2022-07-02 19:00:58
• አንኳን ወደ ክረምቱ አሸጋጋረን •
መዝሙር፦ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም፤ ሶበ ይዘንም ዝናም ይጸግቡ ርኁባን። ደምፀ እገሪሁ ለዝናም። ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን። ደምፀ እገሪሁ ለዝናም። ወሠርዓ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ። ደምፀ እገሪሁ ለዝናም። ደምፀ እገሪሁ ለዝናም።
✞ የዕለቱ መልእክታት፣ ምስባክ፣ ወንጌል
መልእክታት፦
፩☞፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭ ÷ ፴፫ - ፶፩ /15:33-51
፪☞ያዕቆብ ፭ ÷ ፲፮ - ፍጻሜ /5÷16-ፍጻሜ
፫☞የሐዋ/ሥራ ፳፯ ÷ ፲፩ - ፳፩ /27÷11-21
.
ምስባክ፦
ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና።
ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር።
ዘያበቊል ሣዕረ ውስተ አድባር።
ትርጉም:-
ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል።
ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፤
ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል፤
( መዝሙር ፻፵፮ : ፰ /146 : 8 )
.
ወንጌል፦
የሉቃስ ወንጌል ፰ ፥ ፩ - ፳፪ /8 ÷1-22/
፩
ከዚህም በኋላ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እየተናገረ በየከተማይቱ በየመንደሩም ያልፍ ነበር፤
፪
አሥራ ሁለቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፥ ከክፉዎች መናፍስትና ከደዌም ተፈውሰው የነበሩ አንዳንድ ሴቶች፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የምትባል ማርያም፥
፫
የሔሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐናም ሶስናም ብዙዎች ሌሎችም ሆነው በገንዘባቸው ያገለግሉት ነበር።
፬
ብዙ ሕዝብም በተሰበሰቡ ጊዜ ከከተማዎችም ሁሉ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ በምሳሌ እንዲህ ሲል ተናገራቸው።
፭
ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ ተረገጠም፥ የሰማይ ወፎችም በሉት።
፮
ሌላውም በዓለት ላይ ወደቀ፥ በበቀለም ጊዜ እርጥበት ስላልነበረው ደረቀ።
፯
ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾሁም አብሮ በቀለና አነቀው።
፰
ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀ፤ በበቀለም ጊዜ መቶ እጥፍ አፈራ። ይህን በተናገረ ጊዜ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ብሎ ጮኸ።
፱
ደቀ መዛሙርቱም። ይህ ምሳሌ ምንድር ነው? ብለው ጠየቁት።
፲
እርሱም እንዲህ አለ። ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌ ነው።
፲፩
ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
፲፪
በመንገድ ዳርም ያሉት የሚሰሙ ናቸው፤ ከዚህ በኋላም ዲያብሎስ ይመጣል አምነውም እንዳይድኑ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል።
፲፫
በዓለት ላይም ያሉት ሲሰሙ ቃሉን በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ እነርሱም ለጊዜው ብቻ ያምናሉ እንጂ በፈተና ጊዜ የሚክዱ ሥር የሌላቸው ናቸው።
፲፬
በእሾህ መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሔደው በሕይወት ዘመን በዐሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም።
፲፭
በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።
፲፮
መብራትንም አብርቶ በዕቃ የሚከድነው ወይም ከአልጋ በታች የሚያኖረው የለም፥ የሚገቡት ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል እንጂ።
፲፯
የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።
፲፰
እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፥ ከሌለውም ሁሉ፥ ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።
፲፱
እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፥ ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያገኙት አልተቻላቸውም።
፳
እናትህና ወንድሞችህ ሊያዩህ ወድደው በውጭ ቆመዋል ብለው ነገሩት።
፳፩
እርሱም መልሶ። እናቴና ወንድሞቼስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው አላቸው።
ቅዳሴ - ዘኤጲፋንዮስ (በግዕዝ ዜማ)
ከሰንበት ረድኤት በረከትን ይክፈለን። ሰላሙንና ፍቅሩን ይጨምርልን። ዝናመ ምሕረቱን ጠለ ረድኤቱን አያርቅብን። አሜን።
@etsemeaza
298 views16:00