Get Mystery Box with random crypto!

Coram Deo

የቴሌግራም ቻናል አርማ elolam_elolam — Coram Deo C
የቴሌግራም ቻናል አርማ elolam_elolam — Coram Deo
የሰርጥ አድራሻ: @elolam_elolam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.45K
የሰርጥ መግለጫ

Coram Deo is a Latin phrase that means "in the presence of God" or "before the face of God". It is a reminder that we are always in the presence of God and that our lives should be lived in a way that honors Him.
@sami_f_k_1
@Sami_inchrist
@Amuti18

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-04-02 06:20:02
487 views03:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 22:37:17
464 views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 22:09:57
526 views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 01:03:45
539 views22:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 00:39:10 በእነዚህ ነውጦች ሁሉ መካከል፣ “የነፍስ ድቅድቅ የጨለማ ምሽት” በማለት በሚጠራውና አልፎ አልፎ በሚነሣ ሰበብ የለሽ ድባቴም ይቸገር ነበር። በአንድ ስብከቱ መካከል፣ የደባቴውን ክብደት እንዲህ በማለት ገልጾታል፦ “ባለፈው ሳምንት በሶፋ ላይ ገደም ባልሁበት፣ ድባቴ ድንገት መጣና ልቤን አወረደው። ለሰዓታት እንደ ሕፃን ልጅ አለቀስሁ፤ ምክንያቱን ግል(ን) አልውቀውም ነበር።” (The Christian’s Heaviness and Rejoicing: 1 Peter 1:6, November 7, 1858)። ጋውት (Gout) የተሰኘው የጣቶችና (በተለይም የእግር አውራ ጣት) የመገጣጠሚያዎች ቁርጥማት  (አርትራይተስ) እና የኩላሊት ሕመም፣ መከራውን ቀላል አላደረጉለትም። የጋውት ድንገተኛ ጥቃት ሲመጣ የሚሰማው ስለታም የሕመም ስሜት፣ አውራ ጣትን በመዶሻ የማድቀቅ) ያኽል ነው። ከማሕፀን ሕምም ጋር በተየያዘ ምክንያተ በተካሄደ ያለተሳካ ቀዶ ጥገና፣ ለ 27 ዓመታት ከወገብዋ በታች ሽባ የነበረችውን ባለቤቱን ሱዛናን ያስታምም ነበር። የመጨረሻዎቹ ጥቂት ዓመታቶቹ፣ የደስታ አልነበሩም። ልቡ ወድቆ ነበር። ቀድሞ በሞት የተለያት ባለቤቱ፣ “ለእምነቱ የነበረው ተጋድሎ፣ ሕይወቱን አስከፍሎታል” በማለት መስክራለታለች።

ነብዩ ኤልያስ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅቶኛል፤ እኔ ከቀደሙት አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰዳት” በማለት የጸለየበት ምክንያት ይኽው የልብ መውደቅ ነበር።

በብዙ መከራ ውስጥ፣ በትችት፣ በመገፋት ወይም ርኅራኄ በሌላቸውና በሥጋውያን አስቸጋሪ  መሪዎች ጫና ሥር የሚያገለግሉ ብዙ የጌታ ባሪያዎች አሉ። አብዛኛዎቹን ሚድያው አያውቃቸውም። በዚያ ላይ ቤት ኪራይ በመክፈልና ልጅን በማሳከም፤ አስቤዛ በማድረግና ለልጆች ትምህርት ቤት በመክፈል፤ መድሃኒት ለራሳችው በመግዛትና የባለቤታቸው ጥርስ በማሳከምና በመሳሰሉ አስከፊ የኑሮ ምርጫ አጣብቂኝ ውስጥ እያለፉ፣ በየሰንበቱ በታማኝነት የሚያገለገሉ ባሪያዎች አሉ። በአንድ በሌላም መንገድ፣ በአገልግሎት ጉዞ ውስጥ፣ “ዮሴፍን የሚሸጡ ወንድሞች፣ ዳዊትን የሚያሳደዱ ሳዖሎች፣ በሙሴ ላይ የሚነሱ ማርያሞችና አሮኖች፣ ክርስቶስን አሳልፈው እንደሰጡት ያሉ ደቀመዛሙርት፣ ጴጥሮሶችና ይሁዳዎች፣ ዴማሶች፣ አንጥረኞቹ እስክንድሮሶች፣ ሌሎቹ” አይጥፉም።  በአገልግሎት ውጣ ውረድ ውስድ፣ ቅዱስ ቃሉ ሁሉ የጠራችሁ እርሱ የታመነ ነው እንደሚል፣ እግዚአብሔር ታማኝና ሉዓላዊ ነው።

የተጽናናበትንና የጸናበትን ምክንያት ሲናገር፦

እጅግ በከበደ መልኩ ሐዋርያት በመከራ ስለ ታጀበው የወንጌል አገልግሎታቸው ብዙ ጊዜ በምስጋና ልብ ተናገረዋል። በዚህ ዐውድ ሁለቱን መጥቀስ አግባብነት አለው፡፤

ከየአቅጣጫው ብንገፋም አንንኰታኰትም፤ ግራ ብንጋባም ተስፋ አንቈርጥም፤ ብንሰደድም ተጥለን አንቀርም፤ መትተው ቢጥሉንም አንጠፋም። የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ፣ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችን እንዲገለጥ፣ እኛ ሕያዋን የሆንን ሁል ጊዜ ስለ ኢየሱስ ለሞት ዐልፈን እንሰጣለንና። እንግዲህ ሞት በእኛ ይሠራል፤ ሕይወት ግን በእናንተ። (2 ቆሮንቶስ 4:8-12)

“ወዳጆች ሆይ፤ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ በመቀበላችሁ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ በመቍጠር አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ደስ ይበላችሁ . . . ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ሁሉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ ዐደራ ሰጥተው መልካም ማድረጋቸውን ይቀጥሉ።” (1 ጴጥሮስ 4:12-19)

አገልግሎት “ሙያ” ያልሆነበት ቀዳማዊ ምክንያት ከልብ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ነው። በፍትሕ የለሽ በደልና ስብራት የቈሰለ ልብን ተሸክሞ፣ በታማኝነትና በመሰጠት ማገልገል ትልቅ ጽናትና ጸጋ ይጠይቃል። ስፐርጀን እንዳለው፣ “አገልግሎታችን ከአእምሮ ሥራ በላይ ነው። የልብ ጉዳይ ነው፤ የነፍስ ውስጠኛ ድካም። (Spurgeon, Lectures to My Students, [Zondervan Publishing House, 1972], 156). በተሰበረ ልብ እንዴት በሙሉ ኀይልና መሰጠት ለቅዱስ ቃሉ ታማኝ በመሆን ማገልገል ይቻላል? ስፐርጀን እንዳለው “ለራስ በመሞት በእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና ጸጋ በመደገፍ ብቻ ነው።  በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት የነበረው ጽኑ እምነት፣ በልቡ የፈሰሰው ወሰን የለሽና ሁሉን አስጣይ የክርስቶስ ፍቅር፣ በጌታ ጸጋ ተደጋፊነት፣ የጸሎት ትጋቱን፣ ብቻውን ቢቀርም እንኳን ለወንጌል ንጽሕና የነበረው ቀናዒነት፣ ዐቅሙ ነበሩ።

“በብዙ [መከራ] በጌታ አገልግሎት ብዝልና ያለ እድሜያችን ብንሞት፣ ክብር ለግዚአብሔር ይሁን። ምድር ትንሽ፣ ሰማይ ደግሞ ብዙ ይኖረናል ማለት ነው።” (An All Round Ministry, 126–127).

ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)
522 views21:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 00:39:10 “በሲቃ ከማልቀስ በስተቀር ሕመሜ መታገሥ ከምችለው [በላይ] ሆኖብኝ በምሰቃይበት አንድ ወቅት፣ ከጌታ ጋር ብቻ መሆን እንድችል አጠገቤ የነበሩት ወገኖች ከክፍሌ እዲወጡልኝ ጠይቅዃቸው። ወዲያውኑ ከእንባ ጋር ለእግዚአብሔር ቀጥሎ ያለውን ጸሎት ከማለት በስተቀር ምንም ማለት አልቻልሁም ነበር፦

‘አንተ አባቴ ነኽ፤ እኔም ልጅህ ነኝ። አንተ እንደ መልካም አባት ሩኅሩኅና ቸር ነህ። [በማይገባኝ መልኩ] በሰጠኽኝ መከራ ልጄ ሲሰቃይ ባየው፣ እንደ ወላጅ አባት እያየሁ ዝም ማለት አልችልም። እቅፍ አድርጌው አጽናናዋለሁ፤ ከመከራውም ሁሉ እንዲያርፍ ላደርግ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ። ታዲያ አባቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን ከእኔ ለምን ትሰውራለህ? እጅህንስ ለምን ታከብድብኛለህ? ፊትህን በመልካምነትህስ ወደ እኔ አትመልስምን?’”

ስፐርጀን ይቀጥላል፦

“እናም ይህን ስቅዩ ልቤን በእግዚአብሔር ፊት ካፈሰስሁ በኋላ፣ ውስጤን ረፍት ሞላው።  ወገኖች ተመልሰው ወደ ክፍሌ ሲገቡ፣ ‘እግዚአብሔር የጭንቅት ጩኸቴን ሰምቶአል፤ ተሽሎኛል፤ ሸክሜም ቀሊል ሆኖአል። እግዚአብሔርን እባረካለሁ’ አልኋችው።” (C. H.  Spurgeon, Heaven’s Nurse Children, Metropolitan Tabernacle, Newington)

በመንፈስ ቅዱስ ኀይል የቃሉን ብርሃን በሚገልጠው ስብከተ ወንጌሉ እስከ ዛሬ ድረስ የሚወሳው እንግሊዛዊው ቻርልስ ሀደን ስፐርጀን (19 June 1834 – 31 January 1892)፣ አገልግሎቱ በብዙ መከራና የልብ ስብራት የታሸ ነበር። እንደ እርሱ አገላለጽ፣ “በመርዛምና ዐጥነት በሚሰብር ስም ማጠልሽትና ትችት፣ በልዝብተኛ ጋዜጠኞች የማያቋርጥ አቃቂር፣ ከአስቸጋሪ መሪዎች ጋር ማገልገል፣ ምንም ቢደረግላቸው በማይረኩ አባላት፣ በቅርብ ወዳጆች መከዳት፣ በሕመም፣ ለዓመታት በላይ ከወገቧ በታች ሽባ የነበረችውን ባለቤቱን በማስታመም እንዲሁም ምክንያት ከሌለው ድባቴ (causeless depression) ጋር እየታገለ ነበር የሚያገለግለው። 

“ዛሬ ሆሳዕና በማለት ስሜን ያገነነው ያው ሕዝብ፣ ሊሰቅለኝ  . . . ሰው ሲተወኝ፣ ያመንሁት ሲከዳኝ፣ እጁን የሰጠኝ ሲነሣኝ፣ በእጅጉ ያማል። ሆኖም ጌታ ፊቱን ሲያዞር [ወይም ዝም ያለኝ ሲመስለኝ] ከሚሰማኝ ሕመም ጋር ፈጽሞውኑ አይነጻጸርም . . . በሰው በመናቅ፣ በመገፋትና ኢፍትሐዊ መከራ በመቀበል ውስጥ፣ የእኔ ብርታትና ዐቅም ይሟጠጥና የጌታ ጸጋ ይፈሳል፣ አብሮነቱም በአገልግሎቴ ውስጥ የተትረፈረፈ ዐቅም ይሆነኛል . . . ይሁን እንጂ በዚህ ውስጥ ማለፍ እጅግ ከባድ ነው። ከልብ ስብራት የተነሣ፣ ከቅንድቤ ላብ እስኪንቆረቆር ድረስ ብዙ ጊዜ የስም ጉድፈት ዶፍ ወርዶብኛል፤ በጥልቅ ሐዘን የተሰበረው ልቤ ለመቆም ዐቅም አሳጦቶ አንበርክኮኛል። በእግዚአብሔርም ፊት ተደፍቼ አልቅሼአለሁ”  (Salvation of the Lord, Jonah 2:9 -  May 10, 1857, New Park Street Pulpit Volume 3)

