጠት ጀመረ። ሰብሳቢዎቹም ፍፁም በሆነ መረጋጋት የተፈጠረው ነገር ምንም ሳይመስላቸው ፊታቸውን አለስልሰው ልባቸውን አደንድነው ስበሳባቸውን ማካሄድ ቀጠሉ። ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ለአንድ ሀያ ደቂቃ ስብሰባው አብ የሚል ነገር ያለው እስኪመስለው ድረስ ቢቆይም ነገር ግን። ዝም ብሎ ሁኔታውንና ድርጊቱን ውሃ ለመቸለስ ለማቀዝቀዝ እንደሆነ ሲረዳ የደህንነት ምኒስቴሩ ለአስተያየት ሰጪዎች እድል በሚሰጥበት ጊዜ እጁን አውጥቶ እድል ከተቀበለ በኋላ የደህንነት ምኒስቴሩን ይሁንታ ሳያገኝ መናገር ጀመረ። ሁሉም በድንጋጤ ዞረው ተመለከቱት "እስካሁኑ ደቂቃ ዴረስ በትዕግሥት ስጠባበቅ ነበር። ምን አልባት ሄደን ከምንሰራው ስራ በላይ የበለጠ ቁምነገር ካለ ብዬ ነበር የተቀመጥኩት። እንጅ የፖለቲካ ሽኩቻውንና አንድ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ስብሰባ የምትሉት ነገር በጣም ይሰለቻል። ትላንት ንፁሀኖች ሲሞቱ ነበር።ዛሬ ደግሞ ይሄው ቢሯችን ላይ ገብቷል።ዋና ሳጅን አክሊሉ የሺህዋስ ከወራት በፊት ልክ እንደኛ የንፁሀን ደም ደመክልብ ሆኖ እንዳይቀር ለዘመዶቻቸው ደግሞ ፍትህን ለማስገኘት ሌት ተቀን ሲሰራ የነበር ጓዳችን ነበር። ነገር ግን በዚህ ስአት እሱም የነዛ ምስኪን ዜጎች እጣ ፈንታ ደርሶት እሱም አርፏል። እኛ ደግሞ አሁንም በቸልተኝነት ስብሰባ ላይ ተቀምጠን የማይሆነውንም የሚሆነውንም እያወራን ነው። ይቅርታ እኔ በዚህ ስሜት ውስጥ ሆኜ ስብሰቤውን መቀጠል አልችልም!" ብሎ .......

@fetaenbeel
369 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:45:46 "ናፊባ"
ክፍል ~ ሠማንያ አራት
በአምባዬ ጌታነህ
"እስካሁን አልተኛሽም የኔ ፍቅር?" አለ። "እንዴት ብሎ እንቅልፍ ይውሰደኝ አንዱን ከአንዱ እየደራረብኩ ሳስብ"አለች። "ምንድን ነው እንደዚህ በጣም ተጨንቆ ማሰብ እ የኔ ፍቅር ሀሳብሽንም ጭንቀትሽንም ልወስድልሽ ወይም ልጋራሽ አይደል ባልሽ የሆንኩት። በይ ሁሉንም አንድም ሳታስቀሪ ንገሪኝ አለና ብብቶቿን እየነካ ሊያስቃት ሞከረ። ሙከራው ባክኖ አልቀረም። በሚገባ ነው የሳቀችለት። ተሕሚድም በዛው እቅፍ አድርጎ ወደ እቅፉ አስጠግቶ ይስማት ጀመር።ጥልቅ በሆነ የስሜት ውቅያንስ ውስጥ ሆነው እየተሳሳሙ ከቆዩ በኋላ ተሕሚድ በጆሮዋ የሆነ ነገር ሹክ አላት። ሲሐም በሳቋ ልጆቹንም ላለመቀስቀስ እንዲሁም ሸዋንግዛውን ላለመረበሽ አፏን አፍና ለረጅም ጊዜ ሳቀችና "አርፈህ ተኛ የራስህ ቤት እንደለመድከው ይሻልሀል። ይሄ የሰው ቤት ነው። የሆነ ድምፅ ብናሰማ አጎቴ ይረበሻል። አጎቴ ደግሞ እንዲረበሽ አልፈልግም"አለች እየሳቀች።እና በዚህ ስአት ከባልሽ በላይ የምታስቢው ለአጎትሽ ነው ማለት ነው?"አለ ተሕሚድ ለቀልድ ያህል ኮስተር እያለ። "አዎ በመጀመሪያ በቤቱ ልናከብረው ይገባል።ሁለተኛ ደግሞ ያው አጎቴ ነው ሶስተኛው ደግሞ ያው አጎቴ ነው"ብላ ስቃ ከንፈሩን ጉርስ አደረገችውና ሰውነቱ ላይ ልጥፍ አለች።
**************
"አንተ ለሊቱን በሙሉ ሳስብ እኮ ነው ያደርኩት የሆነ ነገር ገርሞኝ" "ደግሞ ምንድን ነው የገረመህ?" "አንድ ያልጠበኩት ልጅ ያልጠበኩት ቦታ ላይ አግኝቼው!"አለ "ደግሞ ማን ነው ያልጠበከው ቦታ ያገኘኸው? ሲጀመር ሸዎች ስንባል እኮ ያልተጠበቅንበት ቦታ መገኘት ደስ ይለናል! ስለዚህ ብዙ መደነቅህን አቁም። እኔ ብዙ ሰዎችን ያልጠበኳቸው ቦታ አግኝቻቸዋለሁ። ሲጀመር የነሱን መዳረሻ የሚያውቁት እነሱ እንጅ አንተ ወይም እኔ አይደለሁም። አሁን ለምሳሌ ባለው የሰዎች ተግባቦትና ለእኛ እሱ በታዬን ልክ ይሄ ልጅ እንዲህ ቢሆን እዚህ ቦታ ላይ እናገኘዋለን። ይሄ ቦታ ይሆነዋል ብለን እናስባለን!። ነገር ግን ሰውዬው ውስጡ ላይ ያለውን መነሸጥ አናውቀውም።ስለዚህ ማንንም በየትኛውም አጋጣሚ ብታገኘው መገረም የለብህም ጃል!" "አንተ ደግሞ እስኪ ዝም ብለህ አትቀደድ ለመሆኑ ስለማን እንደማወራ አውቀህ ነው እይደዚህ የምትለኝ?" "እኔ ደግሞ ማወቅ አይጠበቅብኝም አልኩህ።አጠቃላይ የሰዎችን ስነ ባህሪ ና ድብቅ መሻት ያጠናውን ሳይንስ ቀይጬ ነው የነገርኩህ። ሰዎች አሁን ያልጠበካቸው ቦታ ካገኘኻቸው።ያ ለማንም ያልተገለጠው የእነሱ የውስጥ መሻት ብቻ የነበረ ሁነት እንጅ አንተ እንዳየኸው ባጋጣሚ ላይ የተመረኮዘ አይደለም።ስለዚህ አእምሮህን ሰፋ አድርገውና በሰዎች ከመደነቅ ወጣ በል"አለ "ዛሬ ምንድንነው በጠዋቱ እየጋትከኝ ያለኸው? ለመሆኑ አንተ በምን ስራ እየሰራህ ነው እንደዚህ በጠዋቱ ልቤን የምትጠባው?" "አንተ የማትጠብቀው ቦታ ነው እየሰራሁ ያለሁት"አለና ሳቀ። "በቃ እሺ ወዳጄ ምንም ስራ ችግር የለውም።እኔ አሁን የደወልኩበት የተሕሚድን ጓደኛ ስልክ እንድታፈላልግልኝ ነው።" "ቆይ እስኪ እኔ ጋር ልፈልግልህ።አይጠፋም በቅርብ ነው ከእኔ ጋር ራሱ የተገናኘነው!" "የምር በጣም ደስ ይላል ምን ላይ ተገናኝታችሁ ነው? ስራችሁ ተመሳሳይ ነው እንዴ?" በማለት አጋጣሚውን በመጠቀም ጥያቄዎችን ሲያዥጎደጉድበት "ምነው ሰውዬ የአጋጣሚውን ቀዳዳ ተጠቅመህ በጥያቄ ዘጋኸቸውኮ ቀዳዳዎቹን። የምርመራ ቡድን ውስጥ ነው እንዴ የምትሰራው"ብሎ ኩም ካደረገው በኋላ "ለማንኛውም በአንድ ካምፓኒ በተዘጋጀ ሴሚናር ላይ ነው የተገናኘነው። እሱ ደግሞ የክብር እንግዳ ነበር የሕይወት ልምዱንም (Life Experience Share) ሲያጋራን ነበር። ሲበዛ ትሑትና አስተዋይ ልጅ ነው። የቃላት ቅንብሮቹም እጅግ የሚገርሙ ናቸው በጣም ደስ የሚል ልጅ ነው!" "ኧረ በጣም ይገርማል።