2022-08-27 19:58:01
" የሰላም ንግግር አሁንም ይቻላል " - አምባሳደር ዘነበ ከበደ
በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሰላም ንግግር አሁንም ይቻላል ብለዋል።
ነገር ግን ፤ ይህ የሚወሰነው የሰላም ንግግርን ውድቅ አድርጎ ወደ ጦርነት ባመራው ህወሓት /TPLF/ አቋም ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ያለውን አቋም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ግልፅ አድርጓል ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ ዛሬ ከሰዓት የፌዴራል መንግስት ባወጣው መግለጫ ህወሓት የከፈተውን ወታደራዊ ጥቃት አሁንም አብብሶ ቀጥሏል ብሏል።
ቡድኑ ለሰላም የተዘረጋውን መንገድ ትቶ በሙሉ አቅሙ ለጦርነት ሲዘጋጅ ቆይታል ሲል አስታውሷል።
አሁን ላይ በተለያዩ ግንባሮች የከፈተውን ጥቃት አድማሱን በማስፋት ለፍቶ አዳሪ ንፁሃንን ኢላማ እያደረገ ነው ብሏል።
ህወሓት የሰው ማዕበል የጦርነት ስልት በመከተል በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን በገፍ እየማገደ ነው ያለው የፌዴራሉ መንግስት ቡድኑ ኃሉን አሰባስቦ በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታዎች እየተንቀሳቀሰ ነው ብሏል።
የሰላም አማራጩ እንዳለ ሆኖ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የተከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በተሟላ ሁኔታ እየመከተ ነው ሲል አሳውቋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ካገረሸ ወዲህ ከቀን ወደ ቀን ሁኔታዎች ከመርገብ ይልቅ የመባባስ ምልክት እያሳዩ ሲሆን እስከዛሬ በዜጎች ላይ ከደረሰው ጉዳት የበለጠ እንዳይደርስ ከየአቅጣጫው የሰላም ጥሪዎች እየቀረቡ ናቸው።
@tikvahethiopia
321 views16:58