ስለራሱ መመለስ በማይችልበት ሁኔታ፣ በቅንነት ያገለገለበት የመጥምቃውያን ማኅበር ፍትሕ በሌለው መልኩ በአደባባይ ሲያዋርደው፣ አገልግሎቱ አንዴ በዝና ተራራ ላይ  ከፍ ሲያደርገው፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ መውጫ የሌለው የውርደትና የስብራት ሸለቆ ውስጥ ሲከተው፣ በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ላይ የነበረው ሙሉ እምነትና ለክርስቶስ የነበረው ፍቅር ዐቅም ሆነውታል።

በአገልግሎቱ ማብቂያ ገደማ፣ ሁለት የተቀናጁ ነቀፋዎች እጅግ ጐድተውት ነበር። አንደኛው፣ “The Down-Grade Controversy of 1887–88 ” (የዝቅታ ወይም የቁልቁሎሽ ውዝግብ) በመባል የሚታወቀው ሁለት ዓመት የፈጀና ሥጋዊነት የለበሰ የመጥምቃውያን ማኅበር አድካሚ ስብሰባ ነበር። ወቅቱ የቻርልስ ዳርዊን ሳይንሳዊ ፍልስፍና ለልቅ ነገር መለኮት (theological liberalism) ዘር በመሆን፣  የወንጌላውያኑን መሠረታዊ የእምነት ፋይዳዎች መሸርሸር የጀመረበት ነበር። በተለይም በሁለት ዐበይት ዶክትሪኖች። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የመጸሕፍ ቅዱስን የበለይነት፣ ሕጸጽና (infallible) ግድፈት አልባነት (inerrant) በተመለከተ ሲሆን፣ በመቀጠል የወልድን መለኮታዊነት እንዲሁም ምትክ ቤዛዊ ሞቱን አስመልክቶ፣ የመጥምቃውያኑ ኅብረት የእምነት አቋም አደጋ መኾኑ ነበር። ስፐርጀን የነበረውን ስጋት በግልጽ ተናግሮ ነበር። ከዚያም አልፎ፣ ውዝግቡ እርሱ በሚመራ ወርሃዊ መጽሔት ላይ በመታተሙ፣ ወደ ልቅ ነገር መለኮት ማዘንበል በጀመሩና ቀደም ሲለም ከእርሱ ጋር የሻከረ ግኑኙነት ከነበራቸው ተጽእኖ አምጪ መሪዎች ጋር የከረረ ግጭት ውስጥ ከትቶታል። 

ሁለተኛው ደግሞ፣ “የባሪያን ንግድና አሳዳሪነት” አስመልክቶ የነበረው ተቃውሞ ከአሜሪካ ደቡባዊ መጥምቃውያን ማኅበር ጋር አጋጭቶታል። ስብከተ ወንጌሎቹ በአሜሪካ እንዳይሰራጩ እንዲሁም ተደማጭነት እንዳይኖረው ዘመቻ ተካሂዶበታል።

