Get Mystery Box with random crypto!

elam

የቴሌግራም ቻናል አርማ elam12 — elam E
የቴሌግራም ቻናል አርማ elam12 — elam
የሰርጥ አድራሻ: @elam12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.53K
የሰርጥ መግለጫ

የየሰንበቱ መዝሙር፣ ምስባክና ወንጌል
Elamaba.org

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 18:35:42

390 views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:32:31

390 views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:29:46 መዝሙር ይሁበነ ዝናመ ከነሐሴ ፳፪ - ነሐሴ ፳፮
(በ፫) ይሁበነ ዝናመ በጊዜሁ ይሁበነ ዝናመ በጊዜሁ ወይሁበነ እክለ በረከት (ይ) ያርኁ ክረምተ ይገብር ምሕረተ ወይሁበነ ዝናመ በረከት (ይ) ከሢቶ ዐይኖ ሰፊሖ የማኖ ይፌኑ ሣህሎ ወበዘአእመረ ይሴባሕ (ይ) ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ወብውህ ሎቱ ይኅድግ ኃጢአተ (ይ) ዐይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያሁ ይሁቦሙ ሲሳዮሙ በጊዜሁ።
ትርጕም፦
ዝናምን በጊዜው ይሰጠናል የበረከት እህልን ይሰጠናል ክረምትን ይከፍታል ምሕረትን ያደርጋል የበረከት ዝናምን ይሰጠናል ዐይኑን ገልጦ ቀኙን ዘርግቶ ይቅርታውን ይልካል ባወቀ መንገድ ይመሰገናል ለሰው ዕረፍት ይሆን ዘንድ ሰንበትን ሠራ ኃጢአትን ይቅር ይል ዘንድ ሥልጣን አለው የሰው ሁሉ ዐይን እሱን ተስፋ ያደርጋል በጊዜው ምግባቸውን ይሰጣቸዋል።
የዕለቱ ምንባባት፦
ዕብ ፫፥፩ - ፍ፤
ያዕ ፭፥፩ - ፲፪፤
ግብ ፳፪፥፩ - ፳፪፤
ወንጌል፦ ዮሐ፮፥፵፩ - ፍጻሜ፤
ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ
የዕለቱ ምስባክ፦
ዐይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ፤
አንተ ትሁቦሙ ሲሳዮሙ በጊዜሁ፤
ትሰፍሕ የማነከ ወታጸግብ ለኵሉ እንስሳ ዘበሥርዓትከ። መዝ ፻፵፬፥፲፮
ትርጕም፦
የሰው ሁሉ ዐይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤
አንተ ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ፤
ቀኝህን ትዘረጋለህ በሥርዓትህ ለሚኖሩ እንስሳ ሁሉ ታጠግባለህ።
ምሥጢር፦
የሰው ሁሉ ሰውነት አንተን ተስፋ አለኝታ ያደርጋል።
በየጊዜው ምግባቸውን ትሰጣቸዋለህና በዘር ጊዜ ዘሩን በመከር ጊዜ መከሩን። አንድም የበልጉን በበልግ የመከሩን በመከር ትሰጣቸዋለህና።
እጀ ሰፊ ነህና እጅህን ዘርግተህ በሥርዓትህ ጸንተው ለሚኖሩ ለእንስሳት ምግባቸውን ሰጥተህ ደስ ታሰኛቸዋለህ። ከሰው በቀር ከሥርዓቱ የወጣ የለምና።
መልእክት፦
በሥጋዊውም ሆነ በመንፈሳዊው ሕይወታችን እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግ ጠቃሚ ነው። "ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ" "አስቀድማችሁ መንግሥቱንና ጽድቁን ሹ" የሚሉት ቃላተ ወንጌል በተስፋ መኖርን የሚገልጡ ናቸው። በዘወትር ጸሎታችንም "ትምጻእ መንግሥትከ - መንግሥትህ ትምጣልን" እያልን እንድንጸልይ አምላካችን ያዘዘን ተስፋ ያላዩትን እንዳዩ ያልያዙትን እንደያዙ አድርጎ የሚሳይ መነጽር ስለሆነ ነው።
በተስፋ የሚኖር ሰው ቢወድቅ ለመነሣት፣ ቢሰበር ለመጠገን፣ ቢወጣ ተመልሶ ለመግባት፣ ቢጠራጠር መምህራንን ጠይቆ ለመረዳት፣ ቢረክስ ለመቀደስ፣ ቢጠፋ ለመመለስ እድል ያለው ነው። ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ እንዳስተማረን። "እንግዲህ ወዳጆች ሆይ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ" ፪ቆሮ፯፥፩
ዘበሥርዐትከ የሚለውን ቃል መተርጉማን ሲያብራሩ ከሰው በቀር ከሥርዓቱ የወጣ የለም ብለዋል። ይህንን ማብራሪያ ከልባችን በማስተዋል ያለሥርዓት መሄድ ያስከፈለውንና የሚያስከፍለውን ዋጋ በመገንዘብ ያለሥርዓት እንድንሄድ የሚገፋፋንን የራሳችንን ፍላጎትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንድንዳፈርና በዚያ መንገድ እንድንሄድ አላስፈላጊ ልምምድ ከሚያለማምዱን ወይም በተጽእኖ ከሚገፋፉን አካላት በመራቅና መንፈሳዊ በረከትና ጸጋ የምናገኝበት ላይ እንድናተኩር፣ በሥርዓት መሄድ ያለውን ጥቅም ቀምሰን ሌሎችም እንዲቀምሱት በማድረግ ሥርዓት የለሾችን እየመከርንና ወደመዳን ሊያመጣ በሚችል ወቀሳ እየወቀስንና ሥርዓተ አልበኝነትን አርቀን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየተመራን መንፈሳዊ አገልግሎታችንን ልናከናውን ያስፈልጋል።
መንግሥተ ሰማያትን ተስፋ የሚያደርግ ማንነት ካለን በዚህ ዓለም የሚታየው ነገር ሁሉ የሚያጓጓንና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚወስደን አንሆንም ከዕለት ወደዕለት ኃይላችንን እያደስን በትዕግሥት መንግሥተ እግዚአብሔርን እንጠባበቃለን እንጂ። ብፁዕ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን።
"በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን" ሮሜ፰፥፳፬
379 views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 23:01:55