ስለዚህ የዛን እለት ያለ ጉዳዩ ነዋ የመጣው። እኔ ደግሞ ስራው መስሎኝ ነበር!" "ቆይ የፈለከውን ለምን በቀጥታ አትነግረኝም!" "ምን እንደሚሰራ ማወቅ ፈልጌ ነው!" "ለምንህ?" "ያው ማወቁ መች ይጎዳል ይጠቅማል እንጅ። ለአንድ ወንድሜ ስራ እያፈላለኩ ስለሆነ ድንገት ትዝ ብሎኝ ነው። ሌሎቹንም እያስታወስኩ ስለነበር" ብሎ መከላከያ ሀሳብ አቀረበ። አሁንም ግራ በመጋባትና በሰጠው ምክንያት ባለመርካት በእርጣሬ "እንደዛ ከሆነ ቀጥታ ተሕሚድን ከመጠየቅ እኔን አትጠይቀኝም ነበር። ለእኔ ደውለህ እኔን መጠየቅ እንዳለብህ ረስተኸዋል ወይስ ትዝ አላልኩህም?" በማለት የመጨረሻ የሚመስል ጥያቄ ጠየቀው። ስህተቱ ወዲያው ገባውና "ፅ ፅ ልክ ነህ በናትህ እግዚአብሔርን አንተን መጠየቅ እንዳለብኝ ርስተሰ አድርጌዋለሁ። በዛ ላይ ሁልጊዜ የማገኝህ ያህል ሆኖ ነው የተሰማኝ ለማንኛውም አሁን ይቅር ካደረክልኝ አንተም ፈልግለት"አለ መንተፍረቱን "አይይ የአንተ ነገር ለማንኛውም ከቀልብህ ሁን። እንደ እውነቱ ለመማገር ከተሕሚድ ጋር ችግር ያለብህ ነው የምትመስለው አጠያየቅህ አወራርህ"ብሎ ትንሽ ፈገግ ካለ በኋላ "እንደ እውነቱ ለመናገር ምን እንደሚሰራ እንኳ አላውቅም ግን ሲመስለኝ አንድ ትልቅ ድርጅት ላይ ነው የሚሰራው እይደዛ ባይሆን በክብር እንግድነት ተጋብዞ የሕይወት ልምዱን እንዲያካፍል አይጋበዝም ነበር። ዝግጅቱ ደግሞ ደመቅ ያለ ነው። ከዛ አንፃር የገመትኩት ይሄን ነው ግን የጓደኛውን ስልክ እልክልህና እሱን በይበልጥ ትጠይቀዋለህ" አለና ዝም አለ። "አመሰግናለሁ በቃ በቴክስት ላክልኝ ወይም አጠገቤ ማስታወሻ ስለያዝኩ በቃልህ ልትነግረኝ ትችላለህ"አለና ምላሹን ይጠብቅ ጀመር። ጥሩ እሽ ያዝ አለና ንግግራቸውን ያሳየው ቋርጡ እዛው ስልኩ ላይ በመፈለግ የጓደኛውን ስልክ ነገረው።"በጣም አመሰግናለሁ ጓደኛዬ" በማለት ላደረገለት ነገር ሁሉ በትሕትና አመስግኖ ዘግቶ ምንም ደቂቃ ሳያባክን በቀጥታ ወደተቀበለው የተሕሚድ ጓደኛ ቁጥር ደወለ። በአሁኑ ስአት ጓደኛ እንዳልሆኑና በእሱ ስራ ምክንያት ለጊዜው እንደተዘጋጉ አስቀድሞ እያንዳንዱን ነገር አንድ በአንድ ሁሉንም አጫወተው።
"እና አለቃ ጓደኛው እንደነገረኝ ተሕሚድ እጅደጠረጠርነው ስውር ፖሊስ ሳይሆን የኢንስፔክተር ሸዋንግዛውን የወንድም ልጅ አግብቶ ነው። ከእሱ ጋር የተዛመደው። እና ልጁ እንዳለኝ ከሆነ ኢንስፔክተር በፈለገው ጊዜና ወቅት ሁሉ አብሮት ይታያል ነው የሚለው።እንጅ ትክክለኛ የስራ ፖዚሽኑ በአንድ የውጪ ግብረሰናይ ድርጅት ነው የሚሰራው NGO ውስጥ መሰለኝ የሚሰራው"በማለት የሰማውን መረጃ በሙሉ ነገረው። "በጣም ጥሩ ነው የሰራው።እኔ የምወደው እንዲህ አይነት የተፋጠነና ጥራት ያለው ስራ ነው። ጎበዝ በርታ አሁን በአጭር ጊዜ ይሄን ያህል መስራት ከቻልክ ምንም የሚያቅትህ ነገር አይኖርም።በርግጥ እስካሁን ያቃተህ ስራ የለም።አሁን ዋናው ነገር ስለ ተሕሚድ ይሄን ያህል ካወክ ሌላው ትርፍ ስራ ነው። ስለዚህ በቅርቡ የኢንስፔክተር እህት ታግታለች ተብላ የተወራላት የተሕሚድ ባለቤት ነበረች ማለት ነው"አለና "በል ይሄኛውን ግዴታህን በሚገባና ያለጊዜው ስለጨረስክ መጥተህ ቡድንህን መቀላቀል ትችላለህ!" ብሎት ተሰናበተው። የደስታ ወጋገን ፊቱ ላይ እንደ ብርሃን ፀዳል ተጎናፅፎ በሀሴት ፈገግ አለ። ማንም ሰው የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት ሲወጣ በጣም ደስ ይሰኛል።የእሱም የነፍሱ ጥጋብ የተጣለበትን ኃላፊነት እንደተወጣ ኃላፊነቱን በሰጠው ሰው ማረጋገጫ ሲቀበል ነበር።

@fetaenbeel
351 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:45:46 "ናፊባ"
ክፍል ~ ሠማንያ ሦሥት
በአምባዬ ጌታነህ
"ተመልከት ኢንስፔክተር አሁን ለምሳሌ ይችን ፓርት........"አለና ቪዲዮውን አቁሞ ዙም እያደረገ "ይችን አምፖል ቀለሟ እጅግ ድምቅ ያለ ሆኖ ነገር ግን ውስጧ ላይ ምንም አይነት ነገር የላትም። ይችኛዋን ደግሞ ተመልከታት።አንድ ጊዜ ነካ አድርጎ ከእንደገና ቪዲዮውውን እያቆመ።የቅድሟ አበባ በሌላ ከለር ውስጥ ሆና ወደ ግራ በኩል ዘመም ብላ ሌላኛዋ ቅርንጫፏ ደግሞ በቀኝ በኩል ጠንዘል ብሎ ክብ ሰርቷል።ቀለሙ ደግሞ ክቦቹን ፓርት በሚገባ ቀብቶ የቀለበት ቅርፅ አስይዟቸዋል።ሁለቱም ተመሳሳይ የሚያደርጋቸው የቀለበት ቅርፅ መያዛቸውና ትኩረት እንዳይደረግባቸው ደግጋጎ ከለራቸውን የተለያየ አድርገውታል። የዚችኛው ቅርንጫፍ ደማቅ ሰማያዊ ነው የተጠቀሙት።የዚችኛዋን ደግጋጎ ደብዛዛውን ሰማያዊ ነው የተጠቀሙት ይሄ በአጋጣሚ አይመስለኝም። ጥልቅ የሆነ ምስጢር እንደተቀመጠበት ያስታውቃል።ቪዲዮውን ለቀቀ ሳደርገው የፊደል ቅርፅ እየያዘች ትጠፋለች። ይቺ ፊደል ደግሞ ተመልከታትና ከመጀመሪያው መነሻ ቪዲዮ ጋር ስናመሳስላት አንዳች ዝምድና ነገር እናገኝባታለን። "ሌላው ይሄኛው ቪዲዮ ነው የገረመኝ ዓደይ ሞል። እዚህም ላይ "ዓ" ላይና "ሞ"ላይ የተጠቀሱት ፊደል ላይ የተቀረፁት የቀለምና የቅርፅ መጠን ተመሳሳይ መሆናቸው ነው።ስለዚህ በዚህኛው ፊደል መሠረት አጥሩ ላይ ቦግ ብላ ስትጠፋ የነበረው ፊደል "መ" ነች ማለት ነው። አበባዋን በሌላኛዋ ሳይድ ሆነን ስንመለከትና የስር ግንዷን ደግሞ ወደ ታች ሳብ ስናደርገው የ"ሞ"ቅርፅ ይዛ እንመለከታታለን።