Get Mystery Box with random crypto!

Hakim @ሐኪም

የቴሌግራም ቻናል አርማ hakim_doctors_ethio_health_tena — Hakim @ሐኪም H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hakim_doctors_ethio_health_tena — Hakim @ሐኪም
የሰርጥ አድራሻ: @hakim_doctors_ethio_health_tena
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.06K
የሰርጥ መግለጫ

Hakim @ሐኪም
@Hakim365bot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 15:12:55 ጭንቀት በጤናዎ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ?
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1) የፀጉር መነቃቀል ያስከትላል አልፎም መመለጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡

2) እንቅልፍ እጦት፤ራስምታት፤መነጫነጭ፤
መደበት ና እና የባህርይ ለዉጥን ያስከትላል፡፡

3) በከንፈር ላይ የሚወጡ አንዳንድ ቁስለቶች ከጭንቀት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

4) ለደም ግፊት መጨመር በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡ ለልብ ሕመምም ይዳርጋል፡፡

5) ጭንቀት የአስም ሕመምተኞች ላይ ሕመማቸው እንዲነሳባቸው ያደርጋል፡፡

6) በጡንቻዎች ላይ ሕመም ስሜት እንዲኖር ያደርጋል ለወገብ እና ጀርባ ሕመም ያጋልጣል፡፡

7) ጭንቀት የጨጓራ ሕመምን ከማስከተል ባለፈ ለአንጀት ቁስለትም ሊዳረግ ይችላል፡፡

8) ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት የወር አበባ ዑደትን ያዛባል፡፡ ወንዶችን ለስንፈተ ወሲብ ስለሚዳርግ የትዳር እና የፍቅር ግንኙነት እንዲሻክር ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ጭንቀትን በማስወገድ ጤንነትዎን ይጠብቁ!

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ

ጤና ይስጥልኝ

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
138 views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:12:41
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
125 views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:45:12 "የህጻናት አስም" - በዶ/ር ንጉሤ ጫኔ : የህጻናት ስፔሻሊስት ሀኪም

- አስም ምንድን ነው?
አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ የትንፋሽ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎች ተጽእኖ ከሚገባው በላይ በድንገት ለተወሰነ ጊዜ መጥበብ ነው። ይህ የአየር ቧንቧ ጥበት መድሀኒት ሲዎስዱ ወደ ነበረበት በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ነው።

- ምክንያተ መንስኤ
ዋና ምክንያቱ ተፈጥሯዊ ፣ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ በሆኑ ምክንያቶች ይነሳል። የሚፈጠረው መስተጋብር አየር ባንቧን ለዘለቀ ቁስለት/ብግነት በማጋለጥ አለርጅ ቀስቃሽ ሽታዎች ሲኖሩ የአየር ቧንቧ ከልክ ያለፈ ተለዋጭ ጥበት እና የቆሸሸ አየር ከሳንባ በሚፈለገው ልክ አለመውጣት ሳል እና የመታፈን ምክንያትን ያመጣል። ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ ምክንያቶችን መቀነስ ይቻላል።

- የአስም አይነቶች
1. በተደጋጋሚ የሚነሳ አስም/recurrent asthma/seasonal
ይህ ወቅታዊ ሁኔታዎች የሚያስነሱት አስም ነው። ቀስቃሽ ምክንያቶችን በመቀነስ ድግግሞሹን መቀነስ እና ደረጃውንም መቆጣጠር ይቻላል።
2. ረጅም ጊዜ የቆየ አስም /chronic asthma
ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አስም

- አለርጅ/አስም ቀስቃሾች ምንድን ናቸው?
1. የሲጋራ ፣ የከሰል እና የማገዶ ጭስ
2. የአበባ፣ቆሻሻ፣ የፅዳት መጠበቂያ/ዴቶል/ ፣ የሽቶ እና ላበት ማጥፊያዎች ሽታ
3. ላባ እና ጸጉር ያላቸው የቤት እንስሳት
4. የከብቶች ሽንት እና አዛባ
5. በረሮ የሚረጨው ኬሚካል
6. እርጥበት እና ቅዝቃዜ ያለው ስፍራ
7. የጉንፋን ቫይረስ
8. የኬሚካል ሽታ
9. ጭንቀት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
10. ሻጋታ
11. የጨጓራ አሲድ ቅርሻ/Gastro esophageal reflux disease
12. የአፍንጫ አለርጅ እና ሳይነስ ህመም