765 views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 22:53:24

701 views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 22:52:29 ለእመ ኮነ በዓለ ሐዋርያት አመ ፲ወ፭ ለነሐሴ መዝሙር ተጋቢኦሙ

(በ፩/ቆ) ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ ኵሎሙ ሐዋርያቲሁ ተበሃሉ በበይናቲሆሙ ምንተኑመ አስተጋብአነ ውስተ ዛቲ አንቀጽ ለለአሐዱ ይቤሎ ጴጥሮስ ለጳውሎስ ጸሊኬ እኁየ ጳውሎስ ወኢትናፍቅ ቅድመ እግዚአብሔር ይቤሎ ጳውሎስ ለጴጥሮስ እፎ አነ እጼሊ ዘእምቅድሜክሙ እስመ ሐዲስ ተክል አነ ወተፈሥሑ ኵሎሙ ሐዋርያት በእንተ ዘይቤሎሙ ጳውሊ አብዕዋ ቤታ ለማርያም ኦ ትቤ ማርያም ንሥእዎ ወአንብብዎ ለዝንቱ መጽሐፍ ኦ ትቤ ማርያም እወጽእ እምዝንቱ ሥጋየ ወአሐውር ውስተ ሕይወት ዘለዓለም ኦ ትቤ ማርያም ተዘከርኬ ዮሐንስ ዘይቤለከ ሊቅ አመ ትረፍቅ ዲበ እንግድዓሁ።
ትርጕም፦
ሁሉም ሐዋርያት ተሰብስበው እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ እያንዳንዳችንን ከዚች በር ላይ ምን ሰበሰበን? ጴጥሮስ ጳውሎስን ወንድሜ ጳውሎስ በእግዚአብሔር ፊት ጸልይ አትጠራጠር አለው ጳውሎስ ጴጥሮስን ከእናንተ ፊት እንዴት እጸልያለሁ እኔ አዲስ ተክል ነኝና አለው ጳውሎስ ስላላቸው ነገር ሐዋርያት ሁሉ ደስ አላቸው እመቤታችንን ወደ ቤቷ አስገቧት ኦ! ማርያም እንዲህ አለች ይህንን መጽሐፍ ወስዳችሁ አንብቡት ከዚህ ሥጋዬ እወጣለሁ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እሄዳለሁ ኦ! ማርያም እንዲህ ዮሐንስ! አጠገቡ በተቀመጥህ ጊዜ መምህር የነገረኸን አስብ አለችው።
የዕለቱ ምንባባት፦
ሮሜ ፲፭፥፳፰ - ፍ፤
ይሁዳ ፩፥፳ - ፍ፤
ግብ ፬፥፲፮ - ፳፫፤
ወንጌል፦ ሉቃ ፲፩፥፳፯ - ፳፱፤
ቅዳሴ፦ ዘአበዊነ ሐዋርያት
የዕለቱ ምስባክ፦
ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፤
ወትሠዪሚዮሙ መላእክተ ለኵሉ ምድር፤
ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ። መዝ ፵፬፥፲፮፤
ትርጕም፦
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ፤
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ፤
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ።
ምሥጢር፦
ርስዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ ብሎ ነበርና ስለ አባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተተኩልሽ፤
በአራቱ ማዕዘን አለቆች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ፤ ምነው የሚሾምማ ንጉሡ አይደለምን ቢሉ እገሌ ይሾም እያለች እያማለደች የምታሾም ስልሆነ፤ አንድም እሷም በበኩሏ ቀኛዝማች ግራዝማች ደጃዝማች እያለች ትሾማለችና።
የሰብለ ወንጌል የሮማነ ወርቅ ልጆች ነን እያሉ ስምሽን ለልጅ ልጅ ይጠራሉ።
አንድም ስለ ዐበይት ነቢያት ፈንታ ሐዋርያት ስለ ደቂቅ ነቢያት ፈንታ ሰባ አርድእት አንድም ስለ ዓበይት ነቢያት ፈንታ ደቂቅ ነቢያት ስለ ደቂቅ ነቢያት ፈንታ ሐዋርያት ስለ ሐዋርያት ፈንታ ሰባ አርድእት ስለ ሰባ አርድእት ፈንታ ሊቃውንት መምህራን ተተኩልሽ።
በአራቱ ማዕዘን አለቆች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ፤ ማኅበሩ አንድ ሁነው የሚሾሙ ስለሆነ። አንድም ትሰይምዪዮሙ ይላል ስምዖን የተባለውን ጴጥሮስ ሳውል የተባለውን ጳውሎስ ልብድዮስ የተባለውን ታዴዎስ ዲዲሞስ የተባለውን ቶማስ እያልሽ አንድም ሐዋርያት ሰባ አርድእት ሊቃውንት እያልሽ ስም ታወጪላቸዋለሽ። አንድም እመቤታችን ለደቅስዮስ መንበር ለኖቆላዎስ ዐፅፍ ሰጥታቸዋለችና። አንድም ትሰምዪዮሙ ይላል አፈ ወርቅ ልሳነ ወርቅ እያልሽ ስም ታወጪላቸዋለሽ።
ተዘከራ ለአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ሀለወት እምጽንፍ እስከ አጽናፈ ዓለም - ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ያለች አንዲቱን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስብ እያሉ ስምሽን ለልጅ ልጅ ይጠራሉ። አንድም ስምሽን በአራቱ ማዕዘን ይጠራሉ ሰአሊ ለነ ቅድስት ሳይላት የሚውል የለምና።
690 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 21:45:49

