Get Mystery Box with random crypto!

የጤና መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomedhealth — የጤና መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomedhealth — የጤና መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomedhealth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.85K
የሰርጥ መግለጫ

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ግሩፓችንን ይጎብኙ
ይጫኑ 👇👇
TELEGRAM
❀꧁t.me/ethiomedhealth꧂❀
➥ @pharmacy_com
facebook.com/ethiomedhealth

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-14 12:21:04
2.9K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 11:22:06 .....................................................
====ማረጥ (MENOPAUSE )===
.....................................................
ማረጥ ( Menopause ) የሚከሰተው በሰውነት ውስጥ ያለ Estrogen የሚባል ሆርሞን መጠን መቀነስ ሲሆን አብዝኛውን ጊዜ የሚከሰተው ከ 45-50 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ላይ ነው::

ይህ በድንገት የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ ዓመት የወር አበባ መዛባት በኃላ የሚከሰት ነው ይህንንም ጊዜ ቅድመ ማረጥ ( Premenopause ) እንለዋለን::
.....................................................
አንዲት ሴት የmenopause ጊዜ ላይ ነች የምንለው ለተከታታይ 12 ወራት የወር አበባ ሳታይ ስትቀር ነው::
.....................................................
የ Menopause ምልክቶች
.....................................................
- ከፍተኛ ሙቀት (Hot flash)
- በለሊት ጊዜ በላብ መጠመቅ (Night sweat)
- የእንቅልፍ መዛባት ( Sleep problems )
- የብልት አካባቢ መድረቅ (Vaginal dryness)
- የባህርይ መለወጥ; ድብርት( Depression)
- የድካም ስሜት መኖር
- የሀሳብ መበተን ወይም ትኩረትን የመሰብሰብ ችግር

.....................................................
ወደ ህክምና ተቋም መቼ መሄድ ያስፈልጋል?
.....................................................
ማረጥ (Menopause) የተፈጥሮ ዑደት ስለሆነ ሁሉም ሴቶች ህክምና አያስፈልጋቸውም::
.....................................................
በማረጥ ጊዜ የሚኖሩ ምልክቶችን በቤት ውስጥ እንዴት መቀነስ ይቻላል?
.....................................................
- ከፍተኛ ሙቀት ሲኖር ቀለል ያለ ልብስ መልበስ ; ትኩስ ነገር አለመጠጣት ; ቀዝቀዝ ያለ ፎጣ አንገት ላይ ማድረግ እና ሲጋራ የሚያጨሱ ከመሆነ ማቆም ይመከራል
- እንቅልፍን ሊከለክሉ የሚችሉ በውስጣቸው አነቃቂ ( Caffeine) የያዙ መጠጦችን መቀነስ
- ግንኙነት ከማድረግ በፊት የብልት ማለስለሻ ክሬም ወይም ጄል መጠቀም
- ከቤተሰብና ከጏደኛ ጋር መዋል ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማዘውተር ከድብርት እራስን ለመከላከል መሞከር
.....................................................
እነዚህን መንገዶች በመጠቀም ምልክቶች የማይቀሱ ከሆነና የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ከጀመሩ የህክምና ባለሙያዎችን ማማከር ያስፈልጋል::

እንዲት ሴት ከ40 ዓመት በፊት የወር አበባ ማየት ካቆመች ጊዜውን ያልጠበቀ ቅድመ ማረጥ ወይንም በህክምና አጠራሩ Premature Menopause ይባላል:: በዚህም ጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው::

በዶክተር ኢየሩሳሌም ጌቱ

መልካም ጤንነት
----------------------------
@ethiomedhealth
2.4K views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 13:56:36 በአንድ አካባቢ የሚኖሩ አንበሶች እና ጎሾች ነበሩ፡፡
አንበሶቹ ጎሾቹን ለምግብነት ይጠቀቸው ነበር፡፡የአንበሶች መኖር ደግሞ የጎሾቹ ቁጥር ከሚገባው በላይ አልፎ ጎሾች የሚመገቡት ምግብ አልቆ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የሚጨወተው ሚና ነበረው፡፡
እንደዚ በሚገርም መናበብ በመኖራቸው የተነሳ በመሀከላቸው መግባት ያልቻለው አያ ጅቦ ሁል ጊዜም ይብሰለሰል እና እንዴት አድርጎ መሀከላቸው እንደሚገባ ያስብ ነበር፡፡

