Get Mystery Box with random crypto!

ETV.News

የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_news — ETV.News E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_news — ETV.News
የሰርጥ አድራሻ: @etv_news
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.43K
የሰርጥ መግለጫ

@etv_newss (tikvah news)

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-31 12:36:59
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ6 ሳምንታት ውስጥ በአዲስ አበባ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሚጀምር የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር አስነብቧል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀናት በፊት በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ መጀመሩ ይታወሳል። አገልግሎቱ በራሱ መሰረተ ልማት የተጀመረ መሆኑ ተጠቁሟል።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ሲካሄድ የነበረው የመሠረተ ልማት ስምምነት በቶሎ ባለማጠናቀቁ አገልገሎቱን ለማስጀመር ጊዜ መውሰዱን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ትርፍ ለማግኘት ቢያንስ 5 ዓመታት ሊፈጅበት እንደሚችል አስታውቋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ፣ በሲሚንቶና በሌሎች ግብዓች ላይ ዋጋ መጨመሩ ኩባንያው በቶሎ ትርፍ ለማግኘት እንቅፋት ሊሆንበት እንደሚችል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ባልቻ ሬባ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሠጡት ቃል ፤ ኩባንያው እስከ ሚያዚያ 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን 25 በመቶ የኅብረተሰብ ክፍል የሚሸፍን አገልግሎት እንዲያቀርብ ውል ገብቷል ብለዋል።

በዚሁ በተጠቀሰው ጊዜ የሚጠበቅበትን ካላሟላ ኦዲት ተደርጎ በገባው ውል መሠረት ቅጣት ይጣልበታል እንደሚጣልበት፤ ይሁን አንጂ የቴሌኮም ኩባንያው አሁን በተሳካ ሁኔታ ሥራውን እያከናወነ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ኩባንያቸው የዋጋ ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን የቴሌኮም አገልግሎት እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-08-31

@tikvahethiopia
286 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:36:59
የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት

የሩፋኤል በዓል በየአመቱ " ጳጉሜ 3 " ቀን አባይ ወንዝ ላይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ህዝቦች በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል።

ነገር ግን የዘንድሮው (2014 ዓ/ም) ዓመታዊ የሩፋኤል በዓል በተፈጠረው ክልላዊ እና ሀገራዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት #እንደማይከበር የደጀን ከተማ ፖሊስ ባስተላለፈው የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት አሳውቋል።

ይህን የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት ጥሶ የሚገኝ አካል ላይ በሚፈጠረዉ ችግር ፖሊስ ሀላፊነቱን እንደማይወስድና የህግ ተጠያቂነት እንደሚኖረውም በጥብቅ አሳስቧል።

ባለፈው ዓመትም (2013 ዓ/ም) በተመሳሳይ እንደ ሀገር ባጋጠመ ችግር እና በአካባቢው ላይ በነበረ የፀጥታ ስጋት ምክንያት በዓሉ እንዳይከበር ተወስኖ ማለፉ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
235 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:36:58
#ኮምቦልቻ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው በከተማው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 35 ህገ ወጥ ሞተር ብስክሌቶች በቁጥጥር ስር ዋሉን ገልጿል።

ሞተር ብስክሌቶቹ ከወልድያ ፣ መርሳ እና ሀይቅ የመጡ እንደሆነና ከኮምቦልቻ ከተማም ያሉ ሞተሮች እንደሚገኙበት ተመላክቷል።

ሞተሮቹ ሠሌዳ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ የሌላቸው ናቸው ተብሏል።

እነዚህ ሞተሮች እስከ 50,000 ብር የሚጠጋ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የተገለፀ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሞተሮች በህገ ወጥ ተግባራት የመሠማራት ዝንባሌ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከዚህ በፊትም 400 ህገ ወጥ ባጃጆች ወደ መጡበት ተመልሰዋል ብሏል።

@tikvahethiopia
230 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:36:58
" የህፃናት ህይወት ተቀጥፏል " - UNICEF

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ፤" አሁንም በድጋሚ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት የህፃናትን ህይወት ቀጥፏል " ብሏል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነ #የአፋር_ክልል መንደር የተፈፀመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ህፃናትን ገድሏል ፤ በርካቶችንም ቁስለኛ አድርጓል ሲል ድርጅቱ አሳውቋል።

UNICEF በኢትዮጵያ ላሉ ህፃናትና ለወደፊት ህይወታቸው ሲባል ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ሁሉም ወገኖች እንዲስማሙ ተማፅኗል።

UNICEF በመግለጫው ላይ ጥቃት የደረሰበትን የአፋር ክልል መንደር በግልፅ ባይሳውቅም ከቀናት በፊት የህወሓት ኃይሎች በአፋር " ያሎ " በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።

በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዜጎች ለተሻለ ህክምና ዱብቲ ሆስፒታሉ እንደገቡና ሆስፒታል ከገቡት ውስጥ 2 ህፃናት ልጆቿን ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የተገደሉባት እናት እንደምትገኝ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
217 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:36:58
" የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የችግሮች መንስኤ ከመሆን መቆጠብ ይኖርባቸዋል " - አቶ መሐመድ እድሪስ

የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ፍቅር እና ሰላምን መስበክ እንዲሁም የአብሮነት እሴቶችን ማጠናከር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ገለፁ።

