Get Mystery Box with random crypto!

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ eslemanabayy — Esleman Abay የዓባይ ልጅ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ eslemanabayy — Esleman Abay የዓባይ ልጅ
የሰርጥ አድራሻ: @eslemanabayy
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.78K
የሰርጥ መግለጫ

Blog

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-15 17:49:17 ቫለንት ፕሮጀክት: ኢትዮጵያን በመረጃ ጦርነት የወረረው ድርጅት
የዓባይልጅ

ኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን የሀሰተኛ መረጃና የሰነልቦና ጦርነት የመራው ድርጅት በሶሪያው የርስ በርስ ጦርነት ተልእኮ በነበረው ሰው ነው የተቋቋመው። በሶሪያ የመረጃ ጦርነት አዝማች የነበረው ባስማ ፕሮጀክት መባሉን የምናውቀው ነው። በኢትዮጵያ የነበረውን ፕሮፓጋንዳ የመራው ልክ የባስማ አምሳያ ድርጅት መቋቋሙን እንጂ ስሙ ሳይገለጥ ነው የቆየው። ሆኖም በUSAID በኩል ከCIA የተሰጠውን ፀረ-ኢትዮጵያ ተልእኮ አስተግባሪ Valent Projects - ቫለንት ፕሮጀክትስ የሚባል ድርጅት መሆኑን በጥናታ ሪፖርቶች ይፋ ተደርጓል።
ይህ እኩይ ድርጅት ይጋለጥ ዘንድ የምእራባዊያን ጣልቃ ገብነትን የሚያነፈንፉ የተለያዩ ሀገራት ደህንነት መስሪያ ቤቶች የቴክኖሎጂ እና ምርምር ተቋማት ከእጃቸው ያስገቧቸው ሰነዶች ወሳኘ ግብአት በመሆን አገልግለዋል። ሰነዶቹ እየተፈተሹና እየተመረመሩ ቀጥለዋል። በተለይም ሚንት ፕሬስ ኢንስቲትዩት የተሰኘው የጥናት ማእከል በመሰል ስራዎቹ አንቱታን ያተረፈ ሲሆን ዛሬ ይፋ ባደረገው ጥናታዊ ሪፖርቱ የኢትዮጵያና ሱዳን ዜጎችን በዲጂታል የሚያሰሟቸው ድምፆችን ለማፈን በብሪታኒያ ማእከሉን ባደረገውና ቫለንት ፕሮጀክትስ በሚሉት ተቋራጭ በኩል ሲተገበር ይገኛል።
ከኢትዮጵያውያ በተጨማሪ የሱዳን ዜጎች በሀገራቸው ፖለቲካዊ ቀውስ ዙሪያ በኦንላይን የሚያሰሟቸውን ድምጾች ማፈን እንዲሁም የመረጃ ጦርነት ሰንሰለቱ ማዕከላዊ ዕዝ ከዚሁ ቫለንት ከተሰኘው ድርጅት መሆኑም ነው የተደረሰበት።
በአሜሪካው ሲአይኤ እና በእንግሊዝ ደህንነት ተቋም እንዲሁም በዩኤስአይዲ እና በተመሳሳይ አላማ ከተሰማሩ አጋሮች ጋር በመቀናጀት ነበር የፕሮፓጋንዳ ዘመቻው እየተከነወነ የሚገኘው።

