2022-07-02 16:22:36
ራጂ አሸናፊ
በ60 ኮርሶች A+ ያመጣው ባለምጡቅ አእምሮ ባለቤቱ ራጂ አሸናፊ !
ተማሪ ራጂ አሸናፊ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) በ60 ኮርሶች A+ በማምጣት በከፍተኛ ነጥብ ዛሬ ተመርቋል።
ራጂ አሸናፊ የተወለደው በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ጊዳሚ ሲሆን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት ነው ያጠናቀቀው።
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናንም (ከኦሮሚያ ቦርዲንግ ትምህርት ቤት) ከመላው ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቦ ነው ያጠናቀቀው።
በኃላም ወደ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ገብቶበ Applied Physics Department ትምህርቱን የተከታተለ ሲሆን በወሰዳቸው 60 ኮርሶች A+ በማምጣት እጅግ አስደናቂ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።
ራጂ አሸናፊ ባለው ከፍተኛ የሆነ ብቃት በአሜሪካ ሀገር Massachusetts Institute of Technology (MIT) ለ5 ዓመት የPHD ትምህርቱን ለመከታተል እድል አግኝቷል።
ህልሙ በፅንሰ ሀሳባዊ የPhysics መስክ ትምህርቱን ጨርሶ ለሌሎች የሀገሩ ልጆች የተሻለ እድል መፍጠር ሲሆን ከPHD ጥናቱ በኃላ ወደ ASTU በመመለስ የCenter for High Energy Physics የPHD ፕሮግራም መክፈት ነው።
በሌላ በላኩል የሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በከፍተኛ ማዕረግ ለተመረቀው ራጂ አሸናፊ 50 ሺህ ብር ሸልሟል ፤ የዛሬ አራት አመት የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ሲያመጣ ዩኒቨርሲቲው ሽልማት አበርክቶለት ነበር።
891 viewsedited 13:22