ይህን ያሉት ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

አቶ መሐመድ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃኑ ትውልድን በሃይማኖት መርሆዎች በመቅረጽ ለሰላም ግንባታ ሚናቸው የላቀ ነው ያሉ ሲሆን የችግሮች መንስኤ ከመሆን መቆጠብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በአንዳንድ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የሌሎችን ሃይማኖት አለማክበርና ማንቋሸሽ ይስተዋላል፤ ይህ አካሄድ ሊታረም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በዘላቂነት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሃይማኖት ሚዲያ ካውንስልን ለማቋቋም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መደረሱን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣ በአገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተሸረሸሩ የመጡ እሴቶች መበራከትና በየቦታው የሚፈጠሩ ችግሮች የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የቤት ስራዎቻቸውን ላለመስራታቸው ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።

" በርካታ አማኞች ያሉባት አገሪቱ የሚገዳደል እና መንገድ የሚዘጋ ትውልድ ተበራክቶባታል " ያሉ ሲሆን መገናኛ ብዙሃኑ ከመነቃቀፍ ይልቅ መደጋጋፍን እኛ እና እነሱ ከሚል የጥላቻ ትርክት በላይ አብሮነትን መስበክ አለባቸው ብለዋል።

ተገቢ ባልሆነ አካሄድ ውስጥ እየተጓዙ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ሰላምን እንዲሰብኩ እንመክራለን ያሉ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን በሕግ የሚጠየቁበት ሁኔታ መኖሩን አስገዝበዋል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
249 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:49:57
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል።

በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
602 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:49:57
#ATTENTION

ላሊበላ !

የላሊበላ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ የሰዓት ዕላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ውሳኔዎቹ ፦

- ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ወደ ከተማዋ መግባትም ሆነ መውጣት አይቻልም።

- ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋቱ 12:00 ድረስ መንቀሳቀስ አይቻልም።

- ከተፈቀደለት አካል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

- በመንግስት ዕውቅና ካለው የፀጥታ አካል ውጭ የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ ለብሶ መንቀሳቀስ በፍፁም አይቻልም።

የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ህዝቡ በሀሰተኛ ወሬ እና አሉባልታ ሳይደናገር አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
519 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:49:57
* አስቸኳይ

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስ/ር የሰቆጣ ከተማ አስ/ር ምክር ቤት የመንግስት እና የግል ባንኮች አገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያሻሽሉ በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።

ሰቆጣ በርካታ ህዝብ የሚኖርባት እና ከ70,000 ሺህ በላይ ወገኖች ተፈናቅለው የባንክ አገልግሎት እያገኙ የሚገኙባት ከተማ ናት።

ነገር ግን ከላይ በደብዳቤው ስማቸው የተገለፀው (የኢትዮጵያ ንግድ ፣ አባይ፣ ዳሽን፣ አቢሲንያ፣ አንበሳ፣ አዋሽ፣ ቡና፣ ህብረት፣ አማራ፣ ፀደይ ባንኮች) በበሬ ወለደ ምክንያት በከተማው የፀጥታ ችግር እንደተፈጠረ ተደርጎ የባንክ አገልግሎት በተገቢ መንገድ እየሰጡ እንዳልሆነ በምክር ቤቱ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የጥሬ ገንዘብ እጥረት በሚል ሰበብ ህዝብ እንዲረበሽና እንዲሰጋ እያደረጉ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአሉባልታና የሚመለከተው የፀጥታ ምክር ቤት መረጃ ሳይጠይቅ ሆን ተብሎ ጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዲፈጠር በማደረግም ቢሮ ዘግተው አገልግሎት ማቋረጣቸውን ም/ቤቱ አሳውቋል።

ምክ/ቤቱ ባንኮቹ ከዚህ ተግባራቸው እንዲወጡ ያሳሰበ ሲሆን ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ግን ታሪካዊ ስህተት የፈፀሙ እና ህዝብን የካዱ ፣ የህዝቡ እንግልትና ስቃይ ላይ ተባባሪ መሆናቸውን ሊያውቁት ይገባል ሲል አሳስቧል።

ይህንን በመረዳትም አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

ደብዳቤው ፦ ከሰቆጣ ከተማ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
474 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:49:57
#ATTENTION

ደብረ ብርሃን !

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ስጋትን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

- በከተማው አስተዳደር በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ከምሽቱ 12:00  ሰዓት በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ተከልክሏል።

- ሁሉም አይነት ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- መጠጥ ቤቶች ፣ ምግብ ቤቶች ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 2:00 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል።

- የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ ተከልክሏል።

- ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ሀይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ ተከልክሏል።

- ከመንግስት ዕውቅና ውጭ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ ተከልክሏል።

- አዳር የሚሰሩ በከተማው ያሉ ፋብሪካዎችና ድርጅቶች ድርጁቱ በሚሰጣቸው ህጋዊ  መረጃ እና በፀጥታ መዋቅሩ የተረጋገጠ የይለፍ ከያዛ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላሉ።

- ህብረተሰቡን ለማሸብር አሉባልታ መንዛት፣ ወሬ ማሰራጨት በጥብቅ የተከለከለ ነው ፤ መላው ማህበረሰብም አካባቢውን ቀንና ሌሊት በንቃት መጠበቅ አለበት።

- የሆቴል አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ገለሰብ በድርጅታቸው ውስጥ ሲያጋጥም ለህግ አካላት እንዲያሳውቁ ፤ በሌላ በኩል ፤ የቤት አከራዮች የሚያከራዩትን ግለሰብ መታወቂያ በመጠየቅ፣ ፎርምም በመሙላት ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ እንዲያሳውቁ ተብሏል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
507 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 23:25:08
#KOBO

የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብሏል።

በዚህም ፤ " የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል " ሲል አሳውቋል።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል " ብሏል።

ምንም እንኳን ከተለያየ አቅጣጫ ሰላም እንዲሰፍን እና መሳሪያ ወርዶ ንግግር እንዲጀመር ጥሪዎች ቢቀርቡም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል።

@tikvahethiopia
142 views20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