ይህ ቫለንት ፕሮጄክትስ Valent Projects - በተለይም እንደ ፌስቡክ ካሉ የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ጋር በሚስጥር በመስራት ይታወቃል ይላል ሚንት ፕሬስ ኢንስቲቱዩት በጥናቱ። ቫለንት በአሜሪካ መንግስት የሚደገፉ የኦንላይን ፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን በማማከር በየሚታወቅ ኮሙኒኬሽን ድርጅት ነው። ቫለንት በአንድ አጋጣሚ ብቻ የተደረገለትን ክፍያ ለአብነት የሚጠቅሰው የሚንት ፕሬሥ ፅሁፍ እንዳስቀመጠው "የሲአይኤ ተልእኮ አስተግባሪ የሆነው ዩኤስኤአይዲ "የሃሰተኛ መረጃ ካምፔይን እና ማስኬጃ በሚል 1.2 ሚሊዮን ዶላር ለቫለንት ፕሮጀክትስ ክፍያ ተፈፅሟል"። እነዚህ የስውር ተልእኮ ግንኙነቶች እስካሁን ይፋ አለመደረጋቸውን የጠቆመው ጥናታዊ ሪፖርቱ፣ ቫለንት ከተልእኮው አንፃር ያስቀመጠውን ድምዳሜ እና አቅጣጫ ተከትሎ ፌስቡክ ኩባንያ እጅግ በጣም በርካታ የሱዳን አካውንቶችን አግዷል። በተለይም ምዕራባዊያን በፕሮፓጋንዳና ዲፕሎማሲ የሚደግፉ በኃይል ስልጣን የተቆጣጠሩ መለዮ ለባሾችን የሚተቹ ገፆች የዲጂታል አፈናው ኢላማዎች ተደርገዋል። በዚህ አካሄዳቸውም በአልቡርሃን የተመራውን የጁንታ አስተዳደር ከነ አወዛጋቢነቱ ማስቀጠል ያለመ ዘመቻ ነበር።
በኢትዮጵያም በተመሳሳይ ከመንግስት የወገኑ ኢትዮጵያውያን የኦንላይን ድምጾች በጅምላ ማፈን ቫለንት ፕሮጀክትስ ከተሰጠው ተልእኮ መካከል ተጠቅሷል። በዚህም የአሜሪካን ጣልቃ-ገብ ፖሊሲ የሚቃወሙ ኢትዮጵያዊ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን የማሳፈንና የማዘጋት ዘመቻ መክፈታቸው ነው ሚንት ፕሬሥ ኢንስቲትዩት በጥናታዊ ሪፖርቱ ያጋለጠው። በነገራችን ላይ ሚንት ፕሬሥ ኢንስቲትዩት ተራ የምእራባዊያን ተላላኪ ተቋም አይደለም። መሰረቱ በዚያው በአሜሪካ ይሁን አንጂ ተግባሩ ግን ፀረ ኢምፔሪያሊዝም ነው። የምእራባዊያን white helmet ገመና የገላለጠ፣ የበሺር አሳድ ኬሚካል ጥቃት ውንጀላ ትያትርን ከአደባባይ ያዋለ፤ በምእራባዊያን አይን አፍቃ ሩሲያ ብለው የሚፈርጁት፤ የክብር ሽልማቱን እነ ኒማ ኤልቢገር ከሚሸለሙበት የሿሿ ተቋም ሳይሆን እንደ ሴሬና ሺዋ ካሉ ተቋማት ነው ውድ ሽልማት የተበረከተለት...ወዘተ በርካታ ድንቅ ምርመራዎችን ያከናወነ ተቋም ነው - ሚንት ፕሬሥ።

ቫለንት ፕሮጄክትስ የተመሰረተው አሚል ካን በተባለ፤ ለቢቢሲ እና ሮይተርስ ይሰራ የነበረ አንጋፋ ጋዜጠኛ ሲሆን፤ ኋላ ላይ በብሪታንያው MI-6 የስለላ መስሪያ ቤት የመረጃ ጦርነት ክንፍ ባለሙያ ወደመሆን የተሸጋገረ ነው ይላል፤ ሚንት ፕሬሥ የሰውዬውን ዳራ በቃኘበት ዳሰሳው። የመረጃ ጦርነት Information warfare ባለሙያው አሚል ካን በሶሪያ ሚስጥራዊ የውጭ ጉዳይ ተልእኮ ፕሮጀክቶች ለበርካታ አመታት መስራቱንም ጥናቱ ገልጿል። በሶሪያ ተልእኮው የሀገር ውስጥ እንዲሁም ከሶሪያ ውጭ አለምአቀፍ ታዳሚዎች ላይ የተነጣጠረ ስውር የስነ-ልቦና ጦርነት Psychological operation - PSYOP ዘመቻዎች አካሂዷል። የ PSYOP [ስነልቦናዊ ጦርነት] ዘመቻውን ሲያስፈፅም የሚጠቀማቸው ገለልተኛ-መሰል ነገር ግን በሚስጥር ስውር ፖለቲካዊ ተልእኮ ያነገቡ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶችን ሲሆን የፕሮፓጋንዳ ብልጫውን ለመውሰድ መደበኛ ብዙሃን መገናኛዎች ጋር የሚቀናጁበትን ቅድመ ዝግጅት ትስስር እና ስልጠናዎች ተግባራዊ ያደርጋል።

