Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ University

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_university — ኢትዮ መረጃ University
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_university — ኢትዮ መረጃ University
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_university
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.02K

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-10 10:27:44
ተጀምሯል

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።
የፈተናውን ደህንነት በጠበቀ መልኩ ያለምንም የፈተና ስርቆትና ኩረጃ ለመስጠት እንዲቻል ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ዩኒቨርስቲ በመግባት ነው ፈተናውን መውሰድ የጀመሩት።
የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 976 ሺህ 18 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
562 views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:58:18
" ስልክ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባታቸውን ገልጿል።

የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል ያለው አገልግሎቱ ከዚህ በተጨማሪ አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል ሲል አሳውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ #ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።

ድርጊቱ #ከፍተኛ_የፈተና_ደንብ_ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል ሲል አሳውቋል።

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል።

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ሲልም አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል።
290 viewsedited  17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 15:51:12 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገለፀ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ለሚወስዱ 12ኛ ክፍል  ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስታውቋል

በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የመፈተኛ  ተቋማት በማዘጋጀት በኩል ግብረሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መመሪያ ሀላፊ አ/ቶ ጌታሁን ፈንቴ  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። በዞኑ ተማሪዎች የሚፈተኑባቸው አምስት ተቋማት እየተዘጋጁ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል ።
553 viewsedited  12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 21:59:43
" የምንሄድበት የለም፤ መፍትሄ ይፈለግልን " - ተማሪዎች

የከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመከታተል ከተለያዩ የፀጥታ ችግር ካለባቸው የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ተከትሎ ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ ገልፀዋል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሰጠቱን ተከትሎ ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ማንኛውም ተማሪ እንዳይገኝ ተብሏል።

ይህ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ጭንቀት ውስጥ የከተተ ሲሆን ተማሪዎቹ መፍትሄ ይፈለግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልና ቤተሰቦቹ በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ፤ "ወደ መጡበት ቦታ መመለስ የማይችሉ ተማሪዎች ምን ሊደረጉ ነው ? ጦርነት ካለበት ቦታ የመጣን ተማሪዎች አለን ድምፃችን ተሰምቶ መፍትሄ ይፈለግልን፤ ወደ ቤታችን መሄድ አንችልም፤ መሄጃም የለንም" ብሏል።

ሌሎችም ተማሪዎች በተመሳሳይ መሄጃቸው እንደጨነቃቸው ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብቻ 50 የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች መኖራቸው ለማወቅ የቻለ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ መሄጃ ለጠፋቸው ተማሪዎች ምን አሰቧል በሚል ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የቅርብ ሰው ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

እኚሁ ሰው ዩኒቨርሲቲው ለትምርህት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቦ ከግቢ ይውጡ እንደተባለና ምናልባት ከፈተና መለስ እንደሚመለሱ አስረድተዋል።

መሄጃ የሌላቸው ተማሪዎች እስከዛ የት እንዲያርፉ ታስቧል ለሚለው ጥያቄ፤ ከግቢ ወጥተው ወደየ መጡበት/ቤተሰብ ጋር ይሂዱ መባሉን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ ቢያስቀምጡ ጥሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ት/ት ሚኒስቴር ሚሰጠን ምላሽ ካለ እናሳውቃለን።
712 viewsedited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:49:36
በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በክልሉ ለፈተና ከተመዘገቡ 451 ሺህ 21 ተማሪዎች
ውስጥ 98 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን መውሰዳቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ተናግረዋል።

በዚህም የማለፊያ ውጤት ለወንዶች 50 በመቶ፤ ለሴቶች 47 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ አርብቶ አደሩ አካባቢዎች ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 47 በመቶ፤ ለሴቶች 44 በመቶ ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44 በመቶ፤ ለሴቶች 41 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በተከታዩ ሊንክ መመልከት ይችላሉ፦

https://oromia.ministry.et/#/home
727 viewsedited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:09:49
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ!