- ለአስም አጋላጭ ሁኔታዎች
1. የቆዳ አለርጅ/የቆዳ አስም
2. የአፍንጫ እና አይን አለርጅ
3. የምግብ አለርጅ
4. አስም ያለበት እናት ፣ አባት ፣ እህት ወይም ወንድም
5. ከጉንፋን ጋር የማይያየያዝ ሳል

- የህመም ምልክቶች
1. በቅዝቃዜ ወቅት እና ማታ ማታ የሚባባስ ደረቅ ሳል
2. የደረት መጨነቅ/የመታፈን ስሜት
3. የትንፋሽ መፍጠን
4. የድካም ስሜት
5. የሰውነት መዛል እና ላበት
6. ሙዚቃዊ ትንፋሽ
7. ራስ ምታት፣ የትኩረት መቀነስ፣ እና አቅልን መሳት

- አስም አመላካች ነገሮች ምን ናቸዉ
1. በጥርጣሬ የአስም መድኃኒት ሲሰጥ በቶሎ የሚሻል ከሆነ
2. ወላጅ አስም ወይም አለርጅ ካለበት
3.ነባር የትንፋሽ አለርጅ ካለ
4. ተደጋጋሚ የመተንፈሻ አለርጅ:

- ህጻናት ላይ አስም ይምንለው በአመት ውስጥ ሶስት ጊዜ እና ከዚያ በላይ የሆነ ሀኪም ያረጋገጠው የመተንፈሻ አለርጅ ካለ ነው።

- አስምን በምን እናረገግጣለን
1. የሳንባ ምርመራ:
በጤንነታቸው ወቅት ያላቸው የሳንባ አየር የማስገባት እና የማስወጣት የመጨረሻ አቅም ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል በህመሙ ምክንያት ቀነሰ የሚለውን በመለካት።
2. የአየር ቧንቧ ለትንፋሽ ቧንቧ አስፊ ህይዎት አድን መድሀኒት ያለውን ፈጣን ምላሽ በማየት።
3. በአለርጅ አምጭ/ቀስቃሽ መድሃኒት አስም የመከሰት እድሉን መሞከር(ይህ ምርመራ ብዙ አይመከርም)
4. በእስፓርታዊ እንቅስቃሴ ያለውን የተቃጠለ አየር የማስውጣት አቅም በመለካት።

- የአስም ህክምና
1. የአየር ቧንቧን ጥበት የሚያስተካክሉ መድሀኒቶች
2. የአየር ቧንቧ ቁስለትን/ብግነትን የሚቀንስ መድሃኒት
3. አለርጅን የሚቀንስ መድሃኒት
4. አስም ቀስቃሽ የሆነውን ህመም ማከም
5. ቤትን ከአስም ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ነጻ በማድረግ አስም እንዳይነሳ መከላከል
6. በቅዝቃዜ እና ጉንፋን በሚበዛባቸው ወቅቶች የአስም ቅድመ መከላከል መድሃኒት መስጠት

- እንደ መውጫ
የህጻናት የመተንፍሻ ቱቦ በተፈጥሮ ጠባብ በመሆኑ ምክንያት አስም ጋር የሚመሳሰሉ ብዙ ህመሞች ስላሉ አስም አለ የምንለው በታፈኑ ወቅት በአስም መድሀኒት ያላቸው ለውጥ አመርቂ ከሆነ እና ለአስም ተጋላጭነት ካላቸው ነው።

እድሜያቸው ከ4 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የሳንባን በአግባቡ መስራት ወይም አለመስራት ለማወቅ ለምርመራ እድሜያቸው ስለማይፈቅድ በብዛት በክትትል ብቻ ነው መለየት የሚቻለው። አካባቢያዊ አስም ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስተካከል አስምን መከላከል ዉጤታማ ነው።

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
210 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:44:56
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
186 views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:35:20 ማታ duty ነው ያደርኩት

Medical laboratory technologist ነኝ። ወደ ስራ የገባሁት ማታ 11:30 ነው። primary hospital ላይ ነው የምሰራው። በነገራችን ላይ primary lay 1 የlaboratory ባለሞያ ብቻ ነው የምያደረው።