ሁለቱን ፊደሎች ስንገጥማቸው "መሞ"የሚሉ ይሆናቸዋል።በእርግጥ ምንም አይነት ትርጉም አይሰጡም።ግን ሁለቱን ቃላቶች አንድ ላይ ገጥመን ካነበብናቸውና የመጨረሻውን ፊደል በራሳችን ብንገጥመው የሚሰጠን ትርጉም ረብ የለሽ ነው። ማለት መቼም "ይሄን ሁሉ ምስጢራዊ ፅሁፍ ሲያስቀምጡ "መሞት"የሚል ሀሳብ ያለው ፍቺ ቀርፀው አይሆንም።ምክንያቱም ይህ የእነሱን ድብቅነት ስለማያመለክት እናም አንዷን ፊደል ወስደን መፅሐፍህ ላይ ብንመረምር የተሻለ ነው የሚሆነው።በመቀጠልም ሌላም ፍንጭ ልናገኝ እንችላለን"አለ ተሕሚድ። ሸዋንግዛው በአድናቆት እየተመለከተው "እንዴት ግን እንደዚህ በጥልቀት ልትመረምር ቻልህ? የሚገርም ከፖሊስም በላይ ነው የመረዳትና የመመርመር ብቃትህ?"አለ ሸዋንግዛው በአግራሞት ተሕሚድን እየተመለከተው። "ያው ተፅእኖ በለው የልጅነት ጊዜዬን ብዙ ጊዜ በሌባና ፖሊስ ጨዋታ ነው የምናሳልፈው።ከዛ በኋላ ደግሞ አደግ ስል የወንጀል መፅሐፎችን አለም ላይ አሉ የተባሉ ዝነኛ የወንጀል መርማሪዎችን መፅሐፍ አብዝቼ አነብ ነበር። እና እንዲሁም ፊልሞቻቸውን አያለሁ።ለምሳሌ በፊልሙ የአሌክስንና የስኮፊልድን ጨዋታ ሳታየው የቀረህ አይመስለኝም።እኖዲሁም #The fact of abody #The devil on the white city #Empire of pain #People who Eat Darkness የሚሉት መፅሐፎች በደንብ አድርገው ተፅዕኖ ፈጥረውብኛል። የሚገርመው ወንጀለኞቹም አሳዳጆቹም መርማሪዎችም የሚፅፉት እንዴት ተቀናቃኞቻቸው መፅሐፎቻቸው የተረዳሁት የጭንቅላት ውስብስብ ምስጢር ጉዟቸውን ነው።ከዚህ አንፃር ነው። ብቻ ረጅም ታሪክ አለው።ስለ እኔ ታሪክ መናገር የምቀጥል ከሆነ ምርመራችንን እናቆማለን።" በማለት ፈገግ ብሎ በአጭሩ ቋጭቶት ወደ ቪዲዮው መለሰው። ሸዋንግዛው በጥሦና ከሰሜው በኋላ በአድናቆትና በጥርጣሬ ይመለከተው ጀመር። ጥርጣሬ ትልቅ መድኃኒትም ትልቅ በሽታም ነው። በፖሊስነት ሞያ ሁሉንም መጠርጠር ሁሉንም ከማመን በእጥፍ የበለጠ ነው። የሚል የስራ ፍልስምና አላቸው። ፖሊሶች ጋር ተራ ቃላት የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ትርጉም አላቸው።ዝም ብሎ ነው ያወራው ሳላስበው ነው የተናገረው ምናምን የሚባል ነገር አይሰራም። ከምን የተነሳ ነው እንደዚህ ያለው ምን አስቦስ ነው?"በሚል ምንዘራ ነው የሚፈረጀው።በዚህ የተነሳ የተገባ በሚል ጥርጣሬ ያልተገባ ጥርጣሬያቸው ከብዙ ወዳጆቻቸውና የቅርብ ሰዎቻቸው ጋር ያራርቃቸዋል። ሸዋንግዛውም አጉል ጥርጣሬ ወደ ውስጡ ሲመጣበት "ለምን ታዲያ በዚህ ልክ ግልፅ ሆኖ ምርመራውን ያለምንም ፍራቻ ያካፍለኛል?" በማለት ከእንደገና ሀሳቡን ሙሉ ለእሱ ሰጥቶ ምርመራቸውን ቀጠሉ። ተሕሚድ በጥሞና ነው ቪዲዮውን እየመለሰ እየከለሰ የሚያየው። ሸዋንግዛው በውስጡ "ይሄን ነበር አነፍናፊ መርማሪ ማድረግ"እያለ መመልከቱን ቀጠለ።
ለብዙ ደቂቃ እያቆሙ እየቀጠሉ እየመለሱ እያሳለፉ ቢመለከቱም መጀመሪያ ካገኙበት መረጃ የተለዬ ሊያገኙ ባለመቻላቸው በጣም ግራ ተጋቡ። "አሁን i think መተኛት ሳይኖርብን አይቀርም ይሄን ምርመራ ጠዋት ብንቀጥለው ይሻላል!"አለ ሸዋንግዛው "ሳይሻል አይቀርም በአዲስ አእምሮ ግን የተወሰነ ፈሰንጭ እንኳ እንዴት አናገኝም። ትንሽ እንቆይ እንዴ?"አለ ተሕሚድ ""ግዴለህም ተወው አአምሯችን መስራት ከሚገባው ስአት በላይ ነው የተጠቀምነው ስለዚህ እናሳርፈውና ጠዋት ከቻልን ቀደም ብለን ተነስተን ይሻላል"ብሎ ሸዋንግዛው ላፕቶፑን ዘጋው። "ወደ ባልደረባህ ስንት ስአት ላይ ነው የምትሄደው?" አለ ተሕሚድ " ጠዋት ወደ አስራሁለት ስአት ወይም አንድ ስአት አካባቢ"አለ ሸዋንግዛው ላፕቶፑን ወደ ትንሿ ባግ እያስገባ።"ነገ ወደ ስራ ትገባለህ እንዴ?"አለ ሸዋንግዛው "አዎ የሆነች ስራ አለችብኝ ገባ ብዬ እወጣለሁ!"አለ ተሕሚድ "እ እ በቃ እሺ"አለ ሸዋንግዛው የሆነ ነገር ሊል ፈልጎ ነገር ግን ከእንደገና ሀሳቡን ወደ ራሱ እያቆዬ "የምታዘኝ ነገር ካለ ወይም እንዳደርግልህ የምትፈልገው ነገር ካለ ንገረኝ!" "ያው እሱማ ነበር ነገ ልጆቹን ማን ወደ ትምህርት ቤት ወስዶ ያመጣቸዋል።በዛ ላይ ልዩ የሆነ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል።ልቤ የሆነ ነገር ይለኛል። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንደዚህ ፍርሃት ፍርሃት ያለኝ"አለ ሸዋንግዛው። "እሺ ኢንስፔክተር ችግር የለውም በቃ እኔም ሆንኩ ሲሐም ነገ ወደየትም አንሄድም ልጆቹን አስገብተን እነሱን እንጠብቃለን።አንተ ስራህን ያለምንም ስጋት መስራት ትችላለህ!"በማለት ተሕሚድ ምንም ማሰብ እንደሌለበት ለኢንስፔክተር ሸዋንግዛው አስረግጦ ነገረው። ሸዋንግዛው በተሕሚድ ትሕትናና ታዛዥነት ቅንነት በመደሰት የጠዋቱን መርሀግብር አንድ በአንድ ማውጣት ጀመረ። ወደ ዋና ሳጅን አክሊሉ የሺህዋስ አስከሬን ወደሚገኝበት ሆስፒታል ከሄደ በኋላ አንዳንድ መረጃዎችን መሰብሰብ እንዳለበትና ምርመራውንም እስከዛሬ ከሚጠቀመው ሀይል በላይ ተጠቅሞ መመርመር እንዳለበት አንድ በአንድ በሀሳቡ ጨርሶ ተሕሚድን "በል ደህና እደር"በማለት ወደ መኝታ ክፍሉ ሄደ። ተሕሚድም ለሸዋንግዛው ተመሳሳዩን የደህና እደር መልስ መልሶ ሚስቱ ወደ ተኛችበት ክፍል አመራ።ሲሐም አይኖቿን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገች ጠበቀችው። ተሕሚድ የሲሐምን አለመተኛት ሲያይ ድንግጥ ብሎ.....

@fetaenbeel
347 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:45:46 "ናፊባ"
ክፍል ~ ሠማንያ ኁለት
በአምባዬ ጌታነህ
"እስካሁን ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም!" "ለሰከንድ አይናችሁ እንዳይሸፈን ተናግሪያለሁ።ዛሬ የመጨረሻችን ነው የሚሆነው።በእናንተ ስህተት እቅዴ ባይሳካ የሚደርሳችሁ የእሱ እጣፈንታ ይሆናል። በምንም ታዕምር ርህራኄ የሚባል ነገር የለም" "እሺ እመቤት በሚገባ ተልዕኳችንን እንፈፅማለን።ለዚህ ምንም ሀሳብ እንዳይገባሽ።በርግጠኝነት የባልደረባውን ሞት ሲሰማ መውጣቱ አይቀርም። ዜናው ደግሞ እስካሁን ባይደርሰው ነው እንጅ ይወጣ ነበር" "እስኪ በእርግጠኝነት አትበሉ። እንደሱ ስትሉኝ ነው ይበልጥ የምናደደው።እባካችሁ ስለፈጠራችሁ በእርግጠኝነት ቅብርጥሴ ምናምን እያላችሁ አጓጉል መሳነፊያ አትንገሩኝ። እስኪ በእርግጠኝነት ይሆናል እኖዲህ ይሆናል እያላችሁ ስንት ነገሮች ያልሆኑ አሉ? እ እስኪ በል። "እመቤት አሁን ግን ይውጣ እንጅ ችግር የለውም።ለሰከንድም ቢሆን አይኔን አልሸፍንም።ዛሬ ይሄን ተልዕኮ ሳልፈፅም አልመጣም።በማለት በእርግጠኝነት ስሜት ውስጥ ሆኖ ቃለመሀላ የሚፈፅም እስኪመስል ድረስ አንደኛውን እጁን በሌላኛው እጁ ላይ እያኖረ ሰው የሚመለከተው እስኪመስል ድረስ በፍርሃትና በጥንቃቄ ቃል ገብቶ ተሰናበታት። "ዛሬማ መጨረሻህ ነው ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው። ከጓደኛህ ጋር ቀብርህ ይፈፀማል ምንም አታስብ። ዓሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል"አይደል የሚባለው ተረቱ አንተም ዘንዶውን ለማግኘት መበርበርህን መጎርጎርህን አላቆምክም አይደል።ስለዚህ ዋጋህን ታገኛለህ። ሰው አሮ ልጆቹን አያሳድግም ለዛውም እናት የሌላቸውን ልጆች ብቻውን እያሳደገ እንዲህ መዳፈር? የአንተ ልብ ከምን እንደተሰራ ከገደልኩህ በኋላ አጣራለሁ። ሆ ሆይ ፈጣሪዬ ሆይ ምን አይነቱ ድርቅ ያለ ጅል ሰው ነው በፈጣሪ!" በማለት እየተገረመ የመኪናውን ወንበር ወደ ኋላ ለጠጥ በማድረግ ለመመልከት እንዲመቸው ከሸዋንግዛው ቤት ትይዩ በመሆን አስተካክሎ ወደኋላው ለጠጥ ብሎ እጆቹን ራሱን አስደገፈና ስልኩን እየነካካ በስክሪኑ ሰረቅ እያደረገ ይመለከት ጀመር። መኪናውን ያቆመበት ስፍራ የሸዋንግዛውን መውጫና መግቢያ ለማወቅ እንዲሁም በቀላሉ ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ ተጠንታ ነው። በዚህም መሠረት ነው እየተመለከተ ያለው።የመኪናዋ ስሪትም ባለስልጣናት የሚይዟት ቅንጡ መኪናና መስታውቷ ከውስጥ ወደ ውጭ እንጅ ማየት የሚቻለው ከውጪ ወደ ውስጥ ፈፅሞ አታሳይም።ይህቺ መኪና ልዩ ለሆነ የግዳያ ኦፕሬሽን ላይ ነው የሚጠቀሟት። እንዲሁም ባለስልጣናቶች ደግሞ ከቦታ ወደ ቦታ ሲንቀሳቀሱ በማንም ጠላት አይን በቀላሉ እንዳይገቡና አንዳች ችግር እንዳይገጥማቸው ነው።
********
ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው የክፍሉን በር መለስ አድርጎ መብራቱን አጥፍቶ ማስታወሻውን እና ናፊባ የተሰኘችዋን መፅሐፍ ከአጠገቡ አስቀሜጦ ቪዲዮውውን መመልከት ሲጀምር ስልኩ ጠራ። ደግሞ በዚህ ለሊት ማን ነው የሚደውለው በማለት ስልኩን ሲመለከት ደዋዩ አለቅዬው ነበር። አንዳች ነገር እንደተፈጠረ ስሜቱ ሹክ አለውና "አቤት አለቃ"አለ። "እንዴት ብዬ እንደምነግርህ ከብዶኝ ነው።" "ም ም ምን ተፈጠረ አለቃ?" ሸዋንግዘው ድምፁ እየተቆራረጠ ጠየቀው። "ኢንስፔክተር በጣም አዝናለሁ ዋና ሳጅን አክሊሉ የሺህዋስ አርፏል። የገደል ማሚቶ ድምፅ የፈነዳበት እስኪመስል ድረስ ሸዋንግዛው በድንጋጤ አፉን ከፍቶ ቀረ። የአይኖቹ ሽፋሽፍት እርግብግቢት በፍጥነት ይንቀጠቀጡ ጀመር። ሰውነቱ ወደ በድንነት ሲቀየር ተሰማው።ቀስ ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ስልኩን ዘግቶ በሩ ላይ ቆመ።ተሕሚድ ሸዋንግዛው የሰማው ዜና ጥሩ እንዳልሆነና አሳዛኝ እንደሆነ ከሁኔታው ለመረዳት ችሏል።ነገር ግን ሊያፅናናውና አይዞህታውን ሊቸረው ሳይሞክር ዝም ብሎ ቪዲዮውን መመልከቱን ቀጠለ። ግን ውስጡ ተረጋግቶ የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት የሚሞክርበትን ስሜት ረበሸው። ስለዚህ በቃ መጠየቅ ይኖርብኛል በማለት ከራሱ ጋር አስቦ ከወሰነ በኋላ ቪዲዮውን አቁሞ "ኢንስፔክተር ምን ችግር ተፈጠረ?" ብሎ ጠየቀው። ረጅም ሰከንድ ዝም ካለው በኋላ "ምን እኛ ጋር ችግር ይጠፋል ብለህ ነው? አንድ ባልደረባዬን ጉዳት አድርሰውበት ነበር። አሁን ግን ሞተ ነው የሚሉኝ"አለና በትካዜ ወደታች አቀረቀረ።" ተሕሚድ ምን እንደሚለው ይበልጥ ጉዳዩን ከሰማ በኋላ ግራ እተጋባ። አሁን ሁሉም ነገር በጣም አስቸጋሪና ፈታኝ ምዕራፍ ላይ እንዳለ አመነ። "እና ምን አሰብክ?" ተሕሚድ በድጋሚ ጠየቀው። " ያው አሁኑኑ መሄድ ይኖርብኛል።