ከለታት አንድ ቀን አያ ጅቦ አንበሳና ጎሽን ማጣላት መሀከላቸው ለመግባት ጥሩ ዘዴ ሊሆን እንደሚችል በመገመት ለመሞከር ተነሳ፡፡

በዚህም ተደብቆ እየጠበቀ አንበሳ ከገደለ በኋላ አንበሶች በጎሾች ተገደሉ የሚል ወሬ ያናፍሳል፡፡

ይህን የሰሙ አንበሶች ጎሾች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ይሰነዝራሉ፡፡አያ ጅቦም ይቺን ወሬ ይዞ ጎሾች በብዛት ተሰብስበው ወደሚኖሩበት አካባቢ በመሄድ አንበሶች በጎሾች ላይ የዘር ማጥፋት እንደፈጸሙ ይናገራል፡፡

በዚ ነገር የተበሳጩ ጎሾች በተራቸው ጉዳዩ ውስጥ የሌሉ አብረዋቸው የሚኖሩ አንበሶች ላይ ጥቃት አደረሱ፡፡ይህ ችግር እየተባባሰ ሲመጣ አንበሶች አንበሳ ወደበዛበት ቦታ ሲሰደዱ ጎሾችም የጎሾች መንደር ዘለቁ፡፡

በዚህም የአንበሶቹ መንደር በሳር ተወረረ ልምላሜው ጨመረ ነገር ግን ለአንበሶቹ የሚሆን ምግብ አልነበረም እንዲሁ የጎሾች መንደር ተክል አልባ ሆነ፡፡በዚህም ከሁለቱም ወገን ብዙ ነፍስ እረገፈ፡፡

አያ ጆቦም የሞቱትን አንበሶች እና ጎሾች እያማረጠ ይመገብ ጀመረ፡፡ሁሌም መብላት ሊጀምር ሲል ለሙታኖቹ እንዲ ይላቸዋል
የሞታችሁት ዛሬ አይደለም የሞታችሁት ማንን ማመን እንዳለባችሁ ያላወቃችሁ ጊዜ ነው፡፡

የሞታችሁት አርቆ ማሰብ ያቃታችሁ ጊዜ ነው፡፡
እናስብ እርስ በእርስ በመባለት ማንም አሸናፊ አይሆንም ብቸኛው አሸናፊ አያ ጆቦ ብቻ ነው።

የጤና መረጃ
2.2K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-18 11:19:13 የማህፀን ኢንፌክሽን
(ፐልቪክ ኢንፍላማቶሪ ዲዚስ PID)
======================
የማህፀን ኢንፌክሽን (ፐልቪክ ኢንፍላማቶሪ ዲዚስ PID) እንዴት ይከሰታል?
.....................................................
በሴት መራቢያ አካል ላይ የሚደርስ ኢንፌክሽን ሲሆን በወሲብ ወቅት የሚተላለፍ ባክቴሪያ ወደ ማህፀን ፤ የማህፀን ቱቦ እና የማህፀን በር ውስጥ ሲገባ ነው ኢንፌክሽኑ የሚይዘን፡፡ ኢንፌክሽኑ መጀመሪያ በሴት ብልት ውስጥ ይፈጠር እና በቆይታ ወደ ማህፀን ይስፋፋል፡፡

