Get Mystery Box with random crypto!

ነብዩ መሃመድ የተደነቁበት ኢትዮጵያዊው መሪ ንጉሥ አርማህ 2ኛ በሰባተኛው ክ/ዘመን ንጉሥ አርማህ | ታሪካዊት ኢትዮጵያ (History of Ethiopia )

ነብዩ መሃመድ የተደነቁበት ኢትዮጵያዊው መሪ ንጉሥ አርማህ 2ኛ

በሰባተኛው ክ/ዘመን ንጉሥ አርማህ 2ኛ የኢትዮጵያ ንጉሰነገስት በነበሩበት ዘመን ነብዩ መሐመድ በመካ ያሉ ሁኔታዎች አስጊ ስለነበሩ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው የሆኑ 20 ሰዎችን (በኋላ ላይ 70 ተጨምረዋል) "ወደ ሐበሻ መሬት ሽሹ። በዚያ ፍርዱ ቅን የሆነ ህዝቡን በሰላም የሚገዛ ንጉሥ አለ።የአላህ ፈቃድ ሆኖ መከላከል ሀይል እስክናገኝ ድረስ የእውነትና የፅድቅ ሀገር ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ ሂዱ" በማለት ላኩአቸው። ንጉሥ አርማህም ተቀብሎ እንደፍላጐታቸው አስቀመጣቸው። ባቀረቡለት የማምለኪያ ቦታ እጦት መሰረትም ክርስቲያኑ ንጉሥ አርማህ 2ኛ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን "አል ነጃሺ" መስኪድ አስገነባላቸው። ከዚህም ባለፈ የነብዩ መሐመድ ተቃዋሚ የሆኑ የአረብ ገዥዎች ለንጉሥ አርማህ ስደተኞችን አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከእጅግ ብዙ ወርቅ እና ተፈላጊ ስጦታዎች ጋር አድርገው መልክተኞች ላኩበት። የንጉሡ ምላሽ ግን ቁርጥ ያለ ነበር "ተራራ የሚአክል የወርቅ ክምር ብትሰጡኝ እንኳ እነዚህን እንዳድናቸው የተማፀኑኝን ሰዎች አሳልፌ አልሰጥም" የሚል ነበር። እነዚህ እንግዶች በደስታ ኖሩ። ነብዩ መሐመድ በድል/በእርቅ/ ወደ መካ ሲገቡም እንግዶቹ ንጉሡን ተሰናብተው ወደ ሀገራቸው ገቡ። አገራቸው ደርሰውም የተደረገላቸውን እንክብካቤ ለወገኖቻቸው ገለፁ። በንጉሡ ተግባር እጅግ ደስ የተሰኙት ነብዩ መሐመድ ሐበሻንና የሐበሻን ንጉሥ በቅዱስ ቁርዓን ሳይቀር በመልካም እያነሱ "ሃበሻን አትንኩ" የሚል ቃል አፅፈዋል።

እንግዲህ ንጉሥ አርማህ 2ኛ የሐይማኖት ነፃነትን በተግባር በመስጠት እና በዛሬ ዘመን ከሚታየው በበለጠ ጥገኝነትን በመስጠት ስልጡንና ለቃሉ ታማኝ የሆነ ህዝብና ንጉሥ እንደነበራት በግልፅ አሳይቷል።
የተለያዩ የቀደምት ኢትዮጵያንን ስልጣኔዎች በማስረጃ ና በቪዲዮ ለመመልከት የዩቲዩብ ቻናላችን ውስጥ ጎራ ይበሉ፦
https://youtube.com/channel/UCJxIzBiXCY8chIBzfyAGtIA


@ethioabesha @ethioabesha @ethioabesha @ethioabesha

(የታሪካዊት ኢትዮጵያን የዩቲዩብ እና የቴሌግራም ቻናል በራሳችሁ የቴሌግራም ቻናል ላይ የምታስተዋውቁ እንዲሁ ለወዳጅዐዘመዶ #ሼር የምታደርጉ ውድ የታሪካዊት ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ከፍ ያለ ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን ።
በዚሁ አጋጣሚ መናገር የምንፈልገው ከታሪካዊ ኢትዮጵያ ቴሌግራም ቻናል ላይ የሚለቀቁ ፁሁፎችን የራሳችሁ አድርጋችሁ በራሳችሁ ቴሌግራም ቻናል ላይ የምትለቁ ሰዎች ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን ። #ሼር ማድረግ ከፈለጉ ከነሊንኩ ይላኩ።)