Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ደስ ያላቹ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪቻቸውን በዛሬው እለት እያስመረቁ ነው!! የወ | ኢትዮ መረጃ University

እንኳን ደስ ያላቹ

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪቻቸውን
በዛሬው እለት እያስመረቁ ነው!!

የወልቂጤ፣ የሀዋሳ፣ የዋቻሞ ፣ ጂማ፣ ጎንደር እና አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መርሀ ግብሮች ያስተማሯቸውን ተማሪች በዛሬው እለት እያስመረቁ ነው።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም በዛሬው እለት ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎቹን ለ23ኛ ጊዜ እያስመረቀ ሲሆን አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።

ጅማ ዩኒቨርስቲም በተለያዩ የምህርት መስኮች ያስተማራችውን 2 ሺህ 509 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል። በተያያዘ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት 334 የሕክምና ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ67ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺሕ 866 ተማሪዎች በዛሬው እለት እያስመረቀ ይገኛል።