የማህፀን ኢንፌክሽን የሚያመጡ ባክቴሪያዎች ብዙ አይነት ቢሆኑም በተለይ ግን ጨብጥ እና ክላይሚዲያ የሚያመጡ ባክቴሪያዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ጨብጥ እና ክላይሚዲያ በግብር ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎች ናቸው፡፡
.....................................................
ለማህፀን ኢንፌክሽን የሚያጋልጡን ነገሮች ምንምን ናቸው?
.....................................................
 ከ25 አመት በታች ሆኖ ወሲብ ማድረግ
 ከአንድ በላይ ወንድ ጋር (ከተለያዩ ወንዶች ጋር) የግብር ስጋ ግንኙነት ማድረግ
 ኮንዶም አለመጠቀም
 ለመታጠብ ሸተፍ መጠቀም (በሀይል ውሃ የሚረጭ የቧንቧ አይነት ነው)
 ከዚህ በፊት የማህፀን ኢንፌክሽን ከያዝን ተመልሰን የመያዝ እድላችን ከፍ ይላል፡፡

የማህፀን ኢንፌክሸን ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
.....................................................
አንዳንድ ሴቶች የማህፀን ኢንፌክሽን ቢይዛቸውም ምንም ምልክት ሳያዩ ወይም ህመም ሳይሰማቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

የማህፀን ኢንፌክሽን እንዳለባቸው ለማርገዝ ሲቸገሩ ወይም በጣም አሳሳቢ የሆነ የወገብ ህመም ሲያጋጥማቸው ሊታወቅ ይችላል፡፡

አንዳንድ ሴቶች ደግሞ የተለያዩ የህመም ምልክቶች ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡
.....................................................
1. የማህፀን እና የወገብ ህመም
2. በወሲብ ጊዜ የሚያጋጥም ህመም
3. ከብልት የሚወጣ ፈሳሽ (ሽታ ያለው)
4. ሽንት በሚሸናበት ጊዜ የሚያጋጥም ህመም
5. ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት
6. ድካም፤ ማቅለሽለሽ፤ ማስመለስ
7. በወር አበባ ጊዜ የሚመጣ ህመም መጨመር

የማህፀን ኢንፌክሸን ህክምና
.....................................................
አንዲት ሴት የማህፀን ኢንፌክሽን እንደያዛት የሚታወቀው ወደ ሃኪም ጋር ሄዳ አስፈላጊ የሆኑ ምርመራዎች ከተደረጉላት በኋላ ነው፡፡

ከነዚህ ምርመራዎች መካከል የሽንት/የደም ምርመራ፤ የማህፀን ምርመራ ወይም አልትራሳውንድ ናቸው፡፡

ከምርመራዎቹ በኋላ ሃኪሙ አስፈላጊ የሆኑ ፀረ- ባክቴሪያ መድሃኒቶችን ያዛል፡፡

የሚታዘዝልንን መድሃኒት በትክክል እና በሰአቱ ካልወሰድን በስተቀር የማህፀን ኢንፌክሽን አይድንም፡፡ በተቻለ አቅም የፍቅር ጓደኛሽ አብሮሽ ቢታከም ይመረጣል፡፡
እንዲሁም መድሃኒቱን በትክክል ከወሰዳችሁ በኋላ እንደገና ተመርምራችሁ ነፃ መሆናችሁ እስኪታወቅ ድረስ ወሲብ እንዳታረጉ ይመከራል፡፡

የማህፀን ኢንፌክሸን የሚያመጣቸው ችግሮች ምን ምን ናቸው?
.....................................................
የማህፀን ኢንፌክሽን ሳይታከም በሰውነታችን ውስጥ ከቆየ የተለያዩ እክሎችን በጤናችን ላይ ያስከትላል፡፡
1. ለረጅም ጊዜ የሚቆይ እና ሃይለኛ የማህፀን እና የወገብ ህመም
2. ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና
3. ለማርገዝ መቸገር (መውለድ አለመቻል)
4. በማህፀን ቱቦ እና በእንቁላል ማምረቻ ላይ የሚፈጠር እባጭ

የማህፀን ኢንፌክሸን እንዳይዘን ምን ማድረግ አለብን?
• በወሲብ ወቅት ሁል ጊዜ ኮንዶም መጠቀም
• ለመታጠብ ሸተፍ አለመጠቀም
• የአባላዘር በሽታዎች እንዳይዙን መጠንቀቅ እና በየጊዜው መመርመር

