Get Mystery Box with random crypto!

ጭንቀት በጤናዎ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ? (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም) 1) የፀጉር መነ | Hakim @ሐኪም

ጭንቀት በጤናዎ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ?
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1) የፀጉር መነቃቀል ያስከትላል አልፎም መመለጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡

2) እንቅልፍ እጦት፤ራስምታት፤መነጫነጭ፤
መደበት ና እና የባህርይ ለዉጥን ያስከትላል፡፡

3) በከንፈር ላይ የሚወጡ አንዳንድ ቁስለቶች ከጭንቀት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

4) ለደም ግፊት መጨመር በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡ ለልብ ሕመምም ይዳርጋል፡፡

5) ጭንቀት የአስም ሕመምተኞች ላይ ሕመማቸው እንዲነሳባቸው ያደርጋል፡፡

6) በጡንቻዎች ላይ ሕመም ስሜት እንዲኖር ያደርጋል ለወገብ እና ጀርባ ሕመም ያጋልጣል፡፡

7) ጭንቀት የጨጓራ ሕመምን ከማስከተል ባለፈ ለአንጀት ቁስለትም ሊዳረግ ይችላል፡፡

8) ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት የወር አበባ ዑደትን ያዛባል፡፡ ወንዶችን ለስንፈተ ወሲብ ስለሚዳርግ የትዳር እና የፍቅር ግንኙነት እንዲሻክር ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ጭንቀትን በማስወገድ ጤንነትዎን ይጠብቁ!

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ

ጤና ይስጥልኝ

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena