2022-07-12 00:24:32
እባቡ ላይ ሲያተኩሩ ጊንጡን እንዳይረሱ!
____________________
ብዙ ጊዜ ግልጽ በሆነው መሰናክልና ችግር ወይም በታወቀው ጠላት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በምንሰጥበት ጊዜ ግልጽ ያልወጡና በድብቅ የሚንቀሳቀሱ አንዳንዴም ሰላማዊና ወዳጅ የሚመስሉ ጠላቶች ከባድ አደጋ ሊያስከተትሉብን ይችላሉ።
በዙሪያችን ልዩ ልዩ አጀንዳ ያላቸው በርካታ እስስቶች ሊኖሩ ይችላሉ። በተለያዩ የማታለያ ማስኮች የተሸፈኑ ፊቶች ፣ ማንነታቸውን ያልገለጡ ከእባብ በማይተናነስ ሁኔታ ጉዳት አድራሽ በሆኑ ጊንጦች ተከበንም ይሆናል።
አንዳንድ ጊዜ ጠላቶች በመደበኛ አተያይ በጣም ወዳጆች መስለው፣ በጣም ተግባብተውና ቀርበው፣ ከእውነተኛ ጓደኛ ብዙም የተለዩ ሳይመስሉ አብረውን ሊውሉ ሊያመሹና ሊያድሩ ይችላሉ።
በመሆኑም ወዳጅ በሚመስሉ ጠላቶች ጉዳት እንዳይደርስብን ሁሌም በዙሪያችን ለሚደጋገሙ ጥቃቅን ነገሮች ትኩረት በመስጠት መጠንቀቅ ይበጃል።
ድርጊቶች የማስመሰል ሊሆኑ ይችላሉ፣ ቃላቶችም በውሸት የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ፣ የፊት ፈገግታም ትወና ሊሆን ይችላል፣ መሳም እና ማቀፍ ሁሉ ከልብ ላይሆን ይችላልና ወዳጆች የሚሏቸውን ከጠላት ለመለየት በቅድሚያ ስሜታቸውንና መንፈሳቸውን በጥልቀት ለመረዳት ይሞክሩ
1.9K views21:24