በምንፀዳዳበት ጊዜ ከፊት ወደ ኋላ መጥረግ፡፡ ይሄ ባክቴሪያ ወደ ሴት ብልት እንዳይገባ ይከላከላል፡፡

ለጤና የሚጠቅሙ ፅሁፎችን ለማንበብ ገፃችንን ሼር ያድረጉ. @ethiomedhealth

የጤና መረጃ

መልካም ጤንነት


.....................................................
ጤናማና ደስ የሚል ቀን. ይሁንላችሁ፡፡
2.4K views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 13:02:56 የጉበት ስብ ክምችት በሽታ
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
(Fatty Liver Diseases)
በዶ/ር ሃይለማሪም አወቀ
(የዉስጥ ደዌ ሕክምና ረዳት ፕሮፌሰር)

ትርጉም፡-
ከርዕሱ እንደሞንረዳው የሥብ ክምችት በጉበት ውስጥ ከመጠን በላይ ሲሆን የሚከሰት ነው፡፡ ይህም ችግር በጉበት የሚመረተው የሥብ (ቅባት) መጠንና የሚወገደው ቅባት መጠን አለመመጣጠን የሚያመጣው ችግር ነው፡፡

ችግሩ እንዴት ሊፈጠር ይችላል/የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላል ተብሎ ይታሰባል፡- 

1. በጉበት ውስጥ ያሉ ህዋሳቶች የስብ አፀግብሮችን በትክክል ማካሄድ ሳይችሉ ሲቀሩ፣
2. ከመጠን በላይ ስብ ሲመረት ወይም ከመጠን በላይ ስብ ወደ ጉበት ሲገባ፣
3. የጉበት ህዋሳቶች የተመረተውን ስብ በትክክል ከጉበት እንዲወጣና ወደ ሌላ ህዋሳት ክፍል እንዲሸራሸር ማድረግ ሳይችሉ ሲቀሩ ነው፡፡

የችግሩ መነሻ ምክንያቶች
1. ከ60 ግራም መጠን በላይ  አልኮል በቀን በመጠጣት፣
2. ሌሎች በሽታዎች እንደ ውፍረት(በተለይ የማዕከላዊ ሰውነት ውፍረት)፣ የስኳር በሽታ፣የምግብ እጥረት እና ሌሎች፤
3. ልዩ ልዩ መድሃኒቶች፣
4. በእርግዝናም ሊፈጠር ይችላል፣

ሆኖም ግን የችግሩ መነሻ በአብዛኛው የአልኮል መጠጥ ነው፡፡

የበሽታው ምልክቶች
ድካም፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣የሆድ ህመምና የዓይን ቢጫ መሆን፤
የችግሩ መጠን ከፍ እያለ ሲሄድ ደግሞ የሆድ እብጠት እና የእግር እብጠት ያመጣል፤
የጉበት እብጠት ሊከሰት ይችላል፤
ከፍ ሲልም በአፍ ደም መምጣት (የጨጓራ መድማት)፤
ህሌናን መሳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

የጉበት ምርመራ
ደም ከጉበት ናሙና በመውሰድ እና በልዩ ልዩ ምስል ምርመራዎች ይካሄዳል፡፡

የህክምና አይነቶች፡-
-   መጠጥ ማቆም ወይም የችግሩን ምንጭ ማቆም ወይም መቀነስ፣
-   ክብደት መቀነስ ከ10% ያላነሰ፣
- የተመጣጠን እንቅስቃሴ ማድረግ፣
- አመጋገብን ማስተካከል፣
-  ፍቱን የተባለ መድሃኒት ባይኖረውም የስብ መቀነሻ መድሃኒቶችና የተለያዩ ንጥር ነገሮች ሊጠቅሙ ይችላሉ፡፡