ገና እንደገባው ከdelivery የምመጡ መዓት ቴስቶች ልያጨናንቁኝ ጀመሩ። ትንሽ ቆየት ስል በየሰዐታት RBS and ketoneቸውን follow የማደርጋቸው ሁለት የDKA patient, emergency ward ተኝቶልኛል። በዛ ላይ አከባቢው malaria በብዛት የምገኝበት ስለ ሆነ በየደቂቃው febrile እየሆኑ መጥቶ blood film examination የምሰራላቸው በጣም ብዙ ናቸው።
Cbc እና የተለያዩ ቴስቶች ከሁሉም ward ይጎረፉብኛል። እራት ወቶ መብላት አይታሰብም። ቋጥሬ የመጣውትን እዛው በልቼ ፣ ከ GP, nurse እና ከሁሉም እስታፎች ጋር ደፋ ቀና እያለን እስከ ከምሽቱ 8:00 ሰዐት ጋደም ሳልል ቆየው።

9:30 ስሆን ኳኳ... ብንን ብዬ ተነሳው። ከdelivery ነው። እንድህ እንድህ እያለን ከጠዋቱ 2:30 ሆነና ወደ የቤታችን ገባን።

የኔን አነሳው እንጂ ሁሉም ባለሞያ ያለ እንቅልፍ ነው የምያደረው። GP ሁሉንም እየተቆጣጠረ ፣ medication እየፃፈ ፣ nurse medication እየሰጠ ፣ suture እየሰራ... pharmacy, midwive, ሁሉም ባለሞያዎች በየፊናቸው እየሰሩ ያድራሉ።

በምን calculation እንደሆነ ባይገባኝም ማታ 11:30 እስከ ጠዋቱ 2:30 ሰርተን የምታሰብልን ሰዐት ፣ አርብ ማታ ፣ ቅዳሜ ማታ እና የበዓል ዋዜማ ማታ ካልሆነ በቀር 7 ሰዐት ብቻ ነው።

እና ማታ ያገኘነው ብር
- ለnurse, MLT, midwives -7*25.8=180.6birr
- Pharmacy, MRT -- 7*29.5=206birr
- Gp.. 7*37.7=264 birr

ያው እንግድህ ቁርስ ያለ ሻይ 50 ብር፣ ቀለል ያለች ምሳም በ50 ብር፣ እራትም የእትዬ ትርፌን ሽሮ በ50 ብር በልቼ የቀረችዉን DStv ጫወታ አይቼባት ጨርሳታለው። GPው ጓደኛዬ ትንሽ ከኔ የተሻለች ስላገኘ ቡና ምናም ይጋብዘኛል። ተመስገን ነው አቦ

At all its not fair. እንዴት ይህን ሁሉ ሰዐት ሰርተን በዚህ ኑሮ ውድነት እቺን ያክል ብር እናገኛለን?

Misbah Mohamedsani

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
459 views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:34:26
266 views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:42:23 አቮካዶን የመመገብ ጥቅሞች በጥቂቱ
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

የኮሌስትሮል መጠን ይቀንሳል

አቮካዶ በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር (betasisterol) በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘዉን የኮሌስትሮል መጠን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

ለዓይናችን ጤና ጠቃሚ ነው

በውስጡ የሚገኘው ካሮቲኖይድ ሉቲየን (carotenoid lutien) ዓይናችንን ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት የሚመጡ ሕመሞችን እንድንከላከል ይረዳል፡፡

በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን ይቀንሳል

በአቮካዶ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው (folate) ፎሌት በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን እንደሚቀንስ የተደረጉ ጥናቶቸድ ያሳያሉ፡፡

ከካንሰር ይከላከላል

አቮካዶ የሚመገቡ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚቀንስና ወንዶችን ደግሞ ከፕሮስቴት ካንሰር የመከላከል የመከላከል አቅም እንዳለው የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል

አቮካዶ ተፈጥሮአዊ ከሆኑ የመጥፎ አፍ ጠረን መከላከያዎች አንዱ ነው፡፡

ለቆዳችን ጥቅም

የኦቮካዶ ቅባት በብዙ የውበት መጠበቂያዎች ውስጥ የሚገባና ለቆዳ ተስማሚ እና ጤናማነት ጠቃሚነት ያለው የፍራፍሬ ዓይነት ነው፡፡

ጤና ይስጥልኝ!

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
331 views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