አሚል ካን የመሰረተው የመረጃ/ስነልቡና ጦርነት አዝማቹ Valent Projects የተባለ ድርጅት ስለራሱ ከሚገልፀው በተቃራኒው አሜሪካ እና ብሪታኒያ ላሰለጠኗቸው ብሎም በገንዘብ ለሚደግፏቸው የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ ሲያቀርብ ይታወቃል።

#EslemanAbay #የዓባይልጅ

For more

https://eslemanabay.com/leaked-docs-facebook-bot-adviser-secretly-in-pay-of-us-regime-change-agency/
285 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:49:15
276 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 02:23:07
ቅዳሜ ትዊተር ላይ በቀጥታ እንድንወያይ ቀጠሮ እንያዝ

“Scientific Analysis of Environmental Implications of #Egypt’s Deceptive Rationalizations to Drain #SouthSudan’s Marshlands against #Ethiopia #SouthSudan, & #EastAfrica’s future”

Saturday, 07/16/2022, 8 am eastern time, 2:00 pm in South Sudan, 3:00 pm in Ethiopia.

Egypt’s next attempt in to Jonglei of South Sudan

All South Sudanese and worldwide environmental concerns are welcome to join in.


https://twitter.com/i/spaces/1rmxPgggByjJN
1.1K views23:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 02:22:47 ሰበር

CIA እና USAID ኢትዮጵያ ላይ ያዘመቱት የፕሮፓጋንዳና የመረጃ ጦርነት ተቋም ተጋልጧል
ይህን እኩይ ፕሮጀክት ያሰማሩት፣ የሴራው ተላላኪ የውጭ መዳፎች እንዲሁም የውስጥ ባንዳ ፕሮፓጋንዲስቶች አንድ ባንድ ይፋ መሆን ጀመረዋል። የዚህ ፀረ ኢትዮጵያ የመረጃ ጦርነት ተቋራጭ ቫለንት ፕሮጀክትስ መሆኑ ታውቋል። በምርምራቸው አንቱታን ያተረፉት እንደ Mint Press Institute ያሉ ተቋማት ድብቁን ሴራ በጥናታቸው ማጋለጥ ጀምረዋል።

የኦንላይን ድምፆችን ማሳፈን የፕሮፓጋንዳ ተቋራጩ ዋነኛ ተግባር በመሆኑ ይህ እኩይ ድርጊቱ ይህን/ቀጥሎ የምመጣበትንም ፅሁፌን ተከትሎ በገፄ ላይ መስተጓጎል ሊገጥመኝ ይችል ይሆናል...እናየዋለን

መረጃውን ላደርሳችሁ እያዘጋጀሁኝ ነው። ጠብቁኝ

#የዓባይልጅ #EslemanAbay #CIA #USAID
#gerd4all #ItsAfricanDam #egypt #hypocrisy #intervention

https://eslemanabay.com/leaked-docs-facebook-bot-adviser-secretly-in-pay-of-us-regime-change-agency/
1.0K views23:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 02:22:33
1.0K views23:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:03:24 በውግዘት ስም  
▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ከልጅነት እስከዕውቀታችን፣ በየሥርዓቱና በየዘመኑ፣ በየምክንያቱና በየሰበቡ፣ ብዙ ሕይወት ሲቀጠፍ፣ ብዙ ደም ሲፈስ፣ ብዙዎች ሲፈናቀሉና ተስፋቸው ሲፈጠፈጥ የዚህን ሁሉ ግፍ ሥረመሰረት አስተውለን፣  እንደ ደላንታው ትዕቢተኛ “ምነው ባልተሰራሁ! ምነው ይህንን ባልሰራሁ? ምነው ይህንን ባላደረግን ብለን ወደራሳችን ጠቁመን፣ የማያዳግም መፍትሔ እንደማምጣት፣ ልክ እንደአባቶቻችን እኛም ጣታችንን ወደሌሎች መቀሰሪያ “ውግዘት” የተባለች ዘመናዊ ከ“ከደሙ ንጹሕ ነኝ” የምንልባት መንገድ ቀይሰናል።