የበሽታው ደረጃዎች
ይህ በሽታ የተለያዩ ደረጃዎች አሉት

እነዚህም ፡-
-  የስብ ክምችቶች ብቻ (Simple steatostais )፣
- ቁስለት ያለው የስብ ክምችት (Steatohepatitis)፣
- ከፍተኛ የሆነ የጉበት ጠባሳ (Cirrhosis)፣

የህመሙ የመጨረሻ ውጤት
· የመጀመሪያ ሁለቱ ደረጃዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ነበረበት ጤናማ ጉበት ሊመለሱ ይችላሉ፤ ስለሆነም ሁሉም መንስኤዎች ቶሎ በማስወገድ እና የላይኞችን ምክሮች መተግበር ያስፈልጋል፡፡
· የመጨረሻው ደረጃ ግን ሙሉ በሙሉ ሊመለስ የሚችል አይደለም፤ መሻሻል ግን ይኖረዋል፡፡
· አንድ ጊዜ ከጠፋ በኋላ የመመለስ እድል ስለሚኖረው ከላይ የተዘረዘሩትን ምክንያቶች ሙሉ  በሙሉ ማስወገድ ይኖርብናል፡፡



Follow,like now and Invite your friends to our page
የጤና መረጃ #Health info

https://www.facebook.com/ethiomedhealth/
2.3K views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 13:47:19 ጤና መረጃ
Stroke በተለምዶ "መጋኛ" የሚባለው በሽታ ሁለት አይነት ሊሆን ይችላል
፩; ወደ ጭንቅላት የሚሄድ ደም መቋረጥ ወይም
፪; ጥንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ

በምን ምክንያት ሊመጣ ይችላል?
፩; መቆጣጠር የምንችላቸው
√ የደም ግፊት
√ የስኳር ህመም
√ የልብ ህመም
√ የሰውነት የስብ መጠን መብዛት
√ ሲጋራ ማጨስ
√ አልኮል መጠጣት

፪; መቆጣጠረ የማንችላቸው
√ እድሜ"እርጅና"
√ በቤተሰብ የስትሮክ ታማሚ መኖር

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
√ ከፍተኛ የሆነ እራስ ምታት
√ ማስታወክ
√ የሰውነት አካላት መስነፍ
√ የፊት መጣመም
√ ሽንት አና ሰገራ መቆጣጠር አለመቻል
√ የንቃተ ህሊና መቀነስ
√ ማውራት አለመቻል ወይም መኮላተፍ

ስትሮክን እንዴት እንከላከላለን?
ሲጋራ ማጨስ ማቆም
የአልኮል መጠጥ መቀነስ
የደም ግፊትና ኮሌስትሮል መጠንን ማስተካከል
ስኳር ህምን ባግባቡ መቆጣጠር
‍ ቦርጭና ክብደትን ማስተካከል
ጤናማ አመጋገብ
‍ በቀን ለ30ደቂቃ ያክል እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ

ምንጭ
ዶ/ር ካሳዬ ደመቀ ፤ የድንገተኛ እና ፅኑ ህክምና ስፔሻሊስት
2.3K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-29 13:07:10
what is the probable causative etiology?
Anonymous Quiz
23%
A. Chlamydia trachomatis
15%
B. Haemophilus ducreyi
37%
C. Neisseria gonorrhoeae
17%
D. Treponema pallidum
8%
E. Trichomonas vaginalis
189 voters2.5K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 11:31:55 Pharmacology & others medical updated books free pdf
USMLE 2021 Note
Video lecture
qbank book with explanation
.
.
. others whatever you needs

join
Free Medical book
2.4K views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-13 13:22:24 ብቃት ምዘና ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈
በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ጤና መኮንን፣ ፋርማሲ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ፣ ሚድዋይፈሪ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያዎች ተመርቃችሁ
የጤና ሚኒስቴር የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ጤና ባለሙያዎች ፈተናው የሚሰጠው ከታህሳስ 21-27/2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አውቃችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን የፈተናውን ፕሮግራም በቅርብ የምናሳውቅ
መሆኑን እንገልፃለን።

Via: FMOH
2.9K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