ቢያንስ የሆነ መረጃ ካለ እኔ አገኘዋለሁ። በዛውም አሟሟቱን ባዬው" አለ ይበልጥ እምባው ካልወረድኩ ብሎ እየተናነቀው።"ግን ኢንስፔክተር ከአንተ አላውቅም። ዝም ብዬ ውስጤ ላይ ያለውን ነገር ለመናገር ያህል እኔ እንደሚመስለኝ በዚህ ስአት ለመሄድ የማይታሰብ ነው። ምን አልባት መረጃም ካለ ፀድቶ ይሆናል። ሟቹ የፖሊስ ባልደረባ መሆኑን ገዳዮቹ መቼም ሳያውቁት አይቀርም። አንድን ሰው መቼም በደመነፍስ አይገደልም።ፖሊስ እንደመሆኑ መጠን አገዳደላቸውንም በዛው ልክ ረቀቅ ያደርጉታል። ስለዚህ ጠዋት ላይ ዝም ብለህ ብትደርስ ይሻላል።አሁን መሄድህ እንደ እኔ ሄደህ ጉዳዩን ቨአይንህ ከመመልከት ውጪ ብዙም ለውጥ ያመጣል ብዬ አላምንም" አለ ተሕሚድ ሸዋንግዛው በእርጋታ ሆኖ ሲናገር የነበረውን ተሕሚድን በስነስርአት ካዳመጠው በኋላ " በርግጥ አለቃዬ ወደስፍራው አቅንቶ አስፈላጊውን ምርመራ እያደረገ ነው። ግን እኔ ብኖር ደግሞ በጣም ጥሩ ነው ብዬ ነው"አለ። " ልክ ነህኮ ኢንስፔክተር ብትሄድ በጣም መልካም ነው። ግን ደግሞ አሁን የጀመርነው ስራ ወደዛ ከምትሄድበት ጉዳይ የበለጠ ነው።ምን አልባትም ይቺን ቪዲዮ በመመልከት የባልደረባህን ገዳዮች ለፍርድ የምቀርብበትን ጊዜ ብታቀርብ ነው የሚሻለው ባይ ነኝ።"አለ ተሕሚድ በድጋሚ ሸዋንግዛው እምባ የተሸከሙ አይኖቹን በእልህ ጫን አድርጎ አፉን ገጥሞ ጥርሶቹን በንዴት እያጋጨ። "በትክክል! ምን አልባትም የዛሬውን ማምሻዬን ተመልክተው አጀንዳ እንድቀይር ይሆናል የገደሉት!" አለ ሸዋንግዛው።" ይሄም ሊሆን ይችላል።እነዚህ ወንጀለኞች ሲመስለኝ በጣም የተራቀቁና በሞያቸው ከደህንነት ያልተናነሱ ሰዎች ናቸው። ስለዚህ ተረጋጋና ከስሜታዊነትህ አገግመህ ወደ ዋናው እና ሀረጉ ጉዳይህ ትኩረት አድርግ!" በማለት ምክረ ሀሳብ አቅርቦለት ቪዲዮውን አጫውቶ መመልከት ጀመረ። "አመሰግናለሁ ተሕሚድ ይሄን ቪዲዮ በሚገባ ልንመረምረው ይገባል።በቃ ባለመሄድ ወስኛለሁ አለና ተቀመጠ።እልህና ቁጭት ሀዘንና ተስፋ የተቀላቀለበትን ፊቱን ላፕቶፑ ላይ በመጣድ የምሽቱን ሚሽን ለመተንተን ቪዲዮውን አጫውቶ በስነስርአት ይመለከት ጀመር።
"ተመልከት ኢንስፔክተር አሁን ለምሳሌ ይችን ፓርት........"አለና ቪዲዮውን አቁሞ ዙም እያደረገ

@fetaenbeel
358 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 21:40:59 "ናፊባ"
ክፍል ~ ሠማንያ አንድ


ራሷን በሁለት እጆቿ ጭምቅ አድርጋ ይዛ ልትጮህ ዳዳት። አጠገቧ ያሉት ጠባቂዎቿ ግራ በመጋባት የምታደርገውን ነገር ዝም ብለው ይመለከታሉ። በምታደርገው ነገር ጣልቃ መግባትም ሆነ አስተያየት መስጠት ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ያውቃሉና። ዝም ብለው እንደ ህፃን ልጅ እየተቁለጨለጩ ማየት ብቻ።ጊዜ እንደ ወቅት ነው።ይፈራረቃል። መኸሩ ወጥቶ በልጉ እንደሚተካው የሰው ልጅም ልክ እንደወቅቶች ነው። የሚሳምበት፣ የሚሰማበትና፣የሚናገርምበት ዘመን አብቅቶ ወደ ማይሰማበት ወደ ምንምነት ይቀየራል። ዓለም ላይ ያሉ የሀይል አሰላለፎች ደግሞ በዚህ መንገድ ነው የተሰሩት። ካለችበት የጭንቅ ምጥ ትንሽ ተንፈስ አለችና አጠገቧ ያሉትን ሰዎች ተመለከተቻቸው። በድንጋጤና በፍርሃት ውስጥ ሆነው እየተመለከቷት ነው። "እኔ ከእናንተ ውጪ ማንም የማምነው የለም። ጠላቶቼ የኔን ሰዎች እያሸፈቱብኝ ነው። ወንድሜ ራሱ የእኔ የምላቸውን ሰዎች በገንዘብ ይሁን በተንኮል ሳያጠምዳቸው አይቀርም። ስለዚህ እኔና እናንተ አንድ ትልቅ ነገር ማድረግ አለብን። የአሁኑን ጉዟችንን በተመለከተ ምን የምትሉት ነገር አለ?" አለች።ሀሳባቸውን መስማቱ የተሻለ እንደህነና በጉዳዩ ላይም ሆነ በሚሰሩበት ነገር ላይ ሀላፊነት እንዲሰማቸው ከመፈለግ የተነሳ። ጥያቄዋ ድንገት የሆነባቸው ጠባቂዎቿ እርስበእርስ ተያዩና "እኛ አናውቅም እመቤት ምን አስበሽ እንደነበርም አልነገርሽንም።ስለዚህ ምን ልንል እንችላለን?"አለ አንደኛው።ሁሉንም በሚወክል አነጋገር።" ያው እናንተ ላይ ቅሬታ እንዳይኖር ነው። ማለት አላውቅም ምን አልባት ስህተት ካለመፈለግ የተነሳ ሁላችንም ላይ አደጋ እንዳያመጣብን ከመስጋት አንፃር መጥፎ ሰው ሆኜባችሁ ሊሆን ይችላል። በዚህ ሁኔታ ታዲያ ውስጥ ለውስጥ ሳንገናኝ ልንተላለፍ እንችላለን። ስለዚህ እናንተ ውስጥ ላይ ያለውን ሀሳብ ማወቅ ሳያስፈልገን አይቀርም!" ብላ በሀዘን ተቅለሰለሰች። ከወትሮው በተለዬ መነሰገድ መለሳለሷ ጥያቄ ውስጥና መገረም ላይ የከተታቸው ጠባቂዎቿ በዛ ስሜት ውርጥ ላለችዋ እሷ ምንም አይነት ነገር ለመናገር አልፈለጉም። "በርግጥ ልክ ነሽ ነገር ግን አሁን እንዲህ አይነቱን ንግግር የምንነጋገርበት ጊዜ ላይ አይደለንም። ጊዜ ከምንገዛ የመጣንበትን ጉዳይ ፈፅመን ብንመለስ ይሻላል!" አለ አንደኛው።ሌሎቹም በልጁ ሀሳብ ተስማሙና ጉዳዩን በይደር አቆይተው ወደ እለቱ ሚሽን ትኩረት ማድረግ እንዲለባቸው ተማመኑ።
