Get Mystery Box with random crypto!

Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809

የቴሌግራም ቻናል አርማ doctoralle8809 — Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ doctoralle8809 — Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809
የሰርጥ አድራሻ: @doctoralle8809
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 66.78K
የሰርጥ መግለጫ

ጤናዎን ያብዛሎ
8809 ዶክተር አለ
መተኪያ ስለሌለው ጤናዎ የሀኪም መፍትሄ የሚያገኙበት የጥሪ ማዕከል 8809 ዶክተር አለ
- አካላዎ ህመም -
- የውስጥ ደዌ
- የስነልቦና ችግር
- እንዲሁም የሚያስፈልግዎ ህክምና የት ሆስፒታል እንደሚሰጥ እንጠቁምዎታለን፡፡
- የውጪ ሀገር ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ባለን ዓለምአቀፍ ኔትዎርክ ሁሉን ያሟላ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-12 15:57:08 https://vm.tiktok.com/ZMMxvPQ1V/
15.6K viewsRahel, 12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 08:06:33
13.6K viewsRahel, 05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-24 06:09:00 https://www.tiktok.com/@yoyogaddis?_t=8kvz8DEdUOr
13.3K viewsRahel, 03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 06:24:43
13.0K viewsRahel, 03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 06:24:38 #ለጸጉሮት #ቀለም #ይጠቀማሉ? #እንግዲውስ #እነዚህን #ልብ #ይበሉ!


#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

የተከበራችሁ የገጻቸን ቤተሰቦች በአሁን ጊዜ ጸጉርን ለማሳመር ሲባል ብዙዎች ቀለም ይቀባሉ ወንድም ይሁን ሴት ሆኖም ግን ያለውን የጎንዮሽ ጉዳ ያተዋሉት አይመስልም እኛም እንደጤና ባለሙያ ግዴታችን ነውና እስኪ አውቃችሁ ትጠነቀቀቁ ዘንድ እነሆ አልን፡፡

ሽበት፡- የጸጉር ቀለሞች በብዛት አሞኒያ እና ፐርኦክሰሳይድ ንጥረ ነገሮች ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች ደግሞ የጸጉር ተፈጥሯዊ ቀለምን በማሳጣት ሽበት እንዲከሰት እንዲሁም ጸጉር ሳስቶ እንዲሰባበር ያደርጋል፡

የቆዳ አለርጂ፡- የጸጉር ቀለሞች ፓራፌናይልዲአሚን የሚባል አለርጂ አምጪ ንጥረ ነገር ይይዛሉ ይህ ደግሞ ቆዳን እንዲቆጣ፣ እንዲያሳክክ እንዲሁም ቀልቶ እንዲያብጥ ያደርጋል፡፡

በእርግዝና ወቅት፡ ነብሰጡር ሴት በፍጹም የጸጉር ቀለም መጠቀም የለበትም ምክንያቱም ጽንሱን ከማስወረድ ጀምሮ እስከ ካንሰር መከሰት ስለሚዳርግ

አስም፡- ልክ እንደአስም አይነት የመተንፈሻ አለርጂ ችግር ያለባቸው ሰዎች የጸጉር ቀለምን ማሶገድ የግድ ይላቸዋል ምክንያቱም በውስጣቸው የሚይዙት ኬሚካሎች ሳንባን በከባድ ሁኔታ ስለሚጎዳ ነው፡

እርግዝናን ማዘግየት፡- በእርግጥ በዚህ ዙሪያ ብዙ የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም ነገር ግን እንዳንዶች እንደሚያሳዩት የጸጉር ቀለም እርግዝና ለሚጠብቁ ጥንዶች የማዘግየት ሁኔታ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

የአይን ደም ስሮች መቆጣት፡- አይናችን በብዙ ነገር የተከለከለ ቢሆንም ግን አሁንም ቢሆን ከሰደጋ የጸዳ አይደለም በመሆኑም የአይናችን ደም ስሮች ከሚጎዱበት ዋነኛም ምክንያቶች መሀከል የጸጉር ቀለም ዋነኛው ነው፡፡

ካንሰር፡- አንዳንድ የጸጉር ቀለም የቆዳ ካንሰር አምጪ የሆኑ ኬሚካሎችን በውስጣቸው ስለሚይዙ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

