2022-08-04 00:14:03
ሰላም ውድ የታሪካዊት ኢትዮጵያ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ? እስቲ ዛሬ ከአትሌቲክሱ አለም ጎራ ልበልና የታዘብኩትን ላካፍላችሁ ......
በዘመኔ በርካታ ጀግና አትሌቶችን አይቻለሁ። በዉጤታቸዉ ጨፍርያለሁ። በደስታ ሲቃ አንብቻለሁ። ጥሩዬ ሆዷን ይዛ ድል ያደረገችበት፣ ኢብራሂም ጄይላን እንደ ጦር ተወርውሮ ሞ ፋራህን የበላበት፣ የሙክታር ኢድሪስ ክስተትነት፣ ቲኪ ገላና ከረጅም ግዜ በኃላ የኦሎምፒክ ማራቶንን ወደ ሀገሯ የመለሰችበት፣ የሞሐመድ አማን የሞስኮዉ የ800M አስደናቂ አሸናፊነት፣
በሪዮ የአልማዝ አያና ገድል፣ በቶኪዮ የሰለሞን ባረጋ አጨራረስ፣ የኦሬገኑ የለተሰንበት ትንቅንቅና ድል....ስሜትን ከፍ ዝቅ የሚያደርጉ በርካታ አኩሪ ገድሎችን አይቻለሁ።
ግና እርሱ ከሁሉም ይለይብኛል። አሯሯጡ እራሱ የሆነ የራሱ ብራንድ ነች። አድፍጦ ይቆይና ደዉል ሲደወል ይፈተለካል። ወደኃላ ዞር እያለ የስሜት ስቃይ ያበዛብናል።ደግነቱ የመጨረሻዋ 100 እና 200M የራሱ ነች። የተለየ የእግር አጣጣል፣ በራስ መተማመን፣ እልህ፣ ወኔ፣ የማያልቅ የድል ረሃብ...መገለጫዎቹ ናቸው። በፈገግታ ሲያፈተልክ አንገቱ ላይ ያለዉ ወርቅ ከደረቱ ጋር እየተጋጨ እንደኳስ ይነጥራል። እሱ ብቻውን የሆነ የፊልም scene ይመስለኛል።
የጀግንነቱን ግማሽ ያህል እንኳን አልተዘመረለትም። ልታይ ልታይ የሚል ሰዉ ባለመሆኑ በሚዲያም በሚገባው ልክ አልተወደሰም። የከተማዉ ወጣት በድሉ ብጨፍርም እርሱን ለቀልድ ሟሟሻ እና ማድመቂያ ያላዋቂነትና የሞኝነት ማሳያ አድርጎ ለማቅርብ ሲሞክር ይስተዋላል። በኪነጥበብም ከቴዲ አፍሮ ውጭ በሚገባው ልክ እርሱን ያወደሰ ከያኒ የለም። በርግጥ ፖለቲካ ካላቦካክ፣ በየቦታዉ ካልጮኽክ የፈለገ ጀግና ብትሆን በአፋን ኦሮሞ የኪነጥበብ ስራዎችም የመታወስ ዕድልህ አናሳ መሆኑ ይገባኛል። ቢሆንም ቀነኒ የሚረሳ አልነበረም...
ኢትዮጵያን የእርሱን ያህል ወርቅ ያለበሳት የለም። ነጮቹ የክፍለ ዘመኑ ምርጥ የሚሉት ዩሲዬን ቦልት እንኳን የርሱን ያህል ሜዳሊያ ለሀገሩ አላስገኘም። በግል ዉድድሮቹ ካገኛቸዉ ድሎች በላይ ለሀገር ያስገኛቸው ክብሮች ይልቃሉ። ከርሱና ከጥሩዬ ውጪ በኦሎምፒክ 3 ወርቅ ያስገኘ ኢትዮጵያዊ አትሌት የለም። ሶስቱ ወርቅ ላይ አንድ ብር ጨምሩለት። በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናስ ከርሱ ውጭ ሀገርን 5 ወርቅ ያለበሰ አትሌት እስከአሁን አልተገኘም። እዚህም ላይ አንድ ነሐስ ጨምሩለት። በዓለም አቋራጭ ዉድድርስ የርሱን ያህል ገድል የሰራ አለ..? በዚህ ውድድር 13 ወርቅ ማስገኘት ወደፊትስ ይታሰባል...? በሕይወት ዘመኑ ካደረጋቸዉ 170 ዉድድሮች 110 ዉድድሮችን በአንደኝነት የሚያጠናቅቅ ከርሱ ዉጭ ሌለ አትሌት ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ። ለሀገር 35 ዉድድሮች ላይ ተሰልፎ 24 ወርቅ እና 6 የብር ሜዳሊያን ለማምጣት እርሱን መሆን ይጠይቃል። ሀገርን ወርቅ በማልበስ 2ኛ ደረጃ ላይ ያለችው ሌላዋ ያልተዘመረላት ጀግና ጥሩዬ እንኳን 16 ወርቅ ነው ያላት።
ይህን ሁሉ ማንም አትሌት ያልሰራዉን ሕልም የሚመስሉ ገድሎችን ለፈፀመው አትሌት ሀገር ምን አደረገችለት..? ሕዝቡስ ለምን የሚገባውን ክብር ነፈገዉ..? ኪነጥበቡ እና ሚዲያውስ ለምን መዘከር አቃተው...? ሃዉልት አልተሰራለትም። መንገድ አልተሰየመለትም። አደባባይ አልተጠራበትም። ገድሉ በመፅሐፍ አልታተመለትም። አሸናፊነቱ ለትዉልድ አልተተረከለትም።
ከ18 ዓመታት በፊት በአቴንስ ኦሊምፒክ ሞሮኳዊው ሂሻም አልጉሩዥ በ5 ሺህ ቀነኒሳን ያሸነፈበት መንገድ ዛሬም ድረስ ያንገበግበኛል። ቀነኒ በመካከለኛ ርቀቶች የሰራቸውን ገድሎች ኦሊምፒክ ላይ በማራቶን ይደግማል ብዬ ሲጠብቅ በደራርቱ እና ዶር አሸብር ጭቅጭቅ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ እንዲቀር መደረጉ ያሳዝነኛል። የሆነ ሆኖ ቁጥሮች አይዋሹም እንዲሉ ፈረንጆች በቁጥራዊ አሃዞች ቀነኒሳን የሚስተካከል አትሌት በአፍሪካ ምድር ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለምም ማግኘት ይከብደል። ብቻውን ልዕለሰብ ነው። የወርቆች ሁሉ ወርቅ፣ የጀግኖች ሁሉ አዉራ ነው። እርሱ የሰበሰባቸው ወርቆች ብዙ ሀገራት አንድ ላይ ተደምሮ ማምጣት የማይችሉትን ነው።
ቢሆንማ በሞሐመድ አሊ፣ በፔሌ፣ በማይከል ፍሊፕስ፣ በዩሴን ቦ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
የታሪካዊት ኢትዮጵያን የዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ አስተማሪ ቪዲዮዎችን ይመልከቱ፦ https://youtube.com/channel/UCJxIzBiXCY8chIBzfyAGtIA
@ethioabesha @ethioabesha @ethioabesha @ethioabesha
1.6K viewsኢትዮጵያ ነው ስሜ!!, edited 21:14