የቴክኒክ ክፍሉ ኃላፊና ልዩ የኮምፒውተር ባለሞያው በእለቱ ዋርድያ ላይ የፈፀመውን ግድያ ለማለባበስ እየሞከረ ነው። ሁሉም የዛ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶር አባላት ስለሁኔታው እና ስለተፈፀመው ግድያ ቢያውቁም ከጎኑ ከመሆን ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለና ከእሱ ቢያፈነግጡ ያው እጣ ፈንታቸው ሞት እንደሆኑ በማመን የሰጣቸውን ስክሪፕት አጥንተው ለመተ እየተጠባበቁ ባለበት ክፍሉ ያለምንም መንኳኳት የምስጢራዊው ቡድን መሪና አለቃ ጠባቂዎች መሳሪያቸውን አቀባብለው ከፍተው ገቡ። የመብራቱ ነፀብራቅ ክፍሉ ላይ ያለውን ጥቃቅን ነገር ሳይቀር አጉልቶ ያሳያል። "ቴክኒሺያኖቹ የት ሄደው ነው? ለምንድነው ቦታቸው ላይ የሌሉት?"በድንጋጤ እርስበእርስ እየተያዩ ተጠያየቁ። "ከስዐታት በፊት ደውሎልኝ ወደነበረው ልጅ እንሂድና አማሟቱን እንመልከት"ብላ ደረጃውን መውጣት ሲጀምሩ የቴክኒክ ክፍሉ ጀርባ ያለው ሩም ውስጥ የሆነ ድምፅ ሰምተው ዘወር አሉና በሩን አንኳኩ።ነገር ግን ማንም ሊከፍትላቸው አልቻለም። ደረጃውን መውጣታቸውን ቀጥለው መናፈሻው ላይ ካለ ቦታ ሲደርሱ ሁሉም የቴክኒክ ክፍል ቡድኑ ዙሪያ ገባውን እየተቆጣጠሩ ነው። "ምነው ለምን ከክፍሉ ወጣችሁ?" ረጋ ባለና ፍፁም ትሕትና በተላበሰ አነጋገር ቴክኒሺያኑን አናገረችው። "አለቃ ቅድም አንቺን ያወራሽ ዋርድያ ከማን ቡድን እንደነበር በትክክል ለማወቅ እስኪከብደን ድረስ ነው ጥቃት የከፈተብን። መብራቱንም ያበራነው እሱ ጋር በነበረን እሰጣ ገባ ምከንያት ፕሮግራም ያደረግነው ስአት በማለቁና እኛ እዚህ ላይ ትኩረት አድርገን በምንሰራበት ጊዜ ነው።" በማለት ምክንያት ያለውን አቀረበ። ምንም እንኳ የነገራትን ምክንያት ከልቧ ባትቀበለውም።ግን እርምጃም ሆነ ተቃርኖ ለማሳየት አልሞከረችም።ምስንያቱ ደግሞ ቡድኑ ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ከመፈለጓ የተነሳ ነበር።
****
ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ሁሉንም የስራ ባልደረቦቹን ወደ ቤቱ ከሸኜ በኋላ ከተሕሚድ ጋር ወደ ቤት ገቡ። ሲሐም አብዝታ ተጨንቃ ነበርና እንቅልፍ ሳይወስዳት እንዲሁ ነገሮችን እያውጠነጠነች ደረሱባት። "በጣም ፈርቼ ነበር ፈጣሪ ይመስገን በመጨረሻም መጣችሁ "በማለት ደስታዋን ገለጠችላቸው። ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ግን ልቡ ቪዲዮው ላይ ተንጠልጥሎ ነበርና ለሲሐም የእንኳን ደህና መጣችሁ ምኞት በትክክል መልስ እንኳ ሳይሰጣት ቀጥታ ወደ ማንበቢያ ክፍሉ ገባ። ተሕሚድም የሲሐምን ግራ መጋባት በመመልከት "አጎትሽ አሁን ስራ ላይ ነው። ሲረጋጋ በደንብ ያወራሻል። የሆነ ያገኘነው ምስል ስላለ እሱን በፍጥነት መመርመር ስላለበት ነው አትፍረጂበት እሺ የኔ ፍቅር!" አለ የሲሐምን ሀሳብ ለመቀየር ምክንያታዊ የሆነ ሀሳብ በመስጠት። "እሺ እንደዛ ከሆነ ግን አንተ ደህና ነህ አይደል? ያስፈራ ነበር መቼም " "አዎ ግን አሁን ሁሉም ሰላም ነው። ይልቅ ፈቃድሽን ስጭኝና ኢንስፔክተር ጋር ሄጄ አንዳንድ ነገሮች ላይ ባግዘው የተሻለ ነው" "ኧረ አጎቴ እኮ የምርመራ ስራ ሲሰራ ብቻውን መሆን ነው የሚፈልገው። ማንንም ማናገር አይፈልግም። ስለዚህ ሊቆጣህ ስለሚችል አርፈህ ተቀመጥ!"አለችና ጎትታ አስቀመጠችው። ተሕሚድ የሲሐምን ሀሳብ ለማመን ትንሽ ደቂቃ ብቻ ሲቀረው ማለትም ሸዋንግዛው ዝም ቢለው ለተወሰነ ደቂቃ እውነትም ሲሐም ልክ ነች። ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ምርመራ ሲያደርግ ብቻውን መሆን ይፈልጋል ብሎ ወደመደምደም ይደርስ ነበር። ነገር ግን ይህን በማሰብ ላይ እያለ "ተሕሚድ"በማለት ሸዋንግዛው ጠራው። ሸዋንግዛው ሲጠራው አንዳች የመንፈስ እርካታ ተሰማውና በደስታ ሲሐምን ሳም አድርጓት ቀጥታ ወደ ሸዋንግዛው ማንበቢያ ክፍል ገብቶ አቤታውን ሰጥቶ ተቀመጠ። ሸዋንግዛው በቀጥታ የስልኩን ቨመዲዮ ወደ ላፕቶፑ በመላክ ነበር ርስሪኑ ሰፋ አድርጎ ለመመልከት ሲል በፍጥነት ያስተላለፈው። "አሁን እያንዳንዷን ነገር ለመመልከት ይረዳናል። ፕሮጀክተር ቢኖር መልካም ነበር ነገር ግን ባለን የላፕቶፕ እስክሪን መጠቀም ሳይኖርብን አይቀርም አለና ላፕቶፑን በከፊል ወደ ተሕሚድ ዘወር አደረገውና "በል እኔም በጥንቃቄና እመለከታለሁ አንተም ተመልከት የሆነ ያጠራጠረህ ቦታ ላይ ሲኖር ማቆም ትችላለህ እኔም እንደዛው አደርግና እናያለን አለና ቪዲዮውን አስጀመረው።

