Get Mystery Box with random crypto!

በእነዚህ ነውጦች ሁሉ መካከል፣ “የነፍስ ድቅድቅ የጨለማ ምሽት” በማለት በሚጠራውና አልፎ አልፎ በ | Coram Deo

በእነዚህ ነውጦች ሁሉ መካከል፣ “የነፍስ ድቅድቅ የጨለማ ምሽት” በማለት በሚጠራውና አልፎ አልፎ በሚነሣ ሰበብ የለሽ ድባቴም ይቸገር ነበር። በአንድ ስብከቱ መካከል፣ የደባቴውን ክብደት እንዲህ በማለት ገልጾታል፦ “ባለፈው ሳምንት በሶፋ ላይ ገደም ባልሁበት፣ ድባቴ ድንገት መጣና ልቤን አወረደው። ለሰዓታት እንደ ሕፃን ልጅ አለቀስሁ፤ ምክንያቱን ግል(ን) አልውቀውም ነበር።” (The Christian’s Heaviness and Rejoicing: 1 Peter 1:6, November 7, 1858)። ጋውት (Gout) የተሰኘው የጣቶችና (በተለይም የእግር አውራ ጣት) የመገጣጠሚያዎች ቁርጥማት  (አርትራይተስ) እና የኩላሊት ሕመም፣ መከራውን ቀላል አላደረጉለትም። የጋውት ድንገተኛ ጥቃት ሲመጣ የሚሰማው ስለታም የሕመም ስሜት፣ አውራ ጣትን በመዶሻ የማድቀቅ) ያኽል ነው። ከማሕፀን ሕምም ጋር በተየያዘ ምክንያተ በተካሄደ ያለተሳካ ቀዶ ጥገና፣ ለ 27 ዓመታት ከወገብዋ በታች ሽባ የነበረችውን ባለቤቱን ሱዛናን ያስታምም ነበር። የመጨረሻዎቹ ጥቂት ዓመታቶቹ፣ የደስታ አልነበሩም። ልቡ ወድቆ ነበር። ቀድሞ በሞት የተለያት ባለቤቱ፣ “ለእምነቱ የነበረው ተጋድሎ፣ ሕይወቱን አስከፍሎታል” በማለት መስክራለታለች።

ነብዩ ኤልያስ “እግዚአብሔር ሆይ፤ በቅቶኛል፤ እኔ ከቀደሙት አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰዳት” በማለት የጸለየበት ምክንያት ይኽው የልብ መውደቅ ነበር።

በብዙ መከራ ውስጥ፣ በትችት፣ በመገፋት ወይም ርኅራኄ በሌላቸውና በሥጋውያን አስቸጋሪ  መሪዎች ጫና ሥር የሚያገለግሉ ብዙ የጌታ ባሪያዎች አሉ። አብዛኛዎቹን ሚድያው አያውቃቸውም። በዚያ ላይ ቤት ኪራይ በመክፈልና ልጅን በማሳከም፤ አስቤዛ በማድረግና ለልጆች ትምህርት ቤት በመክፈል፤ መድሃኒት ለራሳችው በመግዛትና የባለቤታቸው ጥርስ በማሳከምና በመሳሰሉ አስከፊ የኑሮ ምርጫ አጣብቂኝ ውስጥ እያለፉ፣ በየሰንበቱ በታማኝነት የሚያገለገሉ ባሪያዎች አሉ። በአንድ በሌላም መንገድ፣ በአገልግሎት ጉዞ ውስጥ፣ “ዮሴፍን የሚሸጡ ወንድሞች፣ ዳዊትን የሚያሳደዱ ሳዖሎች፣ በሙሴ ላይ የሚነሱ ማርያሞችና አሮኖች፣ ክርስቶስን አሳልፈው እንደሰጡት ያሉ ደቀመዛሙርት፣ ጴጥሮሶችና ይሁዳዎች፣ ዴማሶች፣ አንጥረኞቹ እስክንድሮሶች፣ ሌሎቹ” አይጥፉም።  በአገልግሎት ውጣ ውረድ ውስድ፣ ቅዱስ ቃሉ ሁሉ የጠራችሁ እርሱ የታመነ ነው እንደሚል፣ እግዚአብሔር ታማኝና ሉዓላዊ ነው።

የተጽናናበትንና የጸናበትን ምክንያት ሲናገር፦

እጅግ በከበደ መልኩ ሐዋርያት በመከራ ስለ ታጀበው የወንጌል አገልግሎታቸው ብዙ ጊዜ በምስጋና ልብ ተናገረዋል። በዚህ ዐውድ ሁለቱን መጥቀስ አግባብነት አለው፡፤

ከየአቅጣጫው ብንገፋም አንንኰታኰትም፤ ግራ ብንጋባም ተስፋ አንቈርጥም፤ ብንሰደድም ተጥለን አንቀርም፤ መትተው ቢጥሉንም አንጠፋም። የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ፣ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችን እንዲገለጥ፣ እኛ ሕያዋን የሆንን ሁል ጊዜ ስለ ኢየሱስ ለሞት ዐልፈን እንሰጣለንና። እንግዲህ ሞት በእኛ ይሠራል፤ ሕይወት ግን በእናንተ። (2 ቆሮንቶስ 4:8-12)

“ወዳጆች ሆይ፤ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ በመቀበላችሁ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ በመቍጠር አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ደስ ይበላችሁ . . . ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ሁሉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ ዐደራ ሰጥተው መልካም ማድረጋቸውን ይቀጥሉ።” (1 ጴጥሮስ 4:12-19)

አገልግሎት “ሙያ” ያልሆነበት ቀዳማዊ ምክንያት ከልብ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ነው። በፍትሕ የለሽ በደልና ስብራት የቈሰለ ልብን ተሸክሞ፣ በታማኝነትና በመሰጠት ማገልገል ትልቅ ጽናትና ጸጋ ይጠይቃል። ስፐርጀን እንዳለው፣ “አገልግሎታችን ከአእምሮ ሥራ በላይ ነው። የልብ ጉዳይ ነው፤ የነፍስ ውስጠኛ ድካም። (Spurgeon, Lectures to My Students, [Zondervan Publishing House, 1972], 156). በተሰበረ ልብ እንዴት በሙሉ ኀይልና መሰጠት ለቅዱስ ቃሉ ታማኝ በመሆን ማገልገል ይቻላል? ስፐርጀን እንዳለው “ለራስ በመሞት በእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና ጸጋ በመደገፍ ብቻ ነው።  በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት የነበረው ጽኑ እምነት፣ በልቡ የፈሰሰው ወሰን የለሽና ሁሉን አስጣይ የክርስቶስ ፍቅር፣ በጌታ ጸጋ ተደጋፊነት፣ የጸሎት ትጋቱን፣ ብቻውን ቢቀርም እንኳን ለወንጌል ንጽሕና የነበረው ቀናዒነት፣ ዐቅሙ ነበሩ።

“በብዙ [መከራ] በጌታ አገልግሎት ብዝልና ያለ እድሜያችን ብንሞት፣ ክብር ለግዚአብሔር ይሁን። ምድር ትንሽ፣ ሰማይ ደግሞ ብዙ ይኖረናል ማለት ነው።” (An All Round Ministry, 126–127).

ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)