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ  በቀን እና በማታ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 ሺሕ 515 ተማሪዎች አስመርቋል።ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺሕ 910፣ በሁለተኛ ዲግሪ 1 ሺሕ 597 እንዲሁም በሶስተኛ ዲግሪ 69 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ተመራቂዎቹ 4ሺሕ 613 ወንድ እና 1ሺሕ 902 ሴት ተማሪዎች ናቸው።

በተጨማሪም ዩኒቨርስቲው በአባትነታቸው የሚያስተምሩ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ የሚወዱ በችግር ግዜ ለወገን ዘብ ለቆሙት አርዓያ ሰብ የሆኑትን ለብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ እና የኢትዮጵያን ሰንደቅ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያስቻለችው ሀገር ወዳድዋ ኢትዮጵያዊት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የዛሬ ምሩቃን የኢትዮጵያን ሸክም የሚያቀሉ ለሀገር ሰላም እና ልማት የሚተጉ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።ዩኒቨርሲቲው 60 አመታትን ባስቆጠረው የመማር ማስተማር ሂደት በኢትዮጵያ ካሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርት ጥራት በግምባር ቀደምትነት ከሚነሱት ተቋማት እንደሚጠቀስም ገልፀዋል። 

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ፣ የኢንዶኔዚያ አምባሳደር እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  የተገኝተዋል። በ1955 ዓ.ም የተመሰረተው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያለፉትን አመታት ብቁ ዜጋን በማፍራት ኃላፊነቱን ሲወጣ እንደነበር ተጠቅሷል።
696 viewsedited  07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:11:31
በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23 - ጳጉሜ 04 ይካሄዳል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም በ2015 የትምህርት ዘመን ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ቢሮው ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጷጉሜን 04/2014 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን የጠቆሙት የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጌታቸው ቢያዝን፤ በዚኽም 895 ሺህ 404 የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ገልጸዋል።

እድሜያቸው 7 ዓመት የሞላቸው ተማሪዎች 714 ሺህ 518 ተማሪዎች እንደሚመዘገቡም አስረድተዋል። በአጠቃላይ 745 ሺህ 708 የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው አንስተዋል።

በአጠቃላይ 4 ሚሊዮን 144 ሺህ 845 ተማሪዎች በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲኹም 1 ሚሊዮን 219 ሺህ 301 ተማሪዎች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚመዘገቡ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።

ምዝገባው አዲስ ተማሪዎችን ብቻ ሳይኾን በተለያየ ጊዜ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን የሚያካትት እንደኾነ አቶ ጌታቸው አስረድተዋል። በ2014 ዓ.ም 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋልም ነው የተባለው። (አሚኮ)
785 viewsedited  15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:03:07
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

ኮሌጁ በ2015 የትምህርት ዘመን ስድስት የሁለተኛ ዲግሪ እና አስር አዳዲስ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ለመጀመር ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።

ኮሌጁ በ2014 ዓ.ም በስምንት የትምህርት ክፍሎች ትምህርት መጀመሩን የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አብርሀም አማረ አስታውሰዋል።

በ2015 ዓ.ም የሕክምና እና ፋርማሲ የትምህርት መስኮችን በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለማስጀመር ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በሕክምና 34 እና በፋርማሲ 30 ተማሪዎች ተለይተው ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
415 viewsedited  06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:42:42
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሁለት ዙር እንደሚሰጥ ተነገረ

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናውን እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱንም ገልፀዋል። ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

@ethio_mereja_university
@ethio_mereja_university
363 viewsedited  14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 19:39:00
NOTICE

ለመንግስት ዩንቨርስቲዎች :-

ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን
2015 ዓ.ም ድረስ በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ተማሪዎች እንዳይገኙ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ከመስከረም 30 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የሚሰጠውን የ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተከትሎ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መመሪያ ማውጣቱን አስታውቋል። በመመሪያው መሰረትም ተቋማቱ የትምህርት ዘመኑን የጊዜ ሰሌዳ በፈተና መርሃ ግብሩ መሰረት እንዲያዘጋጁ፣ በተጠቀሱት ቀናት መደበኛ ተማሪዎች በግቢዎቹ እንዳይገኙ፣ ለፈተና ማቆያ ስፍራ እንዲያዘጋጁ እና የምግብ አቅርቦት ዝግጅትም እንዲያደርጉ አሳስቧል።
667 viewsedited  16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