Share & Join
@fetaenbeel
449 views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 22:32:00 "በሚገባ ደስስስ ብሎት ነው ዳሪክተሩ የፈቀደለት" ስትላት። ሶስና "ተመስገን
ተመስገን የኔ አምላክ" አለችና ፈገግ አለች። ፅናት "ስለ ያቤፆ ንገሪኛ"
አለቻት።ሶስና ፊቷን እንባ እና ፈገግታ አጀበው።
፨ "ልጄ በጣም ጥሩ ልጅ ነው ነገር ግን ሰው ይሉኝታ ይዞት እሚተወውን ነበረ
ስለሚያረግ ልጅሽ እብድ ነው ይሉኝ ነበር እኔ ያቤ ብዬ ነው እምጠራው።
ለምሳሌ ሰው እንቅፋት መቶት ካየ ከጉዳቱ ይልቅ ሁኔታውን በማየት የወደቀው
ሰው ላይ ይስቃል።
ሊላው ደሞ በየ ለቅሶ ቤቱ ስጠራ ይዤው እንደሄድ ይጎተጉተኛል። እና
ለቅሶኛውን እና አጃቢዎቹን ከሀዘን ለማውጣት ጮክ ብሎ ዘፈንም ይዘፈናል
ይዤው ባልሄድ እንኳን ተከትሎኝ ተደብቆ ይመጣል። ትኩስ ለቅሶ ላይ
ሀዘንተኛውን ከሀዘን ለማውጣት ከማፅናናት ይልቅ ለምን ቀልድ
አትነግሪያቸውም ብሎኛል እንዳውም የሆነ ቀን ሊላው ለሊት ላይ ወይም ቀን
ላይ አልያም ቤተክርስቲያን መሳቅ ከፈለገ ጮክ ብሎ ይስቃል መጮህ ከፈለገም
እንደዛው ልጄ በእራሱ አለም ውስጥ ያለ ሰው" አለችው። ያቤፅ የማይነሳ ቋሚ
የቡና እቃው ላይ በማስታጠቢያ ጆግ እና ውሀ አምጥቶ አስቀመና ብና መቁላት
ጀመረ። ሶስና እና ፅናት እያወሩ ስልክ ጠራ ፅናት ከጠረጲዛው ላይ ስልኩን
ብድግ አረጋ "ሄሎ" አለች። ከዛም ስልኩ ተዘጋ በድጋሜ ተደወለ "ሄሎ"
አለች። አሁንም በድጋሜ ስልኩ ተዘጋ።
፨ፅናት ስልኩን ጠረጲዛው ላይ አስቀመጠችው። ያቤፅ "ማነው ፅኑ" አላት።
ፅናትም "እኔጃ ማን እንደሆነ ያቤፆ ሄሎ ስል ዝም ነው የሚሉት" አለችው።
በድጋሜ ስልኩ ጠራ ያቤፅ ወደ ፅናት መጣ። ሶስናም "እስቲ አንሽው አሁን"
አለቻት። ያቤፅም "አዎ አዎ አንሽው በፂ ወይም ሊባ ናቸው የሚሆኑት" አላት።
ፅናት "ግን እኮ የሀገረ ውስጥ ቁጥር ነው" አለች። እና አነሳችው ቀጠን ያለ
የወንድ ድምፅ "ሰላም ሊባኖስዋ ዛሬ ብዙ ሙታን መተዋል መተሽ ማየት
ትፈልጊያለሽ?" አለ። ፅናት ደንግጣ ስልኩን ዘጋችው። ስልኩ በድጋሜ ጠራ
ፅናት እጅዋ ተንቀጠቀጠ። ሶስና እና ያቤፅም በድንጋጤ ውስጥ ናቸው።

ይቀጥላል.........
945 views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 22:32:00 ፅናት

ክፍል 34

ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)
.
.
#30 ሰዉ ብቻ share ካደረገዉ ዛሬ ማታዉኑ ክፍል 35 የሚለቀቅ ይሆናል !!

.
.
፨
ፅናትም ደነገጠች። ያቤፅ ወደ ፅናት ዞሮ "ፅኑ ሰማሽ ሶስና እያሉ ነው ፤ ፅኑ
ሶስና እኮ እናቴ ናት ፤ ፅኑ ሶስና እኮ ማለት የኔ እናት ናት " አለ በተናገረ ቁጥር
ድምፁ እየቀነሰ። ፅናትም ተረጋጋ እባክህ አለችው። ያቤፅ በለቅሶ ታጅቦ ጮክ
ብሎ ፅናትን ትከሻዋን ይዞ እየነቀነቃት። ያቤፅ "እናቴቴቴቴቴቴቴ"ብሎ ፅናት
አይን ላይ አፈጥጦ ጮኸ።
፨ ፅናት ወደነ ያቤፅ ቤት አፈጠጠች። ያቤፆ "እናትህን ትወዳታለክ?" አለችው
ልክ እሱ ትከሻዋን አጥብቆ እንደያዛት ይዛው። ያቤፅም እጁን ከፅናት ትከሻ
አውርዶ በጎዳናው ላይ ቁጭ ብሎ "ፅኑዬ" አላት። ፅናት "እናትህ በህይወት
ብትኖር ልክ ባለፈው እንደጮክባት ትጮህባታህ?" አለችው። ያቤፅ በመዳፎቹ
ጆሮውን አጥብቆ ይዞ ጮክ ብሎ "አይ አይ አይ ፅኑዬ አላረገውም" አላት። ፅናት
ፈገግ ብላ እንደዛ ከሆነ ወደ በሩ ተመልከት" አለችው።
፨ ያቤፅ ወደ በሩ አየ በሩ ላይ ሶስና የያቤፅ እናት ያቤፅን እያየችው ነው እና
ደሞ እያለቀሰች ነው። ያቤፅ በዝግታ ቁጢጥ ካለበት መሬት ተስቶ ቆሞ ከአይኑ
እንባ እየፈሰሰ ፊቱ በእንባ እየታጠበ አያት ሶስናም ከያቤፅ በተመሳሳይ መልኩ
ልጅዋን ያቤፅን እያየችው ነው። ያቤፅ በፍጥነት ወደ እናቱ ሶስና መሮጥ ጀመረ።
ሶስናም እጅዋን ዘረግታ ሮሮ መጥቶ ልክ እንደ ልጅነቱ እስኪጠመጠምባት
መጠበቅ ጀመረች። ትንሽ ሰከንድ ግን ደሞ ብዙ ጥበቃ ፈጅቶ ያቤፅ እናቱ እቅፍ
ውስጥ ገብቶ ማልቀስ ጀምሯል። ፅናትንም በቀስታ ወደነሱ ተጠጋች።
፨ ሶስና ያቤፅን ደጋግማ ሳመችው። ሶስና ፅናትን አየቻት "በፈጣሪ በጣም
ቆንጆ ሴት ናት በዘመኔ ያላየውትን ውበት ዛሬ አየው አንቺ የልጄ ምንድነሽ?"
