Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ አካባቢ የሚኖሩ አንበሶች እና ጎሾች ነበሩ፡፡ አንበሶቹ ጎሾቹን ለምግብነት ይጠቀቸው ነበር | የጤና መረጃ

በአንድ አካባቢ የሚኖሩ አንበሶች እና ጎሾች ነበሩ፡፡
አንበሶቹ ጎሾቹን ለምግብነት ይጠቀቸው ነበር፡፡የአንበሶች መኖር ደግሞ የጎሾቹ ቁጥር ከሚገባው በላይ አልፎ ጎሾች የሚመገቡት ምግብ አልቆ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የሚጨወተው ሚና ነበረው፡፡
እንደዚ በሚገርም መናበብ በመኖራቸው የተነሳ በመሀከላቸው መግባት ያልቻለው አያ ጅቦ ሁል ጊዜም ይብሰለሰል እና እንዴት አድርጎ መሀከላቸው እንደሚገባ ያስብ ነበር፡፡

ከለታት አንድ ቀን አያ ጅቦ አንበሳና ጎሽን ማጣላት መሀከላቸው ለመግባት ጥሩ ዘዴ ሊሆን እንደሚችል በመገመት ለመሞከር ተነሳ፡፡

በዚህም ተደብቆ እየጠበቀ አንበሳ ከገደለ በኋላ አንበሶች በጎሾች ተገደሉ የሚል ወሬ ያናፍሳል፡፡

ይህን የሰሙ አንበሶች ጎሾች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ይሰነዝራሉ፡፡አያ ጅቦም ይቺን ወሬ ይዞ ጎሾች በብዛት ተሰብስበው ወደሚኖሩበት አካባቢ በመሄድ አንበሶች በጎሾች ላይ የዘር ማጥፋት እንደፈጸሙ ይናገራል፡፡

በዚ ነገር የተበሳጩ ጎሾች በተራቸው ጉዳዩ ውስጥ የሌሉ አብረዋቸው የሚኖሩ አንበሶች ላይ ጥቃት አደረሱ፡፡ይህ ችግር እየተባባሰ ሲመጣ አንበሶች አንበሳ ወደበዛበት ቦታ ሲሰደዱ ጎሾችም የጎሾች መንደር ዘለቁ፡፡

በዚህም የአንበሶቹ መንደር በሳር ተወረረ ልምላሜው ጨመረ ነገር ግን ለአንበሶቹ የሚሆን ምግብ አልነበረም እንዲሁ የጎሾች መንደር ተክል አልባ ሆነ፡፡በዚህም ከሁለቱም ወገን ብዙ ነፍስ እረገፈ፡፡

አያ ጆቦም የሞቱትን አንበሶች እና ጎሾች እያማረጠ ይመገብ ጀመረ፡፡ሁሌም መብላት ሊጀምር ሲል ለሙታኖቹ እንዲ ይላቸዋል
የሞታችሁት ዛሬ አይደለም የሞታችሁት ማንን ማመን እንዳለባችሁ ያላወቃችሁ ጊዜ ነው፡፡

የሞታችሁት አርቆ ማሰብ ያቃታችሁ ጊዜ ነው፡፡
እናስብ እርስ በእርስ በመባለት ማንም አሸናፊ አይሆንም ብቸኛው አሸናፊ አያ ጆቦ ብቻ ነው።

የጤና መረጃ