Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Neshida & Menzuma

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_neshida — Ethio Neshida & Menzuma E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_neshida — Ethio Neshida & Menzuma
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_neshida
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.99K
የሰርጥ መግለጫ

ወደ #YouTube ቻናል 👇
https://www.youtube.com/ethioneshidamenzuma
ወደ #Facebook Page 👇
https://www.facebook.com/Ethio-Neshida-Menzuma-348031129044029/
ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ በቦት(bot) ተጠቅሞ ያድርሱን✍️
👇
@ETHIO_NESHIDA_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2022-09-24 02:02:24
28 views23:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 15:18:07 መዉሊድ የኢስላም መሰረት

መውሊድ ባልነበር :- አሏህ(ሱ.ወ) ፈጣሪያችን መሆኑን አናውቅም ነበር

መውሊድ ባልነበር :-ቁርዓንን ከጌታችን አሏህ ባልወረደልን ባልቀራነው ባልተመራንበት

መውሊድ ባልነበር :-አምስት ወቅት ሶላት ከአርሹ ጌታ ተለግሶን ባልሰገድን ባልተረጋጋንበት

መውሊድ ባልነበር :-ረመዷን መፆም አይደለም ወሬውም ባልነበር

መውሊድ ባልነበር :-ሀጅና ዑመራ ለማድረግ ወደ በይቱሏህ ባልተጓዝን

መውሊድ ባልነበር :- ሁለቱም ኢዶች ከቶ ባላወቅናቸው ባልተደሰትንባቸው ነበር

በአጠቃላይ መውሊድ ባልነበር ዲነል ኢስላም አይኖርም ነበር ለዚህም ነው መውሊድ የኢስላም መሠረት ነው የምንለው!

فاعتبروا يا أولي الأبصار
‏አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ

አሏህ (ሱ.ወ) ከኩፍር ጨለማ ወደ ዲነል ኢስላም ብርሃን እንድንገባ የመሆኑ ምክኒያት ምርጡ የአሏህ ባሪያ የሆኑትን ነቢያችን ሙሐመድ ሶለ ሏሁ አለይሂ ወሰለም በመወለዳቸው በመገኘታቸው እና ወደ እኛ ቀጥታ መንገድ እንድንመራ ዘንድ ነቢይ አድርጎ ጀሊሉ በመላኩ እንጂ በሌላ በምንም ምክኒያት አይደለም እና ለዚህ ለዋለልን ታላቁ የመውሊድ ፀጋ በመደሰት ምስጋና ለአሏህ እናቀርብ ዘንድ አሏህ አዞናል!

قل بفضل الله وبرحمته فبذلك فليفرحوا هو خير مما يجمعون

«በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው። (ዩኑስ 58)

እናንተ የአእምሮ ባልተቤቶች ሆይ! በነቢያችን ሙሐመድ ﷺ በመወለድ ሰበብ ያገኘነው ፈድል(ችሮታ) እና በሳቸውም ሰበብ የኢስላምን ዲን ከመጎናፀፍ በላይ የበለጠ ምን ችሮታ አሏህ ችሮአችኋል?!

እናንተ የአእምሮ ባልተቤቶች ሆይ! በኩፍር ጨለማ ከመዋጣችንና መሪ አጥተን ቀጥተኛውን መንገድ ፍለጋ ከመባዘናችን በፊት ነቢያችንን ﷺ በመውሊዱ ማስገኘቱ አሏህ ማስገኘቱ ለእኛ ጀሊሉ ታላቅ እዝነቱን ፍቅሩ ያሳየበት የገለጠበት መንገድ የበለጠ ሌላ ምን ነገር ይኖራል?!