ቃሉ ገብቶናል
በመሰረቱ ሊቁ ዐለቃ ደስታ ተክለወልድ “አወገዘ” የሚለውን ቃል ሲፈቱት ፤ “ገዘተ፣ ክፉ  ሥራን፣ ክሕደትን  ከለከለ፣ ተው አለ ፤ እንቢተኛን ፡ ከሕዝብ አንድነት ፡ ለየ ፡ ወገደ...” ነው ይላሉ። መለየት የምትለዋ ቃል... አንድ ሰው ሌላውን በአንድ ተግባር ለማውገዝ፣ እሱ ከዚያ ሥራ ነፃ መሆኑንና ከ“ደሙ ንፁህ” መሆኑን ማረጋገጥ ይገባዋል። በቀላል አማርኛ አውጋዥ፣ ራሱ ተወጋዥ አለመሆኑን ያውቃል ወይ? ነው።
በዚህ ሁሉ ምስኪን ህዝብ ደም ውስጥ ምንም አላዋጣንም?
በቃልም?
በተግባርም?
በጥላቻ ንግግርም?
ግጭት በማማባስም?
ያልገባን ነገር ውስጥ ተሳትፈን በመፈትፈትም?
በአንድም ይሁን በሌላ፣ በቃልም ሆነ በግብር፣ በማስፈፀምም ሆነ በትብብር፣ ጥፋትን ወደብሔርና ሀይማኖት በመለጠጥና እሳቱን ወደ ሰደድ እሳት በመቀየር... አልተሳተፍንም ወይ? 

ግፍ ሲፈፀም... በቅንነት ከሚጮኹት ይልቅ ድምፃቸው ጣሪያ የሚበጥሰው የሟቾችን እምነትና ብሔር እያረጋገጡ የሚጮኹት ናቸው። ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ፀጥ ያሉ መስጊድ ሲቃጠል ድምፃቸው ይጠነክራል፤ መስጊድ ሲቃጠል ጉዳዩን ለማድበስበስ የሚዳክሩት ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ሀገር ካልፈረሰ ይላሉ። ብሔሩም ከሀይማኖቱ ጋር እየተቀየጠና እየተናበበ፣ ሬሳውን እየቆጠረ... ለራሱ በአባላት እና ደጋፊዎቹ መጮህ ማስጮህ... ለሌላው ሲሆን ዝም ጭጭ ማለትን ዓመሉ ካደረገ ከራረመ።  ለምን በጋራ አይወገዝም ሲባል... የኔ ሲገደል እሱ ዝም ብሏል፣ የኔ ሲቃጠል የት ነበራችሁ... ይባባላል በየተራ። ይሄ የውግዘት ቅብብል ... የውግዘት አዙሪት ስር ቀረቀረን እንጂ ምን ጠቀመን?

ከማውገዝ ጠለቅ ያለ እና ፋይዳ ያለው ሚና የለንም?
ሀገራችን ውስጥ ወንጀልና ቅጥ ያጣ ግፍ የገዛ ወገኖቻችን ላይ ሲፈፀም በየተራ ስናወግዝ ነው የኖርነው።
ምን ጠቀመን? ንፁሃንን አተረፍን ወይስ ለሌላ ዙር ግፍ አመቻቸናቸው? ችግሩን ፈታነው ወይስ አባባስነው?
የድርጊቱ ቀጥተኛ ፈፃሚዎችን ፍርድቤት ዳኛቸው እንበል፣ ችግሩ የተፈጸመበት አስተሳሰብ ከማህበረሰባችን ጠፋልን?
ቅራኔዎቻችን ተፈቱ ወይስ ይብስ እየተለያየን መጣን?
ጉዳዩን የፈፀምነው ወይም ያወገዝነው ከሆነ ብሄር ጥላቻ ከሆነስ... ያ ብሄር ምን ይደረግ?
እናጥፋው?
አንድ ሀይማኖት ላይ ጣታችንን ከቀሰርንስ ያ ሃይማኖት ምን ይደረግ? በሕገመንግስት ይታገድ?
.
.
ውግዘት ግቡ ግራ የሚያጋባ ድርጊት ነው። ስር የለውም። ንዴትን፣ ጥላቻን፣ እልህን በተቃውሞ ስም የምናወጣበት... እጅም እግርም የሌለው ጊዜያዊ እፎይታ እንጂ እረፍት አይደለም። ስንሮጥ እንታጠቀዋለን ስንሮጥ ይፈታል። ትናትን በሰፈርንበት ግፍ ዛሬ ደሞ እንሰፈራለን። ግን እንደትውልድ፣ የተሻለ ዘላቂ መፍትሔ ማቅረብ አለብን... ይገባናል.. ደግሞም እንችላለን!
.
.
ማስታወሻ_ለሀይማኖቱ…
ውግዘት እንኳን ፊደል ለቆጠርነው ለሀይማኖት ሰዎችም ዛሬ ላይ አይሰራም። እነሱም የሞራል ስራቸውን በአግባቡ መስራት ትተው በፖለቲካ ድንኳን ውስጥ የሚጋፉ ሆነዋል። እነሱም ቢሆን በአግባቡ የድርሻቸውን ይወጡ። ልብ ማለት ያለብን ዛሬ በሀገራችን የተደገሰውና የሚነገድበት ሞት አንዱና ዋነኛው መጠቅለያው ሀይማኖት መሆኑ ልብ ይሏል።
#ሀሳብሜዳ
1.5K views20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:07:44 የምዕራባዊያን ውሸት በኤርትራዊ ሥኬት ሲጋለጥ