በማንኛውም የጤና ጉዳይ ባለሙያ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞችን ላይ እየደወሉ የየዕለቱን የጤና ላይ ለውጦችዎን በማማከር ነገ ከሚከሰት የጤና ችግር አስቀድመው ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ ይንከባከቡ::

ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 1 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
12.8K viewsRahel, 03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-23 14:49:24 እውቁ ፀሐፊ ፓውሎ ኪሊዮ እዲህ ይላል፤


ሰዎች እንዲረዱህ ከመጠን በላይ አትድከም ሰዎች እንደሆኑ የሚሰሙት መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ነውና።

አንድቀን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ጊዜህ አልቆ ልታገኘው ትችላለህ፤ ስለዚህ ልታደርገው የምትፈልገውን ነገር አሁኑኑ አድርገው።

ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ አንድ ሕግ አክብር ፈጽሞ ራስህን አትዋሽ።

የህይወት ምስጢሩ ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።

ሕልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ መጥፎ ነገር አለ "አይሳካልኝም" የሚል ፍርሃት።


በዓለም ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊገባው የሚችለው ቋንቋ አለ "ፍቅር "!


ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ!

ምንም ምክንያት ከማያሻቸው ነገሮች አንዱ ማፍቀር ነው።

አንድ ነገር አስታውስ ልብህ ያለበት ቦታ ሀብትህም ተቀምጧል።

መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤
12.8K viewsRahel, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-18 13:08:46
14.7K viewsRahel, 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-18 13:08:41 #በተደጋጋሚ #በሆድ #ጥገኛ #ትላትል #እጠቃለሁ #ምን #ይሻላል?

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን
#የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በየትኛዉም የእድሜ ክልል የሚከሰቱ ሲሆኑ በዋናነት ክብ እና ጠፍጣፋ በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡የሆድ ጥገኛ ትላትሎች ወደ ሰዉነት የሚገቡት በቆዳ፣ በአፍንጫ እና በአፍ በኩል በእንቁላል መልኩ ሲሆን ወደ ሰዉነታችን ከገቡ በኃላ በአንጀታችን ላይ ይራባሉ፡፡
#ለሆድ #ጥገኛ #ትላትል #መንስኤዎች
በንፅህና ያልተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ
የተበከለ ዉሃ
በደንብ ያልበሰለ ምግብ መመገብ
በባዶ እግር መሄድ
የግል ንፅህና አለመጠበቅ
የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ
በጥገኛ ትላትሎች ከተያዙ የቤት እንስሳ ጋር መኖር
#ምልክቶች
የሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ
የምግብ ፍላጎት መቀነስ/መጨመር
ማቅለሽለሽና ማስመለስ
የሆድ ህመም/ቁርጠት
በሰገራ ላይ የሆድ ጥገኛ ትላትሎችን መታየት
የሆድ መነፋት እና ጋዝ መብዛት
በፊንጢጣ ወይም ብልት ዙሪያ ማሳከክ
#የሆድ #ጥገኛ #ትላትሎችን #መከላከል #መንገዶች
ፍራፍሬዎች ከመመገብ በፊት በደንብ ማጠብ
ከመመገብ በፊት ምግብን በደንብ ማብሰል
ፈልቶ የቀዘቀዘ ወይም የተጣራ ዉሃ መጠቀም
ንፅህና መጠበቅ
ከመመገብ በፊት፣ ምግብ በሚያበስሉበት ወቅትና ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅን በዉሃና ሳሙና መታጠብ፤ እንዲሁም የቤት እንስሳዎችን ከነኩ በኋላ እጅን በደንብ መታጠብ፡፡
በባዶ እግር አለመሔድ እና ንጽህናዉ በተጠበቀ/በታከመ ገንዳ ዉስጥ መዋኘት
#ህክምና
ለሆድ ጥገኛ ትላትሎች መኖራቸዉ በሰገራ ምርመራ ከተረጋጋጠ በኋላ ለተገኘዉ የትላትል አይነት መድሐኒት እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች በአግባቡ ካልታከመ እና አመጋገብ ካላስተካከልን ከፍተኛ የአንጀት ጉዳት ያስከትላል፡፡
12.9K viewsRahel, 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-14 11:34:56 Follow my tic toc page
15.9K viewsRahel, 08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-14 11:34:26 https://vm.tiktok.com/ZM6w1WXVU
14.8K viewsRahel, 08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