አለቻት። ያቤፅ ከሶስና እቅፍ ውስጥ ወጥቶ የሶስናን እና የፅናትን እጅ አንድ ላይ
አረጋቸው እና ወደ ፅናት ዞሮ "ይህቺ ማለት ህይወቴ ናት፤ ባለፈው በሻርፕ
ተሸፈና ያየሻት የህይወቴ መለወጫ ምክንያት አረጎ አምላክ የሰጠኝ ሴት ናት
ይህቺ የኔ ሴት ናት" አላት። ሶስናም "ልጄ ይህንን ፈገግታ ካንተ ፊት ላይ
ለመጨረሻ ጊዜ ካየውት ቆየው" አለች። ፅናት ፈገግ አለች። ሶስና በፈገግታ
ፅናትን ማየት ጀመረች። ፅናት ደሞ ያቤፅን በፈገግታ እያየችው ነው ያቤፅም ልክ
እንደ ፅናት ፈገግ ብሎ ፅናትን እያያት ነው ያቤፅ እናቱን ክንዱን ትከሻዋ ላይ
በማረግ አቀፍት። ፅናት "ያቤፆ በጣም ደስ ብሎኛል" አለችው። ሶስናም ፅናትን
"የኔ ልጅ ድምፅሽ እራሱ ማራኪ ነው ልጄን ከልብሽ ነው አደል የምትፈጊው"
አለቻት። ፅናት "በጣም በጣም በጣም እንጂ" አለቻት።
፨ ያቤፅ "ቆይ ውስጥ ለማን ነው እየተለቀሰ ያለው" አላት። ሶስናም "የአባትህ
ዘመዶች ናቸው። የአባትህ እናት ከመጣች ጀምሮ ሶስና እያለች መጮህ
ጀመረች ያው እስካሁን አላቆመችም አባትህ ከሞተ ሁለት ወር አስቆጥሯል ነገር
ግን ለለቅሶ ሳይመጡ ዛሬ በድንገት መጡ"አለችው። ያቤፅ "እና አንቺስ እዚህ
ምን ትሰሪያለሽ"አላት። ሶስናም "አይ ልጄ የአባትህ ጥበቃ መጥቶ ከእዚህ
በኋላ በጭራሽ ባለ ሱቅ አደለሽም ተመልከች ብሎ ወረቀት ሰጠኝ" አለች።
ያቤፅ "ቆይ ምንም አልገባኝም እባክሽ በኋላ እኔ እምኖርበት ቤት መተሽ
እናወራለን አሁን ቤት ገብተሽ የትምህርት ማስረጃዎቼን ልታመጪልኝ ትችያለሽ
ትዝ ይልሻል አንቺ ነበርሽ የትምህርት ማስረጃዎቼን እምታስቀምጭልኝ አሁን
ገብቼ መፈገግ አልፈልግም እባክሽን አምጪልኝ" አላት።ሶስና ምንም ሳትል
በፍጥነት ሄዳ በፋይል መይዣው ያስቀመጠችውን ይዛለት መጣች። ያቤፅ
"አመሰግናለሁ እናቴ በይ በኋላ ነይ እሺ አሁን ሄጄ ያቆረጥኩትን ትምህርት
ለመቀጠል የተቻለኝን አረጋለሁ በእርግጠኝነት የድሮውን ጎበዙን ልጅሽን
እሆንልሻለሁ። በይ ግቢና አያቴን አትጩሂ ስትጮሂ በጣም ትሰቀጥጫለሽ
በያት" አለና ፈገግ ብሎ ፋይሉን ከሶስና እጅ ወስዶ ሶስናን እጅዋን ስሞ የፅናትን
እጅ ይዞ ሄደ።
፨ሶስና ፈገግ ብላ ወደ ቤት ገባች። አማችዋ አሁንም እየጮኸች ነው። ሶስና
"በቃ ይበቃሻል እባክሽን ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ።" አለች። የባልዋ
እናትም "እባክሽን ልጄን ይቅር በይው" አሉዋት ወደ ሶስና ተጠግተው እጁዋን
ያዝዋት ሶስናም "እሺ እሺ እባኮትን አሁን ይውጡ" አለችና ደረጃውን ተጠቅማ
ወደ ላይ ወጣች።
፨ አሁን ያቤፅ እና ፅናት ፅናት በምትማርበት ዩኒቨርስቲ ውስጥ ያለው የዳሪክተሩ
ቢሮ ውስጥ የያቤፅን የትምህርት ማስረጃ በማሳየት ላይ ናቸው።ዳሪክተሩም
የያቤፅን ውጤት አይቶት በጣም በመገረም ላይ ነው።
"አስገራሚ ውጤት ነው በጣም ይገረማል
በእውነት ይገረማል ብዙ ተማሪዎች እኛ ጋር በጣም ምረጥ ውጤት እያስመዘገቡ
ይመጣሉ ያንተ ውጤት ግን አስደማሚ ነው እንኳን ደህና መጣህ በእውነት አንተ
እዚህ ባትመጣ እና ስላንተ ብስማ ኖሮ ገደልም ቢሆን ገብቼ አፈላልጌ እኛ
ዩንቨርስቲ እንድትማር አረግ ነበር ነገ መተክ መጀመር ትችላለህ በምን ፊልድ
ላይ ነው መመዝገብ ወይም መማር እምትፈልገው?"አለው። ያቤፅ ፊት ለፊቱ
የተቀመጠችውን ፅናት እያያት "በማርኬቲንግ ማኔጅመንት" አለ። ዳሪክተሩም
"ጥሩ እንደውም በጣም የተማሪ እጥረት ያለበት ፊልድ ነው ከነገ ጀምሮ ዝግጁ
ከሆንክ መጀመር ትችላለህ።" አለው።
፨ ያቤፅም "እሺ ጥሩ አመሰግናለሁ ሊላ ማሙዋላት ያሉብኝ ነገሮች አሉ?"
አለው። ዳሪክተሩም "በሚገባ" አለና ከጠረጴዛው
መሳቢያ ውስጥ ወረቀት አወጣና "እዚህ ላይ ዝረዝሮች አሉ" አለው። ያቤፅ
ወረቀቱን ተቀብሎ ለፅናት ሰጣት እና ወጡ።
፨ከቢሮው ከወጡ በኋላ ወደ ቤት ተመለሱ ቤት ቁጭ ብለው በሩ ተንኳኳ ያቤፅ
ተነስቶ ከፈተው ሶስና ነበረች።" "እንኳን ደና መጣሽ ነይ ግቢ" አላት። ሶስናም
ያቤፅ በሩን እስኪዘጋው ከፊት ከፊት እየሄደች ሳሎን በር ላይ ደረሳለች። ያቤፅም
በሩን ከዘጋው በኋላ በአጭር እረቀት እየተከተላት ነው።ሶስና ወደ ሳሎን ገባች
እና ፅናትን አየቻት። "ኡፍፍፍ የኔ ቆንጆ የኔ ውብ" አለችና። ሳመቻት። ፅናት
ፈገግ ብላ "እንኳን ደና መጣሽ" አለቻት። ሶስናም "እንኳን ደና ቆየሽኝ" ብላ
አጠገብዋ ተቀመች።
፨ያቤፅም አጠገባቸው ቆሞ "መቆያ እሚሆን ምን ላምጣ" አላት። ሶስናም
"ልጄ እስቲ ድሮ ያስለመድከኝን ቡና አፈላልኝ እባክህ" አለችው። ያቤፅን ሽቅብ
እያየችው "ፅናት እንዴ ቡናም ታፈላለህ?" አለችው። ያቤፅ "እንዴታ" አለና
ሶስናን አየት አረጎ "እሺ እናቴ" አላት። ሶስና ያቤፅን በፈገግታ እያየችው "ልጄ
ጥሩ ቡና ነው የሚያፈላው ብቸኛ ልጄ ስለሆነ እንደ ሴትም እንደ ወንድም ነው
እማየው እና ያሳደኩት" አለች። ያቤፅ "በቃ ቡና ላቀራርብ" ብሎ ሄደ።
ፅናት ልክ ያቤፅ እንደሄደ "እስቲ እባክሽ ሰለ ልጅሽ ንገሪኝ " አለቻት። ሶስናም
እሺ ስለምን ልንገረሽ ይልቅ ከእሱ በፊት የሄዳችሁበት ተሳካ" አለቻት። ፅናም
761 views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 23:00:40 Katayun kfl ka 30share bahuwala


For any comment @Meki3
722 views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