~ የአሥመራ Development Book ~

አብዲዋሐብ ሼክ አብዲሰመድ #የዓባይልጅ

ቀይ ባህር ላይ ስትራቴጂክ ቦታ ላይ በምትገኘው ኤርትራ በቅርቡ ያደረገው ጉብኝት በአስደሳች ውበት እና ሰላም የተሞላ ነበር ሲል የሆርን አፍሪካ ስትራቴጂክ ጥናት ተቋም ሊቀመንበር ፅሁፋቸውን ይጀምራሉ። የተቋሙ ሊቀመንበር አብዲወሃብ ሼክ አብዲሰመድ ኤርትራ አለም አቀፍ ማእቀብ ሳይበግራት በራሷ አቅም ያሳካችው የምግብ ዋስትና ውጤት ለመላው አፍሪካዊ ሀገራት ትምህርት ሰጪ ሆኖ አገኘሁት"" ብለዋል።

"ምእራባዊያን ስለ ኤርትራ የሚነዙትን ትርክት ትልቅ ውሸት መሆኑን እንድታዘብ አድርጎኛል።" በማለት አድናቆታቸው ገልፀው ከኤርትራ ተሞክሮው ሌሎችም ይማሩ ዘንድ አብዲወሃብ ሼክ አብዲሰመድ የከተቡትን አጋራኋችሁ

ሰባት ሚሊዮን ገደማ ሕዝብ ያላት ኤርትራ የተረጋጋ ፖለቲካ የሰፈነባት ከሞላ ጎደልም ከወንጀልና ሙስና የጸዳች ነች። ዜጎቿ ትምህርት እስከ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ክብካቤ በነፃ ያገኛሉ። በሀገራቸው የሚኮሩ ኤርትራውያን፣ ሌሎች አፍሪካዊ ሀገራትን ያጠፋውን የውጭ ተጽዕኖ በተሳካ ሁኔታ ተቋቁመውት ይገኛሉ።
ምእራባዊያን ካቀረቡላት ቀንበር ይልቅ ሉአላዊነቷን በማስቀደሟ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ድጋፍ በነፈጓት ወቅት ካጋጠሟት ጣጣዎች መትረፍ ችላለች። ይህ ኤርትራዊ የስኬት ታሪክ ለአፍሪካ ሀገራት ተስፋ ነው። የኤርትራውያን የፅናት መንፈስ የተቀሩት አፍሪካውያን የልማት አቅጣጫ እናስምርላችሁ የሚሏቸውን አለም አቀፍ ኃይሎች እንዴት መቋቋም እንደሚችሉ የሚያስገነዝብ መማሪያ መጽሐፍ ነው።