871 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 21:43:53

786 views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 21:41:55 መዝሙር ዛቲ ይእቲ ማርያም ከነሐሴ ፰ - ፲፬

(በ፪/ብ) ዛቲ ይእቲ ማርያም ማኅደረ መለኮት እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን በከመ ይቤ ዳዊት በመዝሙር አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር አድባረ ድኁኃን ተሰምየት ዛቲ ይእቲ ቅድስት ድንግል ተዓቢ እምኵሉ ፍጥረት ኢያውዓያ እሳተ መለኮት።

ትርጕም፦

የክርስቲያን ሰንበት/ዕረፍት የተባለች የመለኮት ማደሪያ ይህች ማርያም ናት ዳዊት በመዝሙር ዐይኖቼን ወደ ተራራዎች አነሣሁ እንዳለ፤ ለድኅነት የተመረጡ የሚጠጉባት ተራራ የተባለች ይህ ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች ባሕርየ መለኮቱ አላቃጠላትምና።

የዕለቱ ምንባባት፦

ዕብ ፲፩፥፰ - ፲፱፤
፪ዮሐ ፩፥፩ - ፰፤
ግብ ፳፯፥፴፩ - ፴፰፤
የዕለቱ ወንጌል፦ሉቃ ፩፥፴፱ - ፵፮፤
ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ ማርያም፤

የዕለቱ ምስባክ፦

አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር፤
እምአይቴ ይምጻእ ረድኤትየ፤
ረድኤትየሰ እምኀበ እግዚአብሔር። መዝ ፻፳፥፩፤

ትርጕም፦

ዐይኖቼን ወደ ተራራ አነሣሁ፤
ረድኤቴ ከወዴት ይምጣ?
ረድኤቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

ምሥጢር፦

ዐይኖቼን በተስፋ ወደ ኢየሩሳሌም አቀናሁ፤ አንድም ምነው? ጊዜው ደርሷል አታወጡኝምን እያልሁ ወደ ነቢያት ወደ ካህናት ዐይኖቼን አቀናሁ፤ አንድም ዐይኖቼን ወደ ተራራው አቀናሁ፤ እንወጣለን እያሉ በየተራራው ይቅበዘበዙ ነበርና፤
ረዳቴ ከየትም ከየት ይደረግልኝ ይታዘዝልኝ እንደሆነ ብዬ፤
እንዲህስ እንዳልል የእኔ ረድኤት ከእግዚአብሔር ዘንድ ይደረግልኛል ይታዘዝልኛል።
766 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:48:14

976 views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