2022-08-18 18:18:20
እንኳን አደረሳችሁ! <ነሐሴ ፲፫/13>
[በዓለ ደብረ ታቦር ወልደቱ ለሙሴ ወብንያም ወጋልዮን መስተጋድል]
=> የዕለቱ ግጻዌ
ምስባክ ዘነግህ
ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል።
ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉዓን።
ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ።
ትርጉም፦
የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው።
የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ?
እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ ይህን ተራራ ወደደው።
(መዝ ፷፯ : ፲፭ - ፲፮ /67:15-16)
+ ወንጌል ዘነግህ
የማቴዎስ ወንጌል ፲፯ : ፩ - ፲፬ /17:1-14
፩
ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።
፪
በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።
፫
እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
፬
ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡— ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ፡ አለ።
፭
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፡— በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፡ የሚል ድምፅ መጣ።
፮
ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።
፯
ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡— ተነሡ አትፍሩም፡ አላቸው።
፰
ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።
፱
ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ፡— የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ፡ ብሎ አዘዛቸው።
፲
ደቀ መዛሙርቱም፡— እንግዲህ ጻፎች፡— ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።
፲፩
ኢየሱስም መልሶ፡— ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤
፲፪
ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው፡ አላቸው።
፲፫
በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።
+ መልእክታት:-
1. ወደ ዕብራውያን ፲፩ : ፳፫ - ፴ /11:23-30
2. ፪ኛ ጴጥሮስ ፩ : ፲፭ -ፍጻሜ /1:15-ፍጻሜ
3. ግብረ ሐዋርያት ፯ : ፵፬ - ፶፩ /7:44-51
✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ።
መዝራእትከ ምስለ ኃይል።
ትርጉም፦
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል።
ስምህንም ያመሰግናሉ።
ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፤
(መዝ ፹፰ : ፲፪ - ፲፫/88:12-13)
+ ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ፱ : ፳፰ - ፴፰ /9:28-38
፳፰
ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
፳፱
ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።
፴
እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤
፴፩
በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።
፴፪
ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።
፴፫
ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።
፴፬
ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
፴፭
ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
፴፮
ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ። ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።
፴፯
በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።
✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ / ዘዲዮስቆሮስ {በዕዝል ዜማ ቀድስ}
በቅዱሱ ተራራ መለኮታዊ ክብሩን ለቅዱሳኑ የገለጸ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ለእኛም ዕውቀቱን ይግለጽልን ጥበቡን ማስተዋሉን ያድለን። በመንግሥቱም ያስበን። የክብርት እናቱ ምልጃም አይለየን።
፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠
498 views15:18