ከዓመታት በምዕራባውያንና በአሜሪካ የሚደገፈው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አስተዳደር በኤርትራ አውዳሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት አደረገ። ሊሰብሯቸው በቆረጡ አለም አቀፍ ድርጅቶች ድርጊት እና የተባበሩት መንግስታት ለአመታት ሲነዛው በነበረው ውሸት የተነሳ ኤርትራዊያን ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። በኤርትራ የሥርዓት ለውጥ እንዲመጣ ወይም ደግሞ ቢያንስ አመጽ እንዲቀሰቀስ ብሎም አስመራ ከኢኮኖሚው ተጠቃሚነት ተነጥላ አጠቃላይ ቀውስ ለመፍጠር አበክረው ቢሰሩም ያ ሁላ የተቀናጀ ሴራ አሁን ላይ ከሽፏል። ይህ የምዕራቡ ዓለም ሴራ መጀመሪያ ላይ ሚሊዮኖች ኤርትራዊያን ዘንድ የፈጠረው ፈታኝ ሁኔታ የታቀደውን ቁጣ ከመቀስቀስ ይልቅ በተቃራኒው በረከት ያለው ስራ ይጀመር ዘንድ ሰበብ ሆነ። የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አስተዳደር ኤርትራን ራሷን የምትመግብ ለማድረግ መርሃ ግብራቸውም አስጀመሩ። ይህ ጥረት የታለመለትን ሀገራዊ ግብ ለመምታት ከጫፍ ደርሷል። በቀጣይ ጥቂት አመታት ውስጥም ኤርትራ ህዝቦቿን በመመገብ ሰብአዊ ርዳታ ላይ የማትጠብቅበት ስኬታን ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅታለች።

በጉብኝቴ ያገኘኋቸው የኤርትራ ግብርና ሚኒስትር አረፋይነ በርሄ ሀገራቸው ዜጎቿን በራሷ ለመመገብ የሚያስችል የግብርና መሰረተ ልማት መገንባቷን ይናገራሉ። የግብርና ሚኒስቴሩ ካሳዩኝ ሰነድ እንደተመለከትኩትም 220 ሚሊየን ዶላር የተበጀተለት የአምስት አመት እቅድ ነድፋለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ 18.4 ሚሊዮን ሰዎች ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ተጋልጠዋል። ይህ አሃዝ እስከ ወርሃ መስከረም 20 ሚሊየን ሊደርስ ይችላልም ብሏል።
የተባበሩት መንግስታት እና የምዕራባውያን ማዕቀቦች ከአስር ዓመታት በላይ ቢጣሉባትም ችግሩን ተቋቁማ አሁን ላይ 500,000 ሄክታር መሬት በጥሩ ሁኔታ በጥቅም ማዋል ችላለች።
ይህ ስኬቷ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲሁም አለም አቀፍ የሰብአዊ ርዳታ ድርጅቶች ምግብ ዋስትናን በተመለከተ ቀላል፣ ወጪ ቆጣቢ እና ግልፅ የሆነ አሰራርን ከኤርትራ መዋስ ይችላሉ።

በግብርና ሚኒስቴር የእቅድና ስታስቲክስ ዲቪዥን ዳይሬክተር አቶ በረከት ፀሃዬ በቅርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ በኤርትራ የፍራፍሬ ምርት በ 71 እጥፍ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ደግሞ በ 6 እጥፍ ገደማ ጨምሯል። ባሳለፍነው የፈረንጆች 2021 ላይም ኤርትራ ከምግብና ደረጃ ተላቃ ‘ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ እና አልሚ ምግብ ዋስትና’ ተሻግራለች።
ኤርትራ አሁን ላይ 785 ኩሬዎችና ግድቦች አሏት። ከሰላ አመት በፊት ራሷን የቻለች ሀገር በሆነችበት ወቅት የነበሯት 138 ኩሬዎችና ግድቦች ነበር።

በፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግስት ከተመዘገቡት ሌሎች ስኬቶች መካከል የኤርትራ በግብርና ላይ ያከናወኗቸው ተግባራት ጥቂቱ ነው። የቀጠናው ኤክስፐርት እና የኬንያ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የነበሩት ፋራህ ማሊም ኤርትራ ከዕዳ ነፃ የሆነች፣ በቴክኖሎጂ የዳበረች፣ በምግብ ምርት ራሷን የምትችል እና ወደ ጤናማ መሠረተ ልማትና ደህንነት እንዲህ ስታመራ ማየት አስደሳች ነው ብለዋል። ግዛት - ምንም እንኳን ምዕራቡ ልማቱን ለማደናቀፍ ሁሉንም ነገር ቢያደርግም በጉብኝቴ ወቅት የመንግስት ባለስልጣናት ቀላል አኗኗር ትኩረቴን ስቦ ነበር።
የአፍሪካ አገሮች ከኤርትራ የልማት መጽሐፍ አንድ ገፅ ማውጣት በርግጥም ይችላሉ።