ስለዚህ አሏህ በሰጠኋችሁ ችሮታና በእዝነቴ ተደሰቱ ብሎ ካለን ለእኛ በነቢዩ ﷺ መውሊድ ሰበብ ነውና ኢስላምን የተጎናፀፍነው ደስታችንን ከምንም ነገር በላይ በመውሊዱ እያበላን እየመደህን ሶለዋት በነቢያችን ﷺ እያወረድን እየተደሰትን አሏህን እየሸከርን ከቤተሰቦቻችን ከወንድሞቻችን ከመሻኢሆቻችን ጋር በማሳለፍ አሏህ ፈጣሪያችንን የምናመሰግንበት መንገድ እንጂ ጥራዝነጠቆች እንደሚሉት የአሏህ ባሪያ የሆኑትን ሀቢቡሏህ ሰይደና ሙሐመድን ﷺ አምልኮ የምናደርግበት በኢስላም ዲን ላይ ተቀፅላ ፈጠራ የሆነ ቢድዓ የምንፈፅምበት መንገድ አይደለም እና ብዥ ያለበት ብዥታውን አጥርቶ የኢስላም ወንድማማችነት በነቢያችን ﷺ ዉዴታ ስም በመውሊዱ በመሰባሰብ አንድነታችንን እናጠናክር

ኻሊድ ሙርሰላ
1.3K views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 15:17:29
1.2K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 00:21:36 #ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ኑሩን ከኑሩ ኸለቀው ጀሊሉ!

ጌትዬ በኑር አካብቧቸውም የራሴ ነው ከሚለው ነገር ሁሉ እዬቆረሰ እዬዘገነ አድሏቸዋል። ሁሌም በዚህ ባብ ስገባ ታድያ በራሱ ከላም ላይ ያገኘኋቸው አንዳንድ ታሪኮች እርሳቸውንም የሚገልጹ ይመስለኛል። ሙሳ ከሊሙሏህ ዓ.ሰ ጌታቸውን ጠዬቁ። رَبِّ أَرِنِىٓ أَنظُرْ إِلَيْكَ አሉ።ይችሉ መስሏቸው፣ ናፍቆት ቢጠናባቸው የሚወዱትን ጌታቸውን መገናኘት ከጅለው። ጌትዬው ታድያ የሁሉን ቀድር ያውቃልና እንደማይቋቋሙት ያውቅ ነበር። እንደው በዛት የማይገለጠውን የጀማሉን ሽራፊ እንኳ እንደማይችሉት። የወደደ ልብ ልጅ ያደርጋል። ያሰበውን ካላገኘ አይረጋም አይሰክንም። ሙሳም በሙራዳቸው ፀኑ። ሒጃቡ ይነሳልኝ አሉ። ያኔ ታድያ ወደ ጀማሉ መወጣጫ አቅጣጫ ተቀመጠላቸው። ቀድመው ወደ ተራራው እንዲያዩ ተነገራቸው። ጌታዬ የጀላሉን ፍልቃቂ በራሱ ከይፊያ ለተራራው ሲገልጥና ሲናድ ባዩ ጊዜ ሙሳም ከሑብ የባሰ ድንጋጤ አገኛቸውና ወደቁ። እንደተነሱም መፀፀታቸውን ገለፁ። አጥራሩትም።

ጌትዬ ለነቢ ዘንበል ካደረገላቸው ፈይዶች አንዱ ይሄ ነው። የረሱለሏህ የወጅሃቸው ተጀሊይ ለአያሌዎቹ ሐቀኛ ወዳጆቻቸው ከዓቅላቸው በላይ ነው። ኢማም አል ቀስጦላኒይ ቀ.ሲ "አሏህ የሐቂቃውን የሠይደል ዉጁድ ውበት ይፋ ቢያወጣው ዱንያ ካለመቻሏ ጋር ትጠፋ ነበር።" ብለው የውበታቸውን መግለጪያ ደምድመውታል። ጘራሙ እዬመራረጠ ሲወጋ፣ ፍግግም ሲያደርግ ታይቷል ተሰምቷል። የአገራችን ዑለሞችም "ስንቱን ቆሽቱን ጎዳው ገባና ጨረሩ!" ብለዋል። "ወዳጁን ገዳይ እንዳቱም የለ ወረቴ" ያሉትም ለዚሁ ነው። ሙሐባቸው የሚፋጅ፣ ጀማላቸውም ገዳይ ነው። የሙሐባቸው ኮረንቲ ልዘይር ብሎ የሄደውን ሁላ እንደ አሕመደል ሐዲ ጨምድዶ አስቀርቷል። ለዛውም ቀና ብሎ ሊያያቸው የደፈረ ሳይኖር እንደው በሲትሩ በተሰተረው መጠን! የሙስጦፋን ወጅህ እንዲያዩ የተወፈቁት እነ ሰይድ ነብሃኒም ብዕራቸውን ለማንሳት ጀማሉ እንደከበዳቸው ሲናገሩ ነው የኖሩት። ኑሩን ከኑሩ ጠምቆት!