የልቅ ነገር መለኮትን መብቀልና የሥነ-ምግባር ዝቅጠትን በተመለከተ፣ የነበረውን ሐዘን እንዲህ በማለት ገልጾአል፦

“የከተማችን ለንደን መንገዶች በበደልና በክፋት ተሞልተዋል፤ ብቅ ማለት ለጀመረው እምነት የሌሽነት እያሳየን ያለው ዝምታ (ባይተዋርነት) ያሳስበኛል. . . ያልተቀደሰች ቤተ ክርስቲያንን እግዚአብሔር ፈጽሞውኑ መኖርያው አያደርግም፤ በሥጋዊነት የተዝ(ዥ)ጐረጐረን ሕይወት እግዚአብሔር ይጸየፋል።” (The Best War-Cry, March 4, 1883)።

“የባሪያን ንግድና አሳዳሪነት” አስመልክቶ ደግሞ፣ “ከውስጥ ነፍሴ እጅግ አብዝቼ የምጠላው ነው . . . ከተለያየ እምነት ለሚመጡ [ክርስቲያኖች] የጌታን ራት አካፍያለሁ፤ ኾኖም ከባርያ ነጋጅና አሳዳሪ ጋር ፈጽሞውን ምንም ዐይነት ኅብረት አይኖረኝም።” በማለት በወቅቱ የነበረውን መዋቅራዊ ዘረኝነት ፊት ለፊት ተጋፍጧል። (The Christian Watchman and Reflector,  Boston Baptist Newspaper, January 26, 1860) በመጨረሻም በአደባባይ፣ ቤተ ክርስቲያንንና ኅብረትን እንደማይወድና እንደማይታዘዝ ተቆጥሮ ከኅብረቱ እንዲሰናበት ተደርጐአል። መገለል፣ የቅርቤ ናቸው ያላቸው ማጣት፣ ብቸኝነት፣ የስም ማጥፋቱ ዘመቻ ውስጡን እጅግ ጐድተውታል። ኾኖም እምነቱ ጽኑ ነበር፤ “To pursue union at the expense of truth is treason to the Lord Jesus . . . He is our Master and Lord, and we will keep his words: to tamper with his doctrine would be to be traitors to himself.” (እውነትን መስዋዕት ያደረገ የአንድነት ፍለጋ፣ ክርስቶስን መካድ ነው . . . እርሱ መምህራችንና ጌታችን ነው፤ ቃሉን እንጠብቃለን፤ የእርሱን አስተምህሮ መነካካት እርሱን እራሱን መካድ ነው።” ("A Fragment Upon the Down-Grade Controversy, Sword and Trowel, November 1887)

ስለመገፋቱ ደግሞ፦

“ስሜ ከጠፋው በላይ፣ ሰዎች ሊናገሩ የሚችሉት የከፋ ነገር የለም። ከራስ እስከ እግር ጥፍሬ ድረስ፣ ተወግጃለሁ፤ እስከ ጥግ ድረስ ያልሆኑትን ምስል ተሰጥቶኛል። መልካምነቴን በተመለከት፣ አሁን መልከ ጥፉ ከተደረገበት ባላይ፣ የከፋ ማደር(ረ)ግ ማንም አይችልም። መጥፋት የሚችለውን ያህል ጠፍቶአልና። ያልተጐዳ ምንም የቀረኝ ማንነት የለም።” (An All Round Ministry, 159)
463 views21:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 07:13:11
@ElOLAM_ElOLAM
476 viewsedited  04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 14:46:55
@ElOLAM_ElOLAM
627 viewsedited  11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 12:43:06 ከሳሽህ በዝቶ ጠበቃ ለራቀ
ሀጢያትህ በርትቶ ነፍስህን ላስጨነቀ
ይህ መልእክት ላንተ ነው ተስፋ ለናፈቀ
ፈራጁ ስላንተ በመስቀል ማቀቀ
አንገቱ ደፋ ሲል ነገርህ አለቀ
ከሳሽህ አንደ መብረቅ ከሰማይ ወደቀ
እዳህን ሁሉ ከፍሎ አንተን አፀደቀ
ሁንዴ ዋቅሹም
@ElOLAM_ElOLAM
604 viewsedited  09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