#ItsAfricanDam #HornOfAfrica #Eritrea #Ethiopia #GERD #itsafricandam
#DebtTrap #IMF
1.5K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:07:41
1.4K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:07:29
እዩትላችሁ ፡ ዓባይ ፡ አባቴ ፡ ደሜ ፡ የሁላችን
#የዓባይልጅ

5 ጉ ዳ ይ

#GERD #ItsAfricanDam
1.3K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:07:07 የአይ.ኤም.ኤፍ. ወጥመድ

ግጭት ያስተናገዱ አካላት ፀባቸውን አርግበው ወደ ወዳጅነት መመለስ ሲጀምሩ፣ አዲስ መርህ በአይቀሬነት የሚከተል ይሆናል። ይህ እንኳን በፖለቲካ በስነ-ፅሑፍ ውስጥም ታሪክን አስውቦ ወደ ፊት ለማራመድ ዋነኛው አላባ [element] ነው።

ኢትዮጵያ አፍሪካንና መላውን አለም ያነቃነቀ እምቢተኝነት ማቀጣጠሏ ፀረ-ኢምፔሪያሊዝም መሆኑን የተገነዘቡት ምእራባዊያንም ሆኑ የተቀረው አለም ነው። አንገት ላንገት የተያያዝንበት (በጣም አብላጫው) ምክንያት ሉአላዊነት ነበር ማለት ነው። ይህ የማያግባባ ድምዳሜ አይሆንም ባይ ነኝ።
የምዕራባዊያን ክህደትና ንቀት ሊገርመን አይገባም። መገረም ካለብን አዲስ የግንኙነት ፀኃይ ስትወጣ ያለፈው እንዳይደገም የሚያችል የፖሊሲ ጋሻ በተቻለን መጠን ሳናበጅ የቀረን እንደሆነ ብቻ ነው። ከምእራባዊያን የተከፈተብን ይፋዊ ውጊያ ረግቦ ዲፕሎማሲ ወደሚባለው አካሄድ ስንመለስ ምን አዲስ የፖሊሲ ጋሻ መቅረፅ ይኖርብን ይሆን? ጉዳዩ ይህ ነው..! በተለይም IMF እና World Bank ባመጧቸው አሳሪ ቅድመ ሁኔታዎች ተጠልፈን ላለመውደቅ..። [ የነዳጅ ድጎማ እንዲነሳ፣ የንብረት ታክስ ከነሱው አሳሪ ወጥመዶች መካከል ናቸው።] ኑሮ ውድነትና ግሽበት ህዝቡን እየፈተነው ቀጥሏል። ምዕራቦቹ ግን አሁንም ሌሎች መነሳት ያለባቸው ድጎማዎች እንዲሁም የሚተገበሩ የታክስ አይነቶችን ደርድረው እየጠበቁን ነው። የነፃ ኢኮኖሚ ቀኖና እንዲህ ነው በማለት በክፍተታችን እየተጫወቱ ናቸው። በፓኪስታን ኢምራን ክሃን ላይ ያደረጉትም ይህንኑ ነበር።
እየተደረገብን ያለው ጫና እጅጉን የሚያማርር ነውና ሎርድ ኦፍ ዘ ሪንግስ ፊልም ውስጥ እንዳለው ገፀባህርይ “ምነው በዚህ ጊዜ ባልኖርኩ..።" እሰከማለት ሊያደርስ ይችል ይሆናል..። አማራጮችን አማትሮ የተሻለውን ከመወሰን ውጪ መፍትሄ አይገኝም። ሰው ልጅ ሊመርጥ የሚችለው ቢኖርበት የሚበጀውን ዘመን ሳይሆን በተፈጠረበት/በሚኖርበት ዘመን የሚፈፅመውን ተግባር ብቻ ነውና።

እንደ ሀገር ፈጣን ውሳኔ የምንሻበት 11ኛ ሰዓት ላይ

#የዓባይልጅ Esleman Abay
#IMF #WorldBank #DebtTrap
1.3K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