ወደ ጁምዓው ጌጥ ወደ ሱረቱል ካሕፍ ራመድ ብለን ማኽተሚያው ላይ ስንደርስ ደግሞ ተከታዮቹን ሰበዞች እንመዛለን።
قُل لَّوْ كَانَ ٱلْبَحْرُ مِدَادًۭا لِّكَلِمَـٰتِ رَبِّى لَنَفِدَ ٱلْبَحْرُ قَبْلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَـٰتُ رَبِّى
ለጌታዬ ንግግር ባሕሩ ቀለም ቢሆን የጌታዬ ቃል ከማለቁ በፊት ባህሩ ይደርቃል አይደለም ወይ ያለው? እንደዛው ነው አቦ ዛፉን ሁላ መድ፣ ባሕሩን ሁላ ቀለም አድርገህ ብትነሳ የነቢ ነገር ባሕርን በጭልፋ እንደማለት ነው ትጀምረዋለህ እንጂ አትጨርሰውም! ደጋጎቹም "የሐድራው ሁመያ ቢጠጣ ቢጠጣ ጋኑም አልጎደለ ጥምም አላወጣ!" ብለዋል።
ምስል ከዚሁ መንደር የተገኘ

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!
Atiqa Ahmed Ali
1.7K views21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 00:21:16
1.5K views21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 11:56:09 የፊታችን እሁድ መስከረም 15 የሚደረገው ታሪካዊው የሚሊኒየሙ መውሊድ ሶስት ቀናቶች ብቻ ቀርቶታል ትኬቶን በእጆ አስገብተዋል?

እንግያውስ ትኬቶቾን ለማግኘት

መርካቶ አንዋር መስጂድ
0911197579
0922082068
0910096465
ፒያሳ ኑር (በኒ) መስጂድ
0913675987
0922909503
መገናኛ ሂክማ መስጂድ
0912423620
ጠሮ ኡስማን ኢብን አፋን መስጂድ
0921457070
0978670423
አብነት አካባቢ ኡመር 26 መስጂድ
0960240443
0929380196
0906137992
ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ጃዕፈር መስጂጅ
0930595630 አብበከር
0932508473 ከሪም
ካራ ረህማ መስጂድ እና አካባቢው
0911331784 አንዋር
አቃቂ ቃሊቲ እና አካባቢው
0904625786
0910710889
ቃሊቲ መናሀሪያ አ/ቃድር መስጂድ
0920534084
ካዲስኮ ፍሬ ህይወት ት/ት ቤት ፊት ለፊት ሷሊህ መስጂድ
0921911047

ጦር ሀይሎች አደም በዳኔ መድረሳ

እና በብዛት ለመግዛት ከሊፋ ሴካ ህንፃ 10ኛ ፎቅ የማህበሩ ቢሮ ማግኝት ትችላላችሁ!

መውሊድ ለኢስለማዊ ወንድማማችነት !!
መውሊድ ለሀገራችን ሰላም !!
መውሊድ ለሀገራችን አንድነት !!
2.2K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 11:56:02